መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::




ጾመ ነቢያት
ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር በጸጋ እንደተወለዱ በማመን ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር ከሚገልጡባቸው ነገሮች አንዱ ጾም ነው፡፡ ጾም ፍቅረ መብዓ ከመሆኑ በተጨማሪ ታዛዥነትንና የገቡትን ቃል ኪዳን ጠባቂነትንም ማሳያ ነው፡፡ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አርአያ ተፈጥሯአል፡፡ ኃጢአት ሠርቶ የእግዚአብሔር አርአያነቱን ቢያጠፋውም እግዚአብሔር ግን በአርአያው ሲፈጥረው ምን ያህል እንደሚወደው ማረጋገጫ ስለነበር በኃጢአት ሲወድቅም እንደወጣ ይቅር ሳይል ሊፈልገው መጣ፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሊፈልግ የመምጣቱ ተስፋ የተነገረበትንና ሱባኤ የተቆጠረበትን ዕለት ለማየት በመናፈቅ ከቀረበው መሥዋዕት አንዱ ጾም ነበር፡፡
ሰው በኃጢአት ቢወድቅም ፈጣሪው ሊያነሳው፤ ቢጠፋ ሊፈልገው እንደሚመጣ በተስፋ ሲጠብቀው ወልደ አምላክ ሰው መሆኑ የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡ ስለዚህ አዳም የልደቱን ነገር በትንቢት መነፅርነት ሲመለከተው /በነቢያቱ ትምህርትና ስብከት/፣ በሚኖርበት ዓመተ ፍዳ የምሥጢረ ሥጋዌ ብርሃን ከሩቅ ሲመለከተው ኖረ፡፡ ምሥጢረ ሥጋዌን በትንቢት መነፅርነት ማየቱም መከራውን እንዲቋቋመው የተስፋ ስንቅ ሆነው፡፡
የመንፈስ ልዕልና
ልዕልና ከተለመደ ነገር ላቅ ማለትን፣ ሰው ሊሠራው ከሚችለው በላይ መስራትን ያመለክታል፡፡ በአስተሳሰብ ምጥቀት፣ በሚፈጸም ጀብዱ ይገለጻል፡፡ ጥብዓት፣ በመንፈሳዊ ቆራጥነት፣ ወኔ፣ በተፋፋመ አካላዊ ሆነ መንፈሳዊ ጦርነት ለመግባት መጨከን የልዕልና መገለጫዎች ናቸው፡፡ “በሞት ጥላ መካከል እንኳን ባልፍ ክፉን አልፈራም አንተ ከእኔ ጋር ነህና” እንዳለ መዝሙረኛው፡፡
ሥጋዊ ፈቃድ የጠየቀውን ሁሉ አለመተግበር፣ በስሜት የተፈጠረን ሁሉ ለማስተናገድ አለመሞከር በተቃራኒው መንፈስ በሥጋ ላይ ማሰልጠን ወይም ሥጋን ለመንፈስ ማስገዛት የልዕልና ተግባር ነው፡፡ የሰሙትን ምሥጢር መጠበቅ፣ የተቀበሉትን አደራ መወጣትም እንዲሁ ቃልን መጠበቅ፣ ታምኖ መሰማራት፣ አደራን መመለስ ለሁሉ አይቻለውም፡፡ ልዕልና በፈተና መጽናትን፣ እንደወርቅ መቅለጥን፣ ሌላው እየበላ ጦም ማደርን፣ ሌላው እየዘነጠ በድህነት መማቀቅን ሊያስከትል ይችላል፡፡ የሚያልፈውን በማያልፈው አሸንፈው፣ ጊዜያዊውን በዘለዓለማዊው ተቆጣጥረው የተጋረጠባቸውን ያሸንፉታል ለልዕልና የታጩቱ፡፡
የአትናቴዎስ ትምህርት ስለ መንፈስ ቅዱስ
«ጾምን ቀድሱ» /ኢዮ.2-15/
ጾም
የሰውን ልጆች የሚወደውና ስለ እነርሱም ብሎ በገነት ያሉትን ዛፎች ሁሉ የፈጠረው እግዚአብሔር በገነት ካሉት ዛፎች መካከል አንዲቱን እንዳይበላ አዳምን አዘዘው፡፡ ይኽ አዳምን ለመጫን፣ ኃይሉን በእርሱ ላይ ለማሳየት ሳይሆን ሰው በመጾም /ባለመብላት/ እና በመታዘዝ ለሚወደው አምላኩ ፍቅሩን ይገልጽ ዘንድ ነው፡፡
ከአዳም ድቀት በኋላም በየዘመናቱ የተነሡ መንፈሳውያን ሰዎች እና ሕዝቦች በየግላቸው እንዲሁም በአንድነት /በጋራ/ ሲጾሙ፣ በጾማቸውም ሲጠቀሙ ኖረዋል /ሕዝበ እስራኤል ሙሴ፣ ኤልያስ፣ የነነዌ ሰዎች. . ./፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ከአዲሱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሓላፊ ጋር ስለ ቀጣዩ የአገልግሎት ዘመን ተወያየ፡፡
ኅዳር 8/2004 ዓ.ም በዲ/ን ኅሩይ ባየ ማኅበረ ቅዱሳን ከአዲሱ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሓላፊ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ ኅሩይ ጋር ኅዳር 7 ቀን 2004 ዓ.ም ስለ ቀጣዩ የአገልግሎት ዘመን ተወያየ፡፡ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በሰ/ት/ቤቶች ማደሪጃ መምሪያ ቢሮ በተደረገው ውይይት፣ ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የተነሣባቸውን ወደ ዐሥራ ሁለት የሚሆኑ ነጥቦችን በማብራራት የማኅበሩ ሰብሳቢ ሊቀ […]
ግብጻውያን ኦርቶዶክሳዊ የሕክምና ባለሙዎች በኢትዮጵያ ነጻ አገልግሎት ሰጡ::
በኢዮብ ሥዩም በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጠያቂነትና በግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መልካም ፈቃድ ግብጻውያን ኦርቶዶክሳዊ የሕክምና ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ነጻ አገልግሎት ሰጡ፡፡ የሕክምና ቡድኑ አባላት ከ27/2/2004 ዓ.ም – 1/3/2004 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ ሆስፒታሎች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አገልግሎት እንደሰጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሃያ ሦስት አባላት ያሉት የሕክምና ቡድን አባላት መሪ የሆኑት ዶክተር ጆርጅ ታድሮስ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ […]
የሰለሞን ምቅናይ ምስል ወድምጽ /ቪሲዲ/ ተመረቀ
ኅዳር 6/2004 ዓ.ም
በፈትለወርቅ ደስታ
በምረቃው ላይ ብፁዕ አቡነ ሰላማ የአክሱም ጽዮን ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ የደቡብ ጐንደር ሊቀ ጳጳስና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ዘመነ አስተምህሮ
ኅዳር 6/2004 ዓ.ም
በቤተ ክርስተያናችን የዘመን አቆጣጠር /አከፋፈል/ መሠረት ከኀዳር 6 ጀምሮ እስከ ታኀሣሥ 13 ድረስ ያለው ወቅት ዘመነ አስተምህሮ ይባላል፡፡
መሀረ ማለት ይቅር አለ ማለት ሲሆን፤ ዘመነ አስተምህሮ ማለት ይቅርታ የመጠየቅ /የምልጃ/ ዘመን ማለት ነው፡፡ ዘመኑ ቤተ ክርስቲያን ስለ ልጆቿ ይቅርታ የምትጠይቅበት፤ ምዕመናንንም ስለ በደላቸው ይቅርታ የሚጠይቁበት፤ ስለዚህም በስፋት ትምህርት የሚሰጥበት ዘመን ነው፡፡
ከትርፍ ነፃ የሆኑ የምስልና የድምጽ ሲዲዎች እንደሚሠራጩ ተገለጠ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል የተዘጋጁ 3 ሺህ የሚሆኑ የምስልና የድምጽ ሲዲዎች ኅዳር 8 ቀን 2004 ዓ.ም በማኅበሩ ጽ/ቤት እንደሚሠራጭ የምክረ ሐሳቡ አስተባባሪ ኢንጂነር ሙሉጌታ ጌትነት አስታወቁ፡፡
ኢንጅነር ሙሉጌታ እንደገለጡት የምስልና የድምጽ ሲዲዎችን ለማግኘትና ለማሠራጨት ምንም ዐይነት ትርፍ ታሳቢ ሳይደረግ የሲዲውን ዋጋ ብቻ በመሸፈን ማግኘት ይቻላል፡፡ በማያያዝም የሥርጭቱ ዋና ዓላማ ስብከተ ወንጌልን በተፋጠነ መንገድ ለምእመናን ማዳረስ ሲሆን በገበያ ላይ የሚገኙት የምስልና የድምጽ ሲዲዎች የምእመናንን ምጣኔ ሀብት የሚጎዱ በመሆናቸው በቀላሉ ቃለ እግዚአብሔር የሚስፋፋበትን መንገድ ለማመቻቸት፣ የተሐድሶ መናፍቃን ስሑት ትምህርቶች በሕዝበ ክርስቲያኑ ሰርገው ስለገቡ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ያላቸውን የስብከት ሲዲዎች ምእመናን እንዲያገኙና ስለ ሃይማኖታቸው እንዲያውቁ ለመደገፍ፣ በከተማ የሚኖሩ ጥቂት ምእመናን የመካነ ድር አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቢሆኑም አገልግሎቱ ውድና ዝቅተኛ ፍጥነት ስላለው የምስልና የድምጽ ዝግጅቶችን መመልከትና መስማት ስለማይችሉ ችግሩን አስወግዶ ተደራሽነትን ለማስፋፋት እንዲቻልና የቪሲዲ አገልግሎት ከገጠር እስከ ከተማ እየተስፋፋ በመምጣቱ ንጹህ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶችን ለሁሉም እንዲዳረስ ለማድረግ እንደሆነ አስተባባሪው አስገንዝበዋል፡፡
እነሆ እኔ በእናንተ ደስ ይለኛል፡፡ ፊል. 2፡17
ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተችበት ጊዜ አንሥቶ የቀና እውነተኛና መልካም ጉዞዋን የሚፈታተኑ በዙሪያዋ ጠፍተው አያውቁም፡፡ ከሰው መፈጠር በፊት በመላእክት ዘንድ የነበረችው የመላእክት ማኅበር በክፉው መልአክ /በዲያብሎስ/ እና እርሱን በመሰሉ ጭፍራዎቹ መካከል
ያለ ነውርና ነቀፋ በመገኘቷ የተመረጠች ነበረች፡፡
በጥንተ አበው ታሪክም የምናየው ይህንኑ ነው፡፡ ከአቤል ጀምሮ እስከ ዮሴፍ ያሉ አበው በክፉዎች ብዙ መከራ የደረሰባቸው፣ በዚህች ምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች ሆነው የኖሩ ናቸው፡፡ጌታችን ወደዚህ ምድር በሥጋ እስከመጣበት ድረስ የነበሩት የእስራኤል ልጆች ታሪክም በክፉና መልካም ነገሮች ከሚጎረብጠው ትውልድ መካከል የነበረ ውጣ ውረድ የበዛበት ነው፡፡