መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የቅዱስ ያሬድን 1500ኛ የልደት በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀ ዐውደ ጥናት ተከፈተ
ዲ/ን መርሻ አለኸኝ(ዶ/ር)
የቅዱስ ያሬድን 1500ኛ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ በማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የተዘጋጀ ዐውደ ጥናት በግዮን ሆቴል ሳባ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተከፈተ፡፡ በዐውደ ጥናቱ ላይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የልዩ ልዩ መምሪያዎች ሓላፊዎች፣ በዋና ዋና አብነት ት/ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንና የመንግሥትና ልዩ ልዩ ተቋማት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው ሊቃውንት ተገኝተዋል፡፡
ቀሲስ ዶክተር ሰሙ ምትኩ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ማኅበሩ ቅዱሳት መካናት ራሳቸውን ችለው የሚተዳደሩባቸውን ዘላቂ የልማት ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና በመተግበር ለአብነት መምህራንና ተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ ከፍተኛ ሥራ አየሠራ እንደኾነ ከገለጹ በኋላ፤ ሊቁ ለሀገራችን ከሰጠው አበርክቶ አንጻር ማኅበሩ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውን የቅዱስ ያሬድን የ1500ኛ ዓመት የልደት በዓል በሰፊ ዝግጅት ለማክበር እንደወሰነ ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ቤተ ክህነት ደብሩ በ‹‹አጥማቂው›› ላይ የጣለውን እገዳ አጸና
በምሥራቅ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ‹‹ሲያጠምቅ›› በነበረው ግለሰብ ላይ ያሳለፈውን የእግድ ውሳኔ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አጸናው፡፡ ከደብሩ ሰበካ ጉባኤ ያገኘውን የእግድ ደብዳቤ መሠረት በማድረግ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በቁጥር 9474/756/2005 በቀን 08/09/05 ያወጣው ደብዳቤ ‹‹መ/ር ግርማ ወንድሙ ሰባኬ ወንጌልና አጥማቂ ነኝ፤ የማዳን ፈውስ […]
የአዲስ ዘመን ቆይታችን
ግንቦት 9 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ጸበል ጸዲቅ /ክፍል ስድስት/
የማኅበሩ ጋዜጠኞች ቡድን ወደ ሰሜን ጎንደር፤ ደቡብ ጎንደር፤ ምእራብ ጎጃምና አዊ ዞን የሚገኙ ቅዱሳት መካናትንና የሀገረ ስብከቶቹን የሥራ እንቅስቃሴ ለመዘገብ ከሚያዚያ 3 -20 ቀን 2005 ዓ.ም. ያደረገውን ጉዞ አጠናቅቆ ተመልሷል፡፡ በዚህም መሠረት በጉዟችን ያሰባሰብናቸውን መረጃዎች አቀናጅተን በድረ ገጻችን ማቅረባችንን እንቀጥላለን፡፡
ማእከላት ለኦዲትና ኢንስፔክሽን ሥራዎች ትኩረት እንዲሰጡ ተጠየቀ
ሚያዚያ 22 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደጀኔ
የማኅበረ ቅዱሳን ኦዲትና ኢንስፔክሽን አገልግሎት ክፍል ማእከላት ለኦዲትና ኢንስፔክሽን ሥራዎች ትኩረት እንዲሰጡ የክፍሉ ሓላፊ አቶ የሸዋስ ማሞ አስታወቁ፡፡
በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ለሀገር ውስጥ ማእከላት ስለ ኦዲትና ኢንስፔክሽን አገልግሎትና አሠራር ዙሪያ ሚያዝያ 12 እና 13 ቀን 2005 ዓ.ም. በተሰጠበት ወቅት ነበር ማእከላት አገልግሎቱን አጠናክረው መቀጠል የሚገባቸው መሆኑን የተገለጸው፡፡
ሰሙነ ሕማማት በሊቀ ሊቃውን ዕዝራ ሐዲስ
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ አባላት መንፈሳዋ ጉዞ አካሄዱ
ሚያዚያ 21 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዳዊት ደስታ
የማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል “መራሔ ፍኖት” በሚል መሪ ቃል በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተማሩ ላሉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ሱሉልታ ደብረ ምሕረት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሚያዚያ 20 ቀን 2005 ዓ.ም. አካሄደ፡፡
አትማረኝ ዋሻ
ሚያዚያ 18 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
/ጸበል ጸዲቅ ክፍል አምስት/
“አትማረኝ” እያሉ ስለ ጸለዩ አባት የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት በትምህርታቸው እያነሱ በምሳሌነት ከሚጠቅሷቸው ትምህርቶች አንዱ ነው፡፡ ከጣና ሐይቅ ጉዞ ከቃረምኳቸው መረጃዎቼ መካከል ለዛሬ በጸበል ጸዲቅ ጽሑፌ አትማረኝ ዋሻንና ታሪኩን በጥቂቱ ላስተዋውቃችሁ፡፡
አትማረኝ ዋሻ በጣና ሐይቅ ደሴቶች መካከል ከሚገኙ ገዳማት መካከል ከማን እንደ አቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም አንድነት ገዳም በስተ ምእራብ አቅጣጫ የጣና ሐይቅን ጉዞ ከገታው አንደ ተራራ ሥር የሚገኝ ዋሻ ነው፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩ ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጋር ልዩ ቃለ መጠይቅ አደረጉ
ሚያዚያ 17 ቀን 2005 ዓ.ም.
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጋር በዓለ ትንሣኤን ምክንያት በማድረግ ልዩ ቃለ መጠይቅ አደረጉ፡፡ በዚህ አንድ ሰዓት የፈጀ ቃለ መጠይቅ ላይ ቅዱስነታቸው ስለ ልጅነት ጊዜያቸው ፣ በትምህርት ቤት ሳሉ ስለነበሯቸው ገጠመኞች ፣ ስለ ምንኩስና ሕይወት፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስላሉ ልዩ ልዩ አስተዳደራዊና ችግሮች እና በተሠጣቸው ሓላፊነት ምን ሊሠሩ እንዳሰቡ ፣ ስለ ቅድስት ሀገር የርስት ጉዳይ ከግብፅ ቤተ ክርስቲያን ጋር ለመሥራት ስለታሰበው መፍትሔ እና ስለ ዕርቀ ሰላሙ ጉዳይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሠጡ ሲሆን ሙሉ ቃለ መጠይቁ በማኅበሩ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር ከበዓለ ትንሣኤ ጀምሮ እንደሚቀርብ የማኅበሩ ሬድዮና ቴሌቪዥን ክፍል አስተባባሪ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ገልጸዋል፡፡
ሆሣዕና(ለሕፃናት)
ሚያዚያ 17 ቀን 2005 ዓ.ም.
በቤካ ፋንታ
በኢየሩሳሌም ሀገር ውስጥ በምትገኝ በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ ነው የምኖረው፡፡ ከተወለድኩ ዛሬ 5 ዓመት ሞልቶኛል፡፡ ቀኑ ሰንበት ነው እቤት ውስጥ እየተጫወትኩ እናቴም በጓዳ ሥራ እየሠራች ድንገት የብዙ ሰዎች የእልልታ ድምጽ ሰፈሩ ውስጥ ተሰማ፡፡ እናቴም በፍጥነት ከጓዳ ሮጣ ወጥታ “ልጄ ልጄ ነይ እንሂድ ብላ በጀርባዋ ላይ አዝላኝ ሮጣ ከቤት ወጣች፡፡ እኔም በሁኔታው ተገርሜያለሁ፡፡
ቤተ ክርስቲያን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ
ሚያዚያ 15 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ጸበል ጸዲቅ /ክፍል አራት/
ከጎንደር ከተማ በጎርጎራ ወደብ አድርገን ልንቃኛቸው በመረጥናቸው አምስት የጣና ሐይቅ ገዳማትን ለመዘገብ የተነሳነው ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ነው፡፡ የጀልባ ላይ ጉዞ አድርጌ አላውቅም፡፡ ነገር ግን ቅዱሳን አበውን ያፈሩ፤ በጾም በጸሎት፤ በተጋድሎ የጸኑባቸው ገዳማትን በረከት ለማግኘት፤ ታሪካቸውን ለመቃኘት ቸኩያለሁ፡፡ የጋዜጠኞቹ ቡድን በአንድነት ሆነን የ64 ኪሎ ሜትሩን መንገድ ተያያዝነው፡፡