መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ዐቢይ አገባብ
የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! ባለፈው የትምህርታችን ክፍለ ጊዜ ‹‹ዘርና ቦዝ አንቀጽ›› በሚል ርእስ አስተምረናችሁ ነበር፡፡ በዚህ ሳምንት ደግሞ ለሰጠናችሁ መልመጃ ምላሽና ስለ ዐቢይ አገባብ እንመለከታለን፤ በጥሞና ተከታተሉን!
‹‹እግዚአብሔር ግን ለዘለዓለም ይኖራል›› (መዝ.፱፥፯)
ዘመን የማይቆጠርለት፣ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር፣ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው አምላካችን እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይኖራል፡፡ በምድር ላይ ያሉ የምናያቸው አስደናቂና አስገራሚ የምንላቸው ነገሮች ሁሉ ያልፋሉ፡፡ እግዚአብሔር ግን እነዚህን ሁሉ አሳልፎ የሚኖር ዘለዓለማዊ አምላክ ነው፡፡‹ ‹‹እምቅድመ ዓለም ወእስከለዓለም ሀሎ እግዚአብሔር በመንግሥቱ፤ ዓለምን ከመፍጠሩ በፊት ዓለምን ከፈጠረ በኋላ ለዘለዓለም እግዚአብሔር በመንግሥቱ አለ›› እንዲል ቅዳሴ::
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
በዓለ ቅዱስ ያሬድ
ኢትዮጵያዊው ሊቅ የዜማ ደራሲ ቅዱስ ያሬድ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተሠወረበት ቀን ግንቦት ፲፩ የከበረ በመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታከብረዋለች። ይህ ቅዱስ ከአባ ጌዴዎን ዘመዶች ወገን ነው። እርሱም በኢትዮጵያ ሀገር ከታነጹት አብያተ ክርስቲያናት ለምትቀድም ከአክሱም ካህናት ውስጥ ነው፡፡ እርሷም አስቀድሞ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በውስጥዋ የተከበበና አምላክን በወለደች በእመቤታችን በከበረች ድንግል ማርያም ስም የከበረች ናት::
ዕረፍቱ ለቅዱስ አትናቴዎስ
ቅዱስ አትናቴዎስ የተወለደው ግብጽ ውስጥ እስክንድርያ ነው:: ሐናፊ ከሚባል የእስላም ነገድና ከአረማውያን ወገን በመሆኑ በልጅነቱ ክርስትናን መማር አልቻለም ነበር::አንድ ቀን ግን ክርስቲያን ሕፃናት እርስ በእርሳቸው እየተጫወተ ተመለከተ። ጨዋታቸውም የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመሥራት ስለነበር ከመካከላቸው ዲያቆናትንና ኤጲስ ቆጶሳትን ሲመርጡ እንዲያጫውቱት ለመናቸው። ነገር ግን ‹‹አንተ አረማዊ ነህና ከእኛ ጋር አትደመርም›› በማለት ከለከሉት፡፡አትናቴዎስም ‹‹ክርስቲያን እሆናለሁ›› ባላቸው ጊዜ ሕፃናቱ ደስ ተሰኝተው ማዕረጋቸውን ለመለየት ዕጣ ተጣጣሉ::ለአንዱ ቄስ፣ ለአንዱም ዲያቆን መሆን ሲደርሳቸው ለአትናቴዎስ ፓትርያርክ መሆን ስለ ደረሰው ሌሎቹ ሕፃናት ይሰግዱለት ጀመር::…
ወርኃ ግንቦት
በቀደምት ዘመናት ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን በተለይም ምእመናን ስለ ወርኃ ግንቦት (የግንቦት ወር) የነበራቸው አመለካከት የተሳሳት እንደነበር ታሪክ ያስረዳል፡፡ በዚያን ጊዜ ወቅቱ የተረገመ እንደሆነ በማሰብም ማንኛውንም ተግባር አይፈጽሙም ነበር። በዚህ ወቅት ነገሮች ሁሉ መጥፎ የመሆን ዕድል እንዳላቸው በማመን ምንም ዓይነት ምግባር አያከናውኑም፡፡ በርካቶችም የሚሠሩት ቤት ወይም የሚያስገነቡት ሕንፃ ፍጻሜው ጥሩ እንደማይሆንላቸው ያስቡ ነበር፡፡ ትዳር በግንቦት ወር የፈጸሙ ምእመናን ካሉ መጨረሻው እንደማያምር ያምኑም ነበር። ለዚህም አስተሳሰባቸው የሚያነሡት ሁለት ምክንያቶች የተሳሳቱ ናቸው፡፡…
ልደታ ለማርያም
በግንቦት አንድ ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች። እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት፡፡ ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ። በዚያ ወራት የመካኖች መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና፡፡ እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር፡፡ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ሐሳባቸውን ተመለከተ፡፡ ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው፡፡
ቅዱስ ማርቆስ
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? እንኳን ለዚህ ዕለት አደረሳችሁ! በእግዚአብሔር ምሕረት፣ በትንሣኤው ትንሣኤያችን ተበሥሮልን ከዛሬ ዕለት ደረስን! በቸርነቱ ለዚህ ያደረሰን ፈጣሪ ይመስገን!
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለዛሬ ያዘጋጀንላቸሁ የወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስን ታሪክ ነው፡፡
ዘርና ቦዝ አንቀጽ
የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! በዓለ ትንሣኤን በሰላም እንዳሳለፋችሁ ተስፋ እናደርጋለን፤ መልካም!
ታስታውሱ እንደሆነ ባለፈው የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን ‹ንዑስ አንቀጽና ቅጽሎች› በሚል ርእስ አስተምረናችኋል። በዚያም መሠረት ትምህርቱን በተረዳችሁበት መጠን እንድትሠሩትም የሰጠናችሁ መልመጃ ነበር። ስለዚህም በዚህ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ላቀረብንላችሁ የመልመጃ ጥያቄዎች ምላሻቸውን እንዲሁም ስለ ‹ዘርና ቦዝ አንቀጽ› አቅርበንላችኋል፤ በጥሞና ተከታተሉን!
ምስካዬ ኅዙናን መድኃኒዓለም ገዳም
ምስካዬ ኀዙናን መድኃኒዓለም በታሪካዊ ሂደቱና በአገልግሎቱ የተለያዩ ሥራዎችን በመጀመር ለሌሎች ቤተ ክርስቲያናት አርአያ የሆነ ገዳም ነው፡፡