መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የ2004 የከተራ በዓል አከባበር ከዓድባራቱ እሰከ ጃንሜዳ፡፡
ጥር 11/2004ዓ.ም.
በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ዐበይት በዓላት ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል የጥምቀት በዓል አንዱ ነው፡፡ይህንም በዓል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ፤ በማእከለ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ ከዋዜማው ከጥር 10 ጀምሮ በደመቀ ሁኔታ በማክበር ላይ ትገኛለች፡፡ ለእኛ አብነት ይሆነን ዘንድ፤ የእዳ ደብዳቤያችንን እንደ ገል ቀጥቅጦ እንደ ሰም አቅልጦ በደላችንን ይደመስስ ዘንድ ጌታ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይህንን መሠረት በማረድግ በየአብያተ ክርስቲያናቱ የሚገኙ ታቦታት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በካህናትና ዲያቆናት፤ እንዲሁም በሰንበት ት/ቤቶች መዘምራንና ምእመናን በዝማሬ በመታጀብ በአቅራቢያቸው ወደሚገኘው ታቦት ማደሪያ በማምራት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በመሔድ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ማምራቱን ያበሥራሉ፡፡ ‹‹ያን ጊዜም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ናዝሬት መጣ ዮሐንስም በዮርዳኖሰ ወንዝ አጠመቀው›› እንዲል፡፡/ማቴ.3፡1/
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መሥራቿን መድኀኔዓለም ክርስቶስን ለዓለም የምትሰብክበት፣ ከእርሱም ያገኘችውን፣ ይህም ዓለም እንደሚሰጠው ያልሆነውን፣ የእግዚአብሔር ልጅነት፣ ሰላም፣ ፍቅርና ትሕትና ለዓለሙ ትሰብክበታለች፡፡ እንዲሁም ለአገራችን በጎ ገጽታን በመፍጠር ረገድ ከተለያዩ አገራት የሚመጡ ጎብኚዎች ተደንቀው የሚያዩትና አንዳንዶች ልባችውን ለእውነት ክፍት ያደረጉ የሚያምኑበት በመስተንግዶው የሚደመሙበት በመሆኑ ሃይማኖታዊ በዓሉን በልዩ ትኩረት ታከብራለች፡፡
ሁለቱ የዘመነ አስተርዮ ክብረ በዓላት በዳግማዊት ኢየሩሳሌም
ጥር 11/2004ዓ.ም
ዲ/ን ጌታየ መኮንን
የ2004 ዓ.ም የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ከርስቶስ የልደት (የገና) እና የጥምቀት በዓላት አከባበር እንደወትሮው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቀና ያማረ ነበር፡፡
ካህናቱ ከታኅሣሥ 27 ቀን ጀምሮ በመድኀኒዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን፤ የአማኑኤል በዓል ዋዜማ ጠዋት ደወል ተደውሎ በጣም በደመቀ ሁኔታ ዋዜማው ተቆሞ ውሏል፡፡ 7 ሰዓት ሲሆን ቅዳሴ ተገባ እስከ 9 ሰዓት ቅዳሴ ተጠናቀቀ፡፡ ማታ 2 ሰዓት ማሕሌት ተደውሎ እስከ ለሊቱ 10 ሰዓት የቀጠለ ሲሆን ከ10 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት የቅዳሴው ሥርዓት ተከናውኗል፡፡ ጠዋት 3 ሰዓት የልደት በዓል ዋዜማ ተደውሎ እስከ 10 ሰዓት እንደቦታው ትውፊትና ሥርዓት መሠረት የቦታው ቀለም እየተባለ የዋዜማው ቅኔ ለባለ ተራዎቹ እየተሰጠ ተከናውኗል፡፡ ማታ 2 ሰዓት የበዓሉ ደወል ተደውሎ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የመጡ ምእመናን፣ የውጭ ሀገር ዜጎች፣ የቤተ ማርያምን የውስጥና የውጭ ቦታ ማሜ ጋራ የተባለውን ቦታ ከበው በእልልታ በጭብጨባ ጧፍ እያበሩ ማኅሌቱ በመዘምራኑ፣ በካህናቱ፣ በዲያቆናቱ በድምቀት ቃለ እግዚአብሔሩ እየተዘመረና እየተወረበ አድሯል፡፡
ከቦታው ቀለሞች «ክርስቶስ መጽአ ውስተ ዓለም»
«ኮከብ ርኢነ ወመጽአነ ንሰግድ ሎቱ ለዘፈለጠ ብርሃነ»
የጌታ ጥምቀት(ለሕፃናት)
ጥር 10/2004 ዓ.ም.
በእኅተ ፍሬስብሐት
የጥምቀት በዓል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀበትን ዕለት የምናከብርበት በዓል ነው፡፡
ጌታችን ከተወለደ በኋላ 30 ዓመት ሲሆነው ዮርዳኖስ ወደሚባለው ወንዝ ሔደ፡፡ በዚያም መጥምቁ ዮሐንስ አጠመቀው፡፡ ጌታችን ሲጠመቅ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ነበር፡፡ ሌሊት ደግሞ ርግብ አይኖርም፤ ምክንያቱም ወደ ጎጇቸው ስለሚገቡ ነው፡፡ በዚያች ዕለት ግን ጌትችን ሲጠመቅ ርግብ መጥታ በራሱ ላይ አረፈች፡፡ ከዚያም ከሰማይ አንድ ድምጽ ተሰማ፤ ድምጹም
“የምወደው ልጄ ይህ ነው፡፡ እርሱን ስሙት” የሚል ነበር፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ድምጽ ነበር፡፡
በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናችኋለን ቆላ.1፥19
ጥር 9/2004 ዓ.ም
በዓላት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎቷን ከምትፈጽምባቸው ሥርዓቶች መካከል እንደ አንዱ ሆነው ይጠቀሳሉ፡፡ በበዓላት ምእመናን ረድኤት በረከት ከማግኘታቸው ባለፈ ቤተ ክርስቲያን የምትሰጣቸውን አገልግሎቶች የሚቀበሉባቸው መንፈሳዊ መድረኮች ናቸው፡፡ በበዓላቱ መምህራን ትምህርተ ወንጌልን ለምእመናን ያደርሳሉ፡፡ በበዓላት አከባበር ሥርዓት ውስጥ ምእመናን በቤታቸው፤ በአካባቢያቸውና በአደባባይ ሁሉም በጋራ በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነትና ጌትነት፣ ለሰውም ያደረገውን የማዳን ሥራ የሚመሰክሩበት፣ በቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ላይ ያላቸውን ጽናት ለየትኛውም ወገን ያለሀፍረት የሚገልጹበት የአገልግሎት ዕድል ነው፡፡
ትምህርተ ጥምቀት በአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ
መግቢያ
ይህ ጽሑፍ መጽሐፈ ምሥጢር ከሚባለው ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ድርሰት የተወሰደ ሲሆን አባ ጊዮርጊስ ጥምቀትን አስመልክቶ የሰጠውን ድንቅ የሆነ አስተምህሮ እናስተውልበታለን፡፡
“…እነሆ ቅዱስ ጳውሎስ መንፈስ ቅዱስን “የክርስቶስ ሕይወት” በማለት ሰየመው መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስ ሕይወት ከሆነ እንዴት አያየውም? ከማየት ዐሳብ ይቀድማልና ከውጫዊ እይታ የአእምሮ እይታ ይበልጣልና ዳግመኛ ቅዱስ ጳውሎስ የሰውን ዐሳብ ከራሱ ከሰውየው በቀር የሚያውቅ የለም፡፡ እኛ ግን የተሰወረውን ገልጦ ጥልቁን መርምሮ የሚያውቅ የእግዚአብሔር መንፈስ አለን” 1ቆሮ.2፥11 አለ፡፡ አንተ ግብዝ ሆይ አብን እንደሚያውቀው ዕወቅ /አስተውል/፡፡ በወንጌል እንደተነገረው ወልድ ብቻውን ምንም ምን ሊያደርግ አይችልም ከአብ ያየውን ይሠራል እንጂ፡፡ አብ የሚሠራውን ወልድም ይህንኑ እንደእሱ ይሠራል፣ አብ ልጁን ይወዳልን የሚሠራውንም ሥራ ሁሉ ያሳየዋል፡፡ ከዚህም የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል፣ እናንተም ታውቁና ታደንቁ ዘንድ ስለ መንፈስ ቅድስም አስቀድመን ነገርናችሁ፡፡ በደለኞች ሆይ ከዛሬ ጀምሮ “ወልድ ከአብ ያንሳል አያህለውም” አትበሉ፡፡ “መንፈስ ቅዱስም ከወልድ ያንሳል አያህለውም ” አትበሉ፡፡
ግዝረት
ጥር 5/2004 ዓ.ም
ግዝረት ከጌታችን ከመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ንዑሳን በዓላት አንዱ ነው፡፡ እነዚህ ንዑሳን በዓላት የሚባሉትም ስብከት፣ ብርሃን፣ ኖላዊ፣ ግዝረት፣ ቃና ዘገሊላ፣ ልደተ ስምዖን፣ ደብረ ዘይት፣ የመጋቢት መስቀልና መስቀል ናቸው፡፡ ነቢያት ይወርዳል፤ ይወለዳል ብለው በትንቢት ይጠባበቁት የነበረው መሲሕ የዓለም ብርሃን፣ የነፍሳት ጠባቂ መሆኑን አምነን የምናከብራቸው ስብከት፣ ብርሃንና ኖላዊ ይባላሉ፡፡ ከእናቱና ከደቀመዛሙርቱ ጋር በሰርግ ቤት የተገኙበት ቃና ዘገሊላ፣ በአርባ ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበትና አረጋዊ ስምዖንን የሰላሳ ዓመት ጎልማሳ የሆነበት “ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ ዐይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና” በማለት የተናገረበት ልደተ ስምዖን ከንዑሳን በዓላት ይመደባሉ፡፡ የዚህ ጽሑፍ ትኩረት ግዝረት በመሆኑ ሀተታዬን ወደ እሱ እመልሳለሁ፡፡
በዲታ ወረዳ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን በአጽራረ ቤተ ክርስቲያን የቃጠሎ አደጋ ደረሰበት
ጥር 5/2004 ዓ.ም
በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት፣ በዲታ ወረዳ፣ ጋና ደሬ ቀበሌ፣ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 29 ቀን 2004 ዓ.ም. ከሌሊቱ በስድስት ሰዓት አካባቢ በእሳት ቃጠሎ አደጋ ደረሰበት፡፡
የቦታው አቀማመጥና አደጋው የደረሰበት ሰዓት ሌሊት በመሆኑ በቦታው ምንም ዓይነት ነዋያተ ቅድሳት ማትረፍ እንዳልተቻለ በቦታው የሚገኙት የደብሩ አገልጋይ ገልጸዋል፡፡ የአደጋውን መከሰት ሰምተው የመጡት የአካባቢው ምዕመናን ከሌሊት ጀምሮ ጥልቅ ሀዘናቸውን በለቅሶ ሲገልጹ እንደነበር በቦታው የተገኙት የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ዘግበዋል፡፡
በችግር ላይ የሚገኘው የበኬ ቅድስት ማርያም የአብነት ትምህርት ቤት እርዳታ ተደረገለት፡፡
ጥር 5/2004 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ማእከል ማኅበራዊና ልማት ክፍል የተዘጋጀ ጉዞ ወደ በኬ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርት ቤት የተካሔደ ሲሆን የጉዞውም ዋነኛ አላማ በአስከፊ ሁኔታ ላይ ለሚገኙት ለደብሯ የአብነት መምህራንና ተማሪዎች ጊዜያዊ የቁሳቁስ እርዳታ /ድጋፍ/ ለማድረግ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
በጉዞውም በክፍሉ አስተባባሪነት ከምእመናንና ከማኅበሩ አባላት የተሰበሰቡና የተዘጋጁ 11 ኩንታል ስንዴ ዱቄት፣ 230 ሱሪ፣ 398 ሹራብና ቲሸርት፣ 145 ኮትና ጃኬት፣ 25 የአልጋ ልብስና አንሶላ፣ 43 የተለያዩ ልብሶች፣ 230 ግራም 249 የልብስ ሳሙና እና ለመማሪያ የሚሆኑ 11 መጻሕፍት ተበርክተዋል፡፡
እድለኞቹ እረኞች /ለሕፃናት/
ጥር 3/2004 ዓ.ም በእኅተ ፍሬስብሐት በአንድ ምሽት በቤተለሔም አካባቢ እረኞች በጎቻቸውን ተኩላዎች እንዳይበሉባቸው ይጠብቁ ነበር፡፡ እኩለ ሌሊት ሲሆን በዚያ አካባቢ ልዩ ብርሃን ታየ፡፡ እረኞቹ ያንን ብርሃን ሲያዩ በጣም ተገረሙ፡፡ በዚያም መልአክ መጣ እና በዚያች ሌሊት የዓለም መድኀኒት የሚሆን ሕፃን መወለዱን፤ ያም ሕፃን የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ለእረኞቹ ነገራቸው፡፡ እረኞቹም ተደሰቱ ፈጥነው ሕፃኑ ወደ ተወለደበት ወደ ቤተልሔም […]
መካነ ጉባኤያት ወላዴ ሊቃዉንት ደብረ ሃይማኖት መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ዕድሳት ሊደረግለት ነዉ፡፡
ታኅሣሥ 27/2004 ዓ.ም
ለዕድሳቱ 1.5 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡