ፍልሰተ ዐፅሙ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት

ግንቦት ፲፪ ቀን፣ ፳፻፰ ዓ.ም

በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ ግንቦት ፲፪ ቀን በዚህች ቀን ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት፣ ኢትዮጵያዊው ንጉሥ እስክንድር፣ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቅዱስ መስቀል፣ ቅዱስ ሚናስ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ የመላልዔል ልጅ ያሬድ፣ እንደዚሁም ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ይታሰባሉ፡፡ በዚህ ዝግጅት የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ፍልሰተ ዓፅም የሚያስታውስ ጽሑፍ ይዘንላችሁ ቀርበናል፤

ስምዑ ወለብዉ ኦ ፍቁራንየ መጽሐፈ ዜናሁ ለክቡር ወቅዱስ ወለብፁዕ ፍቁረ እግዚአብሔር ዘይትነበብ በዕለተ ፍልሰተ ሥጋሁ አመ ፲ወ፪ ለግንቦት ዝ ውእቱ ድሙር ምስለ በዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወበዓለ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ፍቁሩ ለተክለ ሃይማኖት፤ ወዳጆቼ ሆይ፣ የከበረ፣ የተቀደሰ፣ የተደነቀ፣ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሚሆን የአባታችን የተክለ ሃይማኖት ክብሩን፣ ገናንቱን የሚናገረውን፣ ዐፅሙ የፈለሰበትን ግንቦት ፲፪ ቀን የሚነበበውን መጽሐፍ አስተውላችሁ ስሙ፤ /ገድለ ተክለ ሃይማኖት ምዕ.፷፪፥፭/፡፡

ተክል ማለት ፍሬያማ ዕንጨት፣ ዛፍ፣ ቅመም፣ ቅጠላ ቅጠል፣ የሚበላ፣ የሚሸተት፣ ገነታዊ ዕፅ፣ እንዲሁም ሕግ ሥርዓት ማለት ነው /ማቴ.15፥13/፡፡ ሃይማኖት ማለት ደግሞ በሀልዎተ እግዚአብሔር፣ እግዚአብሔር የሁሉ አስገኚ መሆኑን፣ በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት፣ በቅዱሳን ተራዳኢነት ማመን አምኖም መመስከር ማለት ሲሆን ተክለ ሃይማኖት የሚለው ሐረግም የሃይማኖት ተክል፣ ይኸውም የጽድቅ ፍሬን ያፈራና ከኃጢአት ሐሩር ማምለጫ ዛፍ፣ ምእመናንን በቃለ ወንጌል ያጣፈጠ ቅመም፣ መዓዛ ሕይወቱ የሚማርክ፣ ቢመገቡት ረኃበ ነፍስን የሚያስወግድ ቅጠል፣ የጻድቃን መጠለያ ዕፅ የሚል ትርጕም ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ መጽሐፈ ገድላቸውም ተክለ ሃይማኖት ማለት የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ተክል ማለት ነው ሲል ይተረጕመዋል፡፡ አባታችን እርሳቸውም በአሚነ ሥላሴ ጸንተው ሌሎችንም እንዲጸኑና እንዲያምኑ አድርገዋልና፡፡

አቡነ ተክለ ሃይማኖት በ፲፫ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ከአገራችን ከኢትዮጵያ ምድር ከሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ከኢቲሳ መንደር ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብ እና ከእናታቸው እግዚእ ኀረያ አብራክ የተገኙ ቅዱስ አባት ናቸው፡፡ አባታችን ሕይወታቸዉን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣ እንደገበሬ ታጥቀው ይህንን ዓለም ንቀው በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና ከመኖራቸው በተጨማሪ እንደቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የሰበኩ፣ በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሐዋርያ ናቸው፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህንን ውለታቸውን በማሰብና ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ቅድስና መሠረት በማድረግ በስማቸው ጽላት ቀርፃ ስታከብራቸው ትኖራለች፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሚታወሱባቸው በዓላት መካከልም በዛሬው ዕለት የሚከብረው ፍልሰተ ዐፅማቸው አንደኛው ሲሆን ታሪኩንም በአጭሩ እነሆ፤

ጻድቁ አባታችን ምድራዊ ሕይወታቸውን በተጋድሎና በሐዋርያዊ አገልግሎት ከፈጸሙ በኋላ ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድ የሚያልፉበት ቀን በተቃረበ ጊዜ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን መላእክት፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ከቅዱሳን ሐዋርያት ጋር ወደእርሳቸው በመምጣት የሚያርፉበት ዕለት መድረሱን ነግሯቸው የተጋድሏቸውን ጽናት አድንቆ በስማቸው መታሰቢያ ለሚያደርጉ፣ ለነዳያን ለሚመጸዉቱ ቤተ ክርስቲያን ለሚያሠሩ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡

አቡነ ተክለ ሃይማኖትም የዕረፍታቸው ጊዜ መቃረቡን ባወቁ ጊዜ የመንፈስ ልጆቻቸውን ጠርተው ጌታችን የነገራቸውን ሁሉ አስረድተው አባታዊ ምክርና ተግሣፅ ከሰጧቸው በኋላ ነሐሴ ፳፬ ቀን ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ፡፡ የመንፈስ ልጆቻቸውም ለአንድ ቅዱስ አባትና ካህን በሚገባ ሥርዓት በማኅሌት፣ በዝማሬና በምስጋና ቀበሯቸው፡፡ ጌታችንም ከእመቤታችንና ከቅዱሳን መላእክት ጋር ተገልጾ ታያቸው፤ ነፍሳቸውንም የጠራሽ፣ ንጽሕት ነፍስ ሆይ ወደእኔ ነዪ ብሎ በክብር ተቀበላት፡፡

በመጽሐፈ ገድላቸው እንደተጠቀሰው ቅዱስ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዚህ ዓለም የኖሩበት ዕድሜ ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከዐሥር ወር ከዐሥር ቀን ነው፡፡ ገድላቸው ዕድሜያቸውን በመከፋፈል፡- በእናት አባታቸው ቤት ፳፪ ዓመት፤ በከተታ ፫ ዓመት፤ በዊፋት ፱ ወር፤ በዳሞት ፲፪ ዓመት፤ በአማራ ፲ ዓመት፤ በሐይቅ ፲ ዓመት፤ በደብረ ዳሞ ፲፪ ዓመት፤ በትግራይ ገዳማት በመዘዋወርና ወደ ኢየሩሳሌም በመመላለስ ፩ ዓመት፤ ዳዳ በሚባል አገር ፩ ወር፤ በአሰቦ ገዳም ፳፱ ዓመት ከ፲ ቀን መቆየታቸውን ይናገራል /ገ.ተ.ሃ.፶፱፥፲፬-፲፭/፡፡

ወደ ፍልሰተ ዐፅማቸው ታሪክ ስንመለስ መጽሐፈ ገድላቸው እንዲህ ሲል ይጀምራል፤ ስምዑ ወለብዉ ኦ ፍቁራንየ መጽሐፈ ዜናሁ ለክቡር ወቅዱስ ወለብፁዕ ፍቁረ እግዚአብሔር ዘይትነበብ በዕለተ ፍልሰተ ሥጋሁ አመ ፲ወ፪ ለግንቦት ዝ ውእቱ ድሙር ምስለ በዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወበዓለ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ፍቁሩ ለተክለ ሃይማኖት፤ ወዳጆቼ ሆይ፣ የከበረ፣ የተቀደሰ፣ የተደነቀ፣ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሚሆን የአባታችን የተክለ ሃይማኖት ክብሩን፣ ገናንቱን የሚናገረውን፣ ዐፅሙ የፈለሰበትን ግንቦት ፲፪ ቀን የሚነበበውን መጽሐፍ አስተውላችሁ ስሙ፤ ይኸውም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል ጋር የተክለ ሃይማኖት ወዳጅ ከመላእክት አለቃ ከቅዱስ ሚካኤል በዓል ጋር የተባበረ ነው፡፡ ወንድሞቻችን እንነግራችኋለን፤ እናስረዳችኋለን፡፡ እንደ ዮሐንስና እንደ ነቢዩ ኤርምያስ ከእናቱ ማኅፀን እግዚአብሔር የመረጠው የክቡር አባታችን ዐፅሙ የፈለሰበት ቀን ዛሬ ነው፤ /ገ.ተ.ሃ.፷፪፥፭-፰/፡፡

አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ዓለም ከተለዩ በ፶፯ኛው ዓመት የካቲት ፲፱ ቀን ለመንፈስ ልጃቸው ለአባ ሕዝቅያስ ብርሃን ለብሰው በሕልም ተገለጡላቸውና ወዳጄ ሕዝቅያስ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን! ጌታዬ በኋለኛው ዘመን ከዚህ ሥፍራ ልጆችህ ሥጋህን ያፈልሳሉ ያለኝ ዘመን ደርሷልና ሳትዘገይ ልጆቼን ሁሉ ቅጠራቸውና እስከምፈልስበት ቀን ድረስ ግንቦት ፲፪ ቀን ይሰብሰቡ፡፡ እናንተም በምስጋና በጸሎት መንፈሳዊ በዓልን አድርጉ፡፡ አባቴ ተክለ ሃይማኖት የሚለኝ ሁሉ በዚህች በፍልሰተ ዐፅሜ ቀን ይምጣ፤ መንፈሳዊ በዓልንም ያድርግ፡፡ እኔና ቅዱስ ሚካኤል ከወዳጄ አባ ፊልጶስ ጋር ስለኔ ፍቅር የተሰበሰበውን ሕዝብ ልንባርክ እንመጣለን፤ ከአሏቸው በኋላ ተሠወሯቸው፡፡

አባ ሕዝቅያስም እንደታዘዙት የአባታችሁን ዐፅም ከዋሻው ወደ ታላቁ ቤተ ክርስቲያን ታፈልሱ ዘንድ ኑ፤ ተሰብሰቡ ብለው የአባታችን ወዳጆች በያሉበት ሀገር ሁሉ መልእክት ላኩ፡፡ ምእመናንም ጥሪውን ተቀብለው በዓሉን ለማክበር ከአራቱም አቅጣጫ ተሰበሰቡ፡፡ ዐሥራ ሁለቱ መምህራንም መጡ፤ እነዚህም፡- የወረብ አገሩ አባ አኖሬዎስ፣ የፈጠጋሩ አባ ማትያስ፣ የእርናቱ አባ ዮሴፍ፣ የሞረቱ አባ አኖሬዎስ፣ የመርሐ ቤቴው አባ መርቆሬዎስ፣ የጽላልሹ አባ ታዴዎስ፣ የወገጉ አባ ሳሙኤል፣ የወንጁ አባ ገብረ ክርስቶስ፣ የድንቢው አባ መድኃኒነ እግዚእ፣ የዳሞቱ አባ አድኃኒ፣ የክልአቱ አባ ኢዮስያስ እና የመሐግሉ አባ ቀውስጦስ ናቸው፡፡

እነዚህ መምህራን ከአባ ሕዝቅያስ ጋር በመሆን የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ዐፅም ከዐረፈበት ዋሻ ባወጡት ጊዜ ዐፅማቸው ዕለት የተገነዘ በድን ይመስል ነበር፤ መዓዛውም ሽቱ፣ ሽቱ ይሸት ነበር፡፡ በአባታችን ዐፅም ቀኝና ግራም መስቀል ተተክሎ ነበር፡፡ በዐፅማቸውም ብዙ ድንቅ ተአምራት ተደርገዋል፡፡ ይህንን የአባታችንን ዐፅም አባ ሕዝቅያስና ዐሥራ ሁለቱ መምህራን በሣጥን አክብረው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ወስደው በመንበሩ ፊት ሦስት ጊዜ አዞሩት፡፡

በዚህች ዕለት አስቀድመው የካቲት ፲፱ ቀን ለአባ ሕዝቅያስ በሕልም እንደነገሯቸው ብፁዕ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከቅዱስ ሚካኤልና ከአባ ፊልጶስ ጋር ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መጥተው ዐፅማቸው እስኪያረፍ ድረስ ከመንበሩ ተቀምጠው ቆይተው ዐፅማቸው ካረፈ በኋላ የተሰበሰበውን ሕዝብ ባርከው በክብር ወደ ሰማይ ዐረጉ፡፡ መምህራኑና ምእመናኑም በዓሉን በታለቅ ደስታ አክብረው በሰላም ወደየቤታቸው ተመለሱ፡፡ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ፍልሰተ ዐፅም ከዋለበት ዕለት ጋር ርክበ ካህናት አብሮ መዋሉ በዓሉን ልዩ ድምቀት ሰጥቶት ነበር /ገ.ተ.ሃ.፷፭፥፩-፳፬/፡፡

ከዚያ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በታላቁ ገዳም በደብረ ሊባኖስ ቅዱሳን ፓትርያሪኮች፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና በርካታ ምእመናን እየተሰበሰቡ በዓሉን በድምቀት ያከብራሉ፡፡ የብፁዕ አባታችን ዐፅማቸው በፈለሰበት ዕለት ዐሥራ ሁለቱ መምህራን እና በርካታ ምእመናንን እንደተሰበሰቡ ሁሉ እኛንም እግዚአብሔር አምላካችን በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ይሰብስበን፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትና የመንፈስ ልጆቻቸው ጸሎት፣ ረድኤትና በረከት ለዘለዓለሙ ይጠብቀን፡፡

ምንጭ፡-

ገድለ ተክለ ሃይማኖት፣ ፲፱፻፹፱ ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፡፡

መጽሐፈ ስንክሳር፣ ግንቦት ፲፪ ቀን፡፡

ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያዊ

ግንቦት ፲፩ ቀን፣ ፳፻፰ ዓ.ም

ዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ በየዓመቱ ግንቦት ፲፩ ቀን ከሚታወሱ ቅዱሳን መካከል የእመቤታችን እናት ቅድስት ሐና፣ ቅድስት ታውክልያ፣ ቅዱስ በፍኑትዩስ፣ አባ አሴር፣ ቅዱስ ያሬድ፣ ብፅዕት አርሴማ፣ ቅድስት ኤፎምያ፣ ቅድስት አናሲማ፣ ቅድስት ሶፍያ፣ አባ በኪሞስ፣ አባ አብላዲስ እና አባ ዮልዮስ ተጠቃሾች ሲሆኑ፣ በዛሬው ዝግጅታችን የቤተ ክርስቲያን እንዚራ፣ የኢትዮጵያ ብርሃን እየተባለ የሚጠራውን የቤተ ክርስቲያናችን ድምቀት፣ የአገራችን ኩራት የሆነውን የጥዑመ ልሳን፣ ኢትዮጵያዊ ማኅሌታይ የቅዱስ ያሬድን ታሪክ በአጭሩ ይዘንላችሁ ቀርበናል፤

በ፭፻፭ ዓ.ም በአገራችን በኢትዮጵያ በአክሱም ከተማ ከአባቱ ከአብዩድ (ይስሐቅ) እና ከእናቱ ታውክልያ (ክርስቲና) አንድ ቅዱስ ተገኘ፤ ይኸውም ቅዱስ ያሬድ ነው /ገድለ ቅዱስ ያሬድ/፡፡ ቅዱስ ያሬድ ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ ከአጎቱ ከአባ ጌዴዎን ዘንድ ትምህርት ሊማር ቢሔድም ለበርካታ ዓመታት ትምህርት ሊገባው አልቻለም ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ መምህሩ ይገርፉት፣ ይገሥፁት ነበር፡፡ እርሱም ከትምህርቱ ክብደት ባለፈ የመምህሩ ተግሣፅ ሲበረታበት ጊዜ ከአባ ጌዴዎን ቤት ወጥቶ በመሸሽ ላይ ሳለ ደክሞት ከአንድ ዛፍ ሥር ተቀመጠ፡፡

ከዛፉ ሥር ተጠልሎ ሳለ አንድ ትል ፍሬውን ለመመገብ ወደ ዛፉ ሲወጣ፣ ነገር ግን መውጣት ስለተሳነው በተደጋጋሚ ሲወድቅ ቆይቶ ከብዙ ሙከራ በኋላ ከዛፉ ላይ ሲወጣ፣ ፍሬውንም ሲመገብ ይመለከታል፡፡ ቅዱስ ያሬድ የትሉን ትጋት ከአየ በኋላ እርሱም በተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግ የከበደው ምሥጢር እንደሚገለጽለት በማመን ወደ መምህሩ ተመልሶ ይቅርታ ከጠየቀ በኋላ ትምህርቱን እንደገና መቀጠል ጀመረ፡፡ እግዚአብሔርን በጸሎት እየተማጸነ ትምህርቱን ሲከታተል ከቆየ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ልቡናው ብሩህ ሆኖለት የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ትርጓሜን አጠናቆ መዓርገ ዲቁና ተቀበለ፡፡

እግዚአብሔርም የክብር መታሰቢያ ሊያቆምለት ወዷልና ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን ልኮ በሰው አንደበት እንዲያናግሩት አደረጋቸው፡፡ እነርሱም ካናገሩት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት አወጡትና በዚያም የሃያ አራቱን ካህናተ ሰማይ (ሱራፌል) ማኅሌት ተማረ፡፡ ወደ ምድርም ተመልሶ በአክሱም ጽዮን በሦስት ሰዓት ገብቶ በታላቅ ቃል፡- ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ፤ ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድ ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል፡፡ የጽዮን ደገኛዋ ሰማይን ፈጠረ፡፡ ዳግመኛም እንዴት መሥራት እንዳለበት የድንኳንን አሠራር ለሙሴ አሳየው፤ አስተማረው እያለ በዜማ እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡ የቅዱስ ያሬድን ድምፅ የሰሙ ሁሉ ጳጳሳቱና ነገሥታቱ ሳይቀሩ ካህናቱም ምእመናኑም ወደርሱ ተሰብስበው ሲሰሙት ዋሉ፡፡ ይህንንም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራው፤ ይኸውም በዜማ ትምህርት ቤት ከቃል ትምህርቶች አንደኛው ሆኖ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

መጽሐፈ ስንክሳር ይህንን ሊቅ፡- አምሳሊሆሙ ለሱራፌል፤ የሱራፌል አምሳላቸው ይለዋል፡፡ ከመላእክት ወገን የሆኑት ሱራፌል እግዚአብሔርን ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ በመንበሩ ፊት ቆመው እንደሚያመሰግኑ ሁሉ ቅዱስ ያሬድም ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያለ በመላእክት ቋንቋ እግዚአብሔርን አመስገኗልና፤ ደግሞም የተማረው ከእነርሱ ነውና የሱራፌል አምሳላቸው ተባለ፡፡ እርሱም፡- ሃሌ ሉያ ዋይ ዜማ ዘሰማዕኩ በሰማይ እመላእክት ግናይ እንዘ ይብሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር መልዐ ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ስብሓቲከ፤ ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን! ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር፤ የምስጋናህ ስፋት ሰማይና ምድርን መላ፤ /ኢሳ.፮፥፫/እያሉ ሲያመሰግኑ ከመላእክት የሰማሁት ምስጋና ምንኛ ድንቅ ነው? በማለት ዜማውን የተማረው ከመላእክት መሆኑን በድርሰቱ መስክሯል፡፡

ከዚያ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ከዓመት እስከ ዓመት ድረስ በየክፍለ ዘመኑ በክረምትና በበጋ፣ በመጸውና በጸደይ፣ በአጽዋማትና በሰንበታት፣ እንዲሁም በመላእክት፣ በጻድቃን፣ በሰማዕታት፣ በደናግል በዓላት የሚደረስ ቃለ እግዚአብሔር በሦስት ዜማዎች ማለትም በግእዝ፣ በዕዝልና በአራራይ ደረሰ፡፡ የሰው ንግግር፣ የአዕዋፍ፣ የእንስሳትና የአራዊት ጩኸት ሁሉ ከነዚህ ከሦስቱ ዜማዎች እንደማይወጡ መጽሐፈ ስንክሳር ይናገራል፡፡

በአንዲት ዕለት ቅዱስ ያሬድ ከብሉይና ከሐዲስ፣ እንደዚሁም ከሊቃውንትና ከመነኮሳት የተውጣጣውን መንፈሳዊ ድርሰቱን በዘመኑ ከነበረው ከንጉሥ ገብረ መስቀል ፊት ቆሞ ሲዘምር ንጉሡ በድምፁ በመማረኩ የተነሣ ልቡናው በተመስጦ ተሠውሮበት (የሚያደርገዉን ባለማወቁ) የቅዱስ ያሬድን እግር በጦር ወጋው፡፡ ከቅዱስ ያሬድ እግር ደምና ውኃ ቢፈስስም ነገር ግን ማኅሌቱን እስኪፈጽም ድረስ ሕመሙ አልተሰማውም ነበር፡፡

ንጉሡም ያደረገዉን ሁሉ ባወቀ ጊዜ ደነገጠ፤ ጦሩንም ከእግሩ ነቅሎ ስለፈሰሰው ደምህ ዋጋ የምትፈልገዉን ሁል ለምነኝ እያለ ተማጸነው፡፡ ቅዱስ ያሬድም ላትከለክለኝ ማልልኝ ብሎ ቃል ካስገባው በኋላ ወደ ገዳም ሔዶ ይመነኩስ ዘንድ እንዲፈቅድለትና እንዲያሰናብተው ለመነው፡፡ ንጉሡም ከመኳንንቱ ጋር እጅግ አዘነ፤ ተከዘ፡፡ ከእርሱ እንዲለይ ባይፈልግም ነገር ግን መሐላዉን ማፍረስ ስለከበደው እያዘነ አሰናበተው፡፡

ከዚያም ቅዱስ ያሬድ በአክሱም ጽዮን ቤተ መቅደስ በታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ፡- ቅድስት ወብፅዕት ስብሕት ወቡርክት ክብርት ወልዕልት አንቀጸ ብርሃን መዐርገ ሕይወት፤ ፈጽሞ የከበርሽና የተመሰገንሽ፣ ከፍ ከፍም ያልሽ፣ የብርሃን መውጫ የሕይወት ማዕረግ የሆንሽƒ‚ƒƒ‚ እያለ አንቀጸ ብርሃን የተባለውን የእመቤታችን ምስጋና እስከ መጨረሻው ድረስ ደረሰ፡፡ ይህንን ጸሎት ሲያደርስም አንድ ክንድ ያህል ከመሬት ከፍ ብሎ ይታይ ነበር፡፡ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሔዶ (ሰሜን ተራሮች አካባቢ) በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያው ፈጸመ፡፡ እግዚአብሔርም ስሙን ለሚጠራ፣ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው፤ ከዚያም በሰላም ዐረፈ፡፡ /ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር፣ ግንቦት ፲፩/

የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በገድለ ቅዱስ ያሬድ ላይና በመጽሐፈ ስንክሳር እንደመዘገቡልን ግንቦት ፲፩ ቀን ቅዱስ ያሬድ ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድ ያረፈበት ቀን ነው፤ እዚህ ላይ ግን አከራካሪ ጉዳይ አለ፤ ይኸውም አንደኛው ቅዱስ ያሬድ ሞቶ ተቀብሯል የሚል ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ቅዱስ ያሬድ እስከነ ነፍሱ ተሠወረ እንጂ አልሞተም የሚል ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ሞተ የሚሉ ወገኖች ከሚጠቅሷቸው ማስረጃዎች ውስጥ በመጽሐፈ ስንክሳር፡- ወበዛቲ ዕለት አዕረፈ ያሬድ ማኅሌታይ፤ በዚህች ዕለት ማኅሌታይ ያሬድ ዐረፈ፤ እና ወእምዝ አዕረፈ በሰላም፤ ከዚህ በኋላ በሰላም ዐረፈ የሚሉት ሐረጋት የሚገኙ ሲሆን፣ ተሠወረ የሚሉት ደግሞ እዚያው ስንክሳሩ ላይ፡- ወእምዝ ሖረ ሀገረ ሰሜን ወነበረ ህየ ወፈጸመ ገድሎ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሒዶ ገድሉን በዚያ ፈጸመ፤ ተብሎ የተገለጸውን እንደማስረጃ ይጠቅሳሉ፡፡

በእርግጥ ቃሉን በትኩረት ለተመለከው ሰው ዐረፈ ማለት ሞትን ብቻ ሳይሆን እንደነ ሄኖክ ከዚህ ዓለም ጣጣና እንግልት ተለይቶ በሕይወት እያሉ (ሳይሞቱ) ተሠውሮ መኖርንም ያመለክታል፡፡ ገድሉን በሰሜን አገር ፈጸመ የሚለውም መሠወሩን ብቻ ሳይሆን መሞቱንም ሊያመለክት ይችላል የሚሉም አሉ፡፡ ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን መምህራን እንደሚያስተምሩን እነእገሌ ቀበሩት የሚል ቃል ስለማይገኝ ቅዱስ ያሬድ ተሠወረ እንጂ ሞተ ተብሎ አይነገርለትም፡፡ ለዚህም ማስረጃ እርሱ በተሠወረበት ተራራ እስከ አሁን ድረስ የከበሮ (የማኅሌት) ድምፅ ይሰማል፤ የዕጣን መዓዛ ይሸታል፡፡ ይህም ቅዱሱ ከሰው ዓይን ተሠውሮ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እንደሚገኝ አመላካች ነው፡፡

የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶችም ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለአገርም ድንቅና ወደር የሌላቸው ሀብቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም የዜማ ድርሰቶቹ (ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ ምዕራፍ፣ ዝማሬ፣ መዋሥዕት) እንደሌሎቹ ቅርሶች ሁሉ በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ከፍተኛ ርብርብ በያደርጉ መልካም ነው፡፡ በቅዱስ ያሬድ ዜማ የሚደምቀው በዓለ ጥምቀት በዩኔስኮ ሲመዘገብ ዜማውን ከበዓሉ ለይቶ ማስቀረት የታሪክ ተወቃሾች ያደርገናልና ሁላችንም እናስብበት እንላለን፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በአባታችን በቅዱስ ያሬድ ጸሎት ይማረን፡፡ በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘለዓለም ትኑር፤ አሜን፡፡

የማኅበሩ መልእክት

የካቲት 14 ቀን 2008 ዓ.ም

በሚመስለን ከተጨባጩ፤ በመላምትም ከእውነታው አንጣላ

በአሁኑ ወቅት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ባሉ አማኞችም ሆነ በሀገራችን ውስጥ ባሉ ዜጎች መካከል ልዩነቶችን አጉልቶ በማሳየት የመጠቃቃትን ስሜት ለመፍጠር የሚጣጣሩ መኖራቸውን ለመታዘብ የተለየ ጥናት የሚጠይቅ ነገር አይደለም፡፡ በተለያየ መንገድ የምንሰማቸው ዜናዎችና ወሬዎችም ከዚህ የራቁ አይደሉም፡፡ ምንም እንኳ ልዩነት ተፈጥሮአዊ እስከሚመስል ድረስ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም ውጤቱ ግን እንደየዘመኑ የማኅበረሰብና የተቋማት መሪዎች አቅም እንደ ማኅበረሰቡም ግንዛቤ ይለያያል፡፡

የማኅበረሰብና የተቋማት መሪዎች ለሚመሩት ማኅበረሰብ እንደ አንድ ጤነኛ ሰው ጭንቅላት የሚታዩ ሲሆን የተለያዩት የማኅበረሰብ አካላትን በአንድ አካል ውስጥ እንዳሉ ብልቶች በማዋሐድና ጤንነታቸውንም በመጠበቅ ልክ እንደ አንድ ጤናማ ሰው ሙሉ ጤነኛ አካል አድርገው ይመሯቸዋል፡፡ ውሕደታቸው፣ መናበባቸው፣ መረዳዳታቸውና መተባበራቸውም ልክ በአንድ ጤነኛ ሰው እንዳሉ የተለያዩ ብልቶች ይሆንና ከልዩነታቸው የሚጎዱ ሳይሆን በልዩነታቸው የሚያጌጡና የሚጠቀሙ ይሆናሉ፡፡ የማኅበረሰቡ አካላትም እንደዚያው ጤነኛ ብልቶች ከሆኑ ለራሳቸውም ሆነ ብልት ለሆኑለት አካል ጠቃሚዎች ይሆናሉ፡፡ በሽተኞች ሲሆኑም ፈጥነው ሕክምና ካላገኙና ካልዳኑ ጉዳታቸው በእነርሱ ሳይወሰን መላው አካልን ይጎዳሉ፤ ሕመሙ ሲከፋም የጋራ ሞትን ያስከትላሉ፡፡ ስለዚህም በሰውነታችን እንደምናየው፣ «አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳል´ ከሚሉት ዓይነት አባባሎችም እንደምንረዳው እያንዳንዱ ብልት ለሌላው ጤንነት የድርሻውን ይወጣል፡፡ ይህ መሆን ካልቻለ ለሁሉም የሚደርስባቸው ጉዳት ታላቅ ይሆናል፡፡ ብልቶች ከተለያዩ ውጤቱ የአካል መለያየትና የሁሉም የሰውነት አካል የጋራ ሞት እንደሆነ የታወቀ ነውና፡፡

ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስለ ሰው ልጆች ማኅበራዊ ሕይወት ጤንነትም ሆነ በውስጧ ስላለው መንፈሳዊ አገልግሎት ልጆቿን ከምታስተምርበትም ሆነ ዓለምን ከምትመክርበት፤ ተቋማዊ ሂደቷንም ከምትመራባቸው መንፈሳዊ አስተምህሮዎችና መርሆዎች አንዱና ዋናው ይህንኑ የሚከተል እንደሆነ ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆርንቶስ ምእመናን በላካት የመጀመሪያይቱ መልእክት ላይ የሚከተለውን ብሏል፡-

አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤ አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል። አካል ብዙ ብልቶች እንጂ አንድ ብልት አይደለምና። እግር፦ እኔ እጅ ስላልሆንኩ የአካል ክፍል አይደለሁም ብትል፥ ይህን በማለትዋ የአካል ክፍል መሆንዋ ይቀራልን? ጆሮም፦ እኔ ዓይን አይደለሁምና የአካል ክፍል አይደለሁም ቢል፥ ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን? አካል ሁሉ ዓይን ቢሆን መስማት ወዴት በተገኘ? ሁሉም መስማት ቢሆን ማሽተት ወዴት በተገኘ? አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ ብልቶችን እያንዳንዳቸው በአካል አድርጎአል። ሁሉም አንድ ብልት ቢሆንስ አካል ወዴት በሆነ? ዳሩ ግን አሁን ብልቶች ብዙዎች ናቸው አካል ግን አንድ ነው። ዓይን እጅን፦ አታስፈልገኝም ልትለው አትችልም፥ ወይም ራስ ደግሞ እግሮችን፦ አታስፈልጉኝም ሊላቸው አይችልም። /1ኛ ቆሮ 12 ፥ 12 – 21/

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሰፊው ግልጽ አድርጎ እንዳስቀመጠው፡- በሀገራችን በኢትዮጵያ የምንገኝ ሁላችን ራሳችን ለራሳችን የሰጠነው የተለያየ ማንነት ቢኖርም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ልዩነታችን እንደ ዓይን እና ጆሮ፣ እጅ እና እግር ወይም እንደ ልብና ኩላሊት ከመሆን ያለፈ አይደለም፡፡ አንዳንዶቻችን የተስማማንን ማኅበረሰባዊ የማንነት መለያዎች ለራሳችን ብንሰጥና በዚያም መለያ ብንመደብ እንኳ ካወቅንበት ይህ ልዩነታችን በአንድ አካል ውስጥ እንዳሉ ብልቶች በየተሰጠን ጸጋ፣ ሙያና ችሎታ የምንጠቃቀምበት የምንከባበርበት እንጂ የሚጎዳን ሊሆን አይችልም፡፡ በመጀመሪያ በተፈጥሮ ሰው ሆነን በመፈጠራችን ልዩነት የሌለን መሆኑን ማስታወስ ነው፡፡ ያም ባይሆን ደግሞ ልዩነትን እንደተፈጥሮ ጸጋ ብንወስደው እንኳ ይህ የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳ አይደለም፡፡

ቅዱሱ ሐዋርያ በደንብ እንደገለጸው ዓይን እጅን አታስፈልገኝም ልትለው የማትችለውን ያህል በሀገራችንም አንዱ ሌላውን የኅብረተሰብ ክፍል አታስፈልገኝም ቢለው ተፈጥሮአዊ አይደለምና ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ምንም እንኳ ጥርስ ምላስን እንደሚነክሰው፣ እግርም እግርን እንደሚረግጠው ወይም እጅ እጅን እንደሚያቆስለው ካለበለዚያም ጣትም ዓይንን እንደሚያስለቅሰው ሁሉ በቀደመው ታሪካችን አልፎ አልፎ የእርስ በርስ ወይም የብልት ከብልት መጎዳዳት ተከስቶ የነበረ መሆኑ ቢታወቅም ይህም ከልዩነት የተነሣ ብቻ ሳይሆን ከተፈጥሮም ጠፍቶ የማያውቅ በመሆኑ በብልቶቻችን ዘንድ በእንደዚህ ዓይነት ምክንያት እስከመጨረሻው መለያየት ሆኖ እንደማያውቀው ሁሉ ራሳችን ሆን ብለን ካልፈቀድንለት በስተቀር እኛንም እንዲህ ዓይነት ታሪካዊ ምክንያቶች ሊለያዩን አይችሉም፡፡ ምክንያቱም እጅ ዓይንን ብቻ ሳይሆን እጅንም የሚጎዳ መሆኑ እንዲህ ያለ ጉዳት የእርስ በርስ መሆኑንም እንድንረዳ ፈጣሪ የሰጠን የማስተዋል ወይም የመመርመሪያ መንገድ ይመስለናልና፡፡

ስለዚህም ታሪካዊ ክስተቶችን እያነሣንና እየጣልን በቁስል ላይ ቁስል ከምንጨምር ይልቁንም በአንድ አካል እንዳሉ ብልቶች የቆሰለውን የማዳን እንጂ ያልቆሰለውን የማቁሰልን ተግባር ልንጸየፈው ይገባናል፡፡ ምንአልባት በሰዎች ዘንድ ቅዱሱ ሐዋርያ እጅን ወይም እግርን አታስፈልጉኝም የሚል ዓይን ወይም ጆሮ ሊኖር አይችልም እንዳለው በእኛም ዘንድ ይህ ሊሆን አይገባውም፡፡ መስሎን የምንል ሰዎች ካለንም መናገር በመቻላችንና ይህንኑንም አብዝተን በማለታችን ምክንያት ግን የአካል ክፍል አድርገን ያልቆጠርነው ክፍል አካል አለመሆን አይችልም፡፡ እንኳን በሌሎቹ በራሳችንም ላይ ቢሆን እንዲህ ያለው ነገር የምንናገረውን ያህል ቀላል፣ ጉዳቱም ለሌሎቹ ብቻ ሊሆን አይችልምና ደጋግሞ መመርመሩ ነገሮችንም በእውነት ማጤኑ በእጅጉ አስፈላጊ ይመስለናል፡፡

ስለዚህም ነገሮችን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በገለጸውና የሕይወታችን መመሪያ በሆነው መንገድ እንድንመረምራቸውና በሌሎች አካላትም ይሁን በራሳችን ስሜት ተገፋፍተን ለእኛ ምንአልባትም ጠቃሚ ከመሰለን፣ ነገር ግን ደግሞ በእውነት ጠቃሚ ካልሆነው ነገር እንድንድንና አንዳችን ለሌላችን ጠቃሚዎች እንድንሆን የሚከተሉትን ነገሮች እንድናጤናቸው ያስፈልጋል፡፡

1.የሚመስለንን አንመነው፤ ይልቁንም እንመርምረው፡፡

በቅዱስ መጽሐፍ ተደጋግመው ከተገለጹልን ነገሮች አንዱ የሚመስለንን ነገር ይዘን እንዳንቀመጥ ነው፡፡ እንኳን እንዳሁኑ አስመሳይ በበዛበት ዓለም ውስጥ እየኖርን ቀርቶ በንጽሕና በቅድስና በሚኖሩትም ዘንድ ይህ ፈተና የሚሆን መሆኑን ዐውቀን እንድንጠነቀቅ ብዙ ጊዜ ተጽፎልናልና፡፡ ለምሳሌ ያህል በሃይማኖት ዐዋቂዎች መምህራን ነን ብለው ከሚኖሩት ብዙዎቹ የራሳቸው መንገድ ብቻ ትክክል መስሏቸው ከኖሩ በኋላ ጌታ አላውቃችሁም ሲላቸው እነርሱ እንደሚያውቁትና ራሱንም ሳይቀር በአንተ ስም አይደለም ወይ ይህን ተአምር ያደረግን እያሉ እንደሚከራከሩትም ራሱ ጌታችንም አስቀድሞ አሳስቧል /ሉቃ 13 ፥ 25/፡፡ ከዐሥሩ ደናግልም አምስቱ ማሰሮ በመያዛቸው ብቻ የሚጠቀሙ ይመስላቸው እንደነበር ነገር ግን በማሰሮው ውስጥ የሚያስፈልገውን ዘይት ይዘው ባለመገኘታቸው የሠርጉ ታዳሚ ሳይሆኑ እንደቀሩ ተጽፎልናል /ማቴ 25 ፥ 1-10/፡፡ እንዲሁም መክሊቱን የቀበረውም ሰው የተሻለ ያደረገና በጌታው ዘንድ የበለጠ የሚመሰገን ይመስለው ነበር፤ ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቀረ፡፡ /ማቴ 25 ፥ 14-30/፡፡ እኒህ ሁሉ የገጠማቸው ከመሰላቸው በተቃራኒው ነው፡፡ ምክንያቱም በመሰላቸው እንጂ በሚሆነውና በእውነታው አልኖሩምና፡፡

ከላይ በጠቀስነው መልእክትም ላይ ቅዱስ ጳውሎስ ነገር ግን ደካሞች የሚመስሉ የአካል ብልቶች ይልቁን የሚያስፈልጉ ናቸው፤ ከአካልም ብልቶች ያልከበሩ ሆነው የሚመስሉን በሚበዛ ክብር እናለብሳቸዋለን፥ በምናፍርባቸውም ብልቶቻችን ክብር ይጨመርላቸዋል /1ኛ ቆሮ 12 ፥ 22 – 23/ ሲል እንደገለጸው የሚመስለን ከእውነታው ብዙ ጊዜ ሊራራቅ እንደሚችል ማሰብና መመርመር ከነባራዊ እውነትም ጋር መታረቅና መስማማት ለሁላችንም ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ነገሮችን በአግባቡ ሳይመረምሩና በአግባቡ ሳያጠኑ ወይም በስሜታቸው ተገፋፍተው የሚቀሰቅሱንን እየሰማን ለራሳችን ባለንና በሰጠነው ማንነት ላይ ተመሥርተን ሌሎች የማያስፈልጉ ከመሰለን በእጅጉ እንሳሳታለን፡፡ እንደ እውነታው ከሆነ ሁላችንም ብንሆን አንዳችን ለሌሎቻን የምናስፈልግና የምንጠቅም መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡

ነገሩን በጽድቅና በኩነኔ ብቻ ሰፍረን የእኛ ያጸድቃል የሌሎች ያስኮንናል ብለን ብናምን እንኳ በዚች ምድር ላይ ለመኖር ግን አንዱ ለሌላው አስፈላጊ መሆኑ ሊታበል አይችልም፡፡ ምክንያቱም የሃይማኖት ውጤቱ በሰማይ (በፈጣሪ በሚሰጥ ፍርድ) የሚገለጽ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን በምድርም ፈጣሪ ለሁሉም ፀሐይ በማውጣቱ ዝናም በማዝነሙና ሁሉንም በመመገቡ የፈቀደለትን እኛ በጉልበትና በግጭት ልናጠፋው እንደማይገባን ብቻ ሳይሆን እንደማንችልም መረዳት አስፈላጊ ነውና፡፡ ስለዚህም ልዩነትን ምክንያት በማድረግ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሚፈጸሙ አብያተ እምነቶችን ማቃጠል፤ በአንድ አካባቢ በቁጥር አነስ ያሉና የተለየ ማንነት ያላቸውን ማሳደድ፣ ማፈናቀልና መጉዳት ለጊዜው ማሸነፍ ቢመስልም እውነታው ተቃራኒው ሊሆን እንደሚችል ማሰብና በመከባበርና በመረዳዳት መኖሩ ሊጠቅም እንደሚችል ማስተዋሉ በእጅጉ ያስፈልገናል፡፡ ስለዚህም በሃይማኖትና በብሔር ከመጣላት ራስን ብቻም የተለየ አስፈላጊና ጠቃሚ ሌላውን ደግሞ ጎጂና የማይረባ፣ አንዳቻንን አሳቢ ሌላውን ማሰብ የማይችል፤ አንዱን ተሸካሚና ሌላውንም ሸክም አስመስለው ከሚያቀርቡ የልዩነት ሐሳቦች ራስን ማቀብ በእጅጉ ያስፈልጋል፡፡ የሚመስለን ሁሉ እውነታ ላይሆን ይችላልና፡፡

ስለዚህም አሁን በሀገራችን ውስጥ ያለው የብሔር፣ የቋንቋም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት እንደ አካል አቅፋ በያዘችን ሀገር ውስጥ በሰላም ለመኖር የሚያስቸግረን አይደለም፡፡ ልዩነቶቻችን የሚጎዱን ወይም ጉዳት ያስከተሉብን ቢመስለን እንኳ እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ መመርመርና በመከባበር መኖር ይገባናል፡፡ በመለያየት የምንጠቀም የሚመስለው ካለም ሐሳቡን እንደገና ቢያጤንና ቢመረምር ይሻላል እንላለን፡፡

2.የማኅበረሰብ መሪዎች የጭንቅላትን ሓላፊነት ቢወጡ መልካም ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች እያጋጠሙ ያሉትን ችግሮች በአግባቡ ለመወጣትና በአካል ውስጥ እንዳሉ ብልቶች ተከባብሮ ለመኖር ማኅበረሰቡን የሚመሩ አካላት ሓላፊነትና ድርሻ ትልቅ መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ስለዚህ መንግሥታዊ የሆኑም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና የማኅበረሰብ መሪዎች ሁሉ በዚህ ጊዜ እንደ ጭንቅላት ሆኖ ማኅበረሰቡን እንደ ብልት ማዋሐድና የሀገርንም ሆነ የሕዝብን ጤንነት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የሚወስዱ ግጭቶችን መፍታት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች አማኞቻቸውን ሃይማኖት የታከከ ግጭት እንዳያስነሡና በዚህም ወዳልተፈለገ ሀገራዊ ቀውስ እንዳይገባ የመጠበቅ ሓላፊነት አለባቸው፡፡ ይህን ማድረግ እስካልተቻለ ድረስ ሁላችንም በተግባር ከመጎዳታችን በላይ በታሪክና በትውልድ ተጠያቂዎች እንሆናለን፤ መውጫውን በማናውቀው ገደልና የችግር አዙሪት (vicious circle) ውስጥም ስንዳንክር ልንኖር እንችላለን፡፡ ስለዚህም ነገሮቹን ሁሉ በአግባቡ የማየት ታሪካዊና ሰብአዊ ሓላፊነት እንዳለባቸው ተገንዝበው በፍጥነት የሚቻላቸውን ሁሉ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ ሁላችንም ብንሆን ደግሞ በጠባብ ሐሳቦች፣ በቅርብ ጥቅሞችና ጠንካራና እውነት በሚመስሉ ነገር ግን ደካማና ስሕተት በሆኑ ትንታኔዎች ተይዘን እንዳንታለል ችግሮችንም እንዳናሰፋ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

3.ማኅበረሰባዊ መስተጋብሮችን ሊያናጉ የሚችሉ ልዩነቶችን ከማጉላት ችግሮችንም ከማስፋት መቆጠብ

እያንዳንዳችን እንደግለሰብም ሆነ እንደተቋም የምንኖርበት ዓለም ከሌሎቹ ጋር አንድ ስለሆነ ከግጭት፣ ከልዩነትና ከመሳሰሉት ነጻ የመሆን እድላችን በእጅጉ አነስተኛ ነው፡፡ ሆኖም ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት ችግሮችን የሚያዩበት፤ የሚተረጉሙበትና እርሱንም የሚያስረዱበትም ሆነ አቋም የሚይዙበት መንገድ ጉዳዩንና ችግሩን ወይ ይፈታዋል ካለበለዚያም ሊያባብሰው ይችላል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ብዙ አካላትን የጥቃት ሰለባ እያደረጋቸውና ማኅበረሰባዊ ቀውሱንም እያባበሰው ያለው የችግሮች በሆነ አካባቢና ዓውድ መከሰታቸው ሳይሆን ከተጨባጭ እውነታው የራቀው መረዳታችን (Perception) እና አንዳንዴም አርቆ አሳቢና ተቆርቋሪነት ያለባቸው የሚመስሉ ትናታኔዎቻችንን መሠረት አድርገን በመጓዛችን ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም ታሪክ ቀመስ ጉዳዮችን እየጠቀስን እርስ በርስ ከምንወራከብባቸው ብዙ ጉዳዮች መረዳት ይቻላል፡፡

ትላንት አሁን ያለው ትውልድ ባልነበረበት፣ እንዳሁኑ ዘመንም ሁሉም ነገር በመረጃ በማይታይበትና ባልተሰነደበት፣ አብዛኛዎቹም ነገሮች አሁን ያለው አካል ነቅፎም ሆነ ደግፎ በሚከራከርላቸው አቋሞች መሠረት ሆነ ተብለው የተደረጉ በማይመስሉ በዚያ ባለፈው ዘመን ክስተቶች ይህን ያክል ውርክብና እሰጥ አገባ ውስጥ ገብተን ከተቸገርን አሁን ራሳችንን አዋቂ አድርገንና ሆነ ብለን እወቁልኝና ስሙልኝ እያልን ብዙ ሚዲያዎችን ተጠቅመን በምናደርጋቸው ነገሮችማ ምን ያህል ችግሮችን ልንፈጥር እንደምንችል መገመት የሚያስቸግር አይመስለንም፡፡ ስለዚህም ምንም እንኳ ሰው ዓላማዬ ብሎ ለያዘው ነገር የሚችለውን ያህል መሥዋዕትነት እስከመክፈል መታገሉ የሚጠበቅ ቢሆንም ለማሸነፍ ወይም ተቆርቋሪና አለኝታ መስሎ ለመታየት በሚደረግ ሩጫ ግን ሳናውቀው ችግሮችን ከእውነታውና ከከባቢያዊ ዓውዳቸው አውጥተን ስሜታችንን በሌሎች ላይ በመጫን ልዩነትን እንዳናሠፋ ችግሮቻችንንም እንዳናውሰበስባቸው ስጋት አለን፡፡ ይህ ማለት አጥፊዎች አይጠየቁ ችግሮችም አይነሱ ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡

አሁን የምናያቸው አብዛኞቹ ግጭቶች ግን ስለትላንት በምናወራው ላይ ሰሚዎቻችን ተናጋሪዎቹን አምነው የሚወስዷቸው አጸፌታዊ እርምጃዎች እንደሆኑ ይደመጣል፡፡ ስለዚህ ስላለፉትም ሆነ አሁን ስላሉት ነገሮች ስንነጋገርና ስንከራከር ዞሮ ዞሮ አንድነታችንን በሚያጠናክር ሓላፊነቱንና ተጠያቂነቱን ባልዘነጋ መልኩ ቢሆን መልካም ይሆናል፡፡ እውነታዎችን ሁሉ እርግጠኞች መሆን እስከምንችል ብናውቅ እንኳ በማወቃችን ብቻ አላስፈላጊ ነገሮችን ላለማድረግ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሁሉን ከመደረጉ በፊት የሚያውቀው ጌታችንም የይሁዳን የማታለልና የማሳመጽ ተግባር ለሚወዱትና ለሚከተሉት ሐዋርያት እንኳ ቶሎ አልገለጸላቸውም፡፡ በዚህም እውነቱን በማወቃችን ብቻ የአንድን ነገር ውጤት ሳናስብና ጉዳቱን ሳንመረምር አፋችን እንዳመጣ ያለጊዜው እንዳንናገር አስተማረን፡፡ ስለዚህም በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በሀገር ደረጃ የምናያቸው ችግሮች ከተፈጠሩ በኋላ ስሜታዊ መሆን አያስፈልገንም፡፡ ይልቁንም ደጋግመን እንደገለጽነው መኖራቸውን ተቀብለን መፈጠራቸውንም እውቅና ሰጥተን ከስሜትና ከችኮላ ተላቅቀን የራሳችንን ትርጉምና መረዳት ብቻ እንደ እውነት ቆጥረን ከመንቀሳቀስ መቆጠብ፣ ካለፈው የተሻልን ሆነን፣ ችግሮቹን ከማስፋት ወደ ማጥበብ መጓዝ ይኖርብናል፡፡ ይህንንም ለማድረግ ጉዳዮችን በጥልቀት መመርመርና ማጥናት በመፍትሔዎቹም ላይ በመደማመጥ መወያየት ያስፈልጋል፡፡

4.በራሳችን የሓላፊነት ስፍራ ውስጥ ብቻ ሥራችንን መሥራት

በአሁኑ ወቅት ችግሮቻችንን እያሰፉና በየአቅጣጫው የሴራ ትንታኔዎች ገዝፈው ሰዎችን በመረዳታቸው መጠን የራሳቸውን እርምጃ በመውሰድ ችግር ውስጥ እንዲገቡ ከሚገፉ ነገሮች፣ ዋነኛው ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት የእነርሱ ባልሆነ ቦታ ውስጥ የሚፈጽሙት ደባና ተንኮል ይመስለናል፡፡ ምንም እንኳ በፖለቲካዊ ዓለም ይህ አሠራር ራሱን የቻለ ሳይንሳዊ ዘዴ ያለው ስልት ቢሆንም በተለይ በእምነት ተቋማት ግን አደገኛና ትልቅ ችግር አምጭ መሆኑን ለመረዳት የሚያስቸግር አይመስልም፡፡ ለዚህም እንደ ምሳሌ ራሳቸውን “ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ” ብለው የሚጠሩ አካላት እየፈጠሩ ያሉትን ችግር ሁሉም አካል በአግባቡ እንዲገነዘበው መሪዎቻቸውም ይህንኑ ሓላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

ራስን ችሎ በሚያምኑበት ሃይማኖት መመራትና ማምለክ እየተቻለ፤ በነባሯና በጥንታዊዋ ሃይማኖት ውስጥ ሠርጎ በመግባትና እራስን ደብቆ ችግሮችን በማባባስ የፈለጉት ቦታ ለመድረስ የሚቻል ቢመስልም፤ እውነታው ከዚህ ሩቅ መሆኑን ተገንዝቦ መሔድ ወቅቱ የሚፈልገው መፍትሔ ነው፡፡ ለራስ የተለየ ግምት በመስጠት ሁሉን ማድረግ እንደሚቻል በማሰብ የተለያዩ የተንኮልና የማስመሰል ዘዴዎችን ተጠቅሞ ችግር ለመፍጠር መሞከር እውነታውን አይለውጥም፡፡ ለአንዳንድ ሞኞችም ተንኮል ጥበብ፣ እብሪትም አሸናፊነት ቢመስላቸውም እውነታው ሁልጊዜም የተለየ ነው፡፡ መፍቀሬ ጥበብ ሰሎሞን ታካች ሰው በጥበብ ከሚመልሱ ከሰባት ሰዎች ይልቅ ለራሱ ጠቢብ የሆነ ይመስለዋል /ምሳ 26፥16/ እንዳለው የተጠበብንና የተራቀቅን ቢመስለንም ሞኝነታችን የተገለጠ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እጥላለሁ ተብሎ ተጽፎአልና። ጥበበኛ የት አለ? ጻፊስ የት አለ? የዚች ዓለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚችን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን? /1ኛ ቆሮ 1 ፥ 19 – 21/ እንዳለው በከንቱ ከመድከም ያመኑበትን በይፋ ይዞ በራስ ቦታ ተወስኖ በመሔድ በግልጽ የማስተማርም ሆነ የማምለክ ነጻነቱ ስላለ ይህንን ሓላፊነት መወጣት አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ሽንገላዎች፣ ጥበብና ቻይነት የሚመስሉ ተንኮሎች፣ ችግሮችን አውሰብስበው ራስን ከመጉዳት በቀር የሚያመጡት ጠቀሜታ አይኖርም፡፡

በቤተ ክርስቲያናችን በሓላፊነት ያሉ አካላትም የታመመውን ብልት እያከሙ እያዳኑ የአካልን ጤንነት መጠበቅ ግዴታቸው መሆኑን እንደማይዘነጉት እሙን ነው፡፡ ሆኖም አንዳንዱ በሽታ የበከለው ብልት በሕክምና የማይድንና ሌላውንም ቀስ በቀስ እያጠቃ አካልን የሚጎዳው፣ መላ ሰውነትንም የሚያጠፋ ከሆነ ደግሞ፣ እርሱን እንደ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በጊዜው ቆርጦ ሌላውን አካል ማዳን አሁንም ጭንቅላት ከተሰኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የተለያዩ ሓላፊዎች የሚጠበቅ ተግባር መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡ ካለበለዚያ ጭንቅላትን ጨምሮ መላውን አካል ማወኩ ማስጨነቁና ብሎም ለሞት መዳረጉ አይቀርምና ሓላፊነትን በአግባቡና በጊዜው መወጣት ይጠይቃል እንላለን፡፡

በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት ያሉብንን ችግሮች በሰከነ መንገድ በአግባቡ መፍታት ከሁላችንም የሚጠበቅ ተግባር ሆኖ ይታየናል፡፡ ልዩ ልዩ መንግሥታዊ አካላት፤ ልዩ ልዩ የማኅብረሰብ መሪዎች ሁሉ በሰከነ መንገድ የጭንቅላትነት ማለትም የማሰብ ሁሉንም ብልት የመጠበቅ የመንከባከብና የአካል መለያየት እንዳይኖር ነቅቶ የመጠበቅ ታሪካዊ ሓላፊነታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል የሚል እምነት አለን፡፡ በተለይም ልዩነቶቻችን እንደ ሰውነት ብልቶች ከመጠቃቀሚያነት ወደ መደባደቢያነትና ጎሳን ብሔርን ቋንቋንና ሃይማኖትን መሠረት አድርጎ ግጭት ውስጥ እንዳይገባ ሓላፊነትን በአግባቡ መወጣት የሁሉም ድርሻ ሊሆን ይገባል፡፡ ካለበለዚያ አንድ ብልት ያመጣው በሽታ መላው አካልን እንደሚጎዳው ሰውነትንም እንደሚያጠፋው ጥፋቱ ለሚመሩት አካል ጭንቅላት ለሆኑትም እንደማይቀር አስበን ካልሠራን ጉዳቱ አይቀርልንም፤ ከእውነታው ጋርም እንደተጣላን እንቀራለን፡፡ ስለዚህ አስቀድመን ከሚመስለንና ከግምታችን ወጥተን እውነቱን እንያዝ ከሚሆነውም አንቃረን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

የተሐድሶ መናፍቃን ድፍረት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ለመቀልበስ እስከ መሞከር

ባለፉት ተከታታይ ዕትሞች ስለ ተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ የትኩረት አቅጣጫዎች፣ ስልትና ግብ ማቅረባ ችን ይታወቃል፡፡ በዚህ ዕትም ደግሞ ተሐድሶ መናፍቃን ጥፋታቸውን አምነ ውና ተጸጽተው ከመመለስ ይልቅ የቅ ዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ካለመቀበል አልፎ ውሳኔዎችን ለማስቀልበስ እስከ መሞከር ድረስ የሚያደርጉትን ከንቱ ሩጫ እናቀር ባለን፡፡ መልካም ንባብ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ ብዙ ፈተና ዎችን እንዳሳለፈችና ፈተናዎቹ መልካ ቸውን እየለዋወጡ ራሳቸውን የሚደ ግሙ እንጂ አዲሶች እንዳልሆኑ ባለፉት ጽሑፎች ተመልክተናል፡፡ በዚህ ክፍለ ዘመን ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ ፈተና የሆኑት ተሐድሶ መናፍቃን አስተም ህሯቸውና ዓላማቸው ፕሮቴስታንታዊ ሆኖ ሳለ ኦርቶዶክሳዊ ነን በማለት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብተው ብዙ የዋሀ ንን ከበረታቸው ለማስወጣት እየሠሩ ነው፡፡ የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በዋናነት የቤተ ክርስቲያን ምንጮችን በመለየት፣ ምንጮቹ ውስጥ ሠርጎ በመ ግባት፣ አስተምህሮ በመቀየርና የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር በመቆጣጠር ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ ለመረከብ፣ መረከብ ካልቻሉ ደግሞ እንደ ሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለመክፈል የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፡፡ በተሐድሶ መናፍቃን የቤተ ክርስቲያን የእምነትና የመንፈሳዊነት ምንጮች ተብለው ለጥፋት ተልእኳቸው ዒላማ የተለዩት ደግሞ የአብነት ትምህርት ቤቶች (የሊቃው ንተ ቤተ ክርስቲያን መፍለቂያ ስለሆኑ)፣ ገዳማት (የሊቀ ጳጳሳትና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መፍለቂያዎች ስለሆኑ)፣ መንፈሳዊ ኮሌጆች (የስብከተ ወንጌል ሓላፊ ዎችና የመምህራን መፍለቂያዎች ስለ ሆኑ)፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶች (ወጣቶ ችንና ምእመናንን ለማግኘት የተመቹ መድረኮች ናቸው ብለው ስላሰቡ) እና የቤተ ክርስቲያን መዋቅር (ድጋፍና ሽፋን ለማግኘት ይጠቅመናል ብለው ስላሰቡ) ናቸው፡፡
ቤተ ክርስቲያንም የተሐድሶ መና ፍቃንን እንቅስቃሴ ለመግታት በተለያዩ ጊዜያት ተኩላዎችን ከበጎች የመለየት ሥራ ሠርታለች፡፡ በተለይም ምእመናንን የመጠበቅ ሓላፊነት ያለበት ቅዱስ ሲኖ ዶስ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጋቸው ጉባ ኤያት ላይ የተሐድሶ መናፍቃንን መሰሪ አካሔድ ተረድተን እንድንጠነቀቅ ያላሳሰ በበት ጊዜ የለም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ቅዱ ሳን ሐዋርያት በአመክንዮአቸው “እኛስ የሃይማኖት ለዋጮችን ግብር እንጸለየ ፋለን” ብለው ባስቀመጡት መመሪያ መሠረት የተሐድሶ መናፍቃንን ኑፋቄ ነቅሶ በማውጣትና የሃይማኖት ለዋጭ ነት ግብራቸውን በማውገዝ መመለስ የፈለጉትን ተመክረው፣ ቀኖና ተሰ ጥቷቸው፣ መምህራን ተመድበውላ ቸው እንዲማሩና ወደ ቤተ ክርስቲ ያን አንድነት እንዲጨመሩ፤ ቀኖናውን ለመቀበልና ለመማር ፈቃደኛ አንሆንም፣ ርትዕት ወደሆነችው ሃይማኖትም አንመለስም ያሉትን ደግሞ ከቤተ ክር ስቲያን አንድነት እንዲለዩ አድርጓል፡፡ በተለይም በ፲፱፻፺ ዓ.ም እና በ፳፻ወ፬ ዓ.ም የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮን የሚጠብቁ ሳይሆኑ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ነን በማለት ሲያደናግሩ የነበሩ ተሐድሶ መናፍቃን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ተወግዘዋል፡፡ የተሐድሶ መናፍቃን አቀንቃኞችን በማውገዝ ብቻ እንቅስቃሴውን መግታት እንደማይቻል የተረዳው ቅዱስ ሲኖዶስ የተሐድሶ መናፍ ቃን ምንጫቸው ምንድን ነው የሚለ ውን ለማወቅ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ባለሙያዎችን ያካተተ ሁሉን አቀፍ የሆነ ጥናት አጥንቶ የሚያቀርብ ኮሚቴ ሠይሞ ቅዱስ ሲኖዶስ በበላይ ነት እየመራና መመሪያ እየሰጠ ጉዳዩ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ክትትል እያደረገ ነው፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ በተለይም ከ፳፻ወ፬ ዓ.ም ጀምሮ የተሐድሶ መናፍቃንን ጉዳይ ዋና አጀንዳ አድርጎ በየጉባኤው ሲወያ ይበት እንደነበር የቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ጉባኤያት ያሳያሉ፡፡ ጉባኤው በመደበኛ ጉባኤያቱ ላይ ተሐድሶ መናፍቃን በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ሠርገው በመግባት ጥፋት እያደረሱ እንደሆነና እንቅስቃሴው በሁሉም አህጉረ ስብከት የሚታይ መሆኑን አስቀምጧል፡፡ በዚህ መነሻነት የተሐድሶ መናፍቃን መገኛ ምንጫቸው ከየት እንደሆነ ለመለየት ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡ በውይይቱም ተሐድሶ መናፍቃን ሠርገው በመግባት ብዙ ጥፋት እያደረሱባቸውና ኦርቶዶክሳ ውያን ልጆችን መናፍቅ ለማድረግ ትኩ ረት አድርገው ከሚሠሩባቸው የቤተ ክርስቲያን ተቋማት መካከል መንፈሳዊ ኮሌጆቻችንም የሚገኙበት በመሆናቸው በእነዚህ የቤተ ክርስቲያን የትምህ ርት ተቋማት ላይ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ በማለት ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ስለዚህም የመንፈሳዊ ኮሌጆች የተማሪ አቀባበል፣ የትምህርት አሰጣጥ፣ የመም ህራን ማንነትና ምንነት እንዲሁም የማስተማሪያ መጻሕፍት ሊፈተሹና ሊመረመሩ እንደሚገባቸው በመግለጽ ጉዳዩን በጥልቀት አጥንቶ የሚያቀርብ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ አቋቁሞ እየሠራ ይገኛል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ጉዳዮችን አስቀድሞ በማየትና ብፁዓን አባቶች በየአህጉረ ስብከታቸው እየተካሔዱ ያሉ እንቅስቃሴዎችን መነሻ በማድረግ በተሐድሶ መናፍቃን ላይ ውሳኔዎች ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ከምእመናን የሚ መጡ ጥቆማዎች በተሐድሶ መናፍቃን ላይ ለሚሰጣቸው ውሳኔዎች ትልቅ ግብዓት ሆነው አገልግለዋል፡፡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም በየአህጉረ ስብከታቸው እንዲሁ በተሐድሶ መናፍቃን ላይ እር ምጃዎችን ለመውሰድ በራሳቸው ክት ትል ከሚደርሱባቸው እውነታዎች በተ ጨማሪ ከሕዝበ ክርስቲያኑ የሚመጡ ጥቆማዎችን በግብዓትነት ይጠቀማሉ፡፡
ተሐድሶ መናፍቃን ከጊዜ ወደ ጊዜ ሥውር ዓላማቸውን ዕውን ለማድረግ በቤተ ክርስቲያን ላይ እያካሔዱት ያለው የጥፋት እንቅስቃሴ በሁሉም ሕዝበ ክርስቲያን ዘንድ እየታወቀ መጥቷል ብለን እናምናለን፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በተሐ ድሶ መናፍቃን ላይ በየጊዜው የሰጣቸው ውሳኔዎች ምእመናን ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ከማድረጉም በላይ እንቅስቃሴ ውን ለመግታት የራሳቸውን ሓላፊነት እንዲወጡም አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑ በተሐድሶ መናፍቃን ላይ ያለው ግንዛቤና በእንቅስቃሴው አደገኛነት ላይ ያለው መረዳት ማደጉ በጉዳዩ ላይ ያገባኛል የሚል ስሜት እንዲ ያሳድር አድርጓል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስና የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ውሳኔዎች ያበረ ታቷቸው ምእመናን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ እየተ ካሔደ ያለውን የውስጥም ሆነ የውጪ ሴራ የማክሸፍ እንቅስቃሴን የራሳቸው ጉዳይ አድርገው እንዲሠሩ እገዛ አድር ጎላቸዋል፡፡ የተሐድሶ መናፍቃንን እንቅስ ቃሴ ሥውር ዓላማና ቤተ ክርስቲያ ንን የማፍረስ ተልእኮ ጠንቅቀው የተረዱ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ማኅበራት፣ ምእመናን እና ወጣቶች መረጃዎችን ስለ እንቅስቃሴው በቂ ግንዛቤ ለሌላ ቸው ምእመናን ለማዳረስ ያደረጉት ጥረት ከፍተኛ ነው፡፡ እነዚህ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው መከታተላቸው እና መረጃው የሌላቸውን ምእመናን ለማንቃት ሰፊ እንቅስቃሴ ማድረጋቸው የተሐድሶ መናፍቃንን መሰሪ ተግባር በማጋለጥ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡
ተሐድሶ መናፍቃን በየቦታው የሚያ ደርጉትን ሥውር እንቅስቃሴ በማጋ ለጥ፣ መረጃዎችን በማሰባሰብ ለሚመለ ከታቸው አካላት በማቅረብ፣ ስለ እንቅስ ቃሴው አደገኛነት ግንዛቤ መፍጠሪያ መርሐ ግብራትን በማዘጋጀት እውነቱ ከሐሰቱ እንዲለይ በማድረግ ትልቅ ሥራ ሠርተዋል፡፡ ግንዛቤ መፍጠሪያ መርሐ ግብራቱ አብዛኛው ምእመናን የቤተ ክርስቲያንን መምህራን የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡ ነጣቂ ተኩላዎች ለይ ተው እንዲያውቁ አድርገዋል፡፡ በዚህ መነሻነት ብዙ ምእመናን የተሐድሶ መና ፍቃንን ሥውር ሴራ በመገንዘብ በግ ልም በማኅበርም በመደራጀት እንቅስቃ ሴውን ለመግታት እየተጉ ይገኛሉ፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ በተለያዩ ጊዜያት የሰጣቸውን ውሳኔዎች እና አቅጣጫ ዎች መሠረት በማድረግ ብዙ አህጉረ ስብከት የተሐድሶ መናፍቃንን ዓላማ አንግበው በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ሠርገው በመግባት ምእመንን የሚያደናግሩ ክፉዎች ሠራተኞችን ከአገልግሎታቸው አግደዋል፡፡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በየአህጉረ ስብከታቸው ለተሐድሶ ዓላማ አስፈጻሚ የሆኑት ልብ ገዝተው መመለስ ለሚፈልጉት ቀኖና በመስጠት እንዲታረሙ፣ ለመመ ለስ ፈቃደኛ ላልሆኑት ደግሞ ተወግ ዘው እንዲለዩ በማድረግ የኖላዊነት ሓላፊነታቸውን በመወጣት አርአያና ተጠቃሽ የሚሆን ተግባር አከናውነ ዋል፡፡ ምእመናንን ከሐሰተኞች መምህ ራን የመጠበቅ ሓላፊነት ያለባቸው ብፁ ዓን ሊቃነ ጳጳሳትና የየሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች በተለይም ከ፳፻ወ፬ ዓ.ም ወዲህ በአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤያት ላይ በዚህ ዘርፍ የተሠሩ ሥራዎችን በሪፖርታቸው ያላቀረቡ በት አጋጣሚ የለም፡፡ በሪፖርታቸው በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ሠር ገው በመግባት የቤተ ክርስቲያንን እን ጀራ እየበሉ የሉተርን ዓላማ ለማስፈ ጸም የሚሠሩ ተሐድሶ መናፍቃንን በማ ጋለጥና አንዳንዶችንም ከአገልግሎት በማገድ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን መፈ ጸም መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡ ሪፖርቱ በሚቀርብበት ወቅት ከተሰብሳቢዎች ይቀርብ የነበረው ድጋፍ የሚያሳየው ተሐድሶ መናፍቃን በሁሉም ቦታ የሚያ ካሒዱት ቅሰጣ ምን ያህል የሚያሳምም እንደሆነ እና እንቅስቃሴውን ለመግታት የሚሠሩ ሥራዎች ደግሞ በተሰብሳቢ ዎች ዘንድ ምን ያህል ተስፋ ሰጪ ዎችና አስደሳቾች እንደሆኑ ማሳያ ነው፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ኮሌጆችን የከፈተችው ሐዋርያዊ አገልግ ሎቷ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ ነው፡፡ በእነዚህ መንፈሳዊ ኮሌጆች ተም ረው እስከ ጵጵስና መዓርግ ደርሰው ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ የነበሩ፣ በማገልግል ላይ የሚገኙ አባቶች አሉ፡፡ ዛሬም ቢሆን በመናፍቃን ስውር ዘመቻ ከአማናዊቷ እምነት ፈቀቅ ያሉና በኑፋ ቄያቸው ከቤተ ክርስቲያን አንድነት የተለዩ አንዳንድ ግለሰቦች እና ጥቂት ደቀ መዛሙርት ቢኖሩም በርትዕት ሃይ ማኖት ጸንተው የተሐድሶን ስውር ደባ ሲታገሉ የነበሩና እየታገሉ የሚገኙ ጽኑዐን ደቀ መዛሙርት በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ መኖራቸው ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ተሐድሶ መናፍቃኑ መንፈሳዊ ኮሌጆችን “የእኛ ዓላማ ማስፈጸሚያ ናቸው”፤ ከመንፈሳዊ ኮሌጆች ተመርቀው የሚወጡ ደቀ መዛሙርትን ደግሞ “በሙሉ ልባችን እንቀበላቸዋለን”፣ ወዘተ በማለት እነዚህን የቤተ ክርስቲያ ናችንን ተቋማት ምእመናን እንዲጠራጠ ሯቸውና እንዲሸሿቸው፣ ከፍሬያቸውም በንጹሕ ልብ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የሚቻላቸውን ሁሉ ሲሠሩ እደኖሩ ይታወቃል፡፡ ተሐድሶ መናፍቃን ይህን እኩይ ተግባር ቢፈጽሙም መንፈሳዊ ኮሌጆች አሁንም የብዙ ሰባክያነ ወንጌል መፍለቂያዎች፣ የብዙ እውነተኛ መም ህራን መገኛዎች መሆናቸውን መረዳት ይገባል፡፡ ስለዚህ ምእመናንም ሁሉንም በጅምላ ከመጠራጠር ርቀን በፍሬያ ቸው ታውቋቸዋላችሁ እንደተባለ በትም ህርታቸው መለየት ይኖርብናል፡፡ ሁሉ ንም በጅምላ መጥላት ከጀመርን ግን ሳናውቀው የተሐድሶ መናፍቃንን ዓላማ እያስፈጸምንላቸው መሆኑን መረዳት ተገቢ ነው፡፡
ሆኖም ግን በእነዚህ ኮሌጆች ውስጥ ኦርቶዶክሳውያን መስለው ገብተው ብዙ ጥፋት እያደረሱ ያሉ፣ መንፈ ሳዊ ኮሌጆች ውስጥ ተምረው ያለ ፉና በመማር ላይ ያሉ ኑፋቄ ያለባ ቸው ደቀ መዛሙርት እንዳሉ በተለያዩ ጊዜያት መናፍቅነታቸው ታውቆ ከመን ፈሳዊ ኮሌጆች የተባረሩና በቅዱስ ሲኖ ዶስ ምልዐተ ጉባኤም ተወግዘው የተ ለዩ ግለሰቦች ማስረጃዎች ናቸው፡፡ በመ ንፈሳዊ ኮሌጆቹ ውስጥ የመናፍቃን ተላላኪዎች መሆናቸው የተረጋገጠባ ቸው ተማሪዎች ከመንፈሳዊ ኮሌጆች ሲባረሩ ጉዳዩን ፖለቲካዊ መልክ በመስ ጠት ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመ ለስ ቢሞክሩም የየተቋሞቹ የቦርድ አመራሮች እስከ መጨረሻ ድረስ በመከ ታተል ውሳኔው እንዲጸና በማድረግ አኩሪ ተግባር ፈጽመዋል፡፡ ይህም ሊደ ገፍ፣ ሊበረታታና በአርአያነት ሊጠቀስ የሚገባው ተግባር ነው፡፡ ተሐድሶ መናፍ ቃን በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ ሊሠ ሩት ያቀዱትን ሴራ በማክሸፍ በኩል ከተሐድሶ መናፍቃን ጋር አንገት ለአን ገት ተናንቀው መረጃ በማሰባሰብ አደራ ጅተው ለየኮሌጆቹ አስተዳዳር በማቅረብ መንፈሳዊ ኮሌጆችን ከሠርጎ ገቦች ለመጠበቅ በአርአያነት የሚጠቀስ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙ ደቀ መዛሙርት አሉ፡፡ እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ልጆች መንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ የራሳቸውን ሥውር ዓላማ ለማሳካት የሚሠሩ ተሐ ድሶ መናፍቃንን በማጋለጥና ተገቢው ውሳኔ እንዲሰጣቸው ለማድረግ መረጃ ዎችን ከማሰባሰብ ጀምሮ ያደረጉት ተጋ ድሎ በጊዜው የሚገኝ ጥቅምን ንቆ ዘለዓ ለማዊ ርስትን በመናፈቅ ከመናፍቃን ጋር ብዙ ተጋድሎዎችን ፈጽመው ያለፉ ቅዱሳን አበውን አርአያነት የተከተለ ነው፡፡ መንፈሳዊ ኮሌጆችን የሚመሩ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና የተቋማቱ ሓላ ፊዎችም በኦርቶዶክሳዊ ተማሪዎች መካከል በተሐድሶ መናፍቃን አቀነባባ ሪነት ሠርገው የገቡ መናፍቃንን ለመለ የት በየጊዜው ብዙ ሥራዎችን ሠርተ ዋል፡፡ የመንፈሳዊ ኮሌጆች ቦርዶችም በተለያዩ ጊዜያት የመናፍቃን ዓላማ አስፈጻሚ የሆኑ ግለሰቦች ላይ የቀረቡ መረጃዎችን መርምረው ኑፋቄያቸው በመረጃ የተረጋገጠባቸውን ከመንፈሳዊ ኮሌጆች እንዲባረሩ አድርገዋል፡፡
ተሐድሶ መናፍቃን እስካሁን ድረስ “ኦርቶዶክሳውያን ነን”፣ “የጥንታዊ አባቶች ልጆች ነን”፣ “ቤተ ክርስቲያንን ወደ ጥንታዊ አስተምህሮዋ እንመልሳ ለን”፣ ወዘተ የሚሉ የማደናገሪያ ቃላ ትን በመደርደር የዋሀንን ሲያታልሉ ቆይተዋል፤ አሁንም በማታለል ላይ ናቸው፡፡ “ወደ እግዚአብሔር መሔጃ መንገዱ ብዙ እንጂ አንድ ብቻ አይደ ለም”፣ “ሁላችንም የምናመልከው የተሰ ቀለውን አንድ ኢየሱስ ነው”፣ ወዘተ በማለት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና በፕሮቴስታንት መካከል የአስተምህሮ ልዩነት የሌለ ለማስመሰል ብዙ ጥረዋል፡፡ ቅድስትና ሐዋርያዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋ ሕዶ ቤተ ክርስቲያንም እነዚህ አካላት “ቤተ ክርስቲያንን እናድሳለን” በሚል ሰበብ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ሥርዓት እና ትውፊት በመቀየር ወይም በመቀየጥ ፕሮቴስታንታዊ ለማድ ረግ የሚሠሩ መሆናቸውን በመግለጽ ለሕዝበ ክርስቲያኑ አሳውቃለች፤ እያሳ ወቀችም ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያንን አስ ተምህሮ ለመቀየር ደፋ ቀና ሲሉ የነ በሩ ተሐድሶ መናፍቃን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ተወግዘው ከቤተ ክርስቲ ያን አንድነት የተለዩ ቢሆንም አሁንም ራሳቸውን ቀሲስ፣ መምህር፣ ዲያቆን፣ ወዘተ እያሉ በመጥራት ስለሚያደናግሩና ከአንዱ ቦታ ሲነቃባቸው ወደ ሌላ ቦታ በመሔድ ስውር ተልእኳቸውን እየፈ ጸሙ ስለሆነ ቅዱስ ሶኖዶስ ከውሳኔው በተጨማሪ አፈጻጸሙን ሊያጤነው ይገ ባል እንላለን፡፡
የሁሉም አካላት መተባበር ዓላማ ቸውን እንደሚያከሽፍባቸው የተረዱት ተሐድሶ መናፍቃን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰ ጣቸውን ውሳኔዎች የማጣጣልና ቤተ ክርስቲያንን የማቃለል ሥራዎችን ለዚሁ ዓላማ ማስፈጸሚያ በከፈቷቸው ድረ ገጾች ሲያስተጋቡት እንደቆዩ በሁሉም ዘንድ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህ ደግሞ አቅ ጣጫ በማስቀየርና በማዘናጋት የፈለጉ ትን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም የሚጠቀሙበት ስልት ነው፡፡ እነዚህ አካላት መናፍቅነታቸው ተረጋግጦ ተወ ግዘው ከቤተ ክርስቲያን መለየታቸው፣ ከአገልግሎት መታገዳቸው እና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ሴራቸው መገለጡ ተሳስተ ናል እንመለስ እንዲሉ አላደረጋቸውም፡፡ ይህን በማለት ፋንታ በተለያዩ ድረ ገጾቻ ቸው ላይ ውሳኔውን በሰጠው በቅዱስ ሲኖዶስ ሲሳለቁና ቤተ ክርስቲያንን ሲሳደቡ ቆይተዋል፡፡ በድርጊታቸው አፍ ረው ከመመለስና ከመጸጸት ይልቅ ቤተ ክርስቲያንና ቅዱስ ሲኖዶስን በማቃለል ምእመናን በብፁዓን አባቶች ላይ ያላ ቸው እምነት እንዲጠፋና ጥርጣሬ እንዲ ያድርባቸው ማድረግን እንደ ሥራ ተያ ይዘውታል፡፡ ይህ ድርጊታቸው ተሐ ድሶ መናፍቃን ምን ያህል ክፉ መንፈስ እንደተቆጣጠራቸውና እግዚአብሔርን እንደ አምላክነቱ ስላላከበሩት ለማይገባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው የሚለው የመጽሐፍ ቃል እየተፈጸመባቸው እን ደሆነ ማሳያ ነው፡፡ የድፍረታቸው ድፍ ረት በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያንን የሚመራት መንፈስ ቅዱስ ሳይሆን ግለሰ ቦች ናቸው በማለት ምእመናንን ከቤተ ክርስቲያን ለማስወጣትና የቅዱስ ሲኖ ዶስን ውሳኔ እንዳይቀበሉ ለማድረግ ብዙ ብለዋል፡፡ በተለይም አባ ሰላማ፣ ጮራና ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሚባሉት ድረ ገጾቻቸው ቅዱስ ሲኖ ዶስ ያወገዛቸውን ተሐድሶ መናፍቃንን በመደገፍና ቅዱስ ሲኖዶስንና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን በማቃለል ድፍረት የተሞሉ ጽሑፎችን የሚያወጡባቸው የስድብ አፎቻቸው ናቸው፡፡
ተሐድሶ መናፍቃን በ፳፻ወ፬ ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የተላለፈ ውን ውሳኔ ተከትለተው አባ ሰላማ በሚ ባል ድረ ገጻቸው ላይ “ተወጋዦች አው ጋዦች፣ አውጋዦች ተወጋዦች የሆኑ ባት ቤተ ክርስቲያን” በሚል ርእስ ባወ ጡት ጽሑፍ ላይ ቤተ ክርስቲያንን እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን እንዲህ በማ ለት ነበር የተሳደቡት፡-
ባለፉት ፳ ዓመታት ተወግዘው የተ ባረሩ ሁሉ በሕጋዊ አካል ተወግዘው የተባረሩ አይደሉም። በሕገ ወጦችና በማያስወግዝ ምክንያት በሕገ ወጥ መንገድ «የተወገዙ» ናቸው። የሕግ የበላይነት ባልሰፈነባትና ሁሉም አዛዥ በሆነባት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መወገዝ የሚገባቸው ሰዎች መወገዝ የማይገባቸ ውን ሰዎች ሲያወግዙ ኖረዋል። ይኸው አሠራር አሁንም ቀጥሏል። ቤተ ክር ስቲያኗ ምን ያህል እንደዘቀጠች፣ ምን ያህል አንቱ የሚባል ሰው እንደታጣ ባት፣ ምን ያህል ከክርስቶስና ከሐዋር ያት፣ እንዲሁም ከሠለስቱ ምእት ትምህርት እንደራቀች ያሳያል።
“በረከታችሁም ሆነ ውግዘታችሁ ማንንም አያድንም፣ አይገድልምም” በሚል ርእስ በጻፉት ሌላኛው ጽሑፋ ቸው ደግሞ ከሐዋርያት ጀምሮ ባልተቋረጠ ሐዋርያዊ ክትትል ሥልጣነ ክህ ነት ያላቸውን ሊቃነ ጳጳሳት በማቃ ለልና ከተሐድሶ መናፍቃን በማሳነስ፡-
አንድ መንፈሳዊ ሥልጣን የሌለ ውና ለመንፈሳዊ ሥልጣንም የማይገዛ ስመ መንፈሳዊ የመናፍስትና የሙታን ጠሪ ስብስብ አንድ መንፈሳዊ የወን ጌል አገልጋይ የማውገዝም ሆነ የመለ የት ሥልጣን የለውም። አቅም ያንሰዋል! ኃይል ያለው ሥራ ለመሥራት በጥቂ ቱም ቢሆን ኃይል ያስፈልጋል። ይህ ማለት በሌላ አገላለጽ ሥጋ የሥጋን ሥራ ከመሥራት በዘለለ በመንፈሳዊ ዓለም ላይ አሁንም በድጋሜ እጽፈዋለሁ አንዳች ሥልጣን የለውም።
በማለት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንደማይገዙ ብቻ ሳይሆን ቅዱስ ሲኖ ዶስ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን ያለው አካል እንዳልሆነ አድርገው ጽፈዋል፡፡ በዚሁ ለጥፋት ዓላማ በከፈቱት አባ ሰላማ በሚባለው ድረ ገጻቸው ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶሱ በ፳፻ወ፯ ዓ.ም በተሐድሶ መናፍቃን ላይ የወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ “ክርስቶስን የምታሳድድ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ቤተ ክርስቲያን ትሆና ለች?” በሚል ርእስ “ሲኖዶሱ በአንድ በኩል ፍልሰት በዝቶአል እያለ ሲናገር በሌላ በኩል ደግሞ ወንጌል እየሰበኩና ሕዝቡን ከፍልሰት እየገቱ ያሉ አገልጋዮ ችን ማሳደድ ሥራየ ተብሎ ተይዟል” በማለት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ አጣጥ ለውታል፡፡
ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በሚለው ድረ ገጻቸው ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ ከሐዋርያት እውነት የራቀ ለቅዱሳን የጸጋ ስግደት ይገባል ብላ የምታስተምር ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን መና ፍቅ፣ ራሳቸውን ደግሞ ጻድቃን አድር ገው ቅዱስ ሲኖዶስም ቅዱሳን የሆኑ እነርሱን እያሳደደ መናፍቅ የተባሉ ኦርቶ ዶክሶችን እንደሚደግፍ በዚህ መልክ አቅርበዋል፡፡
ሲኖዶሳችን እውነትን እንደ ሐዋርያት ቢያውቅና ቢከተል ኖሮ እነዚህን ለማርያም፣ ለመስቀል፣ ለታቦት፣ ለሥ ዕል [የጸጋ ስግደት] መስገድ አይገባም ብለው የሚሟገቱ ሰዎችን ስም በማክ ፋት መናፍቅና ጸረ-ማርያም ብለው በሥ ቃይ እንዲሞቱ ያደረጉ ጸረ-ኦርቶዶክስ አቋም ይዘው ዘወትር በኦርቶዶክስ ተዋ ሕዶ ጥላ ሥር የሚነግዱ መናፍቃንን እሺ ቢሉ በትምህርት ይመልስልን፣ እንቢ ቢሉ ደግሞ በውግዘት ይለይልን ነበር፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ሲኖዶሳ ችን መናፍቃንን በመደገፍ ጻድቃንን ያሳድዳል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ፳፻ወ፯ ዓ.ም መደበኛ ጉባኤው ላይ ስለ ተሐድሶ መናፍቃን በተያዘው አጀንዳ ላይ በተ ወያየበት ወቅት ከችግሩ አሳሳቢነት አንጻር ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰፋ ያለ ጊዜ ተሰጥቶት ጥናቱን በጥልቀት አጥንቶ እንዲያቀርብ በወሰነበት ወቅት “ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶን ከመቀበል ይልቅ ለማጥናት ኮሚቴ የማቋቋሟ አንድምታ” በሚል ጽሑፍ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያሰቡት ዓላማቸው እንዳይከሽፍባቸው ቅዱስ ሲኖዶስን በመቃወም እንዲህ ጽፈዋል፡፡
ከታሪክ መማር የተሳነው ቅዱስ የተባለው ሲኖዶስ ለአስፈላጊውና ለጠቃ ሚው የተሐድሶ እንቅስቃሴ ሌላ ስም በመስጠትና በቤተ ክርስቲያን ሌላ ትልቅ አደጋ ጋርጧል በሚል በማኅ በረ ቅዱሳን ከሳሽነት ሕጋዊም፣ መንፈ ሳዊም፣ ሞራላዊም፣ ሕሊናዊም አካሔድን ባልተከተለና ግብታዊነት በተሞላው መንገድ ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም ውግዘት አስተላለፈ፡፡ … በዚህ ዘመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስ ቲያንንና ሃይማኖትን ከተሐድሶ አራማ ጆች ትምህርት ለመጠበቅ በሚል ተሐ ድሶ ሲል የፈረጃቸውን ወገኖች በማሳ ደድና በማውገዝ ተግባሩ ገፍቶበታል፡፡ ስለተሐድሶ እንዲያጠኑ በሚል ሰዎች ንም ጠቅላይ ቤተክህነት መድቧል፡፡ ጥናቱ አስፈላጊ ሊሆን ቢችልም ትኩ ረቱ ግን ተሐድሶን ለማጥፋት የሚል መሆኑ ቤተክህነቱ አሁንም በእንቅልፍ ላይ እንደሚገኝ የሚያሳይ ነው፤
በ፳፻ወ፬ ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ከተወገዙት ግለሰቦች መካከል አሸናፊ መኮንን፣ አግዛቸው ተፈራና ጽጌ ሥጦ ታው ውግዘቱን በመቃወም ስላስገቡት “የይግባኝ ደብዳቤ” ሲያትቱ ደግሞ፡-
የግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ቤተ ክርስ ቲያንን የዓለም መሳቂያና መሳለቂያ በማድረግ ያዋረደበትን ውሳኔ ማሳ ለፉ ይታወሳል፡፡ ይህን የራሱን ክብር የቀነስበትን፣ በታሪክ ተወቃሽ የሚያደ ርገውንና ብዙዎችን ያሳዘነውን፣ የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት ባልተከ ተለና፣ በየትኛውም መስፈርት ሲመዘን ሕገ ወጥ ሆኖ የተገኘውን ውግዘት፣ «ተወጋዦቹ» እየተቃወሙት ነው፤ በማለት ጽፈዋል፡፡
ውሳኔውን የተሳሳተና ሕገ ወጥ በማድረግ ቅዱስ ሲኖዶስም ቤተ ክርስ ቲያንን የዓለም መሳቂያና መሳለቂያ እንድትሆን ያደረጋት አስመስለው ጽፈ ዋል፡፡ በእርግጥ ይግባኝ አቅራቢ የተባ ሉት ተወጋዦችም ያስገቡት ደብዳቤ በአባ ሰላማ ድረ ገጽ እንደወጣው ይቅ ርታ ይደረግልን ወይም ተሳስተናልና እንታረም የሚል ሳይሆን በጽጌ ሥጦ ታው አገላለጽ “ያስተማርኩት፣ የጻፍኩ ትና የተናገርኩት ሁሉ ስሕተት መሆ ኑን ስላመንኩ ይህን ሁሉ ስሕተቴን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቶልኝ ይቅርታ እንዲያደርግልኝና ትምህርቱን እንድ ማር ይፈቀድልኝ ዘንድ በታላቅ ትሕ ትና አመለክታለሁ የሚል የይቅርታ [አሳብ] እንደሌለኝ በድጋሚ አረጋግጣለሁ” የሚል የትዕቢት ደብዳቤ ነው፡፡ ተሐድሶ መናፍቃን በተለያዩ ዘዴ ዎች ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያስተላልፋቸ ውን ውሳኔዎች ሲቃወሙና በቻሉት መጠን ለተቃውሟቸው ድጋፍ የሚሰጡ አካላትን በቤተ ክስቲያን መዋቅር ውስጥ አሥርገው ለማስገባት ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡ ይኸው ዓላማቸው ተሳክቶ ላቸው በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ የቤተ ክርስቲያንን እንጀራ እየበሉ የቅ ዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በፊርማ ለማስ ቆም የሚሠሩ ጥቂት አካላትን ማግ ኘት ችለዋል፡፡ ለዚህም ነው ተሐድሶ መናፍቃን በተለያዩ ድረ ገጾቻቸው የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ አንቀበልም በማለት ከመጻፍ እና ከመሳደብ አል ፈው ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር አሥርገው ባስገቧቸው አንዳ ንድ ግለሰቦች በኩል የቅዱስ ሲኖዶ ስን ውሳኔዎች ለማስቀልበስ እየ ሠሩ ያሉት፡፡
ይህን ዓላማቸውን ዕውን ለማድ ረግ በተለይም በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ አሥርገው ባስገቧቸው አንዳንድ ተልእኮ አስፈጻሚ ግለሰቦች በኩል እነ ርሱ የማይፈልጉትን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ለመቃወም መምህራንን፣ ተመር ቀው የወጡና በመማር ላይ ያሉ የነ ገረ መለኮት ደቀ መዛሙርትን እና ጉዳዩ የማይመለከታቸው የዋሀን ምእመናንን ፊርማ እንዲያሰባስቡላቸው እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ፡፡ ይህም ድር ጊት ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጣቸው መመ ሪያዎችና የሚወስናቸው ውሳኔዎች ተግባራዊ ቢደረጉ ለእንቅስቃሴያቸው እንቅፋት እንደሚሆንባቸው በማመን አቅጣጫ ለማስቀየርና ለማደናገር የሚ ጠቀሙበት ስውር ስልት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን፣ ቅዱስ ሲኖዶስን፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳ ሳትን እንደፈለጋቸው ሲሳደቡ የሚጠ ይቃቸው አካል ባለመኖሩ ምክንያት የልብ ልብ ተሰምቷቸው የሚፈጽሙት የዕብሪት ተግባር ነው፡፡ ተሐድሶ መና ፍቃን መናፍቅነታቸውን በራሳቸው ጽሑ ፎች አውጀው፣ የራሳቸውን የእምነት ድርጅት አቋቁመውና የራሳቸውን የእምነት መግለጫ አውጥተው ቤተ ክር ስቲያንን የማፍረስ ተልእኳቸውን ዕውን ለማድረግ እየሠሩ መሆናቸው እየታ ወቀ “ዐይናቸውን በጨው አጥበው” አሁንም ኦርቶዶክሳውያን ነን በማለት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሠርገው በመግ ባት ሁከት እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ሰላም የማይወዱት እነዚህ አካላት በአንጻራዊ መረጋጋት ላይ ይገኙ የነበሩትን መንፈሳዊ ኮሌጆችን አሥር ገው ባስገቧቸው ጥቂት ተላላኪዎች አማካኝነት በተለያዩ የስድብ አፎቻቸው ሲያጮኹት የኖሩትን ዓላማ ለማሳካት ሊጠቀሙባቸው በስውር በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጠቃ ላይ በቤተ ክርስቲያን ላይ በተለይ በመ ንፈሳዊ ኮሌጆች ላይ የተነጣጠረው የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ አሳሳ ቢና አስጊ መሆኑን ተረድቶ ኮሚቴ አቋ ቁሞ ሥራዎችን መሥራት በጀመረበት በዚህ ወቅት፣ መንፈሳዊ ኮሌጆችም ስንዴ ውን ከገለባው የማጥራት ሥራ ለመሥ ራት በጀመሩበት ጊዜ፣ ሰንበት ትምህ ርት ቤቶችና ወጣቶችም ተሐድሶ መና ፍቃንን በማጋለጥ መረጃዎችን በማሰባ ሰብ ለሚመለከተው አካል እያቀረቡ ባሉበት በዚህ ሰዓት “መናፍቅ የሚባል ነገር የለም” በማለት የቅዱስ ሲኖዶ ስን ውሳኔ ለማኮላሸት ፊርማ የሚያ ሰባስቡ አካላት መነሣታቸው እየተሰማ ነው፡፡ ይህ ድፍረት ከቤተ ክርስቲያን ዓላማ መውጣትና ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳ ኔም አለመታዘዝ ነው፡፡
ተሐድሶ መናፍቃን ቤተ ክርስቲ ያን ውስጥ አንድ ችግር ፈጥረው መዋ ቅሩ ችግሩን ለመፍታት ደፋ ቀና በሚል በት ሰዓት እነርሱ የራሳቸውን ዓላማ ለማሳካት መሯሯጥን ልምድ አድርገው ሲሠሩበት የቆዩት ጉዳይ ነው፡፡ ቅድ ስት ቤተ ክርስቲያን የመልካም አስተዳ ደር እጦት መኖሩን አምና የመልካም አስተዳዳር ችግሮችን ለመቅረፍ መሥ ራት አለብን በሚል በሁሉም አህጉረ ስብከት በሚባል ደረጃ ውይይቶች እየተደረጉና ሥልጠናዎች እየተሰጡ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም በጥቅምት ፳፻ወ፰ ዓ.ም መደበኛ ጉባኤ ባወጣው መግለጫ የመልካም አስተዳደር እጦትና የሙስና መስፋፋት ለቤተ ክርስቲያን ፈተና መሆ ኑን እና የችግሩ መነሻና ምንጭ ይታ ወቅ ዘንድ አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያ ኗን ሁለንተናዊ ችግር የሚያጠና ብፁ ዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ዐቢይ ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የመልካም አስተዳደር ችግር የአ ንድ ተቋም ችግር ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ መዋቅሮች ላይ የሚታይ አጠቃላይ ችግር መሆኑን ወስኖ እያለ ተሐድሶ መናፍቃን የአስተ ዳደር ችግር አለ ሲባል ለራሳቸው ዓላማ በሚጠቅማቸው መልኩ ሌላ ቅርጽ ሰጥተውና ስድብ አስመስለው ጉዳዩን ያስተጋቡልናል ብለው ለሚያስ ቧቸው አካላት ያቀርቡላቸዋል፡፡ ይህን የመናፍቃን ተንኮል ያልተረዱ በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ሓላፊነት ያላቸው አንዳንድ ግለሰቦችም የመልካም አስተዳዳር ችግር አለ መባሉን መናፍቅ ናችሁ የመባል ያህል ይፈሩታል፡፡ ይህ ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ ታምኖበት ለውጥ ለማምጣት እየተሠራበት ያለ መሆኑን ማንም የማይስተው ሐቅ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያንን መልካም ነገር መስማት የማይፈልጉት ተሐድሶ መናፍቃን ግን በቤተ ክርስቲያን ደረጃ የታመነውን እውነት የተለያዩ የቤተ ክርስቲያን ተቋማትን በመምራት ላይ ለሚገኙ አካላት “እንዲህ ተብላችሁ ተሰ ደባችሁ” በማለት የሐሰት ክስ በማቅረብ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ተፈተው ለውጥ እንዳይመጣ ይሠራሉ፡፡
በአጠቃላይ ተሐድሶ መናፍቃን በተለ ያዩ የስድብ አፎቻቸው የሚጮኹትን ጩኸት የሚሰማቸው አካል ባለማግኘታ ቸው ምክንያት ወደ ቤተ ክርስቲያን አሥርገው ባስገቧቸው አንዳንድ አካ ላት በኩል የራሳቸው ድብቅ ዓላማ ያላቸው ጥቂት ግለሰቦችን በማባበል ከውጪ ሆነው ሲጮኹለት የነበረውን ዓላማቸውን ለማስፈጸም ይጠቅመናል ብለው ያሰቡትን ማደናገሪያ ሁሉ ለመጠ ቀም እየሞከሩ ነው፡፡ ይህም ለቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ በመምሰል በየጊ ዜው የሚፈጠሩ ወቅታዊ ጉዳዮችን ተጠ ቅመው አቅጣጫ በማስቀየር ለዓላማ ቸው ማስፈጸሚያነት የሚጠቀሙበት የተለመደ ስልት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን የራሷ ሥርዓትና መዋቅር ያላት፣ ውሳኔ ዎችን የምትወስነው ከሐዋርያት ጀምሮ በተሠራ ሕግና ሥርዓት በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጥንቃቄ እና በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ሆኖ ሳለ ተሐድሶ መናፍቃን የቅዱስ ሲኖዶ ስን ውሳኔ በግለሰ ባዊ ዓላማ ለማስቀ ልበስ እየተሯሯጡ መሆናቸው ጥፋታ ቸውን አምነው ከመመለስ ይልቅ ኑፋ ቄያቸው በቤተ ክርስቲያን ዕውቅና እን ዲሰጠው ለማድረግ መሞከር ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን የመጨረሻው ውሳኔ ሰጪ አካል በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አለመታዘዝ ትዕቢትም ኑፋቄም ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ተሐድሶ መናፍቃን ብዙ የዋሀንን ለማደናገርና ተባባሪ ለማ ብዛት የሚጠቀሙበት ስልት እውነቱ ተደብቆ ሐሰቱ እውነት መስሎ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሠርጎ እንዲገባ ማድረግ በመሆኑ ይህን የጥፋት ተልእኮ ለመግ ታት ሁሉም አካላት ሊተባበሩበት ይገ ባል፡፡ 

አምልኮተ ሰይጣን – ፍጻሜ “ተሐድሶ”?

ባለፉት ተከታታይ ዕትሞች ስለ ተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ አጠቃላይ ሁኔታ እና የትኩረት አቅጣጫዎች እንዳ ቀረብንላችሁ ይታወቃል፡፡ በዚህ ዕትም ደግሞ የተሐድሶ መናፍቃን ግብ ምን እንደሆነ እናስነብባችኋለን፤ መልካም ንባብ ይሁንላችሁ፡፡
እሱባለው በለጠ የተባሉ ጸሐፊ “የገሃነም ደጆች ፕሮቴስታንታዊ ጅሃድ በኢትዮጵያዊነት – ተዋሕዶነት ላይ ሲፋ ፋም” በሚለው መጽሐፋቸው አውሮፓ ውያን፣ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት እንዲሁም የተሐድሶ መናፍቃን የኢት ዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስ ቲያንን ለማጥቃት የፈለጉበትን ምክን ያት ሲገልጡ “ፈረንጆች ሃይማኖታ ችንን ከገደሉ፣ ቅድስት ኢትዮጵያን በባርነት ለመያዝ ቀላል መሆኑን ስለ ሚያውቁ ነው ቤተ ክርስቲያንን የጥ ቃት ዒላማቸው ያደረጓት” (ገጽ ፳፯) ብለዋል፡፡ በተጨማሪም “ሁሉም ወራሪ ዎች ከግራ ይምጡ ከቀኝ፣ በነጮችም ይፈጸሙ በዐረብ/ቱርክ፣ ወረራው በጦር ይሁን ወይም በሐሳብ፣ ሁሉም ወራሪዎች የጥቃታቸው ዋና ዒላማ የሚያደርጓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ነው፡፡ ግን ሁሉም ወራሪዎች ድል የተደረጉት የአንድነትና የነጻነት ምንጭ በሆነችው በዚች መከረኛ ቤተ ክርስቲያን ነው” (ገጽ ፳፫-፳፬) በማለት ጽፈዋል፡፡

ጸሓፊው ባለፉት አምስት መቶ ዓመታት በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ የተቃጡት የውጪ ወረራዎች፣ በነጮች አማካኝነት የተቀሰቀሱ የእርስ በእርስ ጦርነቶች፣ የካቶሊክ ሚሲዮና ውያን ቅሰጣ፣ ኮሚኒስታዊ ርእዮተ ዓለምና ፕሮቴስታንታዊ ዘመቻዎች ሁሉ አንድ ዓይነት እና ጸረ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አቋም ያላቸው ናቸው፡፡ ሁሉም የቅድስት ኢትዮጵያ ተዋሕዶ ሃይማኖትን “በደንቆሮነት”፣ “በጸረ ሕዝብነት”፣ በኋላ ቀርነት”፣ “በጣ ዖት አምላኪነት”፣ በ”ኦሪታዊነት”፣ አሁን አሁንማ የልብ ልብ አግኝተዋልና በይፋ በየቤተ አምልኮውና ማለቂያ በሌላቸው ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ â€Â¦ ልሳኖቻቸው “በሰይጣንነት” ይከሷታል ይላሉ (ገጽ ፳፬)፡፡
ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ ሊያ ሳኩት የፈለጉትን ግባቸውን ሲናገሩ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፡፡ “በእምነታቸው ፍርድ ቤትም የሚጠይቁት አንድ ነገር ነው – የቅድስት ኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የስቅላት ሞት፡፡ ይህም ተፈርዶላቸው፣ የመስቀያ ገመዱን አዘ ጋጅተው፣ የመስቀያ ቦታውን መር ጠው፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን እግር ተወርች አስረው ዐይኖችዋን ሸፍ ነው፣ ከእስር ቤት አውጥተው ወደ መስ ቀያ ቦታ እየነዷት ይገኛሉ፡፡ በዚህ የቅድ ስት ኢትዮጵያ ተዋሕዶ ሃይማኖት ወደ ሞት መነዳት፣ አጃቢ ወታደር በመሆን ብዙ መቶ ሺ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ አስፈጻሚ፣ ካድሬ፣ ጽንፈኛ፣ ጅሀደኛ፣ ፕሮፖጋንዲስት በመሆን እርማቸውን ለመብላት እየተቅበዘበዙ ነው፡፡ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የፕሮቴስታንት ርእዮተ ዓለም ሰለባ ኢትዮጵያውያን ጀሌዎችም â€Â¦ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስ ቲያንን ተዝካር ለመብላት ከወዲሁ እየጓጉ ነው” (ገጽ ፳፬-፳፭) በማለት አስቀምጠዋል፡፡
የካቶሊክና የፕሮቴስታንት ሚሲዮ ናውያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ በየዘመናቱ ብዙ ደክመዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አስይ ዘው ወንጌል እንስበክላችሁ ያሉበት ጊዜ ነበር፡፡ በኀይል ለመደምሰስ መትረየስና ታንክ ባርከው የላኩበትም ጊዜ ነበር፡፡ በዘመናዊ ሥልጣኔ ወደ ፊት እናራምዳ ችሁ ብለው መጥተው በመርዝ ጋዝ እንድናልቅ ያደረጉበት ጊዜ ነበር፡፡ የሞ ከሩት ሁሉ አላዋጣ ብሏቸው ሌላ ዘዴ ሲፈልጉ የፕሮቴስታንት ድርጅቶችን ተገን አድርገው በመግባት ለሆዳቸው ያደሩ “መሪጌታ፣ መነኩሴ፣ ዲያቆን፣ ወዘተ” ነን ባዮችን መጠቀም ቤተ ክር ስቲያንን ለማፍረስ እንደሚጠቅማቸው ተረዱት፡፡ ስለዚህ የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በጦርና በሰይፍ ለማሳካት ያልተቻለውን የምዕራባውያንን ምኞት “በኢትዮጵያዊ ፈረንጆች” ለማሳካት ታልሞ የተነደፈ እንቅስቃሴ ነው፡፡ የመ ጨረሻ ዓላማው ምዕራባውያን የራሳቸ ውን አብያተ ክርስቲያናት” ጭፈራ ቤት እንዳደረጓቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ጭፈራ አዳራሽነት መቀየር፣ ምእመናንን ደግሞ ፍጹም ዓለማውያን (ሴኩላር) በማድረግ ለግብረ ሰዶማዊነትና ለአምልኮተ ሰይ ጣን ማዘጋጀት ነው፡፡ የተሐድሶ እንቅስቃ ሴው ግብ አንድና ብቸኛ ሳይሆን ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር መንግሥት በመለየት የሰይጣን ተገዢዎች በሚያ ደርጉ አስነዋሪ ድርጊቶች ውስጥ ማስገ ባት ነው፡፡ ክርስቶስን እንሰብካለን ብለው የተነሡት ፕሮቴስታንቶች፣ ሚሲዮኖቻ ቸውን እየላኩ እኛን “ወንጌል እናስተ ምራችሁ” የሚሉን የተሐድሶ መናፍቃን የጥፋት አባቶች እየደረሱባቸው ያሉትን እና ሊደርሱባቸው የሚፈልጓቸውን ግቦች እንመልከት፡፡
፩. ዓለማዊነት (Secularism)፡- የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ የመጨ ረሻ ግብ “ክርስትና በልብ ነው” በሚል ፈሊጥ ልባቸው የፈቀደውን ሁሉ ማድ ረግ ነው፡፡ ሃይማኖት የሰው ልጅ አንዱ ማንነቱና ምንነቱ መገለጫ ነው፡፡ ነቢዩ ዮናስ ምንድን ነህ? ሥራህስ ምንድን ነው? ተብሎ ሲጠየቅ “ዕብራዊ ነኝ፤ ሥራዬም ሰማይና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔርን ማምለክ ነው” ብሎ የተናገረው ሃይማኖት የሰው ልጅ ማን ነት መገለጫ መሆኑን ማረጋገጫ ነው፡፡ ሰው ከቀለሙ፣ ከተወለደበት ዘር፣ ከተወለደበት ቦታ በላይ አምኖና ፈልጎ የተቀበለው ሃይማኖት እውነተኛ የማን ነቱ መገለጫ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከፈለ ገው እናትና አባት፣ ከፈለገው ቦታ፣ ከፈለገው ዘር፣ የሚፈልገውን ቀለም ይዞ መወለድ አይችልም፡፡ ይህ በፈቃደ እግዚአብሔር የሚከናወን ስለሆነ ከሰው ልጆች ቁጥጥርና ከአቅማቸው በላይ የሆነ አምላካዊ ጥበብ ነው፡፡ ስለዚህ ሰው ስለ ማንነቱ ሲጠየቅ በትክክል የሚያውቀውና የሚያምንበት ማንነቱ ሃይማኖቱ ነው፡፡ የሰው ሰብእ ናም የሚወሰነው ሊገራው፣ ሊያሸንፈ ውና ሊያስተካክለው በሚችለው በውሳ ጣዊ ማንነቱ እንጂ በሥነ ፍጥረት በተለገሰው ውጫዊ ገጹ አይደለም፡፡
ይህን የሚያውቁ ምዕራባውያን ሰው ውስጣዊ ማንነቱን ረስቶ በውጫዊ ነገሮች ማለትም በአለባበሱ፣ በአመጋ ገቡ፣ በአነጋገሩ፣ ወዘተ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ በመሥራት ላይ ናቸው፡፡ ሃይማኖት በእኛ በደካሞች እጅ ወድቆ የሆነውን ሳይሆን ዋኖቻችን ኖረው ባሳዩን መሠረት ለዓለም ሙት ሆኖ ለክርስቶስ ሕያው መሆን ነው፡፡ ለመጥፎ ነገር ሞቶ ለመልካም ነገር ሕያው መሆን ነው፡፡ ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር ካመነና በእግዚአብሔር ከታመነ (ፍቅረ እግዚአብሔርን እና ፍቅረ ቢጽን ገንዘብ ካደረገ) የእርስ በእርስ ጦርነት፣ ክህ ደት፣ በሌሎች ጉዳት መደሰት፣ ግዴለ ሽነት፣ የሞራል ዝቅጠት፣ ዝሙት፣ ክፋት፣ ወዘተ አይኖርም፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን መብታችንን ለማስከበር ብለን ለምናቋቁማቸው የፍትሕ ተቋማት፣ ራሳችንን ለመከላለክል ብለን ለመሣሪያ መግዣ የምናወጣው ገንዘብ ለበጎ አድራ ጎት ይውል ነበር፡፡ ያደጉ አገራትም የድሀ አገራት ሕዝቦችን ከምድረ ገጽ ለማጥ ፋት የሚያግዙ የበሽታ መፈልፈያ ቤተ ሙከራዎችን ለመገንባት የሚያወጡት ወጪ ለበጎ ዓላማ ቢውል ስንት ድሆ ችን መመገብ በቻለ ነበር፡፡
የምዕራባውያን “ቸርቾች” ከላይ የጠቀስናቸው ችግሮች እንዲፈጠሩና እንዲባባሱ ታላቅ አስተዋጽኦ አድርገ ዋል፡፡ ሰው በጋራ የሚያምነው እውነት እንዳይኖር “ክርስቶስን በገባህ መልኩ ግለጠው/ አምልከው” እየተባለ ግለኝነት የተስፋፋው በፕሮቴስታንት ቸርቾች ነው፡፡ ቸርቾቻቸው የአምልኮ ቦታነታ ቸው ቀርቶ ቡና ቤት፣ ፊልም ቤት፣ ጭፈራ ቤት፣ ሙዚየም፣ የገበያ አዳራሽ ሆነዋል፡፡ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝ አድርጎ በመቀበል ፈሊጥ የተጀመረው እምነት ቤተ ክርስቲያን ባለመሔድና እግዚአብሔር የለም በሚል ፍልስፍና ተደመደመ፡፡ ዛሬ ላይ የካቶሊክም ሆኑ “ካቶሊክ ኢየሱስን ጥላለች” ብሎ ሉተር የመሠረተው የፕሮቴስታንት እምነት ቸርቾች ወደ ፍጹም ዓለማዊነት (Secularism) “አድገዋል”፡፡ ፕሮቴስታን ቲዝም ከእምነት ደረጃ ወጥቶ ወደ ፖለቲካ ርእዮተ ዓለምነት ተሸጋግ ሯል፡፡
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የካቶ ሊክና ፕሮቴስታንት እምነት ተስፋፍ ቶባቸው የነበሩ አገራት ዛሬ ላይ እግዚ አብሔር የለም የሚል ፍልስፍና የሚከ ተሉ ሆነዋል፡፡ ለምሳሌ፡- የራሷን ሕዝብ ኢ-አማኒ አድርጋ አሁንም ድረስ በተለ ያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ስም ወደ ድሀ አገራት በመግባት (በተለይም አፍሪካውያንን) ፕሮቴስታንት በማድረግ የምትታወቀው ስዊድን ከሕዝቧ ቁጥር ፴፬ በመቶ የሚሆነው እግዚአብሔር የለም የሚል ነው፡፡ ፴፱ በመቶው ስለ እምነት ግድ የሌለው ነው፡፡ በፈረንሳይም እንዲሁ ፵ በመቶ የሚሆነው ሕዝብ የእግዚአብሔርን ህልውና የማይቀበል ነው፡፡ በስመ ክርስትና የሚኖሩትም ወደ ቤተ እምነታቸው አይሔዱም፡፡ ለምሳሌ፡- በታላቋ ብሪታንያ ክርስቲያን ነኝ ብሎ የሚያምነው ሕዝብ ፸፪ በመቶ ሲሆን “ቤተ ክርስቲያን” የሚሔደው ሕዝብ ግን 1.4 በመቶ ብቻ ነው፡፡ የሉተር “ሃይማኖት” በተፈጠረባት አገር በጀር መን ፸፪ በመቶ በተመሳሳይ ሁኔታ ክርስቲያን ነኝ ብሎ የሚያምን ሲሆን “ቤተ ክርስቲያን” የሚሔደው ግን 1.2 በመቶ ብቻ ነው፡፡
ዓለሙ በአሁኑ ሰዓት በዘመናዊ ነት ስም ግለኝነትን እያበረታታና ተደ ጋግፎና ተባብሮ የመኖርን መልካም እሴት እያጠፋ ነው፡፡ የሦስተኛው ዓለም አገራት በምግብ፣ በንጹሕ ውኃ አቅ ርቦት፣ በመጠለያ አቅርቦት፣ በመጀመ ሪያ ደረጃ የትምህርት አገልግሎት፣ በጤና አገልግሎት፣ በአጠቃላይ ለመ ኖር በመሠረታዊነት የሚያስፈልጉ ነገሮችን ማሟላት አቅቷቸው በሺ ዎች የሚቆጠሩ ነፍሳት በየቀኑ ይሞ ታሉ፡፡ ያደጉ አገራት ደግሞ እነዚ ህን መሠረታዊ የሥጋ ፍላጎቶች ለማ ሟላት ከሚያስፈልገው ወጪ በዐሥር እጥፍ የሚበልጥ ገንዘብ ለኮስሞቲክ ስና ለውሻ ምግብ ያወጣሉ፡፡ ዓለም አንዱን በቁንጣን ሌላውን በጠኔ መግደል ጠባይዋ መሆኑን ከዚህ ተግባር መረ ዳት ይቻላል፡፡
የሚቀነቀኑ ርእዮተ ዓለሞች (ፌሚ ኒዝም፣ ሊበራሊዝም፣ ሴኪዩላር ሂውማ ኒዝም፣ ወዘተ) እና የሚቀረፁ ሥር ዓተ ትምህርቶች መንፈሳዊነትና ሥነ ምግባራዊ እሴት እንዳይኖራቸው እየ ተደረጉ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በአገራችን እግዚአብሔር የለም የሚል ርእዮተ ዓለም ነግሦ በነበረበት ጊዜ “ሳይማር ያስተማረንን ሕዝብ ማገልገል አለብን” የሚል አስተሳሰብ ነበር፡፡ ይህም የአብ ነት ትምህርቱን እንደ ትምህርት ላለ መቁጠር የምዕራቡን ትምህርት ባጠኑ ልሒቃን መነገር የጀመረ አስተሳሰብ ነበር፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሕፃናት የሚዘጋጁ የመዝናኛ ቁሳቁሶች፣ ለሴቶች የሚዘጋጁ አልባሳት፣ ለሕ ዝብ ዐይን የሚደርሱ ፊልሞችና ማስ ታወቂያዎች፣ ወዘተ በአጠቃላይ መል ካም ሥነ ምግባርን የሚያስረሱ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች እስካሁን ድረስ በተወሰኑ ቡድኖች አነሣሽነት የሚቀነቀኑ ነበሩ፡፡ አሁን ግን “ሃይማኖታዊ መልክ” እየተሰጣቸው በእምነት ድርጅቶች በዓላማ እየተከናወኑ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ተሐድሶ መናፍቃን የኢትዮጵያ ኦርቶዶ ክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማቃ ለልና አስተምህሮዋን ለመንቀፍ ሲፈ ልጉ፡-
ከወንጌል ተልእኮ አንጻር ፋይዳ ያላቸው ባይሆኑም በርካታ የሥነ ጽሑፍ ውጤቶች በኢትዮጵያ ኦርቶዶ ክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተከማችተው ይገኛሉ፡፡ የብዙዎች ዐይን ያላያቸውና ተነበው ያላለቁ ድርሳና ቶቿም ብዙ ናቸው፡፡ ከግዝፈታቸው የተነሣ ለዐራት ተይዘው የሚከፈቱ የአንድ ሰው ትክሻ ስለማይችላቸው በአህያ የሚጫኑ መጻሕፍቶች አሉ፡፡ አሳዛኙ ነገር ግን ከእነዚህ ሁሉ መጻ ሕፍት ዘጠና በመቶ የሚሆኑቱ ክር ስቶስ ኢየሱስን በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ የመረዳት ነጻነት የሚያደ ርሱ አይደሉም፡፡ (ከሣቴ ብርሃን ጋዜጣ መጋቢት ፳፻ወ፮ ዓ.ም) በማለት ይጽ ፋሉ፡፡
ይህ አሳብ ቤተ ክርስቲያንን በኢየ ሱስ ክርስቶስ የማታምን አድርጎ ከማቅረብ ያለፈ በምዕራባውያን እየተቀነ ቀነ ያለውን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲ ያንን በጎ እሴት፣ መልካም ሥነ ምግባ ርና ሰብአዊነት ለመናድ ምሰሶዋን ለመነቅነቅ ታልሞ የተጻፈ ነው፡፡ መጻ ሕፍቱ ጥቅም ስለሌላቸው አታንብቧ ቸው የሚል መልእክት ማስተላለፍ፣ ምግባር ትሩፋት አያስፈልግም ብሎ መስበክ ሳያስፈልግ ሰዎች በተለያዩ ሱሶች (ፊልም፣ ሙዚቃ፣ እግር ኳስ፣ ጫት፣ ወዘተ) ተጠምደው ከሥራ ውጪ እዲሆኑ ማድረግ ይቻላል የሚል ዓላማ ይዘው ለተነሡ አካላት ድጋፍ መስጠት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በቀጥታ ዓለማዊነ ትን ማበረታታት ነው፡፡
፪. ሥርዓት አልበኝነት፡- ዓለምን ሁሉ ለዓለማዊነት እያዘጋጁ ያሉት ምዕራባውያን በመጀመሪያ ደረጃ የሚ ሠሩት ሥራ ለዶግማ፣ ለሥርዓት፣ ለቀኖና፣ ለትውፊትና ለታሪክ ትኩረት በመስጠት ትውልድን የሚያገለግለውንና የሚያስተካክለውን ሃይማኖት ማጥ ፋት ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የተሐድሶ መናፍቃን ሰይፍ ያነጣጠረው ለዶግማ፣ ለሥርዓት፣ ለቀኖና፣ ለትውፊትና ለታ ሪክ ዋጋ በምትሰጠው ኦርቶዶክሳዊነት ቤተ ክርስቲያን ላይ ነው፡፡ ተሐድሶ መናፍቃን ማመን ብቻ በቂ ነው፤ ስለሚሉ ቤተ ክርስቲያን መሔድ፣ ቅዳሴ ማስቀደስ፣ ቅዱስ ቁርባን መቀ በል፣ መጾም መጸለይ፣ መስገድ፣ መመ ጽወት፣ ምግባር ትሩፋት መሥራት አያስፈልግም፤ ባይ ናቸው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ የክህነት ደረጃ፣ ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መታዘዝ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፤ በማለት ሰው ሕይወቱን በሥርዓት አልበኝነት እንዲመራ ያበረታታሉ፡፡
በተሐድሶ መናፍቃንን በመንገድ ጠራጊነት በሚያገለግሏቸው ሚዲያ ዎች የሚተላለፉ “ትምህርቶች” ሥር ዓት አልበኝነትን የሚያሰፍኑ መሆናቸ ውን የሚከተለው አባባላቸው ማሳያ ነው፡፡
ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል፣ በአፉ መስክሮ ይድናልና፣ መንገዱ ረጅም አይደለም ወገኖቼ፤ ውጣ ውረድ የለበትም፡፡ የምትከፍለው አይደለም፣ የተከፈለበት ነው፡፡ አንተ የምታደር ገው ነገር አይደለም፣ የተደረገልህ ነው፡፡ የምትሆነው አይደለም፣ የሆነልህ ነው፡፡ ይህንን ብታምን በአፍህ ብት መሰክር ትድናለህ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የሚነግረን መዳን ማለት በልብ ማመ ንና በአፍ መመስከር እንጂ እኛ በድ ካም የለመድነውን አይደለም፡፡ እየታገ ልን አንዴ ሲሳካ አንዴ ሳይሳካ እያለ ቃቀስን የምንኖረውን አይደለም፡፡
ይህ ንግግር መዳን በእምነት ብቻ ብሎ የተነሣው የሉተር ትምህ ርት እንጂ የቤተ ክርስቲያን አስተም ህሮ አይደለም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አስተ ምህሮ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ተናገረው “በብዙ ድካምና በብዙ መከራ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንገባ ዘንድ ይገባናል” የሚል ነው፡፡ ሥርዓት አልበኝነትን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለማስገባት ቆርጠው የተነሡት የተሐድሶ መናፍቃን ግን ኦርቶዶክሳዊነትን እን ዲህ ያቃልሉታል፡፡
“ጌታን የምናመልከው የሃይማኖት ድርጅት በመቀያየር አይደለም፡፡ ጴን ጤም መሆን ኦርቶዶክስም መሆን አያጸድቅም፡፡ ሕይወት እና ጽድቅ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን ብቻ ነው የሚገኘው። ጴንጤም ሆነ ኦርቶ ዶክስ መሆን ለእውነተኛ ወንጌል መረ ዳት ዋስትና አይደለም፡፡ ክርስቶስ በመ ጨረሻ ለፍርድ ሲመጣ ጴንጤ በዚህ፣ ኦርቶዶክስ በዚህ፣ ተሐድሶ በዚያ በኩል ብሎ አያሰልፍም፡፡ ሃይማኖት ማለት በእግዚአብሔር ልጅ አምኖ መመስከር ነው እንጂ ድርጅት መከተል አይደለም” በማለት ሃይማኖት አን ዲት ናት ያለውን የቅዱስ ጳውሎስን ቃል ሽረው፣ ብዙ መንገድ እንዳለ አድ ርገው አልፎ ተርፎም ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖትን ድርጅት ብለው አቃለው ይናገራሉ፡፡
የዚህ ሁሉ ዓላማ ሥርዓት አልበ ኝነት የነገሠበት ግላዊ ሕይወትን በም እመናን ላይ ለማንበር ነው፡፡ የጥ ፋት አባቶቻቸው ምዕራባውያን የሰው ልጆች የእግዚአብሔር አጋዥነት ሳያስ ፈልጋቸው ሓለፊነት ያለው “ሞራ ላዊ” ሕይወት በመምራት ለሰው ልጆች ፍጹም ጥቅምና ደህንነት የመብቃት ዐቅምና ሓላፊነት አላቸው፡፡ በምክንያታዊነት በመመራት፣ ጥልቅ በመሆነ መረዳትና በተግባራዊ የሕይወት ልምምድ ሕይወትን ፍጹምና ደስታ የሞላበት ለማድረግ ይችላሉ፡፡ ይህም አስተሳሰብ በየጊዜው በዝግመተ ለውጥ እያደገ የሚሔድ ነው፡፡ አስተሳሰቡ በእሴቶች መሠረት በሚቀመጡ ግቦች እንዲመራ በሚያደርጉ አስተዋይ ሰዎች መሪነት በጥንቃቄ ቅርፅ እያገኘና ከዕውቀታችን ማደግ ጋር እየተለወጠ የሚሔድ ነው፡፡ እሳቤውም እንደ ሰው ልጅ ሕይወት ያላማቋረጥ የሚሻሻ ልና የሚዘምን ነው፤ በማለት ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም የሚለ ውን የጌታ ቃል ለማፍረስ ይሠራሉ (ምንጭ፣ የ፲፱፻፺፫ /እ.ኤ.አ/ የሰብአ ዊነት መግለጫ) በማለት ጽፈዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የሚ ለው “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አት ችሉም” ነው፡፡ ሁሉ በእርሱ ሆነ፤ ከሆነ ውስ አንዳች እንኳን ያለ እርሱ የሆነ የለም፡፡ ምድርና ሞላዋ በእግዚአብሔር ተፈጠሩ፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ይህን ወይም ያን እናደርጋለን በሉ፡፡ ሁሉ የእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ የሆነ አም ላክ የተመሰገነ ይሁን፤ የሚል ነው፡፡ የመልእክቱ አስተላላፊዎች እነዚህን ጥቅሶች ውሸት ለማድረግ የሚሠሩ መሆናቸውን ድርጊታቸው ይመሰክ ራል፡፡
፫. አክራሪነት፡- አክራሪነት ማለት ከእኔ የተለየ አስተሳሰብ ያለው አካል በምድር ላይ ሊኖር አይገባም የሚል ጽንፈኝነት ነው፡፡ ምዕራባውያን አክራሪነ ትን በመዋጋት ስም እያስፋፉ የሚገ ኙት አክራሪነትን ነው፡፡ ልዩነቱ ምዕራ ባውያን አክራሪነትን የሚያስፋፉበት መንገድ እስልምናን ሽፋን አድር ገው አክራሪነትን እንደሚያራምዱ ወገ ኖች በጦር መሣሪያ ሳይሆን በኢኮ ኖሚ፣ በትምህርት፣ በሥልጠና፣ በል ማት፣ በባህልና ሃይማኖት ተሐድሶ፣ በሰብአዊ መብት ማስከበር፣ አክራሪነ ትን በመከላከል፣ ወዘተ ሽፋን መሆኑ ነው፡፡ ምዕራባውያን በዓለም ላይ ፕሮቴ ስታንት ብቸኛ እምነት እንዲሆን፣ ምዕራባዊ ባህልና አስተሳሰብ በዓ ለም ሁሉ እንዲንሰራፋ፣ “በነጻነት” ስም የሚሰበከው ዓለማዊነት እንዲስፋፋ፣ ወዘተ እየሠሩ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ተግ ባራት የመጨረሻ ዓላማቸው የሌሎ ችን አገራት እምነት፣ እሴት፣ አስተ ሳሰብ፣ ባህል፣ ወግ፣ ወዘተ በማፍረስ በፕሮቴስታንታዊ ባህል ለመተካት ከተቻለ ደግሞ ፈጽሞ ዓለማዊ ለማድ ረግ ነው፡፡
በዓለም ላይ ማንነታቸውን እንዲ ያጡ፣ ያላቸው የተፈጥሮ ሀብት በሌ ሎች እንዲወሰድባቸው የተደረጉ አገ ራት ዜጎች አሸባሪዎች ሆነዋል፡፡ አሸባ ሪዎች የሆኑት ግን ተፈጥሯቸው ለሽብር የሚስማማ ሆኖ ወይም አሸባ ሪነትን መርጠውት ሳይሆን አማራጭ ስለሌላቸው ነው፡፡ ጆን ፐርኪንስ በኢኳ ዶር የሆነውን ጠቅሶ ሲናገር እንዲህ ነበር ያለው፡-
â€Â¦ ነዳጅ ለማውጣት ሲባል ከቦ ታቸው ለተፈናቀሉትና ጫካቸው ተመን ጥሮ አካባቢያቸው ወድሞ በእጅጉ ለተጎዱት፣ ገንዘቡም ለዕለት ኑሯቸው እጅግ አስፈላጊያቸው ለሆነውና የሚበላ ምግብና የሚጠጣ ውኃ በማጣት ለሚሰቃዩት ነዋሪዎች የሚደርሳቸው ከአገሪቱ ከሚወጣው ነዳጅ ሽያጭ ከእያንዳንዱ መቶ ዶላር ውስጥ ከ2.5 ዶላር በታች ነው፡፡ እነዚህ ሕዝቦች በሙሉ – በኢኳዶር ያሉ ሚሊዮኖች እና በዓለም ዙሪያ ያሉ ቢሊዮኖች አንድ ቀን አሸባሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንዲህ የሚሆኑት ግን በኮሚዩኒዝም ወይም በነውጠኛነት ስለሚያምኑ አይደ ለም፤ ወይም በተፈጥሯቸው ክፉዎች ስለሆነ አይደለም፤ የእኛ ድርጊት ተስፋ ስላስቆረጣቸው ብቻ ነው እንጂ፡፡ (የተሐ ድሶ መናፍቃን ዘመቻ ገጽ ፳፫)
የካቶሊክና የፕሮቴስታንት ሚሲዮ ናውያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ በእነርሱ ቋንቋ “ለማደስ” ብዙ ጊዜ ተመላልሰ ዋል፡፡ በዚህ ምልልሳቸው የመጨረሻ ግባቸው ተሳክቶ ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ ፕሮቴስታንት ማድረግ ባይች ሉም ብዙ የፕሮቴስታንት ችርቾችን አቋቁመዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመና ንን ዘርፈዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም የሚፈልጉት ልክ በምዕራቡ ዓለም እንዳደረጉት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስ ቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ትውፊት፣ ታሪክና ሥርዓት በማጥፋት ወጥ የሆነ ፕሮቴስታንታዊ አስተሳሰብን ማንበር ነው፡፡ ይህ በእነርሱ ቋንቋ “ሰዎች እጃቸውን ለጌታ እንዲሰጡ ማድረግ ነው” እየተደረገ ያለው ግን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ማንነት ማጥፋት ነው፡፡
ከዚህ በላይ አክራሪነት፣ አክራሪነ ትንም የሚያስፋፋ ተግባር የለም፡፡ ማንም ሰው የፈለገውን እምነት የመከ ተል፣ የፈለገውን አስተሳሰብ የመያዝ መብት አለው፡፡ ይህ ለሁሉም በሥነ ፍጥረት የታደለ መብት ነው፡፡ በተሐድሶ መናፍቃን ዘንድ ግን ይህ አይሠራም፡፡ የእምነቱ ተከታዮች ሳይሆኑ “ኦርቶዶክ ሳውያን ነን” በማለት ምእመናንን ከቤተ ክርስቲያን እያስወጡ ለሌሎች ቤተ እምነቶች ይገብራሉ፡፡ በገንዘብ በማታ ለል፣ በትውውቅ በመቀራረብ አልፎ ተርፎም በጉልበት በማስፈራራት ጭምር ምእመናንን ከበረታቸው የማስወጣት ሰፊ ዕቅድ ይዘው ይሠራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቁጭ ብለው ቤተ ክርስቲያንን ይሳደባሉ፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖትን የሚከተሉ ምእ መናንን ደግሞ ደንቆሮ፣ ያልበራላቸው፣ ኋላ ቀር፣ ጣዖት አምላኪ፣ ግብዝ፣ ወዘተ በማለት ሰው የፈለገውን እምነት የመከተል ሰብአዊ መብቱን ይጋፋሉ፡፡ እንግዲህ ከሰው ቤት ገብቶ አዛዥና ናዛዥ ለመሆን ከመፈለግ እና አልወ ጣም ብሎ ከመሟገት በላይ፣ “ኦርቶዶ ክሳዊ ነኝ” የሚል ጭንብል ለብሰው የማያምኑበትን እምነት ከመሳደብ በላይ፣ የራስን እውነት ከመናገር አልፎ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ትክክል አይደለችም እያሉ ከመሳደብ በላይ አክ ራሪነት ምንድን ነው?
፬. ግብረ ሰዶማዊነት፡- ግብረ ሰዶ ማዊነት ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ የሆነ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ነው፡፡ እግዚ አብሔር በዚህ ዐመጽ ውስጥ የነበሩ የሰዶምንና የገሞራን ሕዝቦች በእሳት ዲን አጥፍቷቸዋል፡፡ እግዚአብሔርን ከሚያስቆጡ የሥጋ ሥራዎች ውስጥ አንዱ ግብረ ሰዶም ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ ምዕራፍ ፩፣፳፬-፳፰ “â€Â¦ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸ ውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው” በማለት ግብረ ሰዶማዊ ነት ትልቅ ኀጢአት መሆኑን ነግሮናል፡፡ “ለባሕርያቸው የማይገባውን” የሚለው ግብረ ሰዶማዊነት የተፈጥሮን ሥርዐት የሚቃረን፣ የርኩሰት ሥራ፣ ጸያፍ፣ ሥጋን የሚያዋርድ፣ እግዚአብሔርን የሚያስቆጣና ቅጣትን የሚያስከትል መሆኑን ያስረዳናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግብረ ሰዶማዊነት ከእግዚአብሔር መን ግሥት የሚያስወጣ መጥፎ ድርጊት መሆኑንም እንዲህ በማለት ነግሮ ናል፡፡ “ዐመጸኞች የእግዚአብሔርን መን ግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖ ትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝ ሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ â€Â¦ የእግዚአብ ሔርን መንግሥት አይወርሱም” (፩ኛ ቆሮ. ፮፣፱)፡፡
አማናዊውና ተፈጥሯዊው ትምህ ርት ይህ ሆኖ ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላትን እንደ ነጻነት የሚቆጥ ሩት ምዕራባውያን ግብረ ሰዶማዊ ነት በሰብአዊ መብት፣ በፍቅር፣ ወዘተ ስም ሕጋዊ እንዲሆን እየጣሩ ነው፡፡ በዓለም ታዋቂ የሚባሉ ሰዎችም ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልክቶ በበጎ ጎን ጽፈዋል፡፡ ለምሳሌ፡- ሲግመንድ ፍሮ ይድ የሚባል የሥነ ልቡና ባለሙያ፡-
ግብረ ሰዶምን እንደ ወንጀል መቁ ጠር ትልቅ ኢፍትሐዊነት ነው፡፡ በጥን ቱም ሆነ በዘመናዊ ዓለም በጣም የሚ ከበሩ ግለሰቦች (ለምሳሌ፡- ፕላቶ፣ ሚካ ኤል አንጀሎ፣ ሊኦናርዶ ዳቪንቺ፣ ወዘተ) ግብረ ሰዶማውያን ነበሩ፡፡ ግብረ ሰዶም ጥቅም የለውም፤ ነገር ግን የሚ ያሳፍር፣ የሚያስጠላ፣ የሚያስቀጣና እንደ በሽታ የሚቆጠር ነገር ሳይሆን እንደ አንድ አማራጭ የሥራ ዘርፍ መታየት አለበት፤ ብሏል፡፡
ካረን ሁከር የምትባል ሴት በጥናት ደረስኩበት የምትለውን “ግብረ ሰዶማው ያን በሕይወታቸው የሥነ ልቡና ቀውስ አልደረሰ ባቸውም፡፡ ስለዚህ ግብረ ሰዶምና ሥነ ልቡናዊ ቀውስ ቀጥተኛ ግንኙነት የላቸውም” ብላ በመገለጽ ግብረ ሰዶማዊነትን ተፈጥ ሯዊ ለማስመሰል ሞክራለች፡፡ ሐቭሎክ ኢሊስ ደግሞ “አብዛኞቹ ግብረ ሰዶ ማውያን ለሚኖሩበት ማኅበረሰብ ከፍ ተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል”፤ ይላል፡፡ እነዚህ ሁሉ አስተሳሰቦች የእግዚአብ ሔርን መኖር በማያምኑ ወይም በሚጠ ራጠሩ አካላት የሚቀነቀኑ ስለሆነ ብዙ ላያስገርሙን ይችላሉ፡፡ የሚያሳዝነው ግን እግዚአብሔርን እናውቃለን፤ “ክርስ ቶስን እንሰብካለን” በሚሉ አካላት እነ ዚህ አስተሳሰቦች ትክክል ናቸው ተብ ለው መወሰዳቸው ነው፡፡
አብዛኛዎቹ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ግብረሰዶማዊነትን የሚደግፉ ናቸው፡፡ ስፔን፣ ጀርመን፣ ቼክ ሪፐብ ሊክ፣ ፈረንሣይ፣ እንግሊዝ፣ ኢጣሊያ፣ ግሪክ፣ ፖላንድ የመሳሰሉ አገራት ግብረ ሰዶማዊነትን የሚደግፉ ናቸው፡፡ በሌላው ዓለም ስናይ አሜሪካ፣ አርጀን ቲና፣ ቺሊ፣ ሜክሲኮ፣ ብራዚል፣ ቬንዙ ዌላ፣ አውስትራሊያ፣ ፊሊፒንስና ጃፓን ደጋፊ አገራት ናቸው፡፡ ግብረ ሰዶማ ዊነትን በሕግ ከፈቀዱ አገራት መካከል ደግሞ፡- አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ኔዘርላ ንድ፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ካናዳ፣ ቤልጂ የም፣ አውስትራሊያና ደቡብ አፍሪካ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ግብረ ሰዶማዊነትን በመቃወም ኢትዮጵያ ከናይጀሪያ ቀጥሎ ሁለተኛ ናት፡፡
በእነዚህ አገራት የሚገኙ እና ወን ጌልን እንስበክላችሁ የሚሉን የካቶሊ ክና የፕሮቴስታንት ቸርቾች ግብረ ሰዶማዊነት የሰውን ልጅ የሚያጠፋ መሆኑን የሚናገረውን የቅዱስ ጳውሎ ስን መልእክት እያስተማሩ ግብረ ሰዶ ማዊነትን በዐዋጅ ተቀብለዋል፡፡ በክር ስትና ስም የሚጠሩ “አብያተ ክርስቲ ያናት” የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ኀጢአት ወይም የሥነ ምግባር ግድ ፈት አድርገው አያዩትም፡፡ እንዲያ ውም ግንኙነቱን በመባረክ እንደ ጋብቻ እየቆጠሩት ነው፡፡ ግብረ ሰዶማዊነትን ፈቅደው በቸርቾቻቸው ወንድን ከወ ንድ፣ ሴትን ከሴት እያጋቡ ነው፡፡ ወን ጌል ገልጠው እያስተማሩ፣ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ነን እያሉ ግብረ ሰዶ ማውያንን በመቅደሳቸው አቁመው የሚያጋቡ የእምነት ድርጅቶች ስለ መኖራቸው ብዙ የተባለበት ነው፡፡ ለም ሳሌ፡- ፈረንሳይ ውስጥ የሚገኙ የፕሮ ቴስታንት “አብያተ ክርስቲያናት” ጠቅ ላይ ሲኖዶስ ግብረ ሰዶማውያን ጋብ ቻቸውን “በቤተ ክርስቲያን” ውስጥ እንዲፈጽሙ ፺፬ በመቶ በሆነ ድምፅ አሳልፏል፡፡
“የአብያተ ክርስቲያናቱ” መሪ ሲኖዶሳቸው ወደፊት እያንዳንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ይህን የግብረ ሰዶማውያን ጋብቻ በማጽደቅ ፍላጎታ ቸው ከሆነ ባርኮ ለማጋባት መንገዱ ተከፍቷል ብለዋል፡፡ የስኮትላንድ ሉተ ራን “ቤተ ክርስቲያን” ደግሞ ተመሳ ሳይ ጾታ ካላቸው ተጋቢዎች መካከል ዲያቆናትንና ካህናትን መሾም የሚቻል በትን ሕግ አጽድቃለች፡፡ በስዊድን የሚገ ኘው የፕሮቴስታንት “አብያተ ክርስቲ ያናት ሲኖዶስ” የግብረ ሰዶማውያንን ጋብቻ ለመባረክ በ፳፻፲፪ ውሳኔ ሲያስተላ ልፍ፣ የዴንማርክ “ሲኖዶስ” በበኩሉ እያንዳንዱ የፕሮቴስታንት “ቤተ ክርስቲ ያን” ይህን ጋብቻ መፈጸም ግዴታው እንደሆነ በመግለጽ ውሳኔውን በሥሩ ላሉ “አብያተ ክርስቲያናት” አስተላ ልፏል፡፡ የኖርዌይ ፕሮቴስታንት “ቤተ ክርስቲያንም” ከዴንማርክ ቀጥሎ ተመሳ ሳይ ውሳኔ አስተላልፋለች፡፡
በአጠቃላይ የካናዳ የተባበሩት “ቤተ ክርስቲያን” (the United Church of Canada)፣ የክርስቶስ የተባበሩት “ቤተ ክርስቲያን” (The United Church of Christ)፣ የጀርመን ሉተራን “አብ ያተ ክርስቲያናት” (all German Lutheran)፣ የኢኬዲ ተሐድሶና የተባ በሩት “አብያተ ክርስቲያናት” (refor med and united churches in EKD)፣ የስዊዘርላንድ ተሐድሶ “አብያተ ክርስቲያናት” (all Swiss reform ed churches)፣ የኔዘርላንድ ፕሮቴ ስታንት “ቤተ ክርስቲያን” (the Protestant Church in the Netherlands)፣ የቤልጂየም የተባበሩት ፕሮ ቴስታንት “ቤተ ክርስቲያን” (the Uni ted Protestant Church in Belgium)፣ የፈረንሣይ የተባበሩት ፕሮቴስታንት “ቤተ ክርስቲያን” (the Unit ed Protestant Church of France)፣ የዴንማርክ “ቤተ ክርስ ቲ,ያን” (the Church of Denmark)፣ የስዊድን “ቤተ ክር ስቲያን” (the Church of Sweden)፣ የአይስላንድ “ቤተ ክርስቲ ያን” (The Church of Iceland)፣ የኖርዌይ “ቤተ ክርስቲያን” (the Church of Norway)፣ የፊንላንድ ወንጌላ ዊት ሉተራን “ቤተ ክርስቲያን” (The Eva ngelical Lutheran Church of Finland)፣ የሜትሮፖሊታን ኅብረት “ቤተ ክር ስቲያን” (The Metropolitan Community Church)፣ የሐዋርያት ጴንጤ ቆስታል አጋዥ ዓለም አቀፋዊ ኅብ ረት (The Global Alliance of Affirming Apostolic Pentecostals (GAAAP)) ግብረ ሰዶማዊ ነትን ያጸደቁና ግብረ ሰዶማውያንን በጸሎት የሚያጋቡ “አብያተ ክርስቲ ያናት” ናቸው፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለወንድም ለሴትም ግብረ ሰዶማውያን ክህነት የሰጡ “አብያተ ክርስቲያናት” ደግሞ፡- የስኮትላንድ፣ የእንግሊዝ፣ የዌልስ፣ የስዊድን፣ የኖርዌይ፣ የዴንማርክና የአይስላንድ “አብያተ ክርስቲያናት”፣ የፊንላንድ ወንጌላዊት ሉተራን “ቤተ ክርስቲያን”፣ የጀርመን ወንጌላዊት ሉተ ራን “ቤተ ክርስቲያን”፣ የኔዘርላንድ ፕሮቴስታንት “ቤተ ክርስቲያን”፣ የቤል ጂየም የተባበሩት ፕሮቴስታንት “ቤተ ክርስቲያን”፣ የስዊዘርላንድ ተሐድሶ “ቤተ ክርስቲያን”፣ የፈረንሣይ የተባ በሩት ፕሮቴስታንት “ቤተ ክርስቲ ያን”፣ የካናዳ ወንጌላዊት ሉተራን “ቤተ ክርስቲያን”፣ የካናዳ አንግሊካን ቤተ ክርስቲያን፣ የጥንቷ ካቶሊክ “ቤተ ክርስቲያን” እና የጃፓን የተባበሩት የክርስቶስ “ቤተ ክርስቲያን” ናቸው፡፡
፭. አምልኮተ ሰይጣን፡- ምዕራባው ያን የሥልጣኔያቸው የመጨረሻ ጥግ “አምልኮተ ሰይጣን” ሆኗል፡፡ በተለያዩ አገራት የሚገኙ በተለይም በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመላው ዓለም የሚታዩት ሙዚቀኞች፣ የእግር ኳስ ተጨዋቾች፣ ሞዴሊስቶች፣ የፊልም ተዋናዮች፣ ወዘተ ሰይጣንን ወደ ማም ለክ ደረጃ ደርሰዋል፡፡ እነዚህ አገራት ግን “የአፍሪካውያንን ዐይን ለማብራት በሚል” ብዙ ሚሲዮኖችን ወደ አፍሪካ ይልካሉ፡፡ አበው የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች እንዲሉ የራሳቸው ዜጎች በነጻነት፣ በዲሞክራሲያና ሰብአዊ መብት፣ በሥልጣኔ፣ በልማት፣ ወዘተ ስም ከአምልኮተ እግዚአብሔር ወጥ ተው ወደ አምልኮተ ሰይጣን እየገቡ፣ የእምነቱ ተከታይ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን መድረክ ላይ ቆመው የክርስቶስን ወን ጌል ገልጠው የሚያስተምሩ ፓስተሮ ቻቸው በአምልኮተ ሰይጣን እየታሙ በአርአያቸውና በአምሳላቸው የፈጠ ሯቸው ተሐድሶ መናፍቃን ለእኛ “ወንጌል ካልሰበክን” ይላሉ፡፡
የተሐድሶ መናፍቃን የመጨረሻ ግባቸው ይህ ነው፡፡ ምክንያቱም ገለጻ ሲያደርጉ በአምኮተ ሰይጣን የሚታ ሙትን ጆሹዋንና ፓስተር ክሪስን እንደ አርአያ ይጠቅሷቸዋልና፡፡ መጽ ሐፍ ቅዱስ የሚያዝዘው “የእግዚአ ብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻች ሁን አስቡ፣ የኑሯቸውንም ፍሬ እየ ተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው” በማለት ነው፡፡ የተሐድሶ መናፍቃን ዋኖቻችን ብለው የሚጠሯቸው ግን ምግባር የሌላቸው ብቻ ሳይሆኑ በእግ ዚአብሔር ማመናቸው እንኳን የማይ ታወቁ ሰዎችን ጭምር ነው፡፡ ጆሹዋና ፓስተር ክሪስ ርኩሳን መናፍስትን በመጥራት አጋንንትን እናወጣለን የሚሉ እንደሆኑ ብዙ ማስረጃዎች እየ ወጡ ነው፡፡ ስለዚህ የተሐድሶ መናፍ ቃን የመጨረሻ ግብ ዓለማዊነትን አልፎ ሰው በዘቀጠ የሕይወት ማንነት ውስጥ እንዲኖር የሚያደርጉ እኩይ ተግባራትን በውስጡ በማንገሥ ግብረ ሰዶማዊና ሰይጣን አምላኪ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡

መንክር ስብሐተ ልደቱ፤ የመወለዱ ምሥጢር ድንቅ ነው

{gallery count=1 width=350 height=300 counter=1 links=0 alignment=center animation=3000}ledete2004{/gallery}

«እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሴትን እናድርግ፤ በእርስዋም ደስ ይበለን፡፡» መዝ. 117·24 ይህች ዕለት ዕለተ ኃይል፣ ዕለተ አድኅኖ፣ ዕለተ ብሥራት፣ ዕለተ ቅዳሴ፣ ዕለተ ልደት፣ ዕለተ አስተርዕዮ ናትና ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ ከአብ ባሕርይ ዘእምባሕርይ፣ አካል ዘእምአካል፣ የተወለደ ወልድ ዋሕድ ኋላም ከድንግል አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ በዚህች ዕለት በኅቱም ድንግልና ተወልዷልና ዕለተ ኃይል ትባላለች፡፡ መላእክት በጎል ተጥሎ፣ በጨርቅ ተጠቅልሎ አይተው ስብሐት ለእግዚአብሔር ብለው አመስግነውበታልና ዕለተ ቅዳሴ፣ መድኅነ ዓለም ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በጎል ተገኝቶበታልና ዕለተ አድኅኖ፣ ቅዱስ ገብርኤል እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ብሎ ተናግሯባታልና ዕለተ ብሥራት ትባላለች፡፡ «እግዚአብሔርም አለኝ አንተ ልጄ ነህ እኔም ዛሬ ወለድሁህ» መዝ 2·7 በተዋሕዶ፣ በቃል ርስትነት ተብሎ የተነገረለት ቀድሞ ብቻውን እግዚአብሔር ከብቻው እግዚአብሔር እንደተወለደ፣ በኋለኛውም ዘመን ብቻውን የሚሆን የእግዚአብሔር ልጅ ብቻዋን ከምትሆን ከዳዊት ልጅ ተወለደ፡፡

በመጀመሪያ የማይታይ እሱ ከማይታየው ተወለደ፤ በኋላም የማይያዝ የሕይወት እስትንፋስ ከምትዳሰስ ሥጋ ተወለደ፡፡
በመጀመያ የአኗኗሩ መጀመሪያ ሳይታወቅ ተወለደ፤ በኋላም የዘመናት ፈጣሪ ዓመታትን የሚወስን እርሱ ዕድሜዋ ዐሥራ አምስት ከሆነ ከታናሽ ብላቴና ተወለደ፡፡
የመጀመሪያ ልደቱን ምሥጢር፣ የኋለኛ ልደቱንም ድንቅ በማድረግ ተወለደ፡፡
በቅድምና የነበረው የአብ አካላዊ ቃሉ በምልዓት ሳለ ተፀነሰ፤ በጌትነቱ በጽርሐ አርያም ሳለ ሰው ሆነ፤ ማኅተመ ድንግልናን ሳይለውጥ የእኛን ባሕርይ ተዋሕዶ ተወለደ፡፡
የሰውን ልጅ በጥንተ ተፈጥሮ የፈጠረ የእግዚአብሔር አብ ልጅ እግዚአብሔር ወልድ አሁን ደግሞ በሐዲስ ተፈጥሮ ለመፍጠር ሰው ሆኖ ተወለደ፡፡ «ሰው ሆይ አስተውል እሱን አስመስሎ ይወልድህ ዘንድ አንተን መስሎ ተወለደ ስለዚህ ነገር ቅዱስ ጳውሎስ መላእክትን የተቀበለ አይደለም፤ የአብርሃምን ዘር ከፍ ከፍ አደረገ እንጂ» እንዳለ ዕብ 2·16 የሰውን ልጅ ክብር ወደ ቀደመ ማንነቱ ለመመለስ እንዲህ ባለ ድንቅ ልደት ዛሬ ተወልዷልና ዕለተ ልደት ትባላለች፡፡
«በሀገራቸው ትንቢት የተነገረላቸው በዕብራይስጥ ልሳንም የተጻፈላቸው እስራኤል ምንም ባያውቁህ ከዓለም አስቀድሞ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ ደግሞ ከዳዊት ዘር ከምትሆን ቅድስት ድንግል ተወልደህ የሰው ልጅ መባልህን አወቅሁ» ማቴ 16·13-18
ትንቢቱስ ምን ነበር እግዚአብሔር፤ አዳምን ከአራቱ ባሕርያት ፈጥሮ ከእንስሳት ከአራዊት ለይቶ በነባቢት ነፍስ አክብሮ ልጅነትን ሰጥቶ ሥራ ሠርቶ ሊጠቀምበት መንፈሳዊ ዕውቀትን አድሎ በአርአያው በአምሳሉ የፈጠረው ነውና የባሕርዩን በጸጋ ሰጥቶ የሁሉ ገዥ አድርጎ በገነት ሹሞ አኖረው፡፡ ነገር ግን የገዥና የተገዥ ምልክት የምትሆን ዕፀ በለስን እንዳይበላ አዘዘው፡፡ ይኸውም የንፍገት አይደለም፤ ከሹመቱ እንዳይሻር፣ ከልዕልናው እንዳይዋረድ፣ ከልጅነት እንዳይወጣ፣ ክብርን እንዳያጣ ነው እንጂ፡፡ ሆኖም ግን የራሱን ክብር ልዕልና በራሱ ያጣ ዲያብሎስ በአዳም ክብርና ልዕልና ቀና፡፡ በሥጋ ከይሲ ተሠውሮ በሽንገላ መጣ፡፡ ክፋትን በተመላ ደስ የሚያሰኝ በሚመስል አነጋገር የሞት ሞት የምትሞቱ አይምሰላችሁ የዕፀ በለስ ፍሬ ብትበሉ የአምላክነት ዕውቀት ይሰጣችኋል፡፡ ክፉውንም ደጉንም ታውቃላችሁ፤ አሁን ካላችሁበት ክብርና መዓርግ ከፍ ትላላችሁ በማለት አታለላቸው፡፡ እነርሱም እውነት መሰላቸው፡፡ ከፈጣሪያቸው ትእዛዝ ወጡ፡፡ ራሳቸውን አጥፊ ሆኑ፤ የቀደመ ማንነታቸውን አጥተው ኃሣር፣ መርገም፣ ድንጋፄ፣ ረዓድ ወደሚበዛበት፣ ክፉና መልካም ወደሚሠራበት፣ ቢያገኙት ቁንጣን፣ ቢያጡት ቀጠና ወደ ሆነበት ዓለም ወረዱ፡፡ ቢሆንም ግን አዳም በፍታዊነቱ አንጻር መሐሪነቱን ተረድቶ በደሉን በማመን አዘነ፤ አለቀሰ፤ በልብ መታሰቡ በቃል መነገሩ ከፍ ከፍ ይበልና ጸዋትወ መከራውን አይቶ አዘነለት፡፡ የሚድንበትን ተስፋ ትንቢት ሰጠው፡፡ አምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ብሎ ከዚህም አያይዞ ከልጅ ልጁ ተወልዶ የሚያድነው ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል መሆኑን፣ እርሱን ለማዳን ስሙን ባሕርዩን ገንዘብ የሚያደርገው ወልድ ኢሳ 9·6 መሆኑንም ጨምሮ ነግሮታል፡፡ ዘፍ 3·22 ይህ የሚፈጸምበትን ቀጠሮም አስረድቶታል፡፡ ገላ 4·4 ከዚያ ቀጥሎ በየጊዜው ለተነሡ ልጆቹ ትንቢቱን በማስነገር፣ ምሳሌውን በማስመሰል፣ እስከ ጊዜው ደርሷል፡፡ ለዚህም ነው በዘመነ አበው የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ ተብሎ የሃይማኖት መሠረት ለሆነው ለአብርሃም የተነገረው ዘፍ 22·18
በዘመነ መሳፍንትም አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ታደምጣለህ ተብሎ በሙሴ ለእስራኤል ሕዝብ በሙሉ አዋጅ ታውጇል፡፡ ዘዳግ 18·15
በዘመነ ነገሥት ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ ብሎ ለዳዊት የገባው ልዩ ቃል ኪዳን አለ፡፡
ስለዚህ እወቅ አስተውልም ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ተብሎ በነቢዩ ዳንኤል 9·25 ተነግሯል፡፡
ያዕቆብም በምርቃት የገለጸው ልጆቹን ለእያንዳንዳቸው እንደሚገባቸው የጸጋ ሀብት በረከታቸውን ባሳየ ጊዜ የይሁዳን መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ግዛትም ከወገኑ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ እርሱም የአሕዛብ ተስፋቸው ነው፡፡ ዘፍ 49·10 ከይሁዳ ወደ ዳዊት እየቀረበ ሲመጣም እርሱም አባቴ አንተ ነህ ይለኛል እኔም በኩር አደርገዋለሁ፡፡ መዝ 88·20 1ሳሙ 16·1-13 በማለት ሥጋ (አካለ) ዳዊትን በተለየ መልኩ እንደመረጠው ፈጣሪው ሲሆን ልጁ ለመባል እንደወደደ እየገለጠው እያቀረበው መጣና ወደ ልጁ አለፈ፡፡
ዳዊትንም ልጁን ለዚህ ታላቅ ምሥጢር እንዲያዘጋጅ በትንቢት አነሣሣው፡፡ እርሱም ልጁን እንዲህ አላት፤ «ልጄ ሆይ የምልሽን ስሚ፤ እይ፤ ጆሮሽንም ወደ ምሥጢሩ ቃል አዘንብይ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤ ያለምንም የልብ መከፈል ራስሽን ለርሱ ስጪ፤ ንጉሥ ውበትሽን ይኸውም ንጽሕናሽን፣ መዓዛሽን፣ ቅድስናሽን ወዷልና፡፡ እርሱ ሌላ አይደለም፤ ለታላቁ ምሥጢር የመረጠሽ ጌታሽ ነውና፡፡» መዝ 44·10-12 አላት፡፡ ደስ በሚያሰኝ የተስፋ ቃል ትንቢቱን ተናገረ፡፡ እርሱም ይሁንልኝ ብላ የአባቷን ምክር ተቀብላ የአምላክ እናት ለመሆን በቃች፤ ትንቢቱም ደርሶ የገባውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ ወደደ፡፡
ደም ግባቷን በወደደ ጊዜም በጽርሐ አርያም እናት ትሆነው ዘንድ ወደ ሰማይ አላሳረጋትም፤ እርሱ ራሱ ወደእርሷ ወረደ እንጂ፡፡ በዚያ ትፀንሰው ዘንድ በኪሩቤል ሠረገላ ላይ አላስቀምጣትም፤ ናዝሬት በተባለች በገሊላ ሀገር ሳለች እርሱ ራሱ በማሕፀኗ አደረ እንጂ፡፡ ገብርኤልንም ዘጠኝ ወር በማሕፀኗ እንድትሸከመኝ ወደዚህ አምጣት አላለም፤ እርሱ ራሱ ትሕትናዋን ተሳተፈ እንጂ፡፡ ይልቁንም መልክተኛውን በትንቢት ወደ መረጣት የዳዊት ልጅ ላከ፡፡ እርሱም ደስ ያለሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው፤ እነሆ ኢሳይያስ ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች እንዳለ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም አማኑኤል ትይዋለሽ፤ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከሥጋችን ሥጋን፣ ከነፍሳችን ነፍስ ነስቶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆነ፤ በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ የሆነውም ኢየሱስ ተባለ፤ ትርጓሜውም ወገኖቹን የሚያድናቸው ማለት ነው፡፡ ይህ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሃ ፈሳሽ የሆነ ሳይሆን ከጥንቱ ሲነገር ሲያያዝ የመጣ ነው አላት፡፡ እርሷም እንዲህ ያለ ሰላምታ እንደምን ይቀበሏል አለች፡፡ በትሕትና መልአኩም በእግዚአብሔር ዘንድ የእናትነት ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ፤ የምትወልጅውም የልዑል እግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ይባላል፤ እግዚአብሔር የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ በያዕቆብ ወገን ለዘለዓለም ነግሦ ይኖራል፡፡ ለጌትነቱ ፍጻሜ የለውም አላት፡፡ ነገሩስ መልካም ነበር፤ ነገር ግን ወንድ ሳላውቅ መፅነስ መውለድ እንደምን ይሆንልኛል? በውኑ ምድር ያለ ዘር ታፈራ ዘንድ ሴት ያለወንድ ትፀንስ ዘንድ ይቻላልን? ሴት ያለ ወንድ ዘር መውለድ ከዚህ በፊት አልሆነምና አለችው፡፡
እውነት ነው ከዚህ በኋላም አይሆንም ነገር ግን ያንች ፅንስ እንደ ሌሎች ፅንስ አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፤ ኃይለ ልዑል ወልድ ሥጋሽን ይዋሓዳል፤ ለሱ የሚሳነው ነገር የለም፤ ሁሉን ማድረግ ይቻለዋል አላት፤ እርሷም ጊዜ በፍጹም እምነት ቃለ ብሥራቱን ተቀብላ አቤቱ እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋዩ ነኝ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ ባለች ጊዜ ፈቃዷን ምክንያት አድርጎ የዓለሙ ሁሉ መድኃኒት የሚሆን ዋሕድ ቃለ እግዚአብሔር በማሕፀኗ ተቀርፆ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የማይወስነው በማሕፀኗ ተወስኖ ሊወለድ የማይቻለው ተወለደ፡፡ በሰው ዘር ያልሆነ ነገር ግን እንደ ሰው የሆነውን ልደቱን እናምናለን፡፡
አምላክ ሲሆን መወለዱን፣ ወደዚህ ዓለም መምጣቱን፣ ከረቂቃን የረቀቀ ድንቅ ነው ከድንግል መወለዱ ፍጹም ሰው ቢሆንም ያለ ዘር በኅቱም ድንግልና ተጸንሶ በኅቱም ድንግልና መወለዱ ግን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በመሆኑ ፍጹም አምላክ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ይህ ልደት እጅግ አስደናቂ ልደት ነው፡፡ በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና መወለድ ለዘለዓለም አዲስ ሥራ ቢሆንም በድንግልና መጸነሱም ሆነ መወለዱ በእርሱ ለእርሱ ብቻ እንጂ በማንም ሥልጣን ለማንም እስካልሆነ ድረስ ከማድነቅ ውጪ እንዴት ሊሆን ቻለ ማለት አይገባም፡፡ ይልቁንም ልደቱን በመመራመር ማወቅ አይቻልም በማመን እንጂ፤ እነዚህም ሁለት ልደታት ናቸው፡፡
1. ከዘመናት በፊት ዓለማት ሳይፈጠሩ ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ የተወለደው፡፡ መዝ 10·3 ይህ የመጀመሪያው ልደት ሲሆን፤
2. በኋላኛው ዘመን ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ በድንግልና የተወለደው ሁለተኛ ልደት ነው፡፡ ኢሳ 7·19 9·6 ማቴ 1·22-23 2·1 ገላ 4·4 ይህን ድንቅ ምሥጢር ሊቁ እንዲህ በማለት ይገልጠዋል፤ «አቤቱ ሆይ በአኗኗርህ የአብ ልጅ፣ በሰውነትህ የድንግል ልጅ፣ በመለኮትህ የአብ ልጅ፣ በትስብእትህ የሰው ልጅ፣ ለወለደህና ለወለደችህ አንድ ልጅ እንደሆንህ አመንሁብህ፡፡ አቤቱ ጌታዬ የላይኛው ቀዳማዊ ልደት ሌላ፣ የታችኛው ሁለተኛው ልደት ሌላ፣ ሰማያዊ ልደት ሌላ፣ ምድራዊ ልደት ሌላ፣ የልዕልና ልደት ሌላ፣ የትሕትና ልደትህ ሌላ፣ የፊተኛው ልደትህ ከሕይወት እሳት የተገኘ የሕይወት እሳት፣ የኋለኛው ልደት ከሴት የተወለደ አካላዊ ቃል የፊተኛውን ፈለግሁት አላገኘሁትም፤ የኋለኛውን አሰብሁት አደነቅሁት፤ የፊተኛውን ሳልደርስበት አመሰገንሁት፤ የኋለኛውን በአብራከ ልቡናዬ ሰግጄ እጅ ነሣሁት፡፡ የፊተኛው ልደት በኋለኛው ልደት ታወቀ ተረዳ፡፡ የመለኮት ወገን በድንግል ወገን ተመሰገነ፡፡ ከድንግል ከተወለድህ ወዲህ ከአብ የመወለድህ ሃይማኖት ተገልጸልን፤ ከድንግል መወለድህን በሚናገር ትንቢት ከአብ መወለድ ተረዳ፡፡ ስለዚህ ባለመጠራጠር አመንሁ» ይላል አባ ጊዮርጊስ፡፡
ምን ጊዜም የልደቱ ነገር ድንቅ ምሥጢር ነው፤ ቅዱስ ኤፍሬም እንደሚለው ሰው የሆነ እርሱን አምላክ እንደሆነ በተረዳ ነገር አውቀነዋልና ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይረቅ ረቂቅ ነው፤ ድንቅ ነው፡፡ ቃልን ወሰነችው፤ ልደቱንም ዘር አልቀደመውም፡፡ በመወለዱም ድንግልናዋን አለወጠም፤ ቃል ከአብ ያለ ድካም ወጣ፤ ከድንግልም ያለ ሕመም ተወለደ፡፡ ለዮሴፍ የታየው መልአክም ከእርሷ በመንፈስ ቅዱስ የሚወለደው ያለመለወጥ ሰው የሚሆነው የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ይኸውም ከባሕርያችን እርግማንን የሚያጠፋልን ያለወንድ ዘር የተወለደልን፣ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ የተባለውም እነሆ ዛሬ ከቅድስት ድንግል ነፍስን ሥጋን ነሥቶ በተዋሕዶ በተገለጠ ጊዜ ተፈጸመ፡፡
አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ተመኘ፤ ቀኔንም /ልደቴን/ አይቶ ተደሰተ ተብሎ የተተነበየለት ዕለተ ምሥጢር ዕለተ ልደት ይህች ናት፡፡ እኛም ያየናት የድኅነት መጀመሪያ የዕለታት በኩር እንደሆነች ተረድተን የምናከብራት ደስታችንን የምንገልጽባት ይህች ዕለት ዕለተ አስተርዕዮ ናት፤ የማይታየው የታየባት፣ የማይዳሰሰው የተዳሰሰበት፣ የማይያዘው የተያዘባት፣ የማይታወቀው የታወቀባት፣ በትንቢት መነፅር አበው ያዩት ረቂት ብርሃን በአካል የተገለጠባት የአብንም ወላዲነት የተረዳንባት ዕለት ናት፡፡ በዚያ በአባቱ ቀኝ ሳለ በዚህ ከእናቱ ዕቅፍ ውስጥ ታየ፣ በዚያ ተሸካሚዎቹ እሳታውያን የሚሆኑ አራቱ እንስሳ ናቸው፡፡ በዚህም የተሸከመችው የፀሠራ አምስት ዓመት ብላቴና ድንግል ማርያም ናት፡፡ በዚያ ያለ እናት፣ አባት አለው፤ በዚህም ያለ ምድራዊ አባት፣ እናት አለችው፡፡
በዚያ በጽርሐ አርያም የሚደነቅ ከማይመረመር ከማይታይ አብ የመወለድ ምስጋና አለው፤ በዚህም በቤተ ልሔም የሚደነቅ ከድንግል የመለወድ ምስጋና አለው፡፡
በዚያ ኪሩቤልና ሱራፌል ከግርማው የተነሣ ይንቀጠቀጣሉ፤ በዚህ ግን ድንግል አቀፈችው፡፡ ሰሎሜም አገለገለችው፡፡ በዚያ የእሳት ዙፋን አለ፤ በዚህም የድንጋይ በረት አለው፤ በዚያ የትጉሃን ሥፍራ በሰማያት ያለች ኢየሩሳሌም አለችው፤ በዚህም የእንስሳት ጠባቂዎች ማደሪያ በዓት አለችው፡፡ በዚያ ገብርኤል በፍርሃት ይቆማል፤ በዚህም በሐሤት የምሥራች ይናገራል፡፡
በዚያ የእሳት ወላፈን ከአዳራሹ ይወጣል፤ በዚህም አህያና ላህም በእስትንፋሳቸው አሟሟቁት፡፡
እነሆ ከሰማይ ትጉሃን ይልቅ የሰው ልጅ ከበረ፤ እግዚአብሔር ከድንግል ማርያም ተወልዷልና፡፡ አንዱ የመወለዱ ምሥጢርም ይህ ነው፤ የሰውን ልጅ ከወደቀበት አንሥቶ በክብር ሰገነት ላይ ለማኖር የሰው ልጅም በጥንተ ተፈጥሮ ካገኘው ክብር የዛሬው በአዲስ ተፈጥሮ የሚያገኘው ክብር በልጧልና፡፡ የፊቱ በአምሳል በመፈጠር የተገኘ ነው፤ የአሁኑ ግን በተዋሕዶ በመወለድ የሚገኝ ነውና፡፡ የፊተኛው ሥጋ በጸጋ ከብሮ የተገኘ ነበር፤ አሁን ግን ሥጋ የባሕርይ አምላክ ሆኖ የተገኘ ከብር ነውና፡፡ የፊቱ ያለ ባሕርይ (በጸጋ) መከበር ነበር፤ ዛሬም በራስ ባሕርይ መከበር ነውና፡፡
ከአቂበ ሕግ በመውጣት ከወረደበት በታች የወረደበት ውርደት የለም፤ ዛሬም በተዋሕዶ በተደረገው ምሥጢር ከከበረበት በላይ ክብር የለም፤ በልዑል ዙፋን እስከመቀመጥ ደርሷልና፡፡
ትናንት ያልነበረ ሰውነት ከዘመን በኋላ የተገኘ ሲሆን፣ መለኮትን በመዋሓድ ሁሉን ግዙ ተብሎ ጥንት በጸጋ ከተሰጠው ግዛት በላይ ግዛቱ ድንበር የማይመልሰው ዘመን የማይለውጠው ከምድር እስከ ሰማይ የመላ ግዛት ሆነለት፡፡ መለኮት ወደሱ የመጣበት አመጣጥ ድንቅ የወደደበት ፍቅር ልዩ፣ በባሕርይ መወለዱም ዕፁብ ነውና ይህም ልደቱ ያለ ዘር የተደረገ ነው፡፡ ስለምን ቢሉ ቀዳማዊ ልደቱ የሚገለጥበት ነውና አምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ከእመቤታችን ያለአባት ያለዘር መወለዱ ቅድመ ዓለም ያለእናት ለመወለዱ ምሥክር መታወቂያ ነውና፡፡ ለዚህም ነው የመጀመሪያው ልደት በሁለተኛው ልደት ታወቀ የሚባለው፡፡ የሁለተኛው ልደት ክብርና ምሥጢርም ከአእምሮ በላይ በመሆኑ በመጀመሪያ ልደት ታወቀ ተረዳ፡፡ ድንቅ የሚሆን ልደቱም በምድር ላይ አባት ስለሌለው ሰው የመሆን መንገድ የጐደለው አይደለም፤ ብቻዋን ከምትሆን ከድንግል ፍጹም ሰው ሆኖ ተወለደ እንጂ ከአዳም ጐን እናት ሳይኖራት ፍጽምት ሴት እንደወጣች ፍጹም ሰው ሆነ፡፡ ማቴ 2·1-12 ሉቃ 2·8-16
የአብ ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው በሆነ ጊዜ የሕፃናትን ጠባይ ሳያስቀር የሰውነትን የጠባይ ሥርዓት እየፈጸመ ከዕለተ ፅንሰ ጀምሮ እስከ ዕለተ ልደት ድረስ በየጥቂቱ በማሕፀነ ማርያም ውስጥ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ቆይቶ ሕፃናት ሲወለዱ የሚሰማቸው ሳይሰማው ተወለደ፡፡ ሲወለድም በግብረ መንፈስ ቅዱስ በድንግልና እንደተፀነሰ በድንግልና ተወለደ እንጂ እናቱንም የድንግልና መለወጥ፣ በወሊድ ጊዜ ጭንቅና ምጥ አላገኛትም፡፡ ሕዝ 34·1 የመውለዷ ክብር ገናንነትም ከአእምሮ በላይ ነው፤ ይህ ተብሎ ሊነገር አይችልም፤ ያለ ምጥ ወልዳዋለችና፡፡
የዲያብሎስና የተከታቹን ሥነ ልቡና የሰበረ በፍርሃት እንዲዋጡ ማንነታቸውን እንዲያጡ ያደረገው አስደናቂው ልደት ጌታ በቤተ ልሔም ሲወለድ ቤተ ልሔም በብርሃን ተከባ፣ በመላእክት ምስጋና ደምቃ፣ በምሥራች ተመልታ ባየ ጊዜ የሰው ልጅ ጠላት ዲያብሎስ ይህን የልደት ምሥጢር ለማወቅ ለመመራመር ወደ ላይ ወደ ዐየር ወጣ፤ ከመሬት በታች ወደ አለው አዘቅት ወረደ፤ ዓለምን በሙሉ ዞረ፤ ግን ሊያውቅ አልቻለም፡፡ ባለማወቅ ሠወራቸው ተብሎአልና መርምሮ ማወቅ ባይቻለው የፍርሃት ጥርጥር መጠራጠር ጀምረ እንዲህ በማለት፤ የኢሳይያስ ድንግል የድንግልና ልጇን ወለደች፤ ተአምረኛው ሙሴ ሲወለድ እንዲህ ያለ ችግር አልገጠመኝም ብዙ ክብር ያላቸው ነቢያት ተወልደዋል፤ እንደዚህ ማንነቴን የሚያሳጣ ከዕውቀቴ በላይ የሆነ ችግር አልገጠመኝም ነበር፡፡ ዛሬ ግን ዓለምን በሙሉ ዞርኳት፤ ይልቁንም ቤተ ልሔምን፡፡ ነገር ግን በእሷ የተደረገ የዚህን ልደት ምሥጢር ተመራምሬ ልደርስበት አልቻልኩም፡፡ ድካሜም ውጤት አልባ ሆኖአል ብሎ ወደ ወገኖቹ ቢመለስ በግምባራቸው ፍግም ብለው ወድቀው አገኛቸው፡፡ ለጊዜው እነሱን አይዟችሁ መንግሥቴ ከእኔ አታልፍም አላቸው፡፡ ከተደረገው ተአምራት ሁሉ በላይ ተአምር ቢደረግም አልፈራም ነበር፡፡ ትንቢቱ ቢደርስ ድንግል ልዑሉን ብትወልድ ይሆናል እንጂ እንዲህ ያለ ኃሣርና ውድቀት ያገኘን ምን አልባት ቤተ ልሔም አምላክ ተወልዶብሽ ይሆን ብሎ ተስፋ ባለመቁረጡ ተመልሶ ሄደ፡፡ መላእክት በአንድነት ሆነው በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እነሆ በምድር ላይ ለሰው የሰላም መሠረት ተጥሏልና እያሉ ሲያመሰግኑ፣ ደግሞ መልአኩ ለእረኞች እነሆ ለእናንተ ደስታ የሚሆን ምሥራች እነግራችኋለሁ፡፡ የዓለም መድኃኒት የሚሆን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዳዊት ባሕርይ በዳዊት ሀገር ተወልዷልና፤ ምልክቱም አንዲት ድንግል ልጅ ሕፃኑን በክንዷ ታቅፋ ታገኛለችሁ ሲል ሰምቶ በሐዘን ላይ ሐዘን ተጨመረበት፡፡ ቢሆንም ግን እርግጡን ለማወቅ የልደት ዘመን መቼ እንደሆነ ለመረዳት የነቢያትን መጻሕፍት ትርጓሜ ወደሚያውቁ ወደ አይሁድ ሊቃውንት ዘንድ ፈጥኖ ሄዶ ስለ ክርስቶስ መወለድ አንሥቶ ያስረዱት ዘንድ አጥብቆ ጠየቃቸው፡፡ የጠየቃቸውን እንደማይሸሸጉት ተስፋ አድርጓልና እነሱም በይሁዳ አውራጃ በምትገኝ በቤተ ልሔም የዓለም መድኃኒት ይወለዳል ብለው ተናግረዋል ብለው መለሱለት፡፡ ሚክ 5·2 የዳንኤል ሱባዔስ ደርሷል? አላቸው፡፡ «አዎ» አሉት፡፡ «ይህ ሁሉ እንደደረሰ በምን አውቃለው?» አላቸው፡፡ የልደቱ መታወቂያ የጊዜው መድረስ የሚታወቅበት ከልደቱ ጋር ቀጠሮ ያለው ልደቱን የሚጠባበቅ ስምዖን የሚባል አለ፡፡ እሱን ጠይቀህ ተረዳ አሉት፡፡ ስምዖን ለልደቱ ምልክት የሆነበት ምክንያት ምንድ ነው? አላቸው፡፡ ለንጉሡ በጥሊሞስ መጻሕፍት ከእብራይስጥ ወደ ፅርዕ ሲተረጉም ኢሳይያስ እነሆ ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች ባለው የትንቢት ቃል በተሰነካከለ ጊዜ የእግዚአብሔርም መልአክ ሕፃኑን ሳታይ አትሞትም ብሎታልና ሉቃ 2·26 አሉት፡፡ ሒዶ አንተ የተባረክህ ሽማግሌ ተስፋ የምታደርገው መድኅን ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መምጫው ደርሷልን? አለው፡፡ አዎ መጥቷል፤ አለው፡፡ በምን አወቅህ? አለው፡፡ በኢሳይያስ ትንቢት በተሰነካከልኩ ጊዜ በሕማም ታሥሮ የነበረው እጄ ተፈትቷልና በዚህ አወቅሁ አለው፡፡ በመልክተኞቹ ይህን ከሰማ በኋላ እውነትም ዛሬ ገና የእኔ ክብር የሚዋረድበት፤ ያዋረድሁት አዳም ከእኔ ባርነት ነጻ የሚወጣበት ቀን ደርሰ አለ፡፡ የአዳም ልጅ ሆይ ጠላት ዲያብሎስ ላይጠቅመው ላይረባው ይህን ያህል ስለ ልደቱ ምሥጢር ለማወቅ አቀበቱን ከወጣ ቁልቁለቱን ከወረደ፣ ዓለምን በመዞር ከተንከራተተ፣ አንተማ ምን ያህል ልትደክም አይገባህ? የማንነትህ ህልውና ነውና የልደቱን ነገር ልታውቅ ይገባሀል፡፡ ግን በምርምር አይደለም፤ እንደ እረኞች በእምነት ነው እንጂ፡፡ እረኞች በምርምር ሳይሆን በምልክት ተረድተው ልደቱን አወቁ፤ አገኙትም፡፡ አንተም ከመጻሕፍት አንብበህ ከመምህራን ተረድተህ የእረኞች ምሥራች የእኔ ነው ብለህ ነው እንጂ በልደት የሠለጠነ አምላክ በጎል ተጥሎ፣ በጨርቅ ተጠቅልሎ፣ በግርግም ተኝቶ አይቶ ዲያብሎስ ፈራ፡፡ አዳም ግን የልዑልን ትሕትና አይቶ ኦ ወዮ ለዚህ ምሥጢራዊ ልደት አንክሮ ይገባል፤ መርምረው ሊያውቁት አይቻልምና፡፡ አምላኬ ለእኔ ሲል የተወለደው ይህ ልደት ብቸኛ ነው ብሎ አመሰገነ፡፡ ብቸኛ ያሰኘውም በዚህ ዓለም እናት አባት አንድ ካልሆኑ ልጅ አይወለድም፤ እሱ ግን ከአባት ያለ እናት ከእናት ያለ አባት ተወልዷልና፤ የዚህ ዓለም ልጅ በዘር በሩካቤ ይወለዳል፤ እሱ ግን ያለ ዘር ያለ ሩካቤ ተወልዷልና፡፡
የዚህ ዓለም ልጅ ልጅ ተብሎ ኑሮ የወለደ ጊዜ አባት ይባላል፤ እሱ ግን ለዘለዓለም ወልድ እየተባለ ይኖራልና፡፡
ይህች ዕለት ለፍጡራን የሚሆን ሁሉ ዕረፍት የሚሆን ወልድ ሰውነቱን በልደት የገለጠበት ዕለት ስለሆነች ፍጡራን ሁሉ መልካም ዜና ሰሙ፤ ደስም አላቸው፡፡ ደስታቸውንም ገለጡ፡፡ ሊቁ እንዳለው ሰው በመሆንህ ሥጋን በመዋሓድህ ወደዚህ ዓለም በመምጣትህ ፍጥረት ሁሉ ደስ አላቸው እንዳለ፡፡
መላእክት ባጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ በድንግል እቅፍ አይተው ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ አሉ፡፡
ሰዎችም የፍጥረት ባለቤት እነሱን ለማዳን ልዑል ሲሆን በራሳቸው ባሕርይ በትሕትና ተወልዶ አይተው ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት አሉ፤ እንሰሳት አራዊት ለሰው በተደረገው ይቅርታና ክብር እስትንፋሳቸውን አምኀ አቀረቡ፡፡ ስሙን እየጠሩ ለዓለም መሰከሩ፡፡ ለምሳሌ ያህል ሚዳቋን ብንወስድ እንኳ ዮም ተወልደ መድኅነ ዓለም፤ ዮም ተወልደ ከሣቴ ብርሃን፤ ዮም ተወልደ ቤዛ ኵሉ ዓለም የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ እያለች ስትዘምር ታይታለች፡፡ አስተዋይ አዕምሮ ካለ ይህ ድንቅ ምሥጢር ነው
ፊተኛ ልደቱ ፍጡራን የማያውቁት፣ በምሥጢር መሠወሪያ የተሠወረ ነው፡፡ ኋለኛ ልደቱ ግን ለእረኞች ተገለጠ፡፡ ለጥበብ ሰዎችም ታየ፡፡ በዓለምም ተሰማ፡፡ ልጄ ወንድሜ ሆይ ቃል /ወልድ/ በምድራችን ተሰማ፤ መታየቱም የታመነ ሆነ፡፡ በአባቱ መልክ /በአምላክነት ባሕርይ/ ተመላለሰ እንዳለ፡፡ መኃ 2·12-13 ጌትነቱን ለሚያምን ሁሉ አባቶቻችን በእሳት አምሳል ያዩትን እኛ ተገልጦ አየነው፤ ቃሉንም ሰማነው እያልን እንመሰክራለን፡፡ ከዚህ ሁሉ ጋር ሰው ሆነም ስንል በፍጹም ተወሕዶ ነው፤ ተዋሕዶ ማለት አንድ መሆን መዋሐድ አለመለያየት፣ የማይታየው ከሚታየው፣ የማይወስነው ከሚወሰነው፣ ጋር አንድ ሆኖ ለዘለዓለም ለመኖር አካላዊ ቃል እግዚአብጠር ወልድ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በማሕፀነ ማርያም አድሮ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወለዱን ነው፤ ወንጌላዊው ዮሐንስም ቃል ሥጋ ሆነ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ ያለው ይህን ፍጹም ተዋሕዶ ነው፡፡ ይህም ተዋሕዶ አካላዊ መሆኑን ይገልጻል፤ ሰው ሆኖ ተወልዷልና፡፡
ስለዚህ በተዋሕዶ ለተፈጸመው ለልደት ምሥጢር አንክሮ ይገባል፡፡ ያለዘርዓ ብእሲ መፀነስ፣ ያለ ተፈትሖ መወለድ፣ ዘመን በማይቆጠርለት ሕፃን አፍ ከድንግል ጡት ወተት መፍሰስ፣ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ለመቅደስ ካህናት ያልተደረገ ለከብት እረኞች ሰማያዊ ምሥጢር መገለጥ፣ ከሩቅ ምሥራቅ ተነሥተው የጥበበኞች በኮከብ እየተመሩ ወደ ቤተልሔም መሔድ፣ አንክሮ ይገባል፤ ከነገሥታት እጂ ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤ መቀበልም ድንቅ ያሰኛል፡፡ በዚያ ሰማያውያን ካህናት በወርቅ ማዕጠንት ያቀረቡትን የዕጣን መዓዛ ይቀበላል፡፡ በዚህም ዛሬ ከሰብአ ሰገል ይህን ተቀበለ፤ መላእክትና እረኞች ዝማሬን፣ እንስሳት እስትንፋሳቸውን፣ ኮከብ ብርሃኑን አቀረቡ፡፡ እኛም ይህን ተረድተን አሕዛብ ሁላችሁ በእጃችሁ አጨብጭቡ፤ በደስታም ቃል ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ ስሙንም አመስግኑ፤ ለጌትነቱም ምስጋና አቅርቡ እንላለን፡፡ መዝ 65·1
በአዳም በደል ያልተጸጸተ በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ያልተደሰተ የለምና የዚህ ልደት ዓላማም ሰውን ከስሕተቱ መልሶ የእግዚአብጠር ለማድረግ ነው ዮሐ 1·12-14 ይህንም ሲያደርግ አስደናቂውን ምሥጢር እያደረገ ነው፡፡ በተወለደ ጊዜ በቤተልሔም ወተትን ከድንግልና አምላክነትን ከሰውነት፣ ሕቱም ማሕፀን ከእናትነት ጋር አንድ አድርጎ አሳይቷናል፡፡ በአምላክነት ሥራ ካልሆነ በስተቀር ወተትና ድንግልና፣ እናትነትና አገልጋይነት፣ አምላክነት እና ሰውነት፣ በአንድነት ሊገኙ አይችሉምና እግዚአብሔርን አመስግኑት ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት እንላለን፡፡ መዝ 65·3 በሥጋዊ ጥበብ ተራቀው ሥጋዊውን ዓለም ያወቁ የአግዚአብሔርንም ሕልውና በእምነት ሳይሆን በጥበባቸው እናውቃለን ለሚሉ ሁሉ ከሰብአ ሰገል ተምረው በእምነት ሊያውቁት ይገባል፤ የተወለደው ለእነሱም ነውና፡፡
ሆኖም ግን መምጣቱን በተስፋ ለሚጠባበቁ የልደቱን ነገር በፍጹም እምነት ለተቀበሉ ሁሉ እነሆ ያማረ የምሥራች በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩት ሁሉ የሕይወት ብርሃን ተወልዷልና ደስ ይበላችሁ፡፡ በብርሃኑ ጨለማ ተወግዷልና እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ፡፡ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው ተብሎ እንደተነገረ የእስራኤል ንጉሥ በእስራኤል ልጅ አድሮ የዳዊት አምላክ ከዳዊት ልጅ ሥጋን ተዋሕዶ ከቀድሞ ጀምሮ ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ተልከው መንፈስ ቅዱስ እንዳናገራቸው ዓለምን ለማዳን ከጽዮን የሚወጣ ከያዕቆብ በደልን የሚያርቅ ጌታ ይወርዳል፤ ይወለዳል በማለት በየወገናቸው በየዘመናቸው የተናገሩት ትንቢት እነሆ ዛሬ ተፈጸመ፡፡ እሱም እናንተን ከመውደዴ የተነሣ ሰው ለመሆን ወደናንተ መጣሁ፡፡ በሕፃንም መጠን ተወለድኩ፤ በጨርቅም ተጠቀለልኩ፤ ፍቅሬንም ገለጥኩላችሁ ብሏልና፣ እርስ በርሳችሁ የምትፋቀሩ የወንጌል ልጆች ወንድሞች ሆይ ይህን ትሕትናና ፍቅር አይተን እርስ በርሳችን እንፋቀር፡፡ ዮም ተወልደ ፍቅር ወሰላም ዮም ተወልደ ቤዛ ኵሉ ዓለም እግዚእ ወመድኅን ዮም ተወልደ ከሣቴ ብርሃን እያልንም እንዘምር፡፡

– ስብሐት ለእግዚአብሔር አብ
– ልጁን ውረድ ተወለድ ብሎ ለሰደደው ለአብ ወላዲ አሥራፂ ተብሎ መመስገን ይገባዋል፡፡
– ለወልድም ተወለደ ተብሎ መመስገን ይገባዋል፡፡
– ማሕየዊ ለሚሆን ለመንፈስ ቅዱስም ሠራፂ ተብሎ መመስገን ይገባዋል
– ሥጋን ላጸናው ለአብ ለተዋሓደ ለወልድ ላዋሓደ ለመንፈስ ቅዱስ ዛሬም ዘወትር በእውነት ምሥጋና ይገባዋል፡፡
– ለዓለሙ ሁሉ ሕይወትን ለወለደች ለድንግል ማርያም ምስጋና ይገባል፤ የድኅነታችን መመኪያ ናትና

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

 ከደቀ መዝሙር አባ ሳሙኤል ንጉሤ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም አዳሪ ት/ቤት የሊቅ ተማሪ

መንፈሳዊ ኮሌጆችና “ደቀ መዛሙርቱ” ምን እና ምን ናቸው?

ኅዳር 21 ቀን 2008 ዓ.ም

ክፍል አምስት

የተሐድሶ መረብ አድማስና የትኩረት አቅጣጫዎች በሚል ባለፉት ሁለት ዕትሞች ስለ አዲስ አበባ፣ ስለ ሰሜን ኢትዮጵያ፣ ስለ ምዕራብና ደቡብ ኢትዮጵያ የተሐድሶ መናፍቃን አቅርበንላችሁ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ መንፈሳዊ ኮሌጆችን መሠረት ያደረገውን የተሐድሶ መናፍቃንን ዒላማ ከብዙው በጥቂቱ፣ ከረጅሙ በአጭሩ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ መልካም ንባብ፡፡

ተሐድሶ መናፍቃን ቤተ ክርስቲያንን ፕሮቴስታንት የማድረግ ዕቅዳቸውን ዕውን ለማድረግ ትኩረት ካደረጉባቸው ተቋማት መካከል የመጀመሪያዎቹና ግንባር ቀደሞቹ የመንፈሳዊ ኮሌጆች ደቀ መዛሙርት€ ናቸው፡፡ እስካሁን በማኅበር ደረጃ የሚንቀሳቀሱት ከሃያ አምስት በላይ የተሐድሶ መናፍቃን ድርጅቶች ቀላል የማይባሉ አባሎቻቸው በመንፈሳዊ ኮሌጆች ተምረው ያለፉ፣ ይሠሩ የነበሩ ወይም በመሥራት ላይ የሚገኙ እንዲሁም የሚማሩ ናቸው፡፡ በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ የሚታየው የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ከተማሪዎች ምልመላ እና ተማሪዎቹ ወደ ኮሌጆቹ ሲገቡ ከሚደረግላቸው ቅበላ ጀምሮ የሚሠራ ነው፡፡ የገንዘብ እጥረት የሚያጋጥማቸውን ደቀ መዛሙርት ደግሞ በድጋፍ ስም ይቀርቧቸዋል፡፡ መጻሕፍትንና ሌሎች አስፈላጊ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን በመዋዋስ ስም ግንኙነት በመፍጠር ኦርቶዶክሳዊ ተማሪዎችን ወደ ቡድናቸው ያስገባሉ፡፡

ከተለያዩ መንፈሳዊ ኮሌጆች የተመረቁ €œደቀ መዛሙርት€ ኅቡዕ ቡድን መሥርተው በቤተ ክርስቲያን ላይ ሰፋ ያለ ዘመቻ ከፍተዋል፡፡ ቡድኑ ዓላማውን ለማሳካት በተለያዩ ቦታዎች ላይ ተወካይ በማስቀመጥ ሥራውን ይሠራል። ይህ ስውር ቡድን በመጨረሻ ላይ ለማሣካት ዓላማ አድርጌ ተነሣኋቸው የሚላቸው የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በራሳቸው መንገድና የኑፋቄ አቅጣጫ በመለወጥ ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ ካስቀመጣቸው የማስመሰያ ግቦች፡-

ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ቃል በምልዓት እንዲኖርባቸው ማድረግ፣

በሥነ መለኮት ትምህርት ገንቢ ዕውቀት ያላቸውን አገልጋዮች በማደራጀት የወንጌልን እን ቅስቃሴ ማስፋፋት፣

 በቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ ከስንዴ ጋር አብረው የገቡትን ትምህርቶችና መጻሕፍት (አስተምህሮዎች) ማስወገድ፣

 ቤተ ክርስቲያን ምንም ከማይጠቅም ወግ፣ ልማድ እና በብልሃት ከተፈጠሩ ተረታዊ ትምህርቶች ተለይታ እውነት የሆነው ክርስቶስ እንዲሰበክ ማድረግ፣

 የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት በክርስቶስ ጥላ ሥር ተሰብስበው እንዲያመልኩና በአንድ እንዲተባበሩ ማድረግ፣

 ወንጌል በእያንዳንዱ ቤት አንኳኩቶ በመግባት መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ፣

 ወጥና ተከታታይ ትምህርትን በማዘጋጀት ወጣቶችን፣ ሕፃናትንና አረጋውያንን በማነቃቃት ለዓለም ብርሃን የሆነውን የጌታን ቃል ለሁሉም እንደየአቅማቸውና እንደየደረጃቸው ማዳረስ፣

 በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት መሥራት፣

 የወንጌልን ተልእኮና ለውጥ ሊያፋጥን በሚቻል መልኩ የተለያዩ ተቋማትን ማእከል በማድረግ መንቀሳቀስ፣

 የቤተ ክርስቲያን ለውጥና ዕድገት የሚሹትን ሁሉ ማደራጀት፣

 በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እራሱን የቻለ ማኅበር ማቋቋም የሚሉ ናቸው፡፡ (ምንጭ፡- የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ገጽ ፺፬)

እነዚህን እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች በመደርደር €œቤተ ክርስቲያናችን እስካሁን ድረስ ዘመናትን የፈጀችው ወንጌልን ስትሰብክ ሳይሆን ስለ ቅዱሳን ስታስተምር ነው፤ አሁን መስበክ ያለብን ክርስቶስን ነው€ የሚለውን ተሐድሶ መናፍቃን ያራምዱት የነበረውን የፕሮቴስታንት አስተምሮ ይዞ የተነሣ ነው። ለቅዱሳን የማስተማር ጸጋ ስለሰጣቸው ስለ ክርስቶስ ማስተማር መሆኑን መረዳት ይገባቸዋል ቤተ ክርስቲያን ጉልላቷ ስለሆነው ስለ ክርስቶስ ሳታስተምር የዋለችበት ዕለት ያለ ለማስመሰል መሞከራቸው ስሕተት ነው፡፡ ዓላማዬን ያሳኩልኛል ብሎ ካሰማራቸው ሰዎች ሲገልጽ ደግሞ እንዲህ ብሏል፡፡ ሥራውን የሚሠራው መንፈስ ቅዱስ ሆኖ የለውጥ መሪ የሚሆኑ በእምነትና በዕውቀት የታመነባቸው የነገረ መለኮት ተማሪዎች፣ ልዩ ልዩ መምህራን፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግሉ ቀሳውስትና ዲያቆናት፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ምእመናን፣ ልዩ ልዩ ድርጅቶች ናቸው፡፡ ይህ ሲባል በመንፈሳዊ ለውጥ የሚሠሩትን አካላትም ያካትታል፡፡

ቡድኑ በዋነኝነት በመንፈሳዊ ተቋማት ያሉና ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎችን ቢያማክልም በግላቸውና በማኅበር ተጀራጅተው ከሚንቀሳቀሱ ማኅበራት ጋር አብሮ ይሠራል። ይህ ማኅበር ዓላማውን ለማሳካት የምንፍቅናውን መርዝ ለመርጨት ያሰበባቸው ቦታዎች መንፈሳዊ ኮሌጆች ብቻ ሳይሆኑ፤ የካህናት ማሠልጠኛ ሥፍራዎች፣ ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ የቤተ ክህነት መሥሪያ ቤቶች፣ የመንግሥት የትምህርት ተቋማት እና ማኅበራት ናቸው፡፡

ለእንቅስቃሴው አስተዋጽኦ ያደረጉ ሁኔታዎች

በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ ያለው የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ እንዲስፋፋ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ሁኔታዎች አሉ፡፡ ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታዩ ከኮሌጆቹ አስተዳደራዊ መዋቅርና አሠራር እንዲሁም ከተማሪዎች ክትትል ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

፩.አስተዳደራዊ ችግሮች

መንፈሳዊ ኮሌጆች ላይ የሚከሠቱት የአብዛኛዎቹ ችግሮች መነሻቸው አስተዳደራዊ ችግር ነው፡፡ ይህ የሁሉም ችግሮች ምንጭ ነው፡፡ መንፈሳዊ ኮሌጆች አስቀድመው አስተዳደራዊውን ችግር ቢፈቱ ሌሎችን በቀላሉ መፍታት ይችላሉ፡፡ ከገንዘብ አያያዝ፣ ከተማሪዎች ጋር ባለው መልካም ግንኙነት፣ ከመምህራን ቅጥር እና ከአስተዳደር ሓላፊዎች ምደባ ጋር ተያይዞ ብዙ ችግሮች ይታያሉ፡፡ እነዚህ አስተዳደራዊ ችግሮች ተቋሙ ዋና ጉዳዩ የሆኑት ደቀ መዛሙርትን ዘንግቶ ሌሎች ጉዳዮች ላይ እንዲጠመድ ያደርጉታል፡፡ ተሐድሶ መናፍቃኑ ደግሞ ይህንን ክፍተት በደንብ እየተጠቀሙበት ነው፡፡ አስተዳደራዊውን ችግር ሃይማኖታዊ አስመስሎ ከማቅረብ ጀምሮ በየጊዜው ለአስተዳደሩ የቤት ሥራ የሆኑ ጉዳዮችን በመብት ስም እያነሡ እነርሱ የውስጥ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ይተጋሉ፡፡

፪.የገንዘብ እጥረትና የአጠቃቀም ችግር

ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንደ አንድ ችግር የሚነሣው የገንዘብ እጥረት ነው፡፡ በእርግጥ ቤተ ክርስቲያን ከማንኛውም አካል በላይ የሆነ ሀብት አላት፡፡ ይህም ሀብት የልጆቿ ዕውቀት፣ ጉልበትና ገንዘብ ነው፡፡ ይህንን በአግባቡ አቀናጅቶ የሚያሠራ መዋቅር፣ አሠራርና ስልት ባለመዘርጋቱ ግን ብዙ አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚሰጥባቸው ጠፍቶ ሲዘጉ ይታያሉ፡፡ ከተማ ላይ አብያተ ክርስቲያናት በሚልዮንና ቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሲያንቀሳቅሱ፣ እያንዳንዳቸው ከአንድ መቶ በላይ አገልጋዮች ሲኖሯቸው በገጠር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ በአንጻሩ ዕጣንና ጧፍ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን የሚከፍት አንድ ካህን አጥተው ሲቸገሩ ይታያል፡፡ ይህም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማእከላዊ የሆነ የገንዘብ አያያዝ ባለመኖሩ የተከሠተ ችግር ነው፡፡

የዚህ ችግር ውጤትም በአጥቢያዎች ውስጥ ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ በሚገኙ ተቋማትም የሚታይ ነው፡፡ መንፈሳዊ ኮሌጆች በዚህ ከሚፈተኑት የቤተ ክርስቲያን ተቋማት መካከል ናቸው፡፡ ኮሌጆቹ እንደ ተቋም ለአገልግሎቱ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ለማሟላት የገንዘብ እጥረት ያጋጥማቸዋል፡፡ ይህ ክፍተት ደግሞ በእርዳታ ስም መናፍቃኑ ወደ ተቋማቱ እንዲገቡ በር ከፈተላቸው፡፡ በመንፈሳዊ ኮሌጆች የሚማሩ ደቀ መዛሙርትም ወደ ሌላ እምነት እንዲገቡና የተሐድሶ መናፍቃኑን ጎራ እነዲቀላቀሉ ከሚያደርጓቸው ችግሮች አንዱ የገንዘብ እጥረት ነው፡፡

፫.የምልመላ መስፈርት

ተማሪዎች ወደ ኮሌጆች የሚገቡት ከዚህ በፊት የነበራቸው ሰብእና (ማንነትና ምንነት) ተጠንቶና ታውቆ ሳይሆን ሀገረ ስብከት ላይ ወደ መንፈሳዊ ኮሌጆች ለመላክ ሓላፊነት ካላቸው አካላት ጋር ባላቸው ቅርበት ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ብዙ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ፣ ትልቅ አቅም ያላቸው ሰዎች እየቀሩ በጓደኝነት፣ በዝምድና፣ አለፍ ሲልም በጥቅማ ጥቅም ወደ ኮሌጆች የሚገቡት ተማሪዎች በርካታ ናቸው፡፡ በዚህ መልኩ ወደ ኮሌጆች የሚገቡ ሰዎች ደግሞ ዐዋቂ ቢሆኑ እንጂ ክርስቲያን መሆን አይችሉም፡፡ ዐዋቂነትና መራቀቅ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ዓላማ አይደለም፡፡ ለቤተ ክርስቲያን በንባብ ላይ ከሚራቀቀው ዐዋቂ ይልቅ፣ እየተንተባተበ ወልድ ዋሕድ ብሎ የሚመሰክር ኦርቶዶክሳዊ ደቀ መዝሙር ያስፈልጋታል፡፡

በተጨማሪም ወደ ኮሌጆች የሚገቡበት የትምህርት መስፈርት ተመሳሳይ ባለመሆኑ በክፍል ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት ለአንዳንዶቹ የሚጠጥርባቸው ለሌሎቹ ደግሞ የሚመጥናቸው አልሆን ይላል፡፡ ለምሳሌ በኮሌጆች ውስጥ በመደበኛው ዲፕሎማ መርሐ ግብር ከዐሥረኛ ክፍል ጀምሮ እስከ ዲግሪ ድረስ፣ ከፊደል ተማሪ እስከ መጻሕፍት መምህራን ድረስ አንድ ላይ በአንድ ክፍል የሚማሩበት ዕድል አለ፡፡ ባለዲግሪው በእንግሊዝኛ የሚሰጡ ትምህርቶች ላይ የተሻለ ግንዛቤ ሊኖረው ሲችል፣ ዐሥረኛ ክፍል የጨረሰው ከትምህርቱ በላይ ፈታኝ የሚሆንበት እንግሊዝኛ ቋንቋ ማጥናቱ ይሆናል፡፡ ወደ ግእዝ ቋንቋ ስንመጣም ችግሩ ተመሳሳይ ነው፡፡ የቅኔ እና የመጻሕፍት መምህራን ግእዝን ካልቆጠረው ጋር አብረው ይማራሉ፡፡

፬.የትምህርት አሰጣጥ

ኮሌጆች ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት አብዛኛው ዕውቀት ተኮር እንጂ ምግባር ተኮር አይደለም፡፡ የትምህርት አሰጣጡም ተማሪዎች ጉዳዩን ዐውቀውት ማስተማር እንዲችሉ ማድረግን እንጂ እንዲኖሩት ማድረግን ዓላማው ያደረገ አይደለም፡፡ የነገረ መለኮት ምሩቅ ከሌሎች ሰዎች የሚለየው በዕውቀቱ እንጂ በሕይወቱ እንዲሆን የተሠራው ሥራ አናሳነው፤ ወይም የለም፡፡ ይህ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለግለሰቡ ሕይወት አንዳች ረብ የሌለው መጻሕፍትን ይዞ እንደማይጠቀምባቸው ቤተ መጻሕፍት መሆን ነው፡፡

ትምህርቱም በመምህራን እውነተኛነት፣ ታማኝነትና ክርስትና ላይ የተመሠረተ እንጂ የኮሌጆቹ አስተዳደሮች ስለሚሰጠው ትምህርት የሚያደርጉት ክትትል የለም፡፡ ኮሌጆቹ አንድ መምህር ክፍል መግባት ወይም አለመግባቱን፣ ገብቶ የሚያስተምረው የትምህርት ይዘት ኦርቶዶክሳዊ ዶግማና ቀኖናን የተከተለ መሆን አለመሆኑን የሚቆጠ ጣጠሩበት ሥርዓት የላቸውም፡፡ ይህ ደግሞ ማስተማር መንፈሳዊ አገልግሎት ሳይሆን የገንዘብ ማግኛ ሥራ አድርገው የሚቆጥሩ ብዙ መምህራን እንዲኖሩ የሚያደርግና ያደረገ አሠራር መፍጠር ችሏል፡፡

፭.የተማሪ አያያዝ

ኮሌጆች ምግብ፣ ልብስ፣ መጠለያና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮችን አሟልተው በመደበኛው የቀን መርሐ ግብር የሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ባላቸው ትርፍ ጊዜ የት እንደሚሔዱ፣ ምን እንደሚሠሩ፣ ከማን ጋር እንደሚውሉ ወዘተ የሚደረገው ቁጥጥር በጣም የላላ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ትምህርት የማይሰጥባቸውን ዕለታት ተማሪዎች መገኘት ከማይገባቸው አልባሌ ቦታዎች ጀምሮ ወደ መናፍቃን አዳራሽ ሳይቀር ይሔዳሉ፡፡ ለምሳሌ በከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ሲማሩ ከነበሩ የተወሰኑ ተማሪዎች መካከል እሑድ ከዐራት ሰዓት ጀምሮ የሚሔዱበት የመናፍቃን አዳራሽ አለ፡፡ ሰፊ እረፍት ሲኖራቸው ደግሞ አዲስ አበባ እንዲመጡ በማድረግ በአሸናፊ መኮንን ሰብሳቢነት በኮሌጁ ውስጥ ስለሚሠሩት የኑፋቄ ሥራ ሥልጠና ይሰጣቸዋል፡፡ የተለያዩ የመናፍቃን መጻሕፍትን በኮሌጁ ውስጥ በነጻ ያድላሉ፣ “የአሸናፊ መኮንንን መጻሕፍት ያላነበበ ተማሪ የነገረ መለኮት ተማሪ አይባልም” የተባለ እስከሚመስል ድረስ በነፍስ ወከፍ ለሚከተሏቸው ሰዎች ሁሉ ይታደላል፡፡ ይህ ሁሉ የሚያሳየው የኮሌጆቹ አስተዳደሮች የሚያስተምሯቸው ሰዎች ሕይወት ገዷቸው የሚሠሩት ሥራ እንደሌለ ነው፡፡

፮.ከወጡ በኋላ ያለው ክትትል ማነስ

ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ከሦስቱም መንፈሳዊ ኮሌጆች ልጆችን ታስመርቃለች፡፡ ነገር ግን በኮሌጆች ውስጥ ቆይተው መውጣታቸውን እንጂ በትክክል የሚገባቸውን ነገር (ዕውቀትን ከሥነ ምግባር አስተባብረው) ይዘው መውጣታቸውን፣ ከወጡም በኋላ በተመደቡበት ሀገረ ስብከት ቤተ ክርስቲያን የምትፈልግባቸውን ያህል እየሠሩ መሆኑን፣ የሚያስተምሩት ትምህርት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት የተከተለ መሆኑን የምታውቅበት ሥርዓት አልዘረጋችም፡፡ እስካሁን ስንት ደቀ መዛሙርት ተመረቁ? ከተመረቁት ውስጥ ስንቶች በአገልግሎት ላይ አሉ?፣ ስንቶች በሃይማኖታቸው ጸንተው፣ በምግባራቸው ቀንተው እያገለገሉ ነው? ስንቶች አገልግሎት አቁመዋል? ስንቶችስ ወደ ሌላ እምነት ገብተዋል? ወደ ሌላ እምነት እንዲገቡ ያደረጋቸው ገፊ ምክንያት ምንድን ነው? አሁን ያሉበት አቋም ምን ይመስላል? የሚሉት ጉዳዮች ለኮሌጆችም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች መሆን አልቻሉም፡፡ ይህ ክፍተት እነሱን መሣሪያ አድርገው ለመጠቀም ሌት ከቀን ለሚተጉት መናፍቃን ጥሩ ዕድል ሆኗ ቸው ውጭ ሆነው ለሚሠሩት የጥፋት ሥራ የውስጥ ዐርበኛ ሆነው የሚያገለግሏቸው ኦርቶ-ጴንጤ€ የኮሌጅ ምሩቃን ሰባኪ፣ የስብከተ ወንጌል ሓላፊና የደብር አስተዳዳሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድጓል፡፡

፯.የትኩረት ማነስ

በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ በዓላማና በረቀቀ ዘዴ እየተሠራ ያለውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ መኖሩን ካለመቀበል ጀምሮ እንቅስቃሴውን ለማስቆም የተሠሩ ሥራዎች አለመኖራቸው ለጉዳዩ የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተሐድሶ ማኅበረ ቅዱሳን የፈጠረው የመወደጃ ፍረጃ€ እንጂ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት የተሸረበ ሥውር ሴራ መሆኑን አልተረዱትም፣ ወይም ሊረዱት ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ ይህ አቋም ሁለት ዓይነት ትርጉም ይኖረዋል፡፡ አንደኛው በአስተዳደር ሓላፊነት ላይ ካሉት አካላት ውስጥ ተሐድሶን የሚደግፉ፣ የውስጥ ዐርበኛ ሆነው የሚሠሩና በዓላማ የተሰማሩ ሰዎች አሉ ማለት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ትኩረት የማይሰጡ፣ ክርስትናን በጊዜያዊ ነገር የሚለውጡ፣ የሚነገራቸውን ነገር ላለመስማት ጆሯቸውን የደፈኑ እና ምን እየተሠራ እንደሆነ እንኳን መረጃው የሌላቸው ሰዎች በሓላፊነት ላይ እንደተቀመጡ የሚያስገነዝብ ነው፡፡

እንቅስቃሴው በቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሰው ጉዳት

፩.ሃይማኖታዊና ሥነ ምግባራዊ ችግር

አንድ መናፍቅ ምንም ትምህርት የሌለውን ክርስቲያን ከማታለል ይልቅ ከመንፈሳዊ ኮሌጅ የተመረቀ ሰባኪን ማሳመን ይቀለዋል፡፡ ለዚህም ነው በተሐድሶ መናፍቃን ማኅበራት ውስጥ ከምእመኑ ይልቅ ከመንፈሳዊ ኮሌጆች ከተመረቁት ደቀ መዛሙርት መካከል የሚበዙት መናፍቅ የሆኑት፡፡ ብዙ ተመራቂዎች እንደሚናገሩት ከመንፈሳዊ ኮሌጅ የተመረቀ ሰው የመጀመሪያ የምስጋና ጸሎቱ €œአቤቱ መናፍቅ ሳልሆን እንድወጣ ስላደረግኸኝ አመሰግንሀለሁ የሚል ነው፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ምሩቅና መናፍቅ አቻ ለአቻ የሚነገሩ ቃላት ናቸው፡፡ እንዲህ ዓይነት ንግግሮች መንፈሳዊ ኮሌጆችና €œደቀ መዛሙርቱ€ ምን እና ምን ናቸው? የሚለውን ጥያቄ እንድንጠይቅ ያስገድዱናል፡፡

ለብዙ የተሐድሶ መናፍቃን መፈጠር፣ ለብዙ ምእመናን ከአገልግሎት መውጣትና ከሃይማኖት መራቅ የዋናውን ድርሻ የሚወስዱት እነዚሁ €œደቀ መዛሙርት€ ናቸው፡፡ ሃይማኖቱን በመተውም ቅድሚያውን የሚይዘውም ያልተማረው ኅብረተሰብ ሳይሆን እነዚሁ ናቸው፡፡ የዚህ ምክንያቱ መጀመሪያ የነበራቸው የትምህርት መሠረት ወይም የትምህርት አሰጣጡ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የመናፍቃኑ የመጀመሪያ €œጥቅሶች€ (ማሳያዎች ማለታችን ነው) መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃላት ሳይሆኑ ከእነዚህ መንፈሳዊ ኮሌጆች አፈንግጠው የወጡ ሰዎች ናቸው፡፡ የደቀ መዛሙርቱ በሃይማኖትና በምግባር መውጣት የቤተ ክርስቲያን ችግር ተደርጎ ተወስዶ ለብዙ ምእመናን ከመንገዳቸው ለመውጣት ምክንያት ሆኗል፡፡

፪.ሁሉንም እንዲጠሉ ማድረግ

ከመንፈሳዊ ኮሌጆች ተመርቀው የወጡ በቃልም በሕይወትም የሚያስተምሩ፣ ሃይማኖትና ምግባር እንደ ድርና ማግ አስተባብረው የያዙ የቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች መኖራቸው እውነት ነው፡፡ በገጠር ያለችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲጠናከር አምሳና መቶ ኪሎ ሜትር በእግራቸው እየሔዱ፣ ወጣቶችን እየሰበሰቡና እያስተማሩ ሌት ከቀን የሚደክሙ ደቀ መዛሙርት አሉ፡፡ እንደእነዚህ ያሉ ደቀ መዛሙርት ያሉትን ያህል ደግሞ፣ ከርሳቸው እስከሞላ ድረስ ለሌላው መዳን አለመዳን ግድ የሌላቸው የቤተ ክርስቲያን የብብት እሳት የሆኑም አሉ፡፡ በሥጋና በመንፈስ መግባ ያሳደገቻቸውን ቤተ ክርስቲያን ከጠላቷ ከአርዮስ ጋር ወግነው ሊያፈርሷት የሚሯሯጡ የእናት ጡት ነካሾች በቁጥር እየበዙ መሔዳቸው ምእመናን እውነተኞችን አገልጋዮች እንዲጠራጠሩ፣ ከመጥፎዎቹ ጋር አብረው ደምረው እንዲጠሉ በር እየከፈተ ነው፡፡

፫.የሰውና የገንዘብ ኪሳራ

የቤተ ክርስቲያን ገንዘቧ ሰው እንጂ ብርና ወርቅ አይደለም፡፡ በመምህራን እግር ተተክተው መንጋውን እንዲጠብቁ ለብዙ ዓመታት የደከመችባቸው ልጆቿን ከማጣት በላይ ለቤተ ክርስቲያን ሌላ ኪሳራ የለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያጣችው ልጆቿን ብቻ አይደለም፤ ለእነዚህ ሰዎች ያባከነችውን ገንዘብ፣ የሰው ኃይልና ጊዜ ጭምር እንጂ፡፡ ከመንፈሳዊ ኮሌጆች የሚመረቁ እውነተኞቹ ደቀ መዛሙርት ከመድረኩ ርቀው የቢሮ ሥራ ላይ ተጠምደዋል፡፡ ይህም ለቤተ ክርስቲያን ሁለት መንታ ችግሮችን አስከትሏል፡፡ አንደኛው ቤተ ክርስቲያን ስትለፋባቸው የኖረቻቸው ልጆቿ ዓላማዋን ሳያሣኩላት መቅረታቸው ሲሆን፤ ሁለተኛውና አሳዛኙ ደግሞ ሌሎች የተሐድሶ አቀንቃኞች ቦታውን እንዲይዙት ማድረጉ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ቦታውን መያዛቸው ብቻ ሳይሆን እውነተኞቹ ከመድረኩ ስለጠፉ እነርሱ እውነተኛ መስለው መታየታቸው የበለጠ ቤተ ክርስቲያንን እየጎዳት ነው፡፡ ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ተሰሚነት ያለው የሚናገር፣ የሚጽፍ ወይም የሚዘምር ሰው ስለሆነ ነው፡፡

የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በሁሉም ኮሌጆች ያለ መሆኑን ከየኮሌጆቹ በተለያዩ ጊዜያት የተባረሩ የተሐድሶ መናፍቃን አቀንቃኞች፣ ምክርና ተግሣጽ ተሰጥቷቸው የቀጠሉ ተማሪዎች ማስረጃዎች ናቸው፡፡ እንቅስቃሴው በሦስቱም መንፈሳዊ ኮሌጆች ያለ ነው፡፡ በየኮሌጆቹ ማሳያዎችን በመጥቀስ ጉዳዮችን ማብራራት ተገቢ ይሆናልና ወደዚያ እንለፍ፡፡

ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አዲስ አበባ መሆኑና መንፈሳዊ ኮሌጆች ላይ መሠረት አድርጎ የሚሠራውን የውጪውን የተሐድሶ መናፍቃን ድርጅትም ትኩረት የሳበ በመሆኑ ብዙ እንቅስቃሴዎች ይደረጉበታል፡፡ ከውጪ እስከ አገር ውስጥ መረባቸውን የዘረጉ የተሐድሶ መናፍቃን ድርጅ ቶች ሰፋ ያለ መሠረት ለመጣል ሲሞክሩ ነበር፣ አሁንም እየሠሩ ነው፡፡ እንቅስቃሴው በአብዛኛው የቀን መደበኛ ተማሪዎችን ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ከኮሌጁ ተመርቀው በተሐድሶ መናፍቃን መረብ ውስጥ ያሉ ደቀ መዛሙርት€ አሉ፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ በትምህርት ላይ ያሉ ወደ መናፍቃን አዳራሽ የሚሔዱ፣ ከአሸናፊ መኮንን ጋር የሚማሩ ብዙ ተማሪዎች አሉ፡፡ ፳፻ወ፮ ዓ.ም ላይ ቁጥራቸው ዐሥር የሚደርሱ ተማሪዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮን የሚነቅፍና የክህደት ትምህርት ሲያሠራጩ በኮሌጁ ደቀ መዛሙርት መረጃ ቀርቦባቸዋል፡፡ ጉዳያቸውም ለኮሌጁ ቀርቦ እየታየ ሲሆን፤ የድምጽና የሰው ማስረጃ የቀረበባቸው የኑፋቄ ትምህርቶቻቸው የሚከተሉት ናቸው፡፡

፩.አማላጃችን ኢየሱስ ነው እንጂ ሌላ አማላጅ የለም፤

፪.በጸጋው አንዴ ድነናል፣ ስለዚህ ሥራ ለምስክርነት ነው እንጂ ለመዳናችን ምንም አያስፈልግም፤

፫.ኅብስቱ መታሰቢያ ነው እንጂ፣ ሕይወት የሚሰጥ አማናዊ የጌታ ሥጋና ደም አይደለም፤

፬.ለፍጡር አድኅነኒ አይባልም፣ ማርያም አታድንም፤

፭.በጸሎት ቤት ስለ ድንግል ማርያም ክብር ትምህርት ሲሰጥ “ተረታ ተረትህን ተውና ውረድ” ብሎ መቃወም፤

፮.ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ መላእክት እያልን ወንጌልን አንሸቃቅጥ፤

፯.ጻድቃን ሰማዕታት፣ መላእክት አያማልዱም፣ አያድኑም፣ አያስፈልጉም፣ አንድ ጌታ አለን፤

፰.ለቅዱሳን ስግደት አይገባም፣ የአምልኮ እንጂ የጸጋ የሚባል ስግደት የለም፤

፱.ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን አትሰብክም፣ የምትሰብከው ፍጡራንን ነው፤

፲.ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምባቸው መጻሕፍት በሙሉ ኮተቶች ናቸው፤

፲፩.እኛ የሐዲስ ኪዳን ልጆች ነን የአንድምታ መጻሕፍት አያስፈልጉንም፤

፲፪.በሐዲስ ኪዳን ካህን አያስፈልግም፣ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ ንስሐም መናገር ያለብን ለጌታ ብቻ ነው፤

፲፫.በጳጳሳት፣ በመነኮሳት፣ በቀሳውስት፣ በዲያቆናት እንዲሁም ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት በሚያስተምሩትና በሚማሩት፣ በሚጾሙትና በሚያስቀድሱት የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ላይ ጸያፍ ስድብና ዘለፋ መናገር፡፡ ከሚናገሯቸው የስድብ ቃላት ውስጥ፡- ግብዞች፣ በጨለማ የሚኖሩ፣ ዶማዎች፣ ደንቆሮዎች፣ ያልበራላቸው፣ የጌታ ጠላቶች፣ ወዘተ ይገኙበታል፡፡

፲፬.ታቦት ጆሮ ስለሌለው አይሰማም፣ ስለዚህ አያስፈልግም ፣

፲፭.ሕዝቡን ለብዙ ሺሕ ዘመናት ለጣዖት ስናሰግደው ኖረናል፣

፲፮.አሁን ካለንበት የጨለማ ጫካ መውጣት አለብን፣

፲፯.ቤተ ክርስቲያን፡- ዘረኝነትንና ጽንፈኝነትን ታስፋፋለች፣ የተወሰነ ጎሳ ናት፣

፲፰.አንደኛ ዓመት ተማሪዎችን ሲያገኟቸው €œቲዮሎጂ መማር ከፈለግህ የበላኸውን መትፋት አለብህ€፣ ወዘተ በማለት መዝለፍና ክፉ ምክር መምከር የሚሉት ናቸው፡፡

ይህ የሚያሳየው ከዚህ ኮሌጅ ተመርቀው የተሐድሶ መናፍቃኑን ጎራ የተቀላቀሉት ሰዎች ኮሌጁን በሚፈልጉት መልኩ ለመቅረፅ ሰፋ ያለ ሥራ እየሠሩ መሆኑን ነው፡፡ ይህም ፍሬ ኮሌጁ በእነዚህ ደቀ መዛሙርት ላይ እንደሆነው በየጊዜው እያጠራ ካልሔደ ችግሩን ውስብስብ እና ከባድ ያደርገዋል፡፡

ሌላኛው ኮሌጅ የተሐድሶ መናፍቃን አቀንቃኞች “ብዙ ሰዎችን ያፈራንበት ቤታችን ነው ብለው በድፍረት የሚናገሩለት” ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ነው፡፡ ተሐድሶዎችና መናፍቃኑ ከዚህ ኮሌጅ ተመርቆ ኦርቶዶክሳዊ ሆኖ መገኘት የተአምር ያህል የሚቆጠር እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ እነርሱም ከዚህ ኮሌጅ የተመረቀ መሆኑን ያረጋገጡትን ሰው በልበ ሙሉነት ይቀበላሉ፡፡ በኮሌጁ የኑፋቄው ጠንሳሽ መሠረት ስብሐት ለአብ ነው፡፡ የእርሱን ፈለግ ተከትለው ብዙ ጥፋት ያደረሱት ደግሞ በ፳፻ወ፬ ዓ.ም ተወግዘው የተለዩት ጽጌ ሥጦታውና ግርማ በቀለ ናቸው፡፡ ከ፲፱፻፺ ዓ.ም ጀምሮ የተከሉት እሾህ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያንን እያደማ ይኖራል፡፡ ከዚህ ኮሌጅ ተመርቀው አንዳንዴ ፕሮቴስታንት፣ ሌላ ጊዜ ሙስሊም አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ኦርቶዶክስ ሆነው የሚተውኑ ደቀ መዛሙርት€ አሉ፡፡

ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በተሐድሶ መናፍቃን ብዙ ተጽእኖ የደረሰበት ኮሌጅ ነው፡፡ ለብዙ ዓመታት በኮሌጁ እንደ ሐሰተኛ የሚቆጠሩትና አንገታቸውን ደፍተው የሚሔዱት የነበሩት ኦርቶዶክሳውያን ነበሩ፡፡ ይህ የሆነው በሓላፊነት ላይ የነበሩት መሪዎች ድጋፍ የሚሰጡት ከትክክለኞቹ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ይልቅ ለተሐድሶ መናፍቃኑ ስለ ነበር ነው፡፡ ይህ የሆነውም እንቅስቃሴውን የሚደግፉ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጀምሮ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ስለሚያግዟቸው ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ጀምሮ ለውጦች እየታዩበት ነው፡፡ የዚህ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተሐድሶ ጠንሳሽ በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የመቀሌ ቅርንጫፍ ሰብሳቢ የነበረ ሰው ነው፡፡ አዳዲስ ተማሪዎች ሲገቡ አጥምደው ወደ ቡድናቸው ያስገቡ ነበር፡፡ በ፳፻ወ፮ ዓ.ም ያለውና በዛብህ የሚባሉ ቀንደኛ የተሐድሶ መናፍቃን አቀንቃኞች ከዚህ ኮሌጅ ኑፋቄያቸው ተደር ሶበት ተባረዋል፡፡

የተሐድሶ መናፍቃን ተላላኪ የሆኑት የኮሌጁ ተማሪዎች በዕረፍት ሰዓታቸው ወደ አዲስ አበባ መጥተው በአሸናፊ መኮንን አስተባባሪነት ይሰበሰባሉ፡፡ ለቡድናቸው አባላት መጽሐፍ ቅዱስ፣ የአሸናፊ መኮንን መጻሕፍት እና ሌሎችም ተሐድሶዎች የጻፏቸው መጻሕፍት ይታደላሉ፡፡ ፳፻ወ፯ ዓ.ም ላይ በኮሌጁ ተማሪዎች በተደረገ የመረጃ ማጠናቀር የተደረሰበት በኮሌጁ ከሚማሩት ተማሪዎች ውስጥ ሃምሳ በመቶ ያህሉ ተሐድሶዎችና የተሐድሶ መናፍቃን ደጋፊዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የኮሌጁ ተማሪዎች ግንባር ቀደም የተሐድሶ አንቀሳቃሾች ናቸው፡፡

ስለ መንፈሳዊ ኮሌጆች ስንናገር መንፈሳዊ ኮሌጆች በእምነት የጸኑ፣ በምግባር የቀኑ ደቀ መዛሙርትን አላፈሩም ማለታችን አለመሆኑን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ከተመሠረቱበት ዓላማ አንጻር የምርቱን ያህል ግርዱም እየበዛ ማስቸገሩን ለማሳየት አቅርበናል፡፡ እንኳን ትልቅ ተቋም አንድ ግለሰብም የወለዳቸው ልጆች ሁሉ መልካሞች፣ ያስተማራቸው ተማሪዎች ሁሉ ዐዋቂዎች ወይም መንፈሳውያን እንደማይሆኑለት ይታወቃል፡፡ ይህ የነበረ፣ ያለና የሚቀጥል እውነት ነው፡፡ ከጌታችን እግር ሥር ቁጭ ብለው ከተማሩት ሐዋርያት መካከል ይሁዳ በስንዴ መካከል የበቀለ እንክርዳድ ነበር፤ በተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ እግር ሥር ቁጭ ብለው ከተማሩት ደቀ መዛሙርት መካከልም አርዮስ በቅሏል፡፡

ነገር ግን በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ እየታየ ያለው ንጹሕና የተቀላቀለ ስንዴ አስገብቶ እንክርዳድ የማምረቱ ጉዳይ እየጨመረ መምጣቱን አህጉረ ስብከትም እየገለጡ ነው፡፡ እዚህ ላይ ለማስገንዘብ የምንፈልገውም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አቅሟን የምታጠናክርባቸው፣ ተተኪ ሊቃውንትን የምታፈራባቸው መንፈሳዊ ካሌጆች፤ የተሐድሶ መናፍቃን መፈልፈያ ለማድረግ በዓላማ ሌት ከቀን እየተሠራ ያለውን ተግባር ምን ያህል አውቀነዋል በሚል እንጂ፤ በየኮሌጆቹ ውስጥ ሆነው አቅማቸው በፈቀደ፣ ይህን ሥውር ደባና ዘመቻ ለማጋለጥ የሚተጉ ደቀ መዛሙርት የሉም ለማለት አይደለም፡፡፡ ሆኖም ግን ተፅዕኖውና ዘመቻው ከእነሱ አቅም በላይ ስለሆነ፤ በመዋቅሩ ደረጃ ችግሩን ለመቅረፍ መሠራት የሚኖርባቸውን ተግባራት ለማመላከትና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች የሆኑ በየኮሌጆቹ የሚገኙ ደቀ መዛሙርትም በፅናት ሆነው የተሐድሶ መናፍቃን ዓላማ ግቡን እንዳይመታ ጥረታቸውን እንዲቀጥሉ ለማሳሰብ ነው፡፡

እውነተኞቹ ደቀ መዛሙርት እኩይ ተግባራቸውን ስለገለጡባቸው ተሐድሶ መናፍቃንም ተነካን በሚል የዋሃንን አስተባብረው ለመጮህ ወደ ኋላ የማይሉ መሆናቸውን ለማስገንዘብ ነው፡፡ ስለዚህ ደግመን እንጠይቃለን መንፈሳዊ ኮሌጆችና €œደቀ መዛሙርት ምን እና ምን ናቸው?€ ይህንን የምንለው ከላይ የተዘረዘሩት ችግሮች ተቀርፈው ኦርቶዶክሳውያን ደቀ መዛሙርት እንዲበዙና ወጥተውም በተማሩት ሙያ እንዲያገለግሉ የሚያ ደርግ ሥራ መሥራት እንደሚገባን ለማመልከት ነው፡፡

ስንክሳር፡- መስከረም ስድስት

መስከረም 6 ቀን 2008 ዓ.ም

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ስድስት በዚች ቀን ታላቅ ነብይ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ዐረፈ፡፡

ይህም ነቢይ ለይሁዳ በነገሡ በአምስቱ ነገሥታት ዘመን አስተማረ ትንቢትም ተናገረ፣ እሊህም ኦዝያን፣ ኢዮአታም፤ አካዝ፤ ሕዝቅያስና ምናሴ ናቸው፡፡

በአካዝ ዘመንም እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ፡፡ እነሆ ስለዚህ እግዚአብሔር ምልክትን ይሰጣችኋል፡፡ እነሆ ድንግል ፀንሳ ወንድ ልጅን ትወለወዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች፡፡

ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አንድ ሆነ ማለት ነው፡፡

እርሱም በኃጢአታቸው ከሚመጣባቸው ፍዳ ወገኖቹን የሚያድናቸው ወደ ሃይማኖቱም የሚያስገባቸው እንደሆነ የእስራኤልንም ልጆች መስዋዕታቸውንና ክህነታቸውን እንደሚሽር ከሐዲስ ወገኖችም የሚያመሰግኑት ካህናትን እንደሚሾም ተናገረ፡፡

የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬምም ኢየሩሳሌምን ከቦ የስድብ ቃልን በክብር ባለቤት በእግዚአብሔር ላይ በተናገረ ጊዜ የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬምን ያጠፋው ዘንድ እግዚአብሔር እንዳለው ለሕዝቅያስ ትንቢትን ተናገረ፡፡

በዚያች ሌሊትም እግዚአብሔር የላከው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደ ሰናክሬም ሠፈር መጥቶ ከፋርስ ሠራዊት መቶ ሰማንያ አምስት ሺሕ አርበኞችን ገደለ፡፡ የለኪሶ ሰዎች ሲነጋ በተነሱ ጊዜ የሞቱትን ሰዎች ሬሳ ሁሉ አዩ፡፡

ሕዝቅያስም ታሞ ለሞት በተቃረበ ጊዜ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ እግዚአብሔር ትሞታለህ አንጂ አትድንም ብሏልና ቤትህን አዘጋጅ አለው፡፡

ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ ወደ እግዚአብሔር ለመነ፣ ፈጽሞ ጽኑ ልቅሶንም አለቀሰ፡፡ ይህን ከነገረው በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ነብዩ ወደ ኢሳይያስ መጣ፣ ሒደህ ለሕዝቅያስ የአባትህ የዳዊት ፈጣሪ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰማሁ፣ ዕንባህንም አየሁ፡፡ እነሆ በዘመንህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት ጨመርኩልህ አለ በለው፡፡

ዳግመኛም ስለ እስራኤል መማረክና ከምርኮ ስለመመለሳቸው ትንቢት ተናገረ፡፡ የፈሳሽ ውኃን ምንጭ በማፍሰስ በእጆቹ ላይ እግዚአብሔር ምልክትን ገለጠ፡፡

ክብር ይግባውና ስለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ ትንቢት ተናገረ፣ እንዲህም አለ፡፡ እርሱም በመከራው ጊዜ ነገርን አልተናገረም እንደ በግ ይታረድ ዘንድ መጣ፣ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንደማይናገር እንዲሁ በመከራው ጊዜ አልተናገረም፡፡

ከዚህም በኋላ ደግሞ በሕዝቅያስ ልጅ በምናሴ ላይ ትንቢት ተናገረ፣ ጣዖትን ስለማቆሙና ስለማምለኩ ገሠጸው፡፡ ስለዚህም ንጉሥ ምናሴ ተቆጥቶ በዕንጨት መሰንጠቂያ መጋዝ በራሱና በእግሮቹ መካከል ሠነጠቀው፣ ምስክርነቱንም በዚህ ፈጸመ፡፡

ትንቢት እየተናገረ የኖረበትም ዘመን ሰብዓ ዓመት ከዚያም በላይ ይሆናል፡፡ እርሱም ያስተማረው ክብር ይግባውና ጌታችን ከመምጣቱ በፊት በዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሦስት ዓመት ነው፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከሁላችን ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን፡፡

ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር ከመስከረም እስከ የካቲት፣ አዲስ አበባ፤ ትንሣኤ ማሳተሚያ ደርጅት፣ 1994 ዓ.ም፣ ገጽ 23-25፡፡ 

ስንክሳር፡- መስከረም አምስት

መስከረም 5 ቀን 2008 ዓ.ም

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም አምስት በዚች ቀን የከበረች ሶፊያ ከሁለት ልጆቿ አክሶስና በርናባ ከሚባሉት ጋር በሰማዕትንት ሞተች፡፡

ይችም ቅደስት አስቀድማ አረማዊ ነበረች፣ ወላጆቿም ጣዖታትን የሚያመልኩ ናቸው፡፡ እርሷም በልቧ አስተዋለች፣ መረመረችም፣ የወላጆቿ ሃይማኖት ከንቱ እንደሆነ ተረዳች፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ መኖፌ ኤጲስ ቆጶስ ሔዳ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ታመነች፡፡ እንዲህም አለችው፤ በሕያው አምላክህ አምኛለሁና አጥምቀኝ እርሱም ሃይማኖትን፣ የቤተ ክርስቲያንም ሕግ አስተማራት፡፡ ከዚህም በኋላ ከልጆቿ ጋር በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃት፡፡

ከዚህም በኋላ የሀገር ሰዎች ለአማልእክት መስገድን ትታ ክርስቲያን እንደሆነች በገዢው በክላድያኖስ ዘንድ ወነጀሏት፡፡ ገዢውም ወደ እርሱ አስቀርቦ መረመራት፡፡ እርሷም ክብር ይግባውና በክርስቶስ አመነች እንጂ አልካደችም፣ ከልጆቿም ጋር ብዙ ሥቃይን አሠቃያት፡፡

በሥቃይም ውስጥ ላሉ ልጆቿ ታስታግሳቸውና ታጽናናቸው ነበር፣ እንዲህም ትላቸው ነበር፡፡ ልጆቼ ጠንክሩ፣ ጨክኑ የአንጌቤንዋን እመቤት ሶፍያን እመስላታለሁ፤ እናንተም ጲስጢስ፤ አላጲስ አጋጲስ የተባሉ ልጆቿን ምሰሉ፣ እነርሱም እንዲህ ብለው መለሱላት፣ እናት ሆይ እኛ ፍለጋሽን እንከተላለንና ስለእኛ አትፈሪ ይህንንም በሚባባሉ ጊዜ ከእናታቸው ጋር ተሳሳሙ፡፡

ገዢውም ሲሳሳሙ አይቶ ደናግል ልጆቿ እንዲፈሩ እናታቸውን በጅራፍ ይገርፏት ዘንድ አዘዘ፡፡ ያን ጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶ እናታቸውን ከግርፋት ሲሠውራት አዩ፡፡

ዝንጉዎችም ይገርፏት ዘንድ ባራቆቷት ጊዜ በዚያን ሰዓት እንዲህ በማለት ትጮህ ነበር፡፡ ዓለሙን ሁሉ በፈጠረ በእውነተኛ አምላክ በእግዚአብሔር የማምን ክርስቲያናዊት ነኝ፣ ያን ጊዜም ገዢው ምላሷን ከሥሩ እንዲቆርጡ አዘዘ፡፡ እርሷ ግን መጮህንና መናገርን አላቋረጠችም፡፡

ከዚህም በኋላ ገዢው ወደ እሥር ቤት እንዲወስዷት አዘዘ፤ ትሸነግላትም ዘንድ ሚስቱን ወደእርሰዋ ላከ፡፡ እርሰዋ ግን ምንም አልመለሰችላትም፡፡ ራሷንም በሰይፍ ይቆርጧት ዘንድ አዘዘ፤ የድል አክሊልም ተቀበለች፡፡ አንዲት ሴትም መጥታ ሥጋዋን በጭልታ ወሰደች፣ ወደ ቤቷም አስገብታ በፊቷ መብራትን አኖረች፡፡

ከዚህም በኋላ ልጆቿን ጠርቶ እሺ ይሉት ዘንድ አስፈራራቸው፣ እምቢ ባሉትም ጊዜ እያከታተለ ራሳቸውን አስቆረጠ፣ ምሥክርነታቸውንና ተጋድሏቸውንም ፈጸሙ፡፡ ከመቃብራቸውም በሽታውንና ደዌውን ሁሉ የሚፈውሱ ብዙ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ፡፡

ደግ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስም ዜናቸውን በሰማ ጊዜ የቅዱሳት ሰማዕታትን ሥጋቸውን ወደ ቁስጥንጥንያ አፍልሶ ወሰደ፡፡

የሶፍያንና የልጆቿን ዜና ከመስማቱ በፊት ታላላቅና ሰፊ የሆኑ ቤቶች እንዲሠሩ በላይዋም ይቺ ቤት የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ናት ብለው ጽሑፍ እንዲቀርጹበት አዘዘ፡፡ እነርሱም ንጉሡ እንዳዘዘ ወደ ማታ ሲሆን ይጽፋሉ፣ የእግዚአብሔርም መልአክ ወርዶ ያንን ደምስሶ ይቺ ቤት የሶፍያ ናት ብሎ ይጽፋል፡፡ የሕንፃውም ባለሙያዎች የሚያደርጉትን አጡ፣ መጻፋቸውንም ተዉ፡፡

በአንዲት ቀንም የንጉሥ ልጅ ብቻውን ሲጫወት መልአክ ተገለጸለትና የዚች ቤት ስሟ ማነው አለው፡፡ ሕፃኑም አላወቅሁም አለው፣ መልአኩም ሁለተኛ እንዲህ አለው አባትህን የሶፍያ ቤት ብለህ ሰይማት ብለህ ንገረው ሕፃኑም ተመልሼ እስክመጣ ትጠብቀኛለህን አለው፣ መልአኩ አዎን እጠብቅሃለሁ አለው፡፡

አባቱም ይህን ሰምቶ መልአክ እንደሆነ ዐወቀ፡፡ ሕፃኑንም በመጠበቅ ምክንያት ያ መልአክ ከዚያች ቦታ እንዳይሄድ ብሎ ንጉሡ ልጁን ገደለው፡፡ መልአኩም ሕፃኑን እየጠበቀ እስከዛሬ ድረስ አለ፡፡

የዚያች ቤተ ክርስቲያም ርዝመቷ ሰባት መቶ ዘጠኝ ክንድ ሆነ፣ አግድመቷም ሦስት መቶ ሰባት ክንድ፣ ምሰሶዎቿም ዐራት መቶ፣ ጠረጴዛዎቿም ስምንት፣ የሚያበሩ ዕንቁቿ ዐራት ናቸው፣ ከአጎበሩ በላይ የተቀረጹ ኪሩቤልም በየሁለት ክንፎቻቸው የእግዚአብሔር ሕግ የተጻፈበትን ታቦት ይጋርዳሉ፡፡

ሥጋቸው በውስጡ ያለበትን የቅድስት ሶፍያንና የልጆቿን ሳጥን በታላቅ ምስጋናና ክብር ወደዚያ አስገብተው አኖሩ፡፡

በድኖቻቸውን የሰበሰበች ያቺንም ሴት ከእርሳቸው ጋር ቀበሯት፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር፣ ከመስከረም እስከ የካቲት፣ አዲስ አበባ፤ ትንሣኤ ማሳተሚያ ደርጅት፣ 1994 ዓ.ም፣ ገጽ 20-21፡፡

የእመቤታችን ዕርገት

ነሐሴ 15 ቀን 2007 ዓ.ም

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ፡፡

ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር፡፡

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው፡፡

ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ፡፡ የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ዘንድ ተቀምጦ አየው፡፡ የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት፡፡

ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ፡፡

የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት፤ የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ፡፡

ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፅዋት ሁሉም አዘነበሉ፤ መላእክት፤ የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት፡፡

አባቷ ዳዊትም ንግሥት እመቤታችን ወረቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች እያለ በበገና አመሰገናት፡፡

በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኃላ በልጆችዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች፡፡

ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ፤ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው፡፡ እርሱም እንዳየ እንደሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንዳሳረጓት ነገራቸው፡፡

ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ፡፡

ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና የፍቅር የአንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ፡፡ እነሆ እኔ እርስዋን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል አላቸው፡፡ ይህንንም ብሎ ከእርሳቸው ዘንድ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡

ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ለሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው፡፡ አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሳየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በጾም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን፡፡

በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ፤ የነሐሴ ወር እንደዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው፡፡ በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት፡፡ እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እያንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው፡፡

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዔ ካህን ሆነ፡፡ እስጢፋኖስም አዘጋጀ፤ ዮሐንስም በመፍራት ቁሙ አለ፡፡ ሁሉም ሐዋርያት በመሰዊያው ዙሪያ ቆሙ፤ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ፡፡

ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው፡፡

ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን  እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት፡፡ በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰበኩ ልጆችሽ  ሐዋርያትን እዘዣቸው፡፡ መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ፡፡ የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለቸው ልጄ ሆይ እነሆ በዓይኖቻቸውም አዩ፤ በጆሮዎቻቸውም ሰሙ፤ በእጆቻቸው ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ድንቆች ሥራዎችን አዩ፡፡

እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ፡፡

የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል፡፡ እርሷ ስለ እኛ ወደተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለች፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን፡፡ በረከቷም ሐዋርያት በሰበሰበዋት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን፡፡

ምንጭ፡-ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ