[smartslider3 slider="3"]

፲፫፻፹፮ አዳዲስ አማንያን የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን ማግኘታቸው ተገለጸ!

በደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ዳሰነች ወረዳ ፲፫፻፹፮ አዳዲስ አማንያን በማኅበረ ቅዱሳን የሐዋርያዊ ተልእኮ አስተባባሪነት የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን ማግኘታቸው የተገለጸ ሲሆን ተጠማቂያኑ ባለፉት ወራት መሠረታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት ሲማሩ  ከነበሩ ወገኖች መካከል  መሆናቸው ታውቋል፡፡ ሥርዓተ ጥምቀታቸውም በኦሞ ብሔረ ብፁዓን አቡነ ዜና ማርቆስ ወአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ  አንድነት ገዳም ጥር ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ተፈጽሟል።

ለቤተ ክርስቲያን የሚበጅ ብቁ ዜጋ ለማፍራት በልዩ ትኩረትና በንቃት መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ!

የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ለትውልድ ማእከል ግንባታ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ በታኅሣሥ ወር ፳፻፲፯ ዓ.ም. ባካሄደው ልዩ መርሐ ግብር ላይ በመሪጌታ ባሕረ ጥበብ ሙጬ “የሉላዊነት ተጽዕኖ በኦርቶዶክስ ላይ” በሚል ርእስ የቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ ለቤተ ክርስቲያን የሚበጅ ብቁ ዜጋ ለማፍራት በልዩ ትኩረትና በንቃት መሥራት እንደሚገባ የሚያመለክት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ብፁዕ አቡነ አብርሃም እየተዳከመ የመጣው የብራና መጽሐፍ ዝግጅት ዳግም ማንሠራራቱን ገለጹ

ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት በኅዳር ፲፭፤ ፳፻፲፯ ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት በአካሄደው የምስጋና መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ባስተላለፉት መልእክት የብራና መጽሐፍት ዝግጅት ረጅም ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ እየተዳከመ የመጣ ቢሆንም ዛሬ ላይ በዚህ መልክ እያደገ መምጣቱ የሚያስደስት መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡