Zewaye 2 (2)

ማኅበረ ቅዱሳን በዝዋይ ተተኪ ሰባክያንን አስመረቀ

ነሐሴ 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

በዳዊት ደስታ

Zewaye 2 (2)በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል ከሐምሌ 24 እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2004 ዓ.ም. በዝዋይ ሐመረ ኖኅ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ያሠለጠናቸውን ተተኪ ሰባክያነ ወንጌል አስመረቀ፡፡

 

ሠልጣኞች በቆይታቸው የጥናትና ምርምር፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት፣ ነገረ አበው፣ የተመረጡ ነገረ ሃይማኖት ርእሰ ጉዳዮች፣ የመማር ማስተማር ዘዴ፣ የታሪክ አጠናን ሂደት፣ የተግባቦት ሥልጠና፣ ሥርዓተ ጾታ፣ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ተግዳሮት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ሥልጠና ወስደዋል፡፡

 

የሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ የኔታ ሐረገ ወይን ለተመራቂ ተማሪዎች ቃለ ምእዳን አስተላልፈዋል፡፡

 

የተማሪዎቹ ተወካይ ወጣት ግርማ አብደታ ማኅበረ ቅዱሳን ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት የሚያደርገው እንደዚህ ዓይነት ሥልጠናZewaye 2 (1) ለመንፈሳዊ አገልግሎታችን ብቻ ሳይሆን ለዓለማዊም ትምህርታችን ጠቅሞናል በማለት ገልጸዋል፡፡

 

አያይዘውም ከወሰድናቸው የሥልጠና ርዕሶች አንዱ ነገረ አበው ትምህርት አባቶችን ለዚህች ሃይማኖት የከፈሉትን መሥዋእት በአጠቃላይ የሰዓት አጠቃቀምን የሥራ ፍቅርንና የጸሎት ሕይወትን የተረዳንበት ነው በማለት ገልጸዋል፡፡

 

በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ የገዳሙ አስተዳዳሪ የኔታ ሐረገ ወይንና የገዳሙ ርዕሰ መምህር አባ ገ/ሕይወት አባቶች መነኮሳት የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮችና መዘምራን ተገኝተዋል፡፡