መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
“በምንም አትጨነቁ” (ፊል.፬፥፮)
በሕይወታችን ለሚገጥመን ማንኛውም ችግር ከእግዚአብሔር ዘንድ መፍትሔ ይኖረዋል፡፡ በእርሱ አምነንና ታምነን እስከኖርን ድረስ ከመከራና ከሥቃይ ያወጣናል፡፡ ሰዎች በተለያዩ ጊዜያት በሕይወታቸው ውስጥ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ የሚረዳቸው ቤተሰብም ሆነ ዘመድ ከሌላቸው ደግሞ ችግራቸውን ስለሚያባብሰው ወደከፋ መከራ ውስጥ ሲገቡ ሰምተንም ሆነ ተመልክተን ይሆናል፡፡ ነገር ግን አምላካችን እግዚአብሔር ሰውን የሚፈትነው ለበጎ እንደሆነ በማወቅና በመረዳት የነገን ተስፋ አድርጎ መኖር ይኖርብናል እንጂ ተስፋ መቁርጥ ወይም ማማረር አይገባም፡፡ በተቻለው መጠን ለኑሯችን ተሯሩጠን የዕለት ጉርሻችን መሙላት እንዲሁም ወደ ተሻለ ሕይወት መትጋት ይገባል፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ
ሥርዓተ አምልኮ
ሥርዓት “ሠርዐ” ሠራ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደንብ፣ አሠራር፣ መርሐ ግብር ማለት ነው። በሃይማኖት ውስጥ የሚፈጸም የመንፈሳዊ አገልግሎትና አሠራር እንዲሁም ክርስቲያናዊ ሥርዓትን ያመለክታል።
ሥርዓተ አምልኮት
የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮት ለአምላካችን እግዚአብሔር የሚቀርብ ሥርዓት ነው፡፡ ይህም ሥርዓተ ጸሎትን፣ ሥርዓተ ጾምን፣ ሥርዓተ ምጽዋት፣ ሥርዓተ ስግደትን፣ ሥርዓተ በዓላትን፣ ሥዕላትን፣ መስቀልንና ንዋያተ ቅድሳትን ያካትታል፡፡
“ለፀሐይም ቀንን አስገዛው፤ ጨረቃንና ከዋክብትንም ሌሊትን አስገዛቸው” (መዝ.፻፴፭፥፰‐፲)
‹‹የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትን ሥራቸውን ዕወቅ፤ ከሁሉ የሚደንቅ ክበባቸውን ከሁሉ የሚበልጥ ብርሃናቸውን ሁሉ ዕወቅ፤ በየወገናቸው የሚያበሩ የሚመላለሱ የእነዚህን የምሳሌያቸውን ሥራ ዕወቅ፤ ሁሉ ጊዜ እርስ በእርሳቸው እንደምንም እንደሚቀራረቡ ዳግመኛም እንደምንም እንደሚራራቁ ዕወቅ…›› (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ባስልዮስ ምዕራፍ ፴፭፥፲፯)
የዕለተ ሠሉስ ፍጥረታት
ዕለተ ማክሰኞ የፍጥረት ሦስተኛ የምስጋና ሁለተኛ ቀን ነች፤ በባሕረ ሐሳብ ቀመር ደግሞ ዕለተ ቀመር ትባላለች፤ በፀሐይ አቆጣጠር ሰባተኛ ቀን ትባላለች፡፡ ዛሬ ግን የምናነሣው በዕለተ ፍጥረት ስለተከናወነባት ክንዋኔ ነው፡፡
በዓታ ለማርያም
ታኅሣሥ በባተ በሦስተኛው ቀን የሚታሰበውና የሚከበረው በዓል ‹‹በዓታ ለማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከእናቷ ከቅድስት ሐና እና ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄም በስዕለት የተወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት የከበረ እንደመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡
እየተሰማ ያለው የሞትና የእልቂት ዜና የብዙዎችን ልብ የሚሰብር፣ የሰላሙን አየር የሚያውክና ቤተ ክርስቲያንን የሚያሳዝን ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
‹‹አትስረቅ›› (ዘፀ.፳፥፲፭)
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? ትምህርት እንዴት ነው? እየበረታችሁ ነውን? የመንፈቀ ዓመቱ (የዓመቱ ግማሽ) የትምህርተ ዘመን ሊጠናቀቅ የቀሩት ጥቂት ሳምንታት ናቸው፡፡ ለመሆኑ ምን ያህል ዕውቀት አገኛችሁ? ትናንት የማታውቁት አሁን አዲስ የተጨመረላችሁ ዕውቀት ምንድን ነው? ይህን ራሳችሁን መጠየቅ አለባችሁ? መማራችሁ ከክፍል ወደ ክፍል ለመሸጋገር ብቻ ሳይሆን ባላችሁ ግንዛቤ ላይ ሌላ ዕውቀት ለመጨመር ነውና በርቱ! መማራችሁ ለተሻለ ሕይወት፣ ዛሬን ከትላንትና፣ ነገን ደግሞ ከዛሬ የተሻለ ሆኖ እንድታገኙት ሊሆን ይገባል፡፡ መልካም! ለዛሬ የምንማረው ከዐሥርቱ ትእዛዛት መካከል አንድ ስለሆነው ‹‹አትስረቅ›› ስለሚለው የእግዚአብሔር ሕግ ነው!
የነፋስ ነገር
እግዚአብሔር ያለ ምክንያት የፈጠረው ፍጥረት የለምና ነፋስንም በምክንያት ፈጥሮታል፡፡ ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ “ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል፡፡ ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፤ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች” በማለት እንደዘመረው ሥነ ፍጥረት አእምሮ ላለው የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን ባሕርያዊ መገለጫዎች ሥራና ፈቃዳት ያስተምራሉ፡፡ (መዝ.፲፰፥፩) ሰውንም ሲፈጥረው ከዐራቱ ባሕርያተ ሥጋ አምስተኛ ባሕርየ ነፍስን አድርጎ በመልኩና በምሳሌው እንደፈጠረው የታወቀ ነው፡፡ (ዘፍ. ፩፥፳፮) እነዚህ አራቱ ባሕርያተ ሥጋ የሚባሉትም ነፋስ፣ እሳት፣ መሬትና ውኃ ናቸው፡፡ በሥነ ፍጥረት ትምህርት እግዚአብሔር ሰውን ከእነዚህ ዐራት ባሕርያት የፈጠረበት ምክንያት በምልዓትና በስፋት ይተነተናል፡፡ በዚህ አጠር ያለ ጽሑፋችንም ከነፋስ ምን እንማራለን? የሚለውን እናነሣለን፡፡
ሥረይ ግሦች
የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! የዚህን ዓመት የኅዳር የመጨረሻ ክፍለ ጊዜያችን የሆነውን ትምህርት ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ ከባለፈው ትምህርታችን ቀጣይ ወይም ሦስተኛና የመጨረሻ የሆነውን ትምህርታችንን ከማቅረባችን በፊት በ ‹‹ሥረይ ግሥ›› ክፍል ሁለት ትምህርታችን ለማየት የሞከርነው በግእዝ ቋንቋ ከግሥ ዓይነቶች አንዱ የሆነው ሥረይ ግሥን በግሥ አርእስት በቀተለ፣ በቀደሰ፣ በተንበለ፣ በባረከና በማህረከ ሥር መድበን ርባታቸውን እንደሆነ እያስታወስናችሁ በመቀጠል ደግሞ በዴገነ/ሴሰየ፣ በክህለ እና በጦመረ ሥር የሚመደቡ ሥረይ ግሦችን እናቀርብላችኋለን፡፡