[smartslider3 slider="3"]

ለሲኖዶሳዊ ልዕልና መከበር የምእመናን ድርሻ አስፈላጊ ነው!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ቤተ ክርስቲያን የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና አለመከበር እንዲሁም በርካታ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ጉዳዮች  ባይታዋር የሆኑበት፣ ቤተ  ክርስቲያንን ለካህናቱና ጳጳሳቱ ብቻ እየተው የመጡበት ሁኔታ ይታያል፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስትያንን ፖለቲከኞች፣ አማሳኞች፣ ምንደኞች አገልጋዮች እንዲሁም የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላቶቿ  አጀንዳ ሲያደርጓት፣ ባልዋለችበት ሲያውሏት፣ የማይገልጻትን ጥላሸት ሲቀቧት፣ ታሪኳን ሲሰርዙ፣ ሲደልዙ፣ የፕሮፖጋንዳ ሰለባ ሲያደርጓት፣ በባሰ ሁኔታ ኵላዊትነቷን፣ ዓለማቀፋዊነቷን  ወደ ጎን በማለት በርካሽ የጎሳ ከረጢት ሊከቷት ሲሞክሩ እያዩ ዝም ማለታቸው ነው፡