መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ሊቀ ጉባኤ ኀይለ ማርያም ዐረፉ
ጥቅምት 20 ቀን 2005 ዓ.ም.
በቀሲስ ለማ በሱፍቃድ
ሊቀ ጉባዔ ኀይለ ማርያም ንጋቱ ከአባታቸው ከአቶ ንጋቱ ወልደ ሐዋርያትና ከእናታቸው ከወ/ሮ ደመዎዝ ወንድም አየሁ ጥር 12 ቀን 1969 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ በሞረትና ጅሩ ወረዳ ልዩ ስሟ ሽነት ቁስቋም በምትባል መንደር ተወለዱ፡፡ ገና በሕፃን ዕድሜያቸው ወደ ታላቁ ገዳም ወደ ደብረ ጽጌ ማርያም በመሄድ ለአጎታቸው ለአባ ፀጋ ወልደ ሐዋርያ በአደራነት ተስጥተው የቅድስት ቤተ ክርስቲያናቸውን ትምህርት ሀ ብለው ንባብ ከአባ ሀብተ ማርያም በሚገባ ካጠናቀቁ በኋላ እዛው ገዳሙ ውስጥ ከሚገኙት ከመምህር አፈወርቅ የቃል ትምህርትና ጾም ምዕራፍ በሚገባ ተማሩ እንዲሁም ከታላቁ ሊቅ ከየኔታ ጽጌ ጾመ ድጓና ድጓ ተምርው በመምህርነት ተመርቀዋል፡፡ ቀጥሎም አቋቋምና ዝማሬ መዋሲእት ከየኔታ መስፍን አበበ በሚገባ ተምርው ተመርቀዋል፡፡ ይህን ሁሉ ትምህርት ተምሬያለሁ በቃኝ ሳይሉ ተጨማሪ ቃለ እግዚአብሔር ፍለጋ በ1984 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም የካህናት ማሠልጠኛ በመግባት የእውቀት አድማሳቸውን በማስፋት የተክሌ አቋቋምን በመማር በመምህርነት ተመርቀዋል፡፡
ስርጭቱን ለማስቀጠል ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑ ተገለጠ፡፡
ጥቅምት 19 ቀን 2005 ዓ.ም. በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን አማካኝነት ከጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ይሠራጫል በሚል በምእመናን ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የማኅበሩ የቴሌቭዥን መርሐ ግብር የኢ.ቢ.ኤስ ጣቢያ ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ ሙሉ ሥርጭቱ በመቋረጡ የተነሣ በታሰበው ጊዜ ለመጀመር አልተቻለም፡፡ ሆኖም የኢ.ቢ.ኤስ ሓላፊዎች በገለጹት መሠረት ጣቢያው እንደገና ሥርጨቱን ለማስጀመር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ሲሆን […]
፬ቱ ሆሄያት
ጥቅምት 19 ቀን 2005 ዓ.ም/
በዲ/ን ኅሩይ ባየ
የመስቀል ደመራ በናፍቆት የምንጠብቀው በዓል ነው፡፡ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ በበዓሉ ይታደማል፤ በመዝሙር አምላኩን ያመሰግናል፡፡ ዛሬም እንደጥንቱ በያዝነው ዓመት በደመቀ መልኩ ተከብሯል፡፡ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችም የተለያዩ መንፈሳዊ ተውኔቶችን በማቅረብ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ የአራት ቀናት ውሎና ውሳኔዎች
ጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስና
በዲ/ን ዩሴፍ ይኲኖ አምላክ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለአስተዳደር እንዲመች በአራት አህጉረ ስብከት ተከፈለ፡፡
ጥቅምት 11 ቀን 2005 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተካሔደው ሥርዓተ ጸሎት የተከፈተው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባሳለፍናቸው አራት ቀናት በስድስት ጠቃሚና ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡
ቃለ ዓዋዲ
ጥቅምት 13 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ኅሩይ ባየ
ቃለ ዓዋዲ ቀጥተኛ ትርጉሙ “የአዋጅ ነጋሪ ቃል” ማለት ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ የአዋጅ ነጋሪ ቃል ብሎ የተነበየለት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን ነበር፡፡ /ኢሳ.40፥1፵፥፩/ ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዊ ልደት ስድስት ወራትን ቀድሞ የተወለደው ቅዱስ ዮሐንስ ጥርጊያውን እያስተካከለ ሰዎችን ለንስሐ እየጠራ ለአማናዊው በግዕ ለኢየሱስ ክርስቶስ አዘጋጅቷቸዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን መተዳደሪያ ደንብም /ቃለ ዓዋዲ/ ሦስቱ ጾታ ምእመናንን/ ካህናት፣ ወንዶች እና ሴቶች/ በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን እየተመሩ ሕይወታቸውን እንዲጠብቁ ስለሚያውጅ ቃለ ዓዋዲ ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ቃለ ዓዋዲ የተባለው መጽሐፍ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ ያለውን አስተዳደራዊ መዋቅር ያካተተ የሕግ መጽሐፍ ነው፡፡ በዚህም ብቻ ሳይወሰን ከምእመናን ጀምሮ እስከ ካህናት ድረስ ያሉትን የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች መብትና ግዴታ በውሉ የሚያስገነዝብ መመሪያም ነው፡፡
ማእከሉ ጠቅላላ ጉባኤውን ሊያካሂድ ነው
ጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም. በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል ጠቅላላ ጉባኤውን የፊታችን ቅዳሜና እሑድ እንደሚያካሂድ የማእከሉ ዋና ጸሐፊ አቶ ካሳሁን ኀይሌ አስታወቁ፡፡ ቅዳሜ ጥቅምት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ከሰዓት በፊት በሚኖረው የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ፣ የሀገረ […]
700 ምእመናን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያናቸው ተመለሱ
ጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
በቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ለማ በየነ አማካኝነት፥ ለ31ኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አጠቃላይ መንፈሳዊ የሰበካ ጉባኤ የቀረበው ሪፖርት፤ ለ28 ዓመታት ያህል በሰዩ ወረዳ ሹሻ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንና በአጥቢያው የሚገኙ ምእመናን ከእናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናቸው በመለየት የቆዩትን ሁለት ቀንደኛ የተሐድሶ መናፍቃን መሪዎች ተውግዘው መለየታቸውን አመለከተ፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ቢያደርገው የምንላቸው ነጥቦች
ጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም.
ቅዱስ ሲኖዶስ ኤጲስ ቆጶሳት የያዘውን፣ የታወቀ ሕጋዊ መንበር፣ ታሪካዊና ሕጋዊ መሠረት እንዲኖረው ሆኖ የተደራጀውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምልዐተ ጉባኤ ነው፡፡ ይህ ምልዐተ ጉባኤ ለአንዲቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና ልዕልና እጅግ አስፈላጊና አንድ ነው፡፡
አስፈላጊነቱም የሚመነጨውና የሚረጋገጠው በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ፣ የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ በመሆኑና ውሳኔዎች ሁሉ ይግባኝ የሌለባቸው ከመሆኑ ላይ ነው፡፡ ሐዋርያት ከክርስቶስ፤ ሐዋርያነ አበውና ሊቃውንት ከሐዋርያት፣ እኛም ከእነዚህ ሁሉ የወረስናቸውን መሠረተ እምነት፣ ሥርዐተ አምልኮና ትውፊት የሚጠብቅና የሚያስጠብቅ ዐቃቤ ሃይማኖት ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያንን ማገልግል አክራሪነት አይደለም !
መጽሔተ ተልዕኮን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ማኅበረ ቅዱሳን በምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም ያስገነባቸው ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡
ጥቅምት 8 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ማኅበረ ቅዱሳን በጉራጌ ሀገረ ስብከት በምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም ሲያከናውናቸው የነበሩት የመጠጥ ውኃና የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም. በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የከምባታ፣ ሀድያ፣ ጉራጌና ስልጢ አህጉረ ስብከትና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ተመረቁ፡፡