መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
“ለቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ መሳካት የገዳማት ድርሻ” በሚል ዐውደ ጥናት ይካሄዳል
ታኅሣሥ 4 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ለማሳካት የገዳማት ድርሻ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ አውደ ጥናት ታህሣሥ 6 ቀን 2005 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሠዓት ጀምሮ 6 ኪሎ በሚገኘው በኢትዮጵያ ስብሰባ ማእከል ከሃምሳ በላይ የሚደርሱ ከታላላቅ ገዳማት የተውጣጡ አበምኔቶች በተገኙበት እንደሚካሄድ በማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ዳይሬክተር ዲያቆን አእምሮ ይሔይስ ገለጹ፡፡
ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ምርጫ ምን ይላሉ?
ታኅሣሥ 4 ቀን 2005 ዓ.ም.
ፕሮፌሰር ባዬ ይማም
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በሞት ሲለዩ ማን ይተካቸዋል? የሚተኩት አባት እንዴት ይመረጣሉ? የሚል ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም፡፡ ከተነሣ ደግሞ የምርጫ መስፈርት ይኖራል ብዬ አስባለሁ፡፡ ከአሁን በፊት ቤተ ክርስቲያኗ ፓትርያርክ መርጣ የምትሾምበት ሥርዐት ካላት፤ ያ ሥርዐት አሁንም በተግባር መዋል አለበት፡፡ ምናልባት አዲስ የመምረጫ መስፈርት ማውጣት የሚያስፈልግ ከሆነ፣ ሲኖዶሱ ተጨማሪ መስፈርት ሊያወጣ፣ ያሉትን መስፈርቶች ሊያሻሽል የሚችልበት ሥልጣን አለው፡፡ በዚህም መሠረት ምርጫው ይከናወናል፡፡
ዕጣ በቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ሥርዓት
ታኅሣሥ 1 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ምትኩ አበራ
ዕጣ /እጻ/ የሚለው ቃል ዐፀወ ዕጣ ተጣጣለ /አወጣ/ ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በግእዝ አማርኛ መዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው “አጭርና ቀጭን እንጨት፤ ከመካከለኛ ጣት የሚበልጥ፤” ብለው ይፈቱታል፡፡ ዕጣ እድል ድርሻም ሊባል ይችላል፡፡ የዕጣ አሠራር ከክርስቶስ ልደት በፊት ከኦሪቱ ጊዜ ጀምሮ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ በጥንት ጊዜ ሰዎች ዕጣን በእንጨት፣ ጽሑፍ ባለበት ድንጋይ /ጠጠር/ ይጥሉ ነበር፡፡
የዕጣ ሥርዓትን ለሰዎች ያስተዋወቀው ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ “እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፡- ለእነዚህ በየስማቸው ቁጥር ምድሪቱ ርስት ሆና ትከፈላለች… ለሁሉ እንደቁጥራቸው መጠን ርስታቸው ይሰጣቸዋል፡፡ ነገር ግን ምድሪቱ በዕጣ ትከፈላለች፤ በብዙዎችና በጥቂቶች መካከል ርስታቸው በዕጣ ትከፈላለች”፡፡ /ዘኁ.26፥52-56/ ይህንን ትእዛዝ እግዚአብሔር ሲያስተላልፍ ሥርዐተ ዕጣውን የሚመሩትንም ጭምር “….ርስት ትሆናችሁ ዘንድ በዕጣ የምትደርሳችሁን ምድር…. የሚከፍሉላችሁ ሰዎች ስማቸው ይህ ነው፤ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ፡፡” በማለት አሳውቋቸዋል፡፡ /ዘኁ.30፥2-16/ በዚህ ዐቢይ ትእዛዝ መሠረት ተሿሚዎቹ በተፈጥሮ ወጣ ገባ፣ ጭንጫና ለም ወዘተ… የሆነችውን ምድር ከሐሜት በጸዳና ከአድልኦ በራቀ መለኮታዊ ሥርዓት ርስቱን አከፋፍለዋል፡፡
በደቡብ ኦሞ ከሰባት መቶ በላይ ሰዎች ተጠመቁ
ታኅሣሥ 1 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራም አስተባበሪነት፤ በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙና በልዩ ልዩ ቤተ እምነቶች ውስጥ የነበሩ ከሰባት መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ሥርዓተ ጥምቀት ተፈጽሞላቸው ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን ተመለሱ፡፡ በሜጸር የቅዱስ ሚካኤል እንዲሁም በቶልታ የቅድስት ሥላሴ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ኅዳር 23 ቀን 2005 ዓ.ም. በተከናወነው ሥርዓተ ጥምቀት ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና ያገኙ ሰዎች በማኅበረ ቅዱሳን የጂንካ ማእከልና በሰንበት ትምህርት ቤት ጥምረት በሁለት ልዩ ልዩ የስብከት ኬላዎች አማካኝነት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲማሩ የቆዩ ናቸው፡፡
የበኬ ደብረ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የልማት ሥራ ተጎበኘ
ታኅሣሥ 1 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማዕከል ሥራ አሥፈጻሚ አባላትን ያቀፈ የልዑካን ቡድን በበኬ ደብረ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እየተከናወነ የሚገኘውን የልማት ሥራ ለመመልከትና ከደብሩ አስተዳደር አካላት ጋር ለመወያየት ኅዳር 23 ቀን 2005 ዓ.ም. ጉብኝት አካሄደ፡፡
የማዕረግ ተመራቂው የወርቅ ሜዳልያውን ለማኅበሩ አበረከተ
29/03/2005ዓ.ም
በእንዳለ ደምስስ
ደብረ ዘይት በሚገኘው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንስሳት ህክምናና ግብርና ኮሌጅ በ2004 ዓ.ም. የተመረቀው ዶክተር መስፍን ማሞ በአጠቃላይ ውጤት (GPA) 3.98 እጅግ በጣም ከፍተኛ ማዕረግ በማምጣት ተመርቋል፡፡ ኮሌጁም ላስመዘገበው ውጤት Outstanding Student Of The Year 2012 College Of Veternary & Agriculture በማለት ኮሌጁ በበላይነት ላጠናቀቁ ተማሪዎች የሚሰጠውን የወርቅ ሜዳልያ ሽልማት አበርክቶለታል፡፡
ዶክተር መስፍን ማሞ ይህንን ሽልማት በመያዝ ወደ ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል በመምጣት “በትምህርቴ ባስመዘገብኩት ውጤት ያገኘሁት ሽልማት ነው፡፡ ለኔ አይገባኝም፡፡” በማለት ለማኅበሩ እንደሚሰጥ አሳወቀ፡፡
የንባብ ባሕልን ለማሳደግ ውይይት ተካሄደ
ኅዳር 26 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የንባብ ባሕልን በማሳደግ በመረጃና በእውቀት የበለጸገ ማኅበረሰብ እንፍጠር በሚል ርዕስ የማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ማእከል ያዘጋጀው የውይይት መድረክ ኅዳር 22 ቀን 2005 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ስዓት ላይ በማኅበሩ ሕንፃ ላይ ተካሄደ፡፡
ቀሲስ ዶ/ር ሰሙ ምትኩ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ በመርሐ ግብሩ ላይ ለተገኙት እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የውይይት መድረኩ የተዘጋጀበትን ዋነኛ ምክንያት ሲገልጹም “በሀገራችን ብሎም በቤተ ክርስቲያናችን በጣም በአሳሳቢ ሁኔታ እየቀነሰ የመጣውን የንባብ ባሕል ለማሳደግ እንዲቻል የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ነው፡፡ የማያነብ ትውልድ አዲስ ነገር መፍጠር አይችልም፤ አዲስ ነገርንም ለመቀበል ያስቸግረዋል፡፡ የንባብ ባሕላችን ምን ላይ እንደሚገኝ፤ ያጋጠሙ ችግሮችና ሊወሰዱ የሚገባቸው መፍትሔዎች ላይ ለመወያትና እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን ትውልዱን በእውቀትና በመረጃ ከማነፅና ከመቅረፅ አንጻር ሊኖራት የሚገባት ሚና ምን መሆን እንዳለበት ለማመላከት ነው፡፡” ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ተልዕኮ ለማሳካት የገዳማት ድርሻ!!
የወርቃማው ዘመን ወርቃማ ደራሲ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የገድል መጽሐፍ ይመረቃል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን ጥንታውያን ገዳማት እና የአብነት ትምህርት ቤቶች ለማጠናከር ላለፉት 10 ዓመታት ዘላቂ የልማት ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ከምዕመናን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህም አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡ ማኅበሩ ይህንን አገልግሎት አጠናክሮ ለመቀጠል ከ50 ጥንታውያን ገዳማት የተውጣጡ አበምኔቶች በተገኙበት “የኢትዮጵያ […]
የአሰቦት ገዳም የመንገድ ችግር በመቀረፍ ላይ ነው
• በሁለት በጎ አድራጊ ወጣቶች የ6 ኪሎ ሜትር የተራራው አስቸጋሪ መንገድ ተሠራ
• የ12 ኪሎ ሜትሩ መንገድ በመሠራት ላይ ነው
የአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድሥት ሥላሴና አቡነ ሳሙኤል ገዳም 6 ኪሎ ሜትር የተራራው መውጫ መንገድ በሁለት በጎ አድራጊ ወጣቶች ሙሉ ወጪውን በመሸፈን የጥርጊያ መንገዱን ሥራ ከመስከረም 7 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በ17 ቀናት ውስጥ በመሥራት ተጠናቀቀ፡፡
የገዳሙ አበምኔት አባ ተክለ ማርያም ተክለ ፃድቅ ስለ መንገድ ሥራው ሲገልጹ “እግዚአብሔር አነሣሥቷቸው ይህ ቅዱስ ገዳም ያለበትን የመንገድ ችግር ተገንዝበው ሙሉ ወጪውን በመሸፈንና መንገዱ ተሠርቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ እዚሁ ከእኛው ጋር በመሆን ሥራውን እየተቆጣጠሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡ የመንገዱ መሠራት ገዳሙን ከእሳት ቃጠሎ፤ በተለይም የደን ጭፍጨፋ ከሚያካሂዱ አካላትና ከተለያዩ አደጋዎች ይታደገዋል፡፡ ምእመናንም ከዚህ ቅዱስ ሥፍራ በመገኘት በረከት እንዲቀበሉ ያስችላቸዋል፡፡ ለኛ ለገዳማውያንም መውጣት መውረዱን ያቀልልናል፡፡ ሁለቱ ወጣቶች ያከናወኑት በጎ ተግባር ሌሎችም አርአያነታቸውን ሊከተሉ ይገባል ” ብለዋል፡፡
የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበር
ኅዳር 19 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ር ሰሎሞን መኩሪያ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
በቤተ እስራኤል ስም ጠባይን፣ ግብርን፣ ሁኔታን እንደሚገልጥ ሁኖ ይሰየማል፡፡ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “ማርያም” የሚለውን ስያሜ ከማየታችን በፊት ስለ ድንግል ማርያም አባቶቻችን በነገረ ማርያም ያሉትን ጥቂት እንመለከታለን፡፡ “ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ በም.1፥9 ላይ እንደተናገረ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር፡፡” እንዳለ በኦ.ዘፍ.ም.19፥1 ጀምሮ እንደተጻፈ የሰዶምና የገሞራ ሰዎች በበደላቸው ምክንያት እንደተደመሰሱ /እንደጠፉ/ እናነባለን፡፡ አዳምና ልጆቹ በሲዖል ባህር ሰጥመን እንዳንቀር እግዚአብሔር በቸርነቱ ንጽህት የሆነች ዘር መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እያማለደች የምታሰጥ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ባያስቀርልን ከእርሷም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን የሚያርቅ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ የሚያድል የባሕርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዶ በሞቱ ሞታችንን ባይደመስስ ወደ ሕይወት ባይመልሰን ኖሮ መኖሪያችን ሲዖል ነበር፡፡