ምኵራብ
‹‹ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤ የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው፡፡ ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት››
‹‹ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤ የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው፡፡ ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት››
ቅድስት ማለት ‹የተለየች፣ የነጻች፣ የከበረች› ማለት ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾም የጀመረባት፣ ልዩ፣ የተቀደሰች፣ የከበረች፣ ንጹሕ፣ ክቡር በሚሆን በጌታችን የተጾመች መሆኗን ያመላክታል፡፡ ይህች ጾም በማቴዎስ ወንጌል የተገለጠች ስትሆን፣ አምላካችን በገዳመ ቆሮንቶስ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት በጾመበት ጊዜያት ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል አድርጓል፡፡ (ማቴ.፬፥፪)
ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም ካለው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በመነሣት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በዚህ ዕለት ምስባክ ‹‹አዳምን ለማዳን ከሰማይ የወረደውን አይሁድ ሰቀሉት፤ የሰማይን ሥልጣን ያለው የሁሉ ጌታ እንደሆነም ምንም አላወቁም›› ብሎ ተናግሮ ነበር፡፡ ይህም ድርሰት በቤተ ክርስቲያናችን የጾም መጀመሪያ የሆነው ዕለተ ሰንበት ዋዜማ፣ መግቢያ (መሐትው) ሆኖ ከዋዜማ በፊት ምንጊዜም በየዓመቱ ይቆማል፤ ይዘመራል፤ ይመሰገናል ማለት ነው፡፡
‹ዐቢይ›› የተባለው የዓለማት ፈጣሪ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአርአያነት ጾሞ የመሠረተው ጾም ስለሆነ ነው፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ካሉት ሰባት የአዋጅ አጽዋማት ረጅሙ (፶፭ ቀን ያለው) ስለሆነ ደግሞ ‹‹ሁዳዴ›› ይባላል፡፡ ኢትዮጵያዊው የዜማና የቅዱሳት መጻሕፍት ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚገኙትን ስምንት ሣምንታት ለትምህርት፣ ለአዘክሮና ለምስጋና በሚመች መልኩ ልዩ ስያሜዎች ሰጥቷቸዋል፡፡ ስለሆነም በእያንዳንዱ ሳምንት (ሰንበት) የሚነበቡ፣ የሚተረጎሙ፣ የሚዘከሩ፣ የሚዘመሩ ልዩ ልዩ መጽሐፍ ቅዱሣዊ ኩነቶችና አስተምህሮዎች አሉ፡፡
በወንጌል ቅዱስ ማቴዎስ ስለ ጌታችን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐቢይ ጾም ሲጽፍ ‹‹ከዚያ ወዲያ›› በማለት ከጀምረ በኋላ እርሱ ለሰዎች ድኅነት ሲል ለዐርባ ቀንና ሌሊት ያለ መብልና መጠጥ በጾም በምድረ በዳ እንደቆየ ይገልጽልናል፡፡
የእግዚአብሔር ነቢይ ኢሳይያስ በዚያን ዘመን ይኖሩ ለነበሩት እስራኤላውያን እንዲናገር በታዘዘው መሠረት ይህን ቃል ነገራቸው፤ ‹‹እናት ልጇን እንደምታጽናና እንዲሁ አጽናናችኋለሁ፡፡›› (ኢሳ.፷፮፥፲፫) ከነበሩበት መከራና ከጭንቀታችው ሁሉ እንደሚያጽናናቸው እግዚአብሔር አምላክ በነቢዩ አማካኝነት ተስፋ ሰጣቸው፡፡ ነገር ግን ይህ ቃል በዚያን ዘመን ላለው ሕዝብ ብቻ የሚያልፍ ሳይሆን ዛሬ ያለነውም ትውልድ በተለይም እኛ ልናስተውለው የሚገባ ቃል ነው፡፡
በዘመነ ሥጋዌ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ከሞተ በኋላ ወደ በረሃ ሄደ፡፡ ሕዝቡም ሰምቶ ተከተለው፡፡ በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሕዝቡን እንዲያሰናብት ጠየቁት፡፡ ይህም ለዚያ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ምግብ ስለሌለ የሚበሉትን እንዲገዙ ነበር፡፡ እርሱ ግን ለጊዜው የተገኘውን አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ ባርኮ ሁሉንም እስኪጠግቡ ድረስ መገባቸው፡፡ ተርፎም አሥራ ሁለት መሶብ ተነሣ፡፡ የተመገቡትም ሕዝብ ሴቶችና ሕፃናት ሳይቆጠሩ አምስት ሺህ ወንዶች ነበሩ፡፡ ‹‹አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ የበሉትም ወንዶች አምስት ሺህ ነበሩ›› እንዲል፤ ሴቶቹ ያልተቆጠሩበት ምክንያት በዐደባባይ ሲበሉ በሃፍረት ዳር ዳር ስለሚሉ ነው፤ ሕፃናት ደግሞ ከሚበሉት የሚፈረፍሩት ስለሚበዛ ነው፡፡ (ማር.፮፥፵፬)
በትዳር ሕይወት ስንኖር ባል ራስ ነውና ሚስቶች ለባሎቻቸው እንዲገዙና እንዲታዘዙ ሲያዛቸው፣ ለባሎች የሰጠው ትእዛዝ ደግሞ ከዚህ የጸና ትእዛዝ ነው። ይኸውም የገዛ ሕይወቱን አሳልፎ እስኪሰጥላት ድረስ ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንደወደዳት ባልም እንዲሁ ሚስቱን እንዲወዳት ጽኑዕ ትእዛዝን አዟል። ታዲያ ከመታዘዝና ከመገዛት ይልቅ ምን ያህል የሚጸና እንደሆነ ልናስተውለው ይገባል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን በፍቅር ሞቷል እና ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ ትገዛለች፤ በተመሳሳይ ፍቅር ምክንያት ‹‹ሚስቶች ሆይ፤ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁም ተገዙ፤ ክርስቶስ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ራስዋ እንደሆነ ሁሉ፣ አዳኝዋም እንደ ሆነ ወንድ ለሴት ራስዋ ነውና፡፡
የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ ‹‹እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ›› ማለት ነው፤ ‹‹ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢይተረጐም ምሥጢር ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር፤ ገብርኤል ሆይ ተመራምሮ ለማይደረስበት ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፤ ነገር ግን አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ይመስላል›› እንዲል፡፡ (መልክዐ ቅዱስ ገብርኤል)