መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ሰማዕታተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ!
‹‹እንደተማራችሁት በሃይማኖት ጽኑ›› (ቆላ. ፪፥፯)
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ ሃይማኖታቸውን እንዲያጸኑ ታስተምራለችና ስለሃይማኖታችን ልንኖር ይገባል፤ ሃይማኖት የእግዚአብሔርን ህልውና ማወቅ ለእርሱ መታመን ነውና ምእመናን ሁሉ በሃይማኖት መጽናት አለብን፡፡ ይህም በሕይወታችን የሚመጣብንን መከራ እና ፈተና ሁሉ በትዕግሥት እንድናልፍ ይረዳናል። ቅዱስ ጳውሎስ አስቀድሞ ለቆላስይስ ምእመናን ማስተማሩን በማስታወስ እኛ ክርስቲያኖች በቅድሚያ የተማርነውን ትምህርት አጽንተን በሃይማኖት እንድንቆይ ነግሮናልና።
‹‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ትወደኛለህን?›› (ዮሐ. ፳፩፥፲፭)
የዮና ልጅ ስምዖን በቤተ ሳይዳ ዓሣ አጥማጅ የነበረ ሰው ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀበት ዕለት ማግሥት ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ አድርጎ መረጠው፤ ስሙም ጴጥሮስ ተባለ፡፡ ወንጌልን ይሰብክ እና ምእመናንም ይፈውስ ዘንድ ሥልጣንና ኃይልን የተሰጠው ቅዱስም ሆነ፡፡ የአስቆርቱ ይሁዳ ጌታን ለአይሁድ አሳልፎ እስኪሰጠው ድረስም ከእርሱ ጋር ኖሯል፡፡ ፍጹም ሃይማኖት፣ ለጌታውም ቅንዓት እና ፍቅርም ነበረው፡፡ (ስንክሳር ሐምሌ ፭)
‹‹የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን›› (ሐዋ.፳፩፥፲፬)
‹‹ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ ክርስቶስ በፍቅር ተመላለሱ›› (ኤፌ. ፭፥፪)
የእግዚአብሔር ልጆች እንሆን ዘንድ አምላኮተ እግዚአብሔርን መፈጸም ይጠበቅብናል፡፡ በመጽሐፍም አባቶቻችን በብሉይ ኪዳን ፍየል፣ በግ፣ ወይፈን፣ ርግብን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ሲያቀርቡ እሳት ከሰማይ ወርዳ መሥዋዕቱን ትበላላቸው እንደነበር ይገልጻል፡፡ መሥዋዕታቸውንም እሳት መብላቱ እግዚአብሔር ለመቀበሉ ማረጋገጫ ነበረች፡፡ እነርሱም በዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀው ይኖሩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባታችን ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን ሲተረጉም ‹‹መሥዋዕት ማለት አንተ ሰው ዛሬ በግ፣ ፍየል፣ ወይፈን ወይም ርግብ የምታርድ አይምሰልህ፤ ራሱን ሠውቷልና፡፡ ከአንተ የሚፈልገው መሥዋዕት ምንድነው ካልከኝ ራስህን መሥዋዕት አድርገህ ማቀረብ ነው፤ ክህነት የማያስፈልጋት መሥዋዕት ማለት ይህች ናት›› ብሏል፡፡ መሥዋዕት የሚቀርብበት መረብረቢያው፣ መጸፍጸፊያው፣ ድንጋዩ፣ ጉልቻው፣ እንጨቱ፣ እና ማገዶው ደግሞ ምሕረትና ርኅራኄ ነው፡፡ ፍቅር፣ ትዕግሥት፣ ትሕትና፣ የዋህነት እና ንጽሕና የመሥዋዕት መረብረቢያዎች ናቸው፡፡ ጸሎት፣ ስግደት፣ ምጽዋት እና ቸርነት መሥዋዕት ሲሆኑ የሚቀርቡበት ምድጃ ትዕግሥትና ትሕትና ነው፡፡ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
«የተራቡትን ከበረከቱ አጠገባቸው» /ሉቃ. ፩፥፶፫/
በፍጡራን አንደበት ተነግሮ ስለማያልቅ ክብሯና ልዕልናዋ ክብር ምስጋና ይድረሳትና ይህንን ኀይለ ቃል የተናገረችው አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ወንጌላዊው ሉቃስ በወንጌሉ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን እንደ ጻፈልን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብዙ ኀይለ ቃላት ያላቸውን ምሥጢራት በዚህ ክፍል ተናግራለች። ይህ የተናገረችው ኀይለ ቃል በውስጡ ብዙ መንፈሳዊ፣ ሰማያዊ ትርጉም አለው። ምልእተ ጸጋ፣ምልእተ ውዳሴ፣ምልእተ ክብር የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ የጸሎት ክፍል ከተናገረችው ብዙ ወርቃማ ቃላት መካከል ለትምህርታችን «የተራቡትን ከበረከቱ አጠገባቸው» የሚለውን ኃይለ ቃል እንመለከታለን። ይህንን ኀይለ ቃል እመቤታችን ስለ ሦስት ነገር ተናግራዋለች፤ እነርሱም የሚከተሉት ናቸው።
‹‹መጠራጠር የእምነትና የጽናት ጉድለት ነው›› ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
መጠራጠር የእምነትና የጽናት ጉድለት ነው፤ መድኃኒታችን ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ ደቀ መዛሙርቱም በመጣ ጊዜ ምትሐት ምስሎአቸው ታወከው በፍርሃት ጮኹ። ጌታችን ኢየሱስም ‹‹አይዞአችሁ፥ እኔ ነኝ አትፍሩ›› አላቸው፤ ቅድስ ጴጥሮስም መልሶ፥ አቤቱ፥ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ›› አለው። እርሱም ‹‹ና›› አለው። ጴጥሮስም ከታንኳው ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው ላይ ሄደ። ነገር ግን ነፋሱ በርትቶ ባየ ጊዜ ፈራ፥ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ ጌታ ሆይ፥ አድነኝ ብሎ ጮኸ። ወዲያውም ጌታችን ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘው ‹‹አንተ እምነት የጎደለህ፥ ስለምን ተጠራጠርህ?›› ብሎታል፡፡ መጠራጠር ያለመጽናት፣ ያለማመን ውጤት ነውና፡፡ (ማቴ. ፲፬፥፳፬-፴፩)
‹‹በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ፤ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑኛል›› (መዝ. ፳፪፥፬)
ዓለም በኃጢአት እና ክፋት ተሞልታ በሰይጣን አገዛዝ ሥር ከሆነች ውላ አድራለች፤ የሰይጣን ሥራ ከዳር እስከዳር ተስፋፍቶ በበዛበት ወቅት ሰዎች የርኩስ መንፈስ ቁራኛ በመሆን የመከራ አረንቋ እየተፈራረቀባቸው ይገኛሉ፡፡ ጦርነት፣ ቸነፈር፣ ረኃብ፣ በሽታና ሥቃይ እንግልትም እየደረሰባቸው ነው፡፡
“ሃይማኖትና ሀገር ወጣት ሲረከበው ነው ሀገርነቱም፣ እምነቱም ሊቀጥል የሚችለው”
የዛሬው የቤተ አብርሃም እንግዳችን መጋቤ ምሥጢር ቀሲስ ቀጸላ ፈንቴ ይባላሉ፡፡ ከአባታቸው ከቄስ ፈንቴ ታረቀ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ጎንደር በቀለ በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም በምዕራብ ጎጃም ሰከላ ወረዳ ልዩ ስሙ ጉሌ ኪዳነ ምሕረት ተብሎ በሚጠራ ቦታ ተወለዱ፡፡ በአብነት ትምህርቱ ቅኔን ጨምሮ ሌሎቹንም ትምህርቶች ተጨልፎ ከማያልቀው ከቤተ ክርስቲያን ማዕድ በአባቶች እግር ሥር ቁጭ ብለው ተምረዋል፡፡ ወደ አዲስ አበባ በመምጣትም በሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ የካህናት ማሠልጠኛ ለአራት ዓመት የነገረ መለኮት ትምህርት ተምረዋል፡፡ በትውልድ አካባቢያቸው ለ፲፫ ዓመት የቅኔና የሐዲሳት መምህር ሆነው አገልግለዋል፣ ከዚያም ወደ ከተማ በመምጣት ከ፳፪ ዓመታት በላይ የቅኔ፣ የሐዲሳትና የብሉያት መምህር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ በርካታ ተማሪዎችን አስተምረው ለአገልግሎት አብቅተዋል፡፡ በአጠቃላይ ባሳለፉት የአገልግሎት ዘመን የቅኔና የትርጓሜ መምህር ሆነው በማገልገል ከ፴፱ ዓመት በላይ አስቆጥረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሃይማኖተ አበው ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡ ከመጋቤ ምሥጢር ቀሲስ ቀጸላ ፈንታ ጋር በሕይወት ተሞክሯቸው ዙሪያ ልምዳቸውን፣ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ያጋሩን ዘንድ የቤተ አብርሃም እንግዳችን አድርገናቸዋል፤ መልካም ንባብ፡፡
ማማተብ
ሰላም ልጆች እንደምን አላችሁ? ደኅና ናችሁ? መቼም እግዚአብሔር ይመስገን እንዳላችሁ ተሰፋ አደርጋለሁ፡፡ ልጆች ምንጊዜም ቢሆን እግዚአብሔርን ማመስገን መዘንጋት የለብንም እሺ? ምክንያቱም እኛ ሰዎች የተፈጠርነው ለምስጋና ስለሆነ ነው፡፡ ስለሆነም ልጆች በዚህ ክፍል በአጭሩ ሰለ ማማተብ እንማማራለን፡፡ እስኪ ስለማማተብ ምን ታውቃላችሁ ልጆች? የማማተብ ትርጉሙስ ምንድ ነው ትላላችሁ? እንግዲያውስ ዛሬ ስለማማተብ አጭር መርጃ ይዠላችው ቀርቤለሁ፤ መልካም ንባብ ይሁንላችሁ፡፡