መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
በፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ፣ በኖቲንግሃምና በጎንደር ከተሞች ዐውደ ጥናቶች ተካሔዱ
ነሐሴ ፬ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በአሜሪካ፣ በአውሮፓና በጎንደር ማእከላት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማእከል በፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ ልዩ ዐውደ ጥናት እንደሚያካሒድ ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም ባወጣነው ዘገባ ማስነበባችን ይታወሳል፡፡ በዚህ መሠረት ማእከሉ ከፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ እና የሴሜቲክና የአፍሮ እስያ ከፍተኛ ምርምርና ጥናት ተቋም (The Institute for Advanced […]
ስለ ሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ
ነሐሴ ፫ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ‹‹ወሰላሙ ለክርስቶስ ይጽናዕ በልብክሙ ዘሎቱ ተጸዋዕክሙ በአሐዱ ሥጋ፤ በአንድ አካል የተጠራችሁለት የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይጽና፤›› (ቆላ 3÷15):: ይህ ቃል ሰው ሁሉ ለሰላም እንደተጠራ፣ ልቡንም ለሰላም ማስገዛት እንዳለበት ያስገነዝበናል፤ በእርግጥም ለሰው ከሰላም የበለጠ አስፈላጊ ነገር የለምና ለሰላም መገዛት ተገቢ ነው፡፡ ሰው ከሰላም ተጠቃሚ […]
ጾመ ፍልሰታ ለማርያም
ነሐሴ ፫ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው በነገረ ማርያም ተጽፎ እንደምናገኘው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ሊቀብሯት ወደ ጌቴሴማኒ ይዘዋት ሲሔዱ አይሁድ “እንደ ልጇ ተነሣች፤ ዐረገች እያሉ እንዳያውኩን በእሳት እናቃጥላት” ብለው በዓመፃ ተነሡ፡፡ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊም አጎበሩን ይዞ ሊያወርዳት ሲል የእግዚአብሔር መልአክ […]
ቅዱስ ፓትርያኩ ጾመ ማርያምን በማስመልከት ቃለ ምዕዳን ሰጡ
ሐምሌ ፳፰ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጾመ ማርያምን በማስመልከት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ የማኅበረ ቅዱሳን፣ የመንግሥትና የግል መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች በተገኙበት ሐምሌ ፳፰ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በመላው ዓለም ለሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል፡፡ የቅዱስ ፓትርያርኩን […]
የሰባክያነ ወንጌል እና የግቢ ጉባኤያት ሥራ አስፈጻሚዎች ሥልጠና ተጠናቀቀ
በማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል በስብከተ ወንጌልና ሥልጠና ክፍል፣ እንደዚሁም በስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብር ከልዩ ልዩ ጠረፋማ አህጉረ ስብከት የተውጣጡ …
የቤተ ክርስቲያን ቅርሶቻችንን ከዘራፊዎች እንጠብቅ!
ስልሳ አምስት ጥንታውያን የቤተ ክርስቲያን የብራና መጻሕፍት ሊሸጡ ሲሉ …
‹‹ያለ ደግ ልጆች ያላስቀረን እግዚአብሔር ይመስገን!›› ብፁዕ አቡነ ሉቃስ
ሐምሌ ፳ ቀን፣ ፳፻፰ ዓ.ም በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው ይህ ‹‹ያለ ደግ ልጆች ያላስቀረን እግዚአብሔር ይመስገን!›› የሚለው ኃይለ ቃል ከብፁዕ አቡነ ሉቃስ ቃለ ምዕዳን የተወሰደ ሲኾን፣ ይኸውም ማኅበረ ቅዱሳን በጀት በመመደብና ምእመናንን በማስተባበር ለገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች ያደረገውን ድጋፍና ያመጣውን ውጤት ለቤተ ክርስቲያን አባቶችና ለበጎ አድራጊ ምእመናን ለማሳወቅ ሐምሌ ፲፯ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በግዮን […]
እናቴ ሆይ እሳቱን አትፍሪ፤ እግዚአብሔር ያድነናል፡፡
በመጽሐፈ ስንክሳር እንደ ተመዘገበው ሐምሌ ፲፱ ቀን ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ የተቀበሉበትና ስማቸውን የሚጠራ፣ ዝክራቸውንም የሚዘክሩ ምእመናን ይቅርታን፣ ምሕረትን እንደሚያገኙ ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ነው፡፡
የአውሮፓ ማእከል ፲፮ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሔደ
ሐምሌ ፲፭ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በአውሮፓ ማእከል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ፲፮ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ከሐምሌ ፩-፫ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በስዊድን አገር ስቶክሆልም ከተማ ተካሔደ። በጠቅላላ ጉባኤው በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች የሚኖሩ ከሰባ በላይ የማእከሉ አባላት፤ የዋናው ማእከልና የሰሜን አሜሪካ ማእከል ተወካዮች፤ እንደዚሁም ጥሪ የተደረገላቸው ካህናትና […]
ዘመነ ክረምት ክፍል አንድ
ሐምሌ ፲፬ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው በበአተ ክረምት ጽሑፋችን እንደ ጠቀስነው በኢትዮጵያ የወቅቶች ሥርዓተ ዑደት አኳያ አሁን የምንገኘው ዘመነ ክረምት ላይ ነው፡፡ በቅዱስ ያሬድ አስተምህሮ ይህ ዘመነ ክረምት በሰባት ንዑሳን ክፍሎች ይመደባል፡፡ በዛሬው ዝግጅታችን የመጀመሪያውን ክፍለ ክረምት የተመለከተ ጽሑፍ ይዘን ቀርበናል፤ ከሰባቱ የዘመነ ክረምት ክፍሎች መካከል የመጀመሪያው ክፍል (ከሰኔ ፳፭ እስከ ሐምሌ ፲፰ […]