መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
ቅዱስነታቸው በጥር ፳፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የሰጡት የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
በዓለ ዕረፍታ ለማርያም
እንኳን ለእናታችን ለቅድስተ ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ!
የቅድስት ድንግል ማርያም ሞት ግን ይደንቃል! የሞትን ኃይል ያጠፋ፣ ሞትን በሞቱ የገደለ፣ ክርስቶስን ወልዳ ሳለ መሞቷ ይደንቃል። እናም “ለምን ሞተች?” ብሎ መጠየቅ የተገባ ነው፤ ይኸውም በተአምረ ማርያም ተጽፎ እንደምናገኘው በሲኦል ያሉ ነፍሳትን አሳይቷት ስለነበር በልጇ ሞት ነፍሳት እንደዳኑ በእርሷ ሞትም ነፍሳትን እንደሚያድንላት ስለነገራት ስለ ኃጢአተኞች ነፍሷን በልጇ ትእዛዝ ሰጠች።
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
“ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አታሸነፍ” (ሮሜ ፲፪፥፳፩)
ክፉና በጎ የሰው ልጆች ባሕርያት ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር ለመልካም ነበረ፡፡ (ዘፍ.፩፥፲፪) ምንም እንኳን የፍጥረት አክሊል የሆነው ሰው ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ከብርሃን ጨለማን፣ ከሕይወት ሞትን፣ ከመታዘዝ አለመታዘዝን ቢመርጥም እግዚአብሔር አምላክ የፈጠረው ስሙን እንዲቀድስ ክብሩን እንዲወርስ ነበረ፡፡ ለዚህም ክፉና ደጉን መለየት ይችል ዘንድ አስቀድሞ የሚያስተውል አእምሮ ሰጥቶት ነበር፡፡ በኅሊናው መመራት ተስኖት የሰው ልጅ ከወደቀ በኋላ ዳግመኛ የተጻፈ ሕግ ሰጥቶታል፡፡ ሰዎች ራሳቸው ላይ የክፉ ብድራት እንዳይደርስባቸው አስበው በባልንጀራቸው ላይ ክፉ እንዳያደርጉ ክፉ ላደረጉ የክፉ ብድራት እንዲከፈላቸው ሙሴ ሕግን ጻፈላቸው፡፡
በዓለ ጥምቀት
እንኳን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት ለበዓለ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ፡፡ የጥምቀት ትርጉም፡- ጥምቀት የሚለው ቃል “አጥመቀ” (አጠመቀ) ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም በተከማቸ ውሃ ውስጥ መነከር፡ መዘፈቅ፡ ገብቶ መውጣት ማለት ነው። ጥምቀት በፅርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒ፣ በግእዝ አስተርእዮ፣ በአማርኛ መገለጥ ይባላል፡፡ ቃሉ በቀጥታ ሲተረጎም በውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት፣ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መጥለቅ ማለት ነው፡፡ ምሥጢረ ጥምቀት በምሥጢራዊ ፍቺው […]
መጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን
መጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን መጽሔት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን በሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ የተዘጋጀ ነው፡፡ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መጽሔቱን ያንብቡ!
ቃና ዘገሊላ
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በጥር ፲፪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ በተደረገ ሠርግ ቤት ያደረገውን ተአምር በማሰብ በዓልን ታደርጋለች፡፡ ጌታችን ከጥምቀቱ በኋላ በዶኪማስ ሠርግ ቤተ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲሁም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ታጋብዞ በነበረበት ጊዜ ለእንግዶች ወይን ጠጅ አለቀባቸው፡፡
‹‹በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ›› (ማቴ.፫፥፲፫)
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ! እንኳን አደረሳችሁ! የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል እንዴት አለፈ? ልጆች! አሁን ያላችሁበት ወቅት የዓመቱ አጋማሽ የፈተና ወቅት ነው! ፈተናውን በደንብ አድርጋችሁ መሥራት አለባችሁ! መቼም በርተታችሁ ስታጠኑና ያልገባችሁን ስትጠይቁ ስለነበር በፈተና የሚቀርቡላችሁን ጥያቄዎች በትክክል እንደምትመልሱ አንጠራጠርም! ምክንያቱም የምትጠየቁት የተማራችሁትን ስለሆነ በአንዳች ነገር እንዳትዘናጉ!
ታዲያ ልጆች! ፈተናውን የምትሠሩት ጥሩ ማርክ ለማምጣት ብቻ ሳይሆን ለእውቀትም መሆን አለበት፡፡ ዕውቀት ማለት በተግባር መተርም መሆኑን እንዳትዘነጉ! መልካም! ልጆች ዛሬ ስለ ጌታችንን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት እንማራለን፡፡
ሥርዓተ አምልኮ
በዓላት ከማንኛውም ቀናት የበለጠ አምላካችን እግዚአብሔርን የምናመሰገንባቸውና የምናወድስባቸው፣ የተቀደሱትን ዕለታት በማሰብና በመዘከር በዝማሬ፣ በሽብሻቦና በእልልታ የምናከብርባቸው ናቸው፡፡ ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው የሚወጡባቸውና ሕዝበ ክርስቲያኑን የሚባርኩባቸው ስለሆኑም በክብርና በድምቀት ይከበራሉ፡፡
“ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው” (ዘፍ.፲፩፥፯)
አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በኃጢያት የተገነባውን የሰናኦር ግንብ ያፈረሱበትና አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ቀን ጥር ሰባት የከበረ በዓል ነው፤