‹‹ሦስቱ የጥፋት ገመዶች እንዳይጥሏችሁ ተጠበቁ!›› አቡነ ተክለ ሃይማኖት
ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በተጋድሏቸው ዘመን በአባ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለዐሥር ዓመት በነበሩበት ጊዜ አገልጋዮቹ ወደ እርሳቸው መጥተው ይመክሯቸው ዘንድ ለመኗቸው፤ እርሳቸውም ‹‹ትዕግሥትን፣ ትሕትናን እና እግዚአብሔርን መፍራት ገንዘብ አድርጉ፤ እነዚህ ሦስት ነገሮች ሰውን ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ያደርሱታል፡፡ እየጎተቱ ወደደይን ጥልቅነት የሚያወርዱ ሦስቱ የጥፋት ገመዶች እርሳቸውም ቅናት፣ ትዕቢትና ትምክሕት እንዳይጥሏችሁ ደግሞ ተጠበቁ›› ብለው መከሯቸው፡፡ (ገድለ ተክለ ሃይማኖት ፵፫፥፬-፮)