መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የግንቦቱ ርክበ ካህናት መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ
ግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ.ም.
በቅዱስ ሲኖዶስ የቀረበው መግለጫ ውሳኔ ያላገኙ አጀንዳዎችን አካቷል
ከግንቦት 6 ቀን 2006 ዓ. ም. ጀምሮ ሲካሔድ የቆየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ. ም. መግለጫ በመስጠት ተጠናቋል፡፡ ጉባኤው ሲጠናቀቅ በቀረበው መግለጫም ውሳኔ ሳያገኙ የቀሩ አጀንዳዎችን አካቷል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡-
የብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቅዱስ ፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ፤ የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረዳት ሊቀ ጳጳስነት ተነስተው የጅማ ሀገረ ስበከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲሠሩ ሲወሰን፤ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሳይመደብለት ታልፏል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ 34 ገጽ ለጉባኤው ቀርቦ ምልዓተ ጉባኤው በስፋት ውይይት ማድረጉን ከመግለጽ ውጪ ውሳኔ ሳይሰጠው ቀርቷል፡፡
ዝርዝሩን ከሙሉ መግለጫው ይከታተሉ፡፡
የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት አከበረ
ግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩበልዩ በዓል ግንቦት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ቦሌ በሚገኘው በድርጅቱ ሕንፃ አከበረ፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶችና የድርጅቱ አባላት ተገኝተዋል፡፡
አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ክፍል ሁለት
ግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በካህናቱ መሪነት ከተራራው ሥር ወደምትገኘው ወደ ቀድሞ ዋሻ ቤተ ክርስቲያን ስናመራ፤ ከተራራው አናት ላይ ሆነን ቁልቁል ስንመለከት ትልቅ ወንዝና ደረቱን ለኛ የሰጠ ተራራ ተመለከትን ፡፡ ካህናቱንና ዲያቆናቱን ተከትለን ቁልቁል የሚወስደውን ቀጭን መንገድ ተያያዝነው፡፡ ወንዙ ምን ይባላል አልናቸው ለአንድ አዛውንት “ የማርያም ዥረት ነው የሚባለው” አሉን ፡፡ እንደመቀነት የሚጠማዘዘውን ቀጭን መንገድ እየተከተልን ወደ ዋሻው አፋፍ ደረስን፡፡ ወደ ዋሻው መግቢያ በስተቀኝ በኩል በመጠኑ የጎደጎደ ሥፍራ ይታያል፡፡ ምን እንደሆነ ጠየቅን፡፡ “ከተራራው ሥር እየፈለቀ የሚወርድ ማየገቦ የሚጠራቀምበት ጉድጓድ ነበር፤ (ማየገቦ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ በቦታው ያልነበረው አንድ ዓይና ሌንጊኖስ ከአይሁድ ጋር ለመተባበር ብሎ ኢየሱስ ክርስቶስን በጦር ቢወጋው ውኃና ደም እንደ ለ ፊደል ፈሷል ፡፡ የፈሰሰው ውኃ ማየገቦ ይባላል፡፡) ዋሻው ቤተ መቅደስ ከተደረመሰ በኋላ ደርቋል” አሉን አዛውንቱ፡፡
ሐዊረ ሕይወት በሀገረ ጀርመን ተካሄደ
ግንቦት 15 ቀን 2006 ዓ.ም.
ከጀርመን ቀጣና ማእከል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የጀርመን ቀጣና ማእከል በአውሮፓ የመጀመሪያውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ከግንቦት 8-10, 2006 በክሩፈልባክህ (Kroeffelbach) በሚገኘው የኮፕቲክ ቅዱስ እንጦንስ ገዳም (Sankt-Antonius Kloster) በደማቅ ሁኔታ አካሄደ።
በዚህ ከ80 በላይ ምእመናን በተሳተፉበት መርሐ ግብር ላይ ሰፊ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን በተለይ ነገረ ድኅነት እና መንፈሳዊ አገልግሎት ላይ የተሰጡት ጥልቅ ትምህርቶች ተሳታፊዎች በጉዳዮቹ ላይ የነበራቸውን እውቀት በከፍተኛ ሁኔታ ያሳደጉ እና ታዳሚው ሐዊረ ሕይወት በቅርቡ ይደገምልን የሚል ጥያቄን እንዲሰነዝር ያነሳሱ ነበሩ። በተጨማሪም መዝሙራት በዘማርያንና በሕብረት የቀረቡ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳን በሀገር ቤት ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋትበተለይም በተመረጡ ጠረፍና ገጠር አብያተ ክርስቲያናት ላይ አቅዶ እያከናወነው ስላለው የስብከት ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራም ገለጻ ተደርጓል።
ሐዊረ ሕይወት(አዳማ ማዕከል)
“የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ. . . ይጠቅማል” 2ኛ ጢሞ.3፤16-17
ግንቦት 12 ቀን 2006 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖአምላክ
“መንፈሰ እግዚአብሔር ያለበት፣ ሰውን ከክፋት፣ ከኃጢአት፣ ከበደል የሚመልስ፤ ይልቁንም ሃይማኖቱን የሚያጸናለት መጽሐፍ ከእግዚአብሔር ነውና ይጠቅማል” በማለት ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረው ቃል ነው፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ቃል ያስተላለፈው ለጊዜው በሃይማኖት ትምህርት ወልዶ ላሳደገው ለደቀመዝሙሩ ጢሞቴዎስ ቢኾንም ፍጻሜው ግን እስከ ሕልፈተ ዓለም ለሚነሡ ክርስቲያኖች ሁሉ የተናገረው ነው፡፡ “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” (፪ኛ. ጢሞ.፫፥፲፮-፲፯)
አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም
ግንቦት 11 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በቀይት ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር በጉዶ በረት አካባቢ የምትገኘውን ጥንታዊትና ታምረኛዋን ገዳም እንድንዘግብላቸው በተደጋጋሚ ቢሯችን በመምጣትና ስልክ በመደወል ቀጠሮ ያስያዙንን የርዕሰ አድባራት ወገዳማት ዳግሚት ፅዮን አዲስ ዓለም ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ ንቡረ ዕድ አባ ገብረ ሕይወት መልሴ ጋር በነበረን ቀጠሮ መሠረት ሚያዚያ 15 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሌሊቱ 12፡30 ወደ አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም ለመጓዝ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በር ላይ እና ላም በረት አካባቢ ከሚገኘው መናኸሪያ በር ተገናኝተናል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልኣተ ጉባኤ የ2006 ዓ.ም. ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ
ግንቦት 6 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የግንቦቱ ርክበ ካህናት ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ግንቦት 5 ቀን 2006 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በጸሎት ተጀምሯል፡፡ ግንቦት 6 ቀን 2006 ዓ.ም. በቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ መልእክት ጉባኤው ቀጥሏል፡፡
ለአብነት መምህራንንና ተማሪዎች የሕክምና አገልግሎት ተሰጠ
ሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም.
በዲ/ን ቴዎድሮስ ኃይሉ
በማኅበረ ቅዱሳን የሙያ አገልግሎትና ዐቅም ማጎልበቻ ዋና ክፍል የጤና ንዑስ ክፍል አስተባባሪነት በደብረ ሊባኖስ ገዳም፣ በምዕራፈ ቅዱሳን በልበሊት ኢየሱስ አንድነት ገዳምና በፍቼ ደብረ ሲና ዐራተ ማርያም ደብር ለሚገኙ የአብነት መምህራንና ተማሪዎች ከሚያዝያ 25 እስከ 27 ቀን 2006 ዓ.ም የሕክምና አገልግሎት ተሰጠ፡፡
በጠረፋማ አካባቢዎች ለተጠመቁ ወገኖች አብያተ ክርስቲያናት ለማነጽ ጥረት እየተደረገ ነው
ሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራም በጠረፋማ አካባቢዎች ለተጠመቁ ወገኖች አብያተ ክርስቲያናት ለማነጽ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡
በጂንካ፤በግልገል በለስ፤ በቦረና /ተልተሌ/፤ በቦንጋ/ጮራ/ እንዲሁም በሌሎች ጠረፋማ ወረዳዎች ነዋሪዎች ጥምቀት ተከናውኖላቸው የነበረ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን ሳይሠራላቸው ቆይቷል፡፡ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራምም ይህንን ችግር ለመፍታት ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ቤተ ክርስቲያን በማጣት ከአገልግሎት ርቀው ወደ ኢ-አማኒነት እንዳይመለሱ ምእመናን እገዛ ማድረግ እንደሚገባቸው የጠቀሰው የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያው በቅርቡ ሊሠሩ ለታቀዱ ለ12 አብያተ ክርስሰቲያናት የግንባታ ግብአቶችን፤ በተለይም ቆርቆሮ፤ ምስማር፤ እንዲሁም ሌሎች ቁሳቁሶችን ምእመናን እንዲረዱ የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጊያ መርሐ ግብር በማኅበሩ ጽ/ቤት አዘጋጅቷል፡፡