መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ጥናትና ምርምር የጥናት ጉባኤው ሊያካሂድ ነው
የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም.
በታመነ ተ/ዮሐንስ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማእከል “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሚና በፀረ-ቅኝ ግዛት ትግል” በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሑፍ ሊያዘጋጅ ነው፡፡
«ተዋሕዶ ለአንድሮይድ» የተሰኘ የስልክ ላይ አገልግሎት ተጀመረ
የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም.
በዝግጅት ክፍሉ ሪፖርተር
ሐዊረ ሕይወት ወደ አዲስ ዓለም ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሊካሄድ ነው
የካቲት 14 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዲ/ን ቴዎድሮስ ኃይሉ
በዚህ ዓመት ለሁለተኛ ጊዜ የታሰበው ሐዊረ ሕይወት ወደ ርእሰ አድባራት ወገዳማት አዲስ ዓለም ደብረ ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን መጋቢት 21 ቀን 2006 ዓ.ም ሊካሄድ መሆኑን፤ የማኅበረ ቅዱሳን ምክትል ዋና ጸሐፊና የጉዞው ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ተሾመ ገለጹ፡፡
ለአብነት መምህራኑ የህክምና ምርመራ ተደረገ፡፡ ክብካቤና ክትትል ካልተደረገ ለዐይነ ስውርነት ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡
የካቲት 13 ቀን 2006 ዓ.ም.
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
በቅርቡ ለሦስተኛ ጊዜ በማኅበረ ቅዱሳን አዘጋጅነት ሊካሄድ የነበረውን የአብነት መምህራን ሀገር አቀፍ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ከመጡት 202 ሊቃውንት ከ70 በላይ የአብነት መምህራን ካታራክት እና ትራኮማ ችግር እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡ክብካቤና ክትትል ካልተደረገ ለዐይነ ስውርነት ሊዳረጉ እንደሚችሉ የማኅበሩ የሞያ አገልግሎት ዋና ክፍል የሕክምና ቡድን ገለጸ፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩ ዐብይ ጾምን አስመልክቶ ቃለ ምዕዳን አስተላለፉ
የካቲት 13 ቀን 2006 ዓ.ም.
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2006 ዓ.ም. ዐቢይ ጾም አስመልክቶ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ባሉበት ወቅት “ጾም ለመንፈሳዊ ሕይወት መጎልበት፣ ራስን ለመግዛት፣ ከእግዚአብሔር ጋር ልዩ ግንኙነትና አንድነት ለመፍጠር እጅግ አስፈላጊ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ቅዱስነታቸው ዐብይ ጾሙን አስመልክቶ ያስተላለፉትን ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ይመልከቱ፡፡
ዐቢይ ጾም
የካቲት 13 ቀን 2006 ዓ.ም.
ሊቀ ጉባኤ ቀለመ ወርቅ ውብነህ
ጾም ማለት መተው መከልከል ማለት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ሠርታ ጾመን ከአምላካችን ጋር ህብረት እንዲኖረን ፤መንፈሳዊ ኃይል እንድናገኝ አድርጋለች፡፡ ጾም በእግዚአብሐር የተቀደሰ ስለሆነ ወደ ቅድስና ጎዳና የሚመራ ነው፡፡
በጾም ወራት ከመባልዕት መከልከል ብቻ ሳይሆን ዐይን ክፉ ከማየት አንደበት ክፉ ከመናገር ጆሮ ክፉ ከመስማት መቆጠብ እንደሚገባ ተጽፎአል፡፡ “ይጹም ዐይን፣ ይጹም ልሳን፣ እዝንኒ ይጹም እምሰሚዓ ኀሡም በተፋቆሮ” /ቅዱስ ያሬድ ጾመ ድጓ/፡፡ በጾም ወራት፣ ላምሮት፣ ለቅንጦት፣ የሚበሉ ወይም ለመንፈሳዊ ኃይል ተቃራኒ የሆኑ ሥጋዊ ፍትወትን የሚያበረታቱ፣ ሥጋንና የሚያሰክሩ መጠጦችን /ዳን.10፥2-3/ ቅቤና ወተትን ማራቅ ታዟል፡፡ /መዝ.108፥24፣ 1ቆሮ.7፥5፣ 2ቆሮ.6፥6/
የማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማእከልን ወደ ተቋምነት ለማሳደግ ምክክር ተካሄደ
የካቲት 13 ቀን 2006 ዓ.ም.
በመ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
በተካሄደው የምክክር ጉባኤ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የሴቲት ሁመራ ሊቀ ጳጳስና የማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ፣ የማኅበሩ የሥራ አመራርና ሥራ አስፈጻሚ አባላት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የምክክር ጉባኤው በጸሎት የተከፈተው በብፁዕ አቡነ ሉቃስ ሲሆን፤ የምክክር ጉባኤውን የመነሻ ጥናት ይዘው የቀረቡት ደግሞ የጥናትና ምርምሩ አማካሪ ቦርድ አባልና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ ናቸው፡፡
የደሴ ማእከል ቅዱሳት መካናትና ማኅበራዊ አገልግሎት ክፍል ስለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ ልማት ከበጎ አድራጊዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
የካቲት 13 ቀን 2006 ዓ.ም.
ወርቁ በላይሁን ከደሴ ማእከል
የደሴ ማእከል ቅዱሳት መካናትና ማኅበራዊ አገልግሎት ክፍል “ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት በጋራ እንሥራ” በሚል መርህ ከደሴ ከተማ በጎ አድራጊዎች ጋር ቤተ ክርስቲያን በዘላቂነት ራሷን ለማስቻል እንዲረዳ ጥር 25 ቀን 2006 ዓ.ም
የግማሽ ቀን ውይይት አደረገ፡፡
መርሐ ግብሩ በጸሎት ተከፍቶ የበገና መዝሙር ከቀረበ በኋላ ስለቦሩ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ፤ የመምህር አካለወልድ አዳሪ ት/ቤት እና ስለ አቡነ አኖሬዎስ ገዳም የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ልማትና የእደ ጥበብ ፕሮጀክት ዶክመንተሪ ፊልም ቀርቧል፡፡ በዶክመንተሪ ፊልሙም ገዳማትንና የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን ለመርዳት በተናጠል የሚደርገው ሩጫ ለችግሮቹ ዘላቂ መፍትሄ የሚያስገኝ ባለመሆኑ በተጠና መልኩ የተቀናጀ እንቅስቃሴ ማድረጉ የተሻለ እንደሚሆን አስገንዝቧል፡፡
ለአብነት መምህራን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ
የካቲት 12 ቀን 2006 ዓ.ም.
ህሊና ሲሳይ ከሐዋሳ
በማኅበረ ቅዱሳን ሐዋሳ ማዕከል የቅዱሳት መካናት ልማት እና ማኅበራዊ አገልግሎት ክፍል ለግቢ ጉባኤያት የአብነት መምህራን ከጥር 21-23 2006 ዓ.ም የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትሪያሪክ ዘኢትዮጵያ በሐዋሳ ደማቅ አቀባባል ተደረገላቸው
የካቲት 12 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዲ/ን ያለው ታምራት ከሐዋሳ
ጥር 29 ቀን 2006 ዓ.ም በእምነት ተቋማት ኀብረት በተዘጋጀው የሰላም ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሐዋሳ ለተገኙት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትሪያሪክ ርዕሰ ሊቃለ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ እና ለሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት በሐዋሳ ከተማ ምዕመናን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡