• እንኳን በደኅና መጡ !

ዜናዎች፣ ወቅታዊ ክንውኖች እና ልዩ ልዩ ይዘቶች

ሱባኤ፣ምንነቱ፣ሥርዓቱ

ሥርዓተ ሱባዔ

ሱባዔ ምንድን ነው? ሱባዔ በሰዋስው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ሱባዔ በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪዬ እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፈጣሬ  ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ማረፉ፣ ለጸሎት የሚተጉ ምእመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል፡፡ ዘፍ.2፥2፤ መዝ.118፥64፡፡ ከዚህ አንጻር አንድ ሰው ለሰባት ቀናት ቢጾም «አንድ ሱባዔ ጾመ» ይባላል፡፡ ለዐሥራ አራት ቀን ቢጾም «ሁለት ሱባዔ ጾመ» እያለ እየጨመረ ይሄዳል፡፡

dsc01699

የማኅበራዊ አገልግሎትና ልማት ክፍሉ ለአረጋውያን እርዳታ አደረገ፡፡

ሐምሌ 24 ቀን 2004 ዓ.ም.

በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ


በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል የማኅበራዊ አገልግሎትና ልማት ክፍል ባሳለፍነው ሳምንት ረጅም ዘመናትን በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ላሳለፉ አረጋውያን ጊዜያዊ የአልባሳትና የሕክምና እርዳታ አደረገ፡፡

የአገልግሎት ክፍሉ አብዛኛውን የእድሜ ዘመናቸውን በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ አድርገው ለኖሩ ሰባት አባቶች የአልባሳት እገዛ dsc01699ያደረገው በ2004 ዓ.ም. መሪ እቅዱ መሠረት መሆኑን የጠቀሱት የክፍሉ ሓላፊ ወይዘሪት መቅደስ ዓለሙ፤ “ይህንን ለማቀድ ምክንያት የሆነን አባቶቻችን ከሰፊ የአገልግሎት ዘመናቸው በኋላ የሚታሰብላቸው የጡረታ አበል አለመኖሩ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ አባቶችም በቅርብ የሚረዳቸውና የሚንከባከባቸው ሰው የሌላቸው ናቸው፡፡ ስለሆነም ምንም ዓይነት አገልግሎት እንዳልሰጡ በቂ ትኩረት ተነፍጓቸውና ተረስተው በየመቃብር ቤቱና ንጽሕና በተጓደለባቸው ሥፍራዎች ወድቀው የሚገኙትን አባቶች፤ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ባካሄድነው ጥናትና ባገኘነው መረጃ መሠረት መርጠን ረድተናል፡፡” በማለት ምክንያቱን አስረድተዋል፡፡

በዝቋላ ገዳም የወተት ላም እርባታ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡

ሐምሌ 24 ቀን 2004 ዓ.ም. በእንዳለ ደምስስ ለዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የወተት ላም እርባታ ፕሮጀክት ለመተግበር ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ፡፡   በገዳሙ በቅርቡ ከፍተኛ የደን ቃጠሎ ተከስቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ገዳሙን ለመርዳት በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የሚገኙ ምእመናን የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን ምእመናንን በማስተባበር […]

ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን የወሰነው ውሳኔ ለማኅበሩ መድረሱ ተገለጸ

ሐምሌ 23ቀን 2004 ዓ.ም

በእንዳለ ደምስስ


የ2004 ዓ.ም. የግንቦቱ ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን የወሰነው ውሳኔ   በደብዳቤ የተገለጸ መሆኑን የማኅበሩ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት፤ የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የኢሉባቦርና ጋምቤላ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጻፉት ደብዳቤ ማኅበሩ ለብፁዕነታቸው ተጠሪ እንዲሆን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መወሰኑን ጠቅሰው ከማኅበሩ እድገት ጋር አብሮ ሊሄድ እንዲችል የማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ አስጠንተው ለጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡

 

1

“ዝክረ ቅዱስ ቂርቆስ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው መንፈሳዊ መርሐ ግብር ተጠናቀቀ፡፡


ሐምሌ 17 ቀን 2004 ዓ.ም.

በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ

1በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ያዘጋጀው መርሐ ግብር ከሐምሌ 12 እስከ ሐምሌ 15 ቀን ተካሄደ፡፡ ዝግጅቱ በሁለት ዐበይት ክፍሎች ተከፍሎ የተካሄደ ሲሆን፡- ይህም ከመክፈቻው ሐምሌ 12-14 በዐውደ ርዕይ፣ እንዲሁም ሐምሌ 15 ቀን 12 ሰንበት ትምህርት ቤቶች የተሳተፉበት መንፈሳዊ መርሐ ግብር የቀረበበት መሆኑ ታውቋል፡፡

 

ክረምት

ሐምሌ 14 ቀን 2004 ዓ.ም.

በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ


“ክረምተ ወሐጋየ ዘአንተ ፈጠርከ” መዝ.73÷17 “በጋንም ክረምትንም አንተ አደረግህ” መዝ.71÷17

እግዚአብሔር የዓለምን ምግብ ሥጋዊውንም መንፈሳዊውንም በአራት ከፍሎታል ሥጋዊውን በአራቱ ክፍላተ ዘመን መንፈሳዊውን በአራቱ ወንጌላዊያን ትምህርት፡፡ የሰው ሥጋዊ ምግብና ከአራቱ ክፍላተ ዘመን እንዳይወጣ መንፈሳዊ ምግብናውም ከአራቱ ወንጌላውያን አይወጣም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላካችን የሥጋም የነፍስም ፈጣሪ፣ መጋቢ ነውና፡፡ አሁን ያለንበት ከአራቱ ክፍላተ ዘመን አንዱ የሆነው ክረምት ነው፡፡ከዚህም የምናገኘው ሥጋዊ ምግብ ብቻ ሳይሆን ከሥጋዊ ምግብ ያለፈ መንፈሳዊ ምግብም አለ፡፡

 

ክረምት ምንድነው?

ክረምት ማለት ከርመ ከረመ ካለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን መክረም የዓመት መፈጸም፣  ማለቅ መጠናቀቅ ማለት ነው፡፡ በዚህ ወቅት በፀሐይ አማካኝነት የደረቁ ኮረብቶች ተራሮች በዝናም አማካኝነት ውኃ የሚያገኙበት በዚህም ምክንያት በልምላሜ የሚሸፈኑበት፣ የደረቁ ወንዞች ጉድጓዶች ውኃ የሚሞሉበት፣ በፀሐይ የተቃጠለች ምድር ከሰማይ በሚወርድ ጠለል በረከት የምትረካበት፣ በውኃ ጥም የተሰነጣጠቁ የምድር ጉረሮዎች ውኃን የሚጠግቡበት፣ ሰማይ  በደመና የተራሮች ራስ በጉም  የሚጎናጸፉበት በሙቀት ፋንታ ቅዝቃዜ በድርቅ ፈንታም ልምላሜ የሚነግስበት ተሰባብሮ የወደቀ ሐረግ ቀና ብሎ ከየቦታው የሚሳብበት ወቅት  ነው፡፡

 

ec_members

አውሮፓ ማእከል ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

ሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም.

በዲ/ን ዶ/ር መርሻ አለኸኝ


  • የማኅበረ ቅዱሳን 20ኛ ዓመት እና የአውሮፓ ማእከል 12ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል በስውድን ተከበረ።

በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ጠቅላላ ጉባኤውን ከሰኔ 29 እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2004 ዓ.ም. በሀገረ ስዊድን ስቶክሆልም ከተማ አካሄደ። ከመላው አውሮፓ የተሰባሰቡ ec_membersየማኅበሩ አባላት፣ በስዊድን የተለያዩ ከተሞች የሚያገለግሉ ካህናትና ምእመናን በተሳተፉበት በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ የማእከሉ የ2004 ዓ.ም. የአገልግሎት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በውይይቱም ማእከሉ በአገልግሎት ዘመኑ አጠናክሮ የሰጣቸውን አገልግሎቶች በቀጣዩ ዓመትም አጠናክሮ እንዲቀጥልባቸው ሊፈጽማቸው ያቀዳቸው ነገር ግን በልዩ ልዩ ምክንያት መፈጸም ያልቻላቸውን ወይም ከታቀደው በታች ያከናወናቸውን አገልግሎቶች በሚቀጥለው ዓመት እንዲፈጽማቸው ውሳኔ አሳልፏል።

 

hitsanat

ልዩ የሕፃናት መርሐ ግብር ተዘጋጀ

ሐምሌ 10 ቀን 2004 ዓ.ም. በፍጹም ዓለማየሁ በ12 የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የጋራ ጥምረት እና በአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት አዘጋጅነት ለሕፃናት የሚሆን መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል፡፡ መርሐ ግብሩ ከሐምሌ 12-15/2004 ዓ.ም. ለአራት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በሦስቱ የመጀመሪያ ቀናት “ዝክረ ቅዱሳን ሕፃናት በልሣነ ሕፃናት” በሚል መሪ ቃል በአስተናጋጅ ሰንበት ትምህርት […]

“ከሁሉ በላይ በምትሆን፤ ሐዋርያት በሰበሰቧት፤ በአንዲት፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እናምናለን”

ሐምሌ 10 ቀን 2004 ዓ.ም.


ይህ አንቀጸ ሃይማኖት የጉባኤ ቁስጥንጥንያ አንቀጸ ሃይማኖት ነው፡፡ የእውነተኛዋ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መታወቂያ ትእምርትም ነው፡፡ ይህን አጉድሎ መገኘት የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዐት ማፍረስ ብቻ ሳይሆን እምነትንም እንደማጉደል ይቆጠራል፡፡ እንዲህ ዐይነት ማንነታዊ ተክለ ቁመናን ገንዘብ ያደረገ ግለሰብም ሆነ ማኅበር ራሱን የክርሰቶስ አካልና አባል አድርጎ አለመቀበሉን ያሳየናል፡፡ በክርስቶስ ብቻ አምኖ በግለኝነት መኖር በቂ አይደለም፡፡ የክርስቶስ አካል በሆነችው ሐዋርያት በሰበሰቧት፣ በአንዲት፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም አምኖ አባል መሆን ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው፡፡

 

ይሁንና ይህን አንቀጸ ሃይማኖት ያለ ዐውዱና ከተሸከመው መልእክት ውጪ በመለጠጥና አዲስ የትርጓሜ ቅርጽ በመስጠት በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ቅላጼና ወዝ “ማኅበራት አያስፈልጉም” የሚል እና ራሱን “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” ብሎ የሚጠራ የቤተ ክርስቲያናችን ሕመም የሆነ ቡድን ያለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ዕውቅናና ይሁንታ ከሰሞኑ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መሽጎና የተለያዩ ስብሰባዎችን እያካሄደ እንደሚገኝ ማረጋገጥ ችለናል፡፡

 

ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ

  ዲያቆን ታደሰ ወርቁ   እነዚህ ሁለት ቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስት ቤተክርስቲያናችን አዕማድ ናቸው፡፡ በመሠረትነት በአጸኗት ቤተክርስቲያን ያላቸው የክብር ሥፍራ ላቅ ያለ ነው፡፡ ይህ የሆነው እንዲሁ አይደለም፡፡ ለቤተክርስቲያንና በቤተክርስቲያን የፈጸሙት አገልግሎት በዚህም የተቀበሉት ሰማዕትነት ነው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትም ይህን መልካም የሆነውን ታሪካቸውን ለእኛ አርአያነት በሚሆን መልኩ ከትበውልናል፡፡ እኛም ለአርአርያነት በሚሆን መልኩ የእነዚህን ደጋግ ሁለት ቅዱሳን አባቶች ታሪክ፣ […]

በፌስቡክ የትስስር ገጽ ያግኙን

ስለ ማኅበረ ቅዱሳን መሰረታዊ መረጃዎች

ስያሜ

ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ያከበራቸው የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፣ ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከርበት በመሆኑ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› የሚል ስያሜውን አግኝቷል፡፡

የማኅበሩ ርእይ

ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ የመሪነት ሚናዋን ስትወጣ ማየት

ተልእኮ

ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካት እና ለሕልውናዋ የሚተጋ፣ የተደራጀ ፣ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ፤ ርቱዕ ዘመናዊ፤ ሁለገብ መሪ ትውልድ ማፍራት እና ማሰማራት

እሴቶች

  • መንፈሳዊነት

    ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
  • አገልጋይነት

    የማኅበሩ አባላት አገልግሎትን የክርስቲያናዊ ሕይወታቸው መገለጫ አድርገው በመቀበል በበጎ ፈቃድ ሰማያዊውን ክብርና ጸጋ በመሻት፣ ምድራዊ ክብርና ውዳሴ ከንቱን ሳይፈልጉ፣ በትሕትና እና በክርስቲያናዊ ፍቅር በታማኝነት ያገለግላሉ::
  • የሐሳብ መሪነት

    ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ አገልግሎት የሚያስፈልጉ፣ ኦርቶዶክሳዊ እሳቤን የተከተሉና ዘመኑን የዋጁ የመሪነት ሐሳቦችን በማፍለቅ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር በመመካከር ይሠራል::
  • ተባባሪነት

    ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሁሉም የቤተ ክርስትያን አካላት የወል ተግባር ነው ብሎ ያምናል:: በመሆኑም እንደየጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ባለ ድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በመግባባት፣ በመመካከር እና በቅንነት ለተልእኮ አንድነት ብዝኃ ጸጋን በማክበር አብሮ ይሠራል::
  • ሙያ አክባሪነት

    የማኅበሩ አባላት ባላቸው ልዩ ልዩ ሙያ /ዕውቀት/ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የተሰባሰቡ በመሆናቸው፣ በማኅበሩ አሠራሮች ሁሉ ከኦርቶዶክሳዊው ትምህርተ ሃይማኖት ጋር በማይጋጩ በእውነተኛ መረጃ ለሚደገፉ ሙያዊ ምክረ ሐሳቦች ተገቢውን ክብርና ቅድሚያ ይሰጣል:: በቤተ ክርስቲያንም ለመንፈሳዊ እና ለዘመናዊው (አስኳላ) ሙያ ተገቢው ክብር እንዲሰጥ ይሠራል::
  • ምክንያታዊ ሞጋችነት

    ማኅበሩ በእውነተኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ ቤተ ክርስቲያንን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚፈትኑ አስተሳሰቦችን፣ አሠራሮችን፣ ልማዶችን እና ትርክቶችን በግልጽና በመንፈሳዊ ጥብዓት እና በእውነት እንዲሞገቱና መፍትሔ ላይ እንዲደረስ ይሠራል::
  • ተጠያቂነት

    የማኅበሩ አገልግሎት ግብ ሰማያዊ ዋጋ ማግኘት ስለሆነ ኀላፊነትን በአግባቡ አለመወጣት በእግዚአብሔር እና በሰዎች ዘንድ የሚያስጠይቅ በመሆኑ በየትኛውም እርከን ላይ ያለ አባል እና አመራር በማኅበሩ አሠራር መሠረት በተሰጠው ኀላፊነት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

ዓላማዎች

  • የቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ አስተዳደር፣ የአሠራር ሥርዐትና አስተሳሰብ፣ በቴክኖሎጂ እና በልዩ ልዩ መንገዶች በመደገፍ ዘመኑን ለዋጀ ጠንካራ አገልግሎት ማብቃት፤
  • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ሙሉ ሰብእናን የሚገነባ ሥርዐተ ትምህርት በማስተማር ዘመኑን የዋጁ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር የሚያገለግሉ እንዲሁም በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ በፖለቲካዊ እና በሀገር አስተዳደር ጉዳዮች መሪ/ንቁ ተሳታፊ አገልጋዮችን ማፍራት እና ማሠማራት፤
  • የተተኪውን ትውልድ ምንጭ ለማጎልበት የሰ/ት/ቤቶችን አቅም በማጠናከር የሕጻናት እና የወጣቶችን የተተኪነት ሚና ማሳደግ፤
  • ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነትን በተግባር የሚገልጽ ቤተሰብ እና አንድነቱን የጠበቀ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ በመገንባት የተደራጀ እና የተናበበ አገልግሎት መስጠት፤
  • በተደራጀ እና ተደራሹን ማእከል ባደረገ መንገድ ስብከተ ወንጌልንና ሐዋርያዊ ተልእኮን ዘርፈ ብዙ በሆኑ መንገዶች በመላው ዓለም ማስፋፋት፤
  • በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚነዙትን የርእዮተ ዓለም፣ የሐሰት ትርክቶች እና የአጽራረ ቤተ ክርስቲያንን እንቅስቃሴ ጥናት እና ምርምር ላይ ተመርኩዞ መሞገት እና የተሳሳቱትን በማረም፣ በጠንካራ የዕቅበተ እምነት አገልግሎት የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና ማስጠበቅ፤
  • በተመረጡ ገዳማት እና አብነት ትምህርት ቤቶች የልኅቀት ማእከል እና የተለየ ክርስቲያናዊ ተልእኮ የሚፈጽሙ እንዲሆኑ የሚያስችል ሁለገብ የአእምሮ ልማት ድጋፍ ማድረግ፤
  • ማኅበሩ ዘመኑን የዋጀ ተቋማዊ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ተልእኮውን ማሳካት የሚችልበት አቅም መፍጥር ( በአመራር፣ በሰው ኃይል፣ በመንፈሳዊነት፣ በግንኙነት፣ በዕውቀት፣በልማት፣ በፋይናንስ፣ በቴክኖሎጂ)፤
  • ዓለም አቀፍ ግንኙነትና የትብብር አገልግሎትን መርሕ ያደረገ የኦርቶዶክሳውያን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ማሳደግ፣

አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የሸዋ ሊቀ ጳጳስ ፲፱፻፴፪-፲፱፻፹፪ዓ.ም.

የማኅበሩ ህንጻ