ሥረይ ግሦች

ክፍል አንድ

ጥቅምት ፳፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት

የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! የጥቅምት ወር የመጨረሻ ክፍለ ጊዜያችን የሆነውን ትምህርት ለዛሬ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ ከዚያ በፊት ግን የባለፈው ትምህርታችን ላይ ስላስተማርናችሁ ‹‹ረብሐ ግሥ›› ጥቂት እናስታውሳችሁ፡፡

ከግሥ ዓይነቶች አንዱ የሆነው ረብሐ ግሥ ዘማች ግሦችን ከቀዳማይ አንቀጽ ጀምሮ እስከ አርእስት እና ከዚያ በላይ ያሉትን ቅጽሎችን የሚያገሰግስ ማለት እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ በዚህ የግሥ ዓይነት ሥር የሚገኙት የዋህና መሠሪ ግሦች መሆናቸውንና እነርሱንም በግሥ አርእስት ማለትም በቀተለ፣ በቀደሰ፣ በተንበለ፣ በባረከ፣ በማህረከ፣ በሴሰየ፣ በክህለ እና በጦመረ ዘርዝረን ለማየት ሞክረናል፡፡ የዚህንም ግሥ ዝርዝር ርባታ እንዳጠናችሁት ተስፋ እያደረግን ወዳዘጋጀንላችሁ ትምህርት እናልፋለን፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የምንመለከተው የግሥ ዓይነት ‹‹ሥረይ ግሥ›› ይባላል፡፡

በግእዝ ቋንቋ የማንቁርት ድምጾች/ንባበ ጉርዔ ታ፣ሐ፣ ኀ እና ዐ፣ ኂ ከፊል አናባቢ ድምጾች (ወ፣ የ) ወይም መሣግር ድምጾች (ሀ፣ረ፣ አ፣ ወ፣ ዘ) በግሥ ርባታ ላይ በሚያመጡት ለውጥ  ምክንያት በቅርጽ ወይም በርባታ ለስምንት አለቆች የማይበዙ ግሦች አሉ። እነዚህ ግሦች እንደ ሠራዊት መቆጠር ስለሌለባቸው የእነርሱ አምሳያ ለሆነው ጠቅላላ ግሥም ምሳሌ ስለሆነ ሥረይ ግሦች የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በመቀጠልም ሥረይ ግሦቹን በስምንት አርእስት ሥር መድበን ርባታቸውን እንደሚከተለው አቅርበናል።

. በቀተለ ሥር የሚመደቡና የርባታ አመል ያላቸው ሥረይ ግሦች        

ሥረይ ግሥ ትርጉም ሰዋሰዋዊ ሙያ
ሐተተ መረመረ ኃላፊ አንቀጽ
የሐትት ይመረምራል ትንቢት አንቀጽ
ይሕትት ይመረምር ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይሕትት ይመርምር ትእዛዝ አንቀጽ
ሐቲት/ሐቲቶት መመርመር ንዑስ አንቀጽ
ሐታቲ/ሐታትያን መርማሪ/መርማሪዎች ሣልስ ቅጽል
ሐታቲት/ሐታትያት የምትመረምር/የሚመረምሩ አንስታይ ቅጽል
መሕትት የሚያስመረምር ባዕድ ቅጽል
ሐቲቶ/ሙ መርምሮ ቦዝ አንቀጽ
ሐተታ ምርመራ፣ፍተሻ ዘመድ ዘር

ደጊመ ድምጽ ያላቸው ግን መድረሻ ድምጻቸውን ጐርደው ቅድመ መድረሻቸውን ያጠብቃሉ፤ ርባታቸው ግን ተመሳሳይ ነው።

ሐጸ የሐጽጽ ይሕጽጽ ይሕጽጽ
ሐመ የሐምም ይሕምም ይሕምም

ምሳሌ፡-

መሐለ ማለ ኃላፊ አንቀጽ
ይምሕል ይምላል ትንቢት አንቀጽ
ይምሐል ይምል ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይምሐል ይማል ትእዛዝ አንቀጽ
ምሒል/ምሒሎት መማል ንዑስ አንቀጽ
መሓሊ የሚምል ሣልስ ቅጽል
ምሒሎ/ሙ ምሎ ቦዝ አንቀጽ
መሐላ ማላ ዘመድ ዘር
ነቀወ ጮኸ ኃላፊ አንቀጽ
ይነቁ ይጮሀል ትንቢት አንቀጽ
ይንቁ ይጮህ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይንቁ ይጩኽ ትንቢት አንቀጽ
ነቂው/ነቂዎት መጮኽን ንዑስ አንቀጽ
ነቃዊ የሚጮኽ ሣልስ ቅጽል
ነቃዊት የምትጮኽ አንስታይ ቅጽል
ነቂዎ ጩኾ ቦዝ አንቀጽ
ንቃው ጨኹት ዘመድ ዘር

‹‹ወ፣ኂ እና ታ፣ የ፣ ኂ›› የግሥ መድረሻ ሲሆኑ በትንቢት፣ በዘንድና በትእዛዝ አንቀጽ ይጐርዳሉ። ያም ሆኖ ቅድመ መድረሻ እና መድረሻ ድምጻቸው ደጊመ ድምጽ ሲኖረው አይጐርድም። እርሱም    እንደሚከተለው ነው፡፡

ከወወ ቀለጠፈ፣ፈጠነ ኃላፊ አንቀጽ
ይከውው ይቀለጥፋል ትንቢት አንቀጽ
ይክውው ይቀለጥፍ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይክውው ይቀልጥፍ ትንቢት አንቀጽ
ከዊው/ከዊዎት መቀልጠፍ ንዑስ አንቀጽ
ከዊዎ/ሙ ቀልጥፎ ሣልስ ቅጽል
ወሀበ ሰጠ ኃላፊ አንቀጽ
ይውህብ (ይሁብ) ይሰጣል ትንቢት አንቀጽ
የሀብ ይሰጥ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
የሀብ ይስጥ ትንቢት አንቀጽ
ውሂብ/ውሂቦት መስጠት ንዑስ አንቀጽ
ወሃቢ የሚሰጥ፣ሰጪ ሣልስ ቅጽል
ወሃቢት የምትሰጥ አንቀጽ
ወሁብ የተሰጠ ንዑስ አንቀጽ
ወሂቦ ሰጥቶ ቦዝ አንቀጽ
ሀብት በቁሙ ስጦታ ዘመድ ዘር

/ወ/የግሥ መነሻ ሲሆን በዘንድና በትእዛዝ ይጐርዳል።

ወረደ ወረደ ኃላፊ አንቀጽ
ይወርድ ይወርዳል ትንቢት አንቀጽ
ይረድ ይወርድ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይረድ ይውረድ ትንቢት አንቀጽ
ወሪድ/ወሪዶት መውረድ ንዑስ አንቀጽ
ወራዲ የሚወርድ፣ወራጅ ሣልስ ቅጽል
ወራዲት የምትወርድ አንቀጽ
ርደት መውረድ፣አወራረድ  ሳቢ ዘር
ወሪዶ ወርዶ ቦዝ አንቀጽ
ወርድ ስፋት፣ጐን ዘመድ ዘር

ገብረ፣ ቅድመ መድረሻው ሳድስ ድምጽ የሆነ ግሥ

ገብረ አደረገ፣ሠራ ኃላፊ አንቀጽ
ይገብር ያደርጋል ትንቢት አንቀጽ
ይግበር ያደርግ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይግበር ያድርግ ትንቢት አንቀጽ
ገቢር/ገቢሮት ማድረግ ንዑስ አንቀጽ
ገባሪ አድራጊ ሣልስ ቅጽል
ገባሪት የምታደረግ አንስታይ ቅጽል
ግቡር የተደረገ ሣልስ ቅጽል
ግብረት ማድረግ፣መሥራት ሳቢ ዘር
ገቢሮ አድርጎ ቦዝ አንቀጽ
ግብር ሥራ፣ተግባር ዘመድ ዘር
ገብር አገልጋይ፣ረዳት ሣልስ ቅጽል
ምግባር/ተግባር በቁሙ ሥራ  ባዕድ ዘር

 ሤመታ በማለት ፈንታ (የ)ንጐርዶ ባለ ሁለት እግር የሆነ ግሥ ነው፡፡

ሤመ ሾመ ኃላፊ አንቀጽ
ይሠይም ይሾማል ትንቢት አንቀጽ
ይሢም ይሾም ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይሢም ይሹም ትንቢት አንቀጽ
ሠይም/ሠይምት መሾም ንዑስ አንቀጽ
ሠያሚ ሹ/ሿዋሚ ሣልስ ቅጽል
ሥዩም የተሾመ ሣልስ ቅጽል
ሠይም ሹም ቦዝ አንቀጽ
ሢመት ሹመት  ሳቢ ዘር
ምሥያም መሾሚያ  ባዕድ ዘር

ቆመታቀወመ በማለት ፈንታ () ን ጐርዶ ሁለት እግር ያለው ግሥ

ቆመ ቆመ፣ተነሣ ኃላፊ አንቀጽ
ይቀውም ይቆማል ትንቢት አንቀጽ
ይቁም ይቆም ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይቁም ይቁም ትንቢት አንቀጽ
ቀዊም/ቀዊሞት መቆም ንዑስ አንቀጽ
ቀዋሚ የሚቆም ሣልስ ቅጽል
ቀዋሚት የምትቆም አንስታይ ቅጽል
ቅውም የቆመ ሣልስ ቅጽል
ቁመት መቆም  ሳቢ ዘር
ቀዊሞ ቁሞ ቦዝ አንቀጽ
ተቅዋም መቅረዝ፣ማብሪያ ባዕድ ዘር
ምቅዋም መቆሚያ ባዕድ ዘር

ይቆየን!

ምንጭ፡- ሰዋስው ወልሳነ ግእዝ መጽሐፍ ከገጽ ፻፬‐፻፰