መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ቅዱስ ማርቆስ
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? እንኳን ለዚህ ዕለት አደረሳችሁ! በእግዚአብሔር ምሕረት፣ በትንሣኤው ትንሣኤያችን ተበሥሮልን ከዛሬ ዕለት ደረስን! በቸርነቱ ለዚህ ያደረሰን ፈጣሪ ይመስገን!
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለዛሬ ያዘጋጀንላቸሁ የወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስን ታሪክ ነው፡፡
ዘርና ቦዝ አንቀጽ
የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! በዓለ ትንሣኤን በሰላም እንዳሳለፋችሁ ተስፋ እናደርጋለን፤ መልካም!
ታስታውሱ እንደሆነ ባለፈው የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን ‹ንዑስ አንቀጽና ቅጽሎች› በሚል ርእስ አስተምረናችኋል። በዚያም መሠረት ትምህርቱን በተረዳችሁበት መጠን እንድትሠሩትም የሰጠናችሁ መልመጃ ነበር። ስለዚህም በዚህ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ላቀረብንላችሁ የመልመጃ ጥያቄዎች ምላሻቸውን እንዲሁም ስለ ‹ዘርና ቦዝ አንቀጽ› አቅርበንላችኋል፤ በጥሞና ተከታተሉን!
ምስካዬ ኅዙናን መድኃኒዓለም ገዳም
ምስካዬ ኀዙናን መድኃኒዓለም በታሪካዊ ሂደቱና በአገልግሎቱ የተለያዩ ሥራዎችን በመጀመር ለሌሎች ቤተ ክርስቲያናት አርአያ የሆነ ገዳም ነው፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ዕረፍት
በሚያዝያ ሃያ ሦስት ቀን ፀሐይና የአጥቢያ ኮከብ የተባለ ታላቅና ክቡር የሆነ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ የምስክርነት ፍጻሜ ሆነ፡፡
‹‹ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል›› (መዝ.፲፪፥፭)
በሰው ዘንድ የነበረውን መርገም በማጥፋት የሁሉም ፈጣሪ አምላካችን እግዚአብሔር ሞትን ድል አድርጎ ዓለምን አዳነ። ትንሣኤ ሙታን በተባለው የሙታን መነሣትም ነፍስና ሥጋ ተዋሕደው በመነሣት የዘለዓለማዊ ሕይወት መገኛ ጥበብ ወይም የድኅነት መንገድ ሆነልን፡፡
እንኳን ለበዓለ ትንሣኤ አደረሳችሁ!
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች እንዴት አላችሁ? እንኳን ለዚህ ዕለት አደረሳችሁ! በእግዚአብሔር ቸርነት የጾሙ ጊዜ ተፈጽሞ፣ በትንሣኤው ትንሣኤያችን ለተበሠረበት ዕለት ደረስን! በቸርነቱ ለዚህ ያደረሰን ፈጣሪ ይመስገን!
ትንሣኤ
ለሰው ልጆች ዘለዓለማዊ ትንሣኤ በኩር የሆነው የክርስቶስ ትንሣኤ ነው፡፡ መድኃኒዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባታችን ለአዳም በገባው ቃልኪዳን መሠረት በአይሁድ እጅ መከራ መስቀልን ከተቀበለና ነፍሱን በራሱ ሥልጣን አሳልፎ ከሰጠ በኋላ ዐርብ በ፲፩ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ መስፍኑ ጲላጦስን አስፈቅደውና ከመስቀል አውርደው ዮሴፍ ራሱ ባሠራው መቃብር በንጹሕ በፍታ ገንዘው ቀበሩት፤ መቃብሩንም ገጥመው ሲሄዱ ጸሐፍት ፈሪሳውያንና መስፍኑ በመቃብሩ ላይ ማኅተማቸውንና ጠባቂዎችን አኖሩ፡፡ በሦስተኛው ቀን እሑድ በእኩለ ሌሊት መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በታላቅ ኃይል ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ተነሣ!!!
አንተ ጽኑ አለት ነህ
በጽናትህም ላይ እሠራለሁ መቅደስ
እያለ ሲነግረው ጌታችን ለጴጥሮስ
በምድርም ያሠርኸው በሰማይ ይታሠር
በሰማይ ይፈታ የፈታኸው በምድር
ብሎ ሾሞት ሳለ በክብር ላይ ክብር
መሳሳት አልቀረም አይ መሆን ፍጡር!
ሰሙነ ሕመማት
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች እንዴት ሰነበታችሁ? ትምህርት እንዴት ነው? የዐቢይ ጾም ወቅትንስ እንዴት እያሳለፋችሁ ነው? ይህ ጾም ጠላታችን ዲያቢሎስ ያፈረበት፣ ትዕቢት፣ ስስት፣ፍቅረ ንዋይ ድል የተደረጉበት፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጹሞ እንጾም ዘንድ ባርኮ የሰጠን ታላቅ ጾም ነው፡፡ ታዲያ ይህን ወቅት መልካም ሥራ እየሠራን፣ ለሀገር፣ ለቤተ ክርስቲያን እየጸለያችሁ እንዳሳለፋችሁ ተስፋ እናደርጋለን! መልካም!
ውድ የእግአብሔር ልጆች! ባለፉት ጊዜያት በዐቢይ ጾም ስለሚገኙ ሳምንታት ስያሜ ባስተማርናችሁ መሠረት በርካታ ቁም ነገሮችን ስንማማር እንደነበር ታስታውሳላችሁ አይደል? አሁን ደግሞ ስለ ሰሙነ ሕማማት ጥቂት ልናካፍላችሁ ወደድን፤ መልካም ቆይታ
ሆሣዕና
‹ሆሼዕናህ› ከሚለው በዕብራይስጥ ቃል የተገኘው ‹ሆሣዕና› ትርጉሙ ‹እባክህ አሁን አድን› ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል በዘመነ ብሉይ በቀደምት ነቢያት ዘንድ የተለመደ ቃል ነው፡፡ ‹‹አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፡፡›› (መዝ.፻፲፯፥፳፭-፳፮) የሆሣዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት ‹‹ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም›› በማለት ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡ በዓሉም ሆሣዕና የሚለውን ስያሜ ያገኘው በዕለቱ ከተዘመረው መዝሙር ነው፡፡ (ዮሐ.፲፪፥፲፫)