ለሲኖዶሳዊ ልዕልና መከበር የምእመናን ድርሻ ከፍተኛ ነው!
በሀገር አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ ተሰሚነት እና ውክልና እንዳይኖራት፣ እጅግ ብዙ ችግር እንዲከባት ተሠርቷል፤ አሁንም እየተሠራ ይገኛል፡፡ ይህንም ለማድረግ የተቻለው በተቀናጀ ስልት ሲሆን ሲኖዶሱ ክብሩ ልዕልናው እንዳይጠበቅ በማድረግ፣ የመሪነት ሚናውን እንዳይወጣ፣ የተጠራበትን ሰማያዊ ተልእኮውን እንዳያሳካ፣ በመከፋፈል እና በራሱ ውስጣዊ አጀንዳ እንዲጠለፍና፣ ውሳኔው መሬት እንዳይነካ በማድረግ ነው፡፡ ከምንም በላይ መሪና ተመሪ እንዳይገናኙ፣ ሲኖዶሱ በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ አድርጎታል፡