“መሠረተ ሃይማኖት” የተባለ የልጆች መጽሐፍ የፊታችን እሑድ እንደሚመረቅ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ገለጸ
የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎትን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ የሚውል “መሠረተ ሃይማኖት” በሚል ርእስ የተዘጋጀ የልጆች መጽሐፍ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በማኅበሩ ሕንጻ 3ኛ ወለል ንቡረ ዕድ ድሜጥሮስ አዳራሽ እንደሚመረቅ በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዳይሬክተር ዲ/ን ሙሉጌታ ነጋ ገልጸዋል።
መጽሐፉ በዲ/ን ማርኤል ሽመልስ የተዘጋጀ ሲሆን የክርስትና መሠረተ እምነት የሆኑትን አምስቱን አዕማደ ምሥጢራት ለልጆች በሚገባ መልኩ የተጻፈ መሆኑን ዲ/ን ሙሉጌታ ነጋ ተናግረዋል።
በመርሐ ግብሩ ትምህርተ ወንጌል፣ የስብከተ ወንጌል ዘጋቢ ፊልምና የመጽሐፍ ምርቃቱ ይከናወናል ተብሏል።
