መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ አባላት መንፈሳዋ ጉዞ አካሄዱ
ሚያዚያ 21 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዳዊት ደስታ
የማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል “መራሔ ፍኖት” በሚል መሪ ቃል በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተማሩ ላሉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ሱሉልታ ደብረ ምሕረት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሚያዚያ 20 ቀን 2005 ዓ.ም. አካሄደ፡፡
አትማረኝ ዋሻ
ሚያዚያ 18 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
/ጸበል ጸዲቅ ክፍል አምስት/
“አትማረኝ” እያሉ ስለ ጸለዩ አባት የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት በትምህርታቸው እያነሱ በምሳሌነት ከሚጠቅሷቸው ትምህርቶች አንዱ ነው፡፡ ከጣና ሐይቅ ጉዞ ከቃረምኳቸው መረጃዎቼ መካከል ለዛሬ በጸበል ጸዲቅ ጽሑፌ አትማረኝ ዋሻንና ታሪኩን በጥቂቱ ላስተዋውቃችሁ፡፡
አትማረኝ ዋሻ በጣና ሐይቅ ደሴቶች መካከል ከሚገኙ ገዳማት መካከል ከማን እንደ አቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም አንድነት ገዳም በስተ ምእራብ አቅጣጫ የጣና ሐይቅን ጉዞ ከገታው አንደ ተራራ ሥር የሚገኝ ዋሻ ነው፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩ ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጋር ልዩ ቃለ መጠይቅ አደረጉ
ሚያዚያ 17 ቀን 2005 ዓ.ም.
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጋር በዓለ ትንሣኤን ምክንያት በማድረግ ልዩ ቃለ መጠይቅ አደረጉ፡፡ በዚህ አንድ ሰዓት የፈጀ ቃለ መጠይቅ ላይ ቅዱስነታቸው ስለ ልጅነት ጊዜያቸው ፣ በትምህርት ቤት ሳሉ ስለነበሯቸው ገጠመኞች ፣ ስለ ምንኩስና ሕይወት፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስላሉ ልዩ ልዩ አስተዳደራዊና ችግሮች እና በተሠጣቸው ሓላፊነት ምን ሊሠሩ እንዳሰቡ ፣ ስለ ቅድስት ሀገር የርስት ጉዳይ ከግብፅ ቤተ ክርስቲያን ጋር ለመሥራት ስለታሰበው መፍትሔ እና ስለ ዕርቀ ሰላሙ ጉዳይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሠጡ ሲሆን ሙሉ ቃለ መጠይቁ በማኅበሩ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር ከበዓለ ትንሣኤ ጀምሮ እንደሚቀርብ የማኅበሩ ሬድዮና ቴሌቪዥን ክፍል አስተባባሪ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ገልጸዋል፡፡
ሆሣዕና(ለሕፃናት)
ሚያዚያ 17 ቀን 2005 ዓ.ም.
በቤካ ፋንታ
በኢየሩሳሌም ሀገር ውስጥ በምትገኝ በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ ነው የምኖረው፡፡ ከተወለድኩ ዛሬ 5 ዓመት ሞልቶኛል፡፡ ቀኑ ሰንበት ነው እቤት ውስጥ እየተጫወትኩ እናቴም በጓዳ ሥራ እየሠራች ድንገት የብዙ ሰዎች የእልልታ ድምጽ ሰፈሩ ውስጥ ተሰማ፡፡ እናቴም በፍጥነት ከጓዳ ሮጣ ወጥታ “ልጄ ልጄ ነይ እንሂድ ብላ በጀርባዋ ላይ አዝላኝ ሮጣ ከቤት ወጣች፡፡ እኔም በሁኔታው ተገርሜያለሁ፡፡
ቤተ ክርስቲያን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ
ሚያዚያ 15 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ጸበል ጸዲቅ /ክፍል አራት/
ከጎንደር ከተማ በጎርጎራ ወደብ አድርገን ልንቃኛቸው በመረጥናቸው አምስት የጣና ሐይቅ ገዳማትን ለመዘገብ የተነሳነው ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ነው፡፡ የጀልባ ላይ ጉዞ አድርጌ አላውቅም፡፡ ነገር ግን ቅዱሳን አበውን ያፈሩ፤ በጾም በጸሎት፤ በተጋድሎ የጸኑባቸው ገዳማትን በረከት ለማግኘት፤ ታሪካቸውን ለመቃኘት ቸኩያለሁ፡፡ የጋዜጠኞቹ ቡድን በአንድነት ሆነን የ64 ኪሎ ሜትሩን መንገድ ተያያዝነው፡፡
ሠራተኛ ጉባኤያት በቤተ ክርስቲያን ትልቅ ድርሻ እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ
ሚያዚያ 15 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዳዊት ደስታ
የማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል የሠራተኛ ጉባኤ የአንድነት መርሐ ግብር ሚያዚያ 13 ቀን 2005 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በተካሄደው መርሐ ግብር ሠራተኛ ጉባኤያት በቤተ ክርስቲያን ትልቅ ድርሻ እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ፡፡
ለአብነት ተማሪዎች በጤና አጠባበቅ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጠ
ሚያዚያ 14 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ከጎንደር ማእከል ጋር በመተባበር በጎንደር ውስጥ ከሚገኙ አብነት ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ተማሪዎች በግልና በአካባቢ ንጽህና አጠባበቅ ላይ ያተኮረና አንድ ቀን የወሰደ ስልጠና በደብረ ኀይል ወደብረ ጥበብ በዓት ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ ሚያዚያ 12 ቀን 2005 ዓ.ም. ተሰጠ፡፡
ጎንደር – የቅዱሳት መካናት ማኅደር
ሚያዚያ 14 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ጸበል ጸዲቅ /ክፍል ሦስት/
ጎንደር ገብተናል፡፡ ዞር ዞር እያልኩ ለመቃኘት ጊዜ አልወሰድኩም፡፡ የምችለውን ያህል እግሬ እሰከመራኝ ተጓዝኩ፡፡ ጎንደር ውስጥ አንድ ቤተ ክርስቲያን ለማግኘት አንድ ኪሎ ሜትር መጓዝ አይጠበቅብዎትም፡፡ ቀና ብለው አካባቢውን በዓይንዎ መቃኘት ብቻ ይበቃዎታል፡፡ ከሰሜን ወደ ደቡብ፤ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ቢመለከቱ በእርግጠኝነት የቤተ ክርስቲያን የጉልላት መስቀል እንዳሻዎት ያገኛሉ፡፡ በቃ ወደ ተመለከቱበት አቅጣጫ ማምራት፡፡ 44ቱ ተቦት የሚለው አባባል ቀድሞ በጎንደር 44 ታቦታት ስለነበሩ አይደል?
ኒቆዲሞስ
ሚያዚያ 12 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
እግዚአብሔር “ጾምን ቀድሱ ጉባኤውንም ዐውጁ ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ሰብስቡ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ በጽዮን መለከት ንፉ ጾምንም ቀድሱ” በማለት ዐውጀን መጾም ያለብንን ጾም እንድንፆም በነብዩ ኢዩኤል ነግሮናል፡፡ ኢዩ.1፥14፣ 2፥15
እግዚአብሔር ሙሴን በእሥራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳም ማኅፀንን የሚከፍት በኲርን ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ በማለቱ /ዘጸ.13፥12 ከሰው፣ ከዕለታትት ተለይተው የተቀደሱ ነበሩ፡፡ አጽዋማትም በዐዋጅ ተለይተው ይጾማሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥም፡- የዐብይ ጾም ይገኛል፡፡
የኔታ ይቆዩን የገዳማት ዐውደ ርእይ በፓሪስ ከተማ
ሚያዚያ 11 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ደረጄ ግርማ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የፈረንሳይ ግንኙነት ጣቢያ ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶችን የሚያስተዋውቅ ዐውደ ርእይ ማዘጋጀቱን ገለጠ።
ዐውደ ርእዩም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ታሪክና ለሀገር ያበረከተችውን አስተዋጽኦ፣ በተለይም ጥንታዊ ገዳማት ትናንትና ዛሬ እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቶችን ነባራዊ ሁኔታ የሚዳስስ፤ እየተደረጉ ያሉ ድጋፎችን የሚጠቁም እንዲሁም ከሕዝበ ክርስቲያኑ የሚጠበቀውን ድርሻ የሚያመላክት ዐውደ ርእይ ይቀርባል።