መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ገብርኄር /ለሕፃናት/
መጋቢት 14/2004 ዓ.ም.
በቴዎድሮስ እሸቱ
ደህ
ና ሰነበታችሁ ልጆች? እንዴት ናችሁ? በጾሙ እየበረታችሁ ነው አይደል? ጎበዞች፡፡ ዛሬ ስድስተኛው ሳምንት ላይ ደርሰናል፡፡ ይህ ሳምንት ገብርኄር ይባላል፡፡ ገብርኄር ማለት ልጆች መልካም አገልጋይ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሳምንት በቤተ ክርስቲያናችን ክርስቶስ ስለመልካም አገልጋይ ያስተማረው ትምህርት ይነገራል፡፡ ይህን የተመለከተ ምስጋናም ይቀርባል፡፡
አንድ ባለጸጋ አገልጋዮቹን ያስጠራቸውና ለአንኛው 5 መክሊት ለሁለተኛው 2 መክሊት ለሦስተኛው ደግሞ 1 መክሊት ወርቅ ይሰጣቸዋል፡፡ ከዚያም እኔ እስክመጣ በዚህ ወርቅ በመነገድ ተጠቀሙ ብሏቸው ወደሩቅ ሀገር ይሔዳል፡፡ ልጆች መክሊት የወርቅ መለኪያ /መስፈሪያ/ ነው፡፡
ሆሣዕና (የዐቢይ ጾም 8ኛ ሳምንት)
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ) ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ፡፡ ትርጉም: “በፋሲካ በዓል ሰሞን የእውነት አምላክ ደቀ መዛሙርት ወደ ደብረ ዘይት ቀረቡ፤ […]
የትንሣኤ 2 መዝሙርና ምንባባት
የትንሣኤ 2 መዝሙር (ከመጽሐፈ ዚቅ) ትትፌሣሕ ሰማይ ወትታኃሠይ ምድር ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ ወይጸውዑ አድባር ወአውግር ወኩሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዐባይ ፍሥሐ በሰማያት ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐፂባ በደመ ክርስቶስ፡፡ ትርጉም: ሰማይ ይደሰታል ምድርም ትደሰታለች የምድር መሠረቶችም ቀንደ መለከትን ይንፉ /ይደሰቱ/ ተራሮችና ኮረብቶችም /ነገሥታት መኳንንት/ ይጩኹ/ይደሰቱ/ የምድረ በዳ እንጨቶችም ይጩኹ ዛሬ በሰማያት ታላቅ ደስታ ሆነ ምድርም […]
ሰበር ዜና ከአሰቦት ገዳም
መጋቢት 12/2004 ዓ.ም.
የአብነት ተማሪው በታጣቂዎች ተገደለ
በምዕራብ ሐረርጌ ሜኤሶ ወረዳ በአሰቦት ሥላሴና አባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ገዳም የአብነት ተማሪ የሆነው የ7 ዓመቱ ሕፃን ናታን አንበስ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በ3 ጥይት ተመትቶ መገደሉን የገዳሙ ዋና መጋቢና ምክትል አበምኔት አባ ዘወልደ ማርያም ገለጹ፡፡ ከአባ ሳሙኤል ገዳም በተወሰኑ ሜትሮች ርቀት ላይ ከእናቱ ጋር ወደ ገዳሙ በመውጣት ላይ እያለ ከእናቱ እጅ ቀምተው በመውሰድ ፊት ለፊቷ በሦስት ጥይት ገድለውት ሊያመልጡ ችለዋል፡፡ በእናትየው ጩኸትና በጥይት ድምጽ የተደናገጡት መነኮሳት ገዳዮቹን ለመያዝ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
የዝቋላ ገዳም እንዴት አደረ?
መጋቢት 12/2004 ዓ.ም. በእንዳለ ደምስስ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ገዳም ደን ላይ ከቅዳሜ ጀምሮ የተቀሰቀሰው ቃጠሎ እስከ ማክሰኞ ምሽት ድረስ የዘለቀ ሲሆን ሌሊቱን ግን በሰላም እንዳደረና የመርገብ ሁኔታ እየታየበት መሆኑን በስፍራው የሚገኙ ምእመናን ገለጹ፡፡ ቃጠሎው ቢበርድም የተዳፈነው ፍም ነፋሱ እያራገበው በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ጭስ እየታየ እንደሆነ በተለይም የቅዱሳን ከተማ የተሰኘው የአባቶች የጸሎት […]
የመነኮሳቱ የድረሱልን ጥሪ ከዝቋላ ገዳም
መጋቢት 11/2004 ዓ.ም. በእንዳለ ደምስስ ቃጠሎውን መቆጣጠር አልተቻለም ከገዳሙ ጸሐፊ የደረሰን መረጃ፡- ቃጠሎው ከአቅም በላይ ሆኗል፡፡ መነኮሳቱና ምእመናን በመዳከም ላይ ናቸው፡፡ ከእግዚአብሔር በረከትን የምትሹ ምእመናን ድረሱልን፡፡ እሳቱ በአንድ አቅጣጫ ጠፋ ሲባል በሌላ በኩል እየተነሣ ተሰቃይተናል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ በመገሥገሥ ላይ ስለሆነ የቅዱስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች፣ ማኅበራት፣ ከዩኒቨርሲቲዎችና የኮሌጅ ተማሪዎች፣ እንዲሁም ምእመናንና ወጣቶች፣ አቅም ያለው ሁሉ […]
የዝቋላ ደን ቃጠሎ ተጨማሪ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ተገለጠ፡፡
መጋቢት 11/2004 ዓ.ም
በተ/ሥላሴ ጸጋ ኪሮስ
የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ደን ቃጠሎ ተጨማሪ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ተገለጠ፡፡
በቦታው የተገኙት የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እንደገለጡልን በቦታው በርካታ ምእመናን ተገኝተው እሳቱን ለማጥፋት ጥረት ቢያደርጉም በአስቸጋሪው የአየር ጠባይ የተነሣ ፍህሙ እየተነሳ እንደገና እንዲያገረሽ ስለሚያደርገው ከፍ ያለ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
A Burning Heaven in This World – Mt. Zeqwala Monastery
በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የደን ቃጠሎ በባሰ ሁኔታ ላይ ይገኛል!
መጋቢት 10/2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
እሳት ወይስ መአት?
በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የደን ቃጠሎ በባሰ ሁኔታ ይገኛል፡፡ ቅዳሜ መጋቢት 8/2004 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 በኋላ ልዩ ስሙ አዱላላ ከሚባለው አቅጣጫ የተቀሰቀሰው ቃጠሎ በመነኮሳትና በአካባቢው ምእመናን ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙና ከደብረ ዘይት የአየር ኀይል አባላት ትላንት ምሽት መጥተው እገዛ ለማድረግ ጥረት ማድረጋቸውን የገዳሙ ጸሐፊ አባ ወ/ሩፋኤል ቢገልጹም መፍትሔ እንዳልተገኘ ታውቋል፡፡
የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ደን እየተቃጠለ ነው፤ የምእመናንን እገዛ ይሻል፡፡
መጋቢት 10/2004 ዓ.ም. በተ/ሥላሴ ጸጋ ኪሮስ ቅዳሜ መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 በኋላ የጀመረው የገዳሙ ቃጠሎ እየተባባሰ እንደሆነ የገለጹልን ያነጋገርናቸው የገዳሙ መነኮሳት እሳቱን ለማጥፋት የምእመናንን እርዳታ እንደሚሻ አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም ለእርዳታ የሚመጡ ምእመናን ስንቅ እንዲይዙና በውኃ ጥም እንዳይቸገሩ ከቻሉ ውኃ እንዲይዙ፤ ቦቴ መኪና ያላቸውም እንዲተባበሩ ጠይቀዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ምእመናን ከደብረ ዘይትና አዲስ […]