የነነዌ ጾም

እግዚአብሔር አምላካችን ወዶ እና ፈቅዶ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ለሆነው የነነዌ ጾም አድርሶናል፡፡ ሦስት ቀናት የሚጾመው ይህ ጾም የነነዌን ሕዝብ ከጥፋት መመለስ፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እንዲሁም የነቢዩ ዮናስን የዋህነት ያስረዳናል፡፡

ዘመነ ስብከት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዘመን አከፋፈል መሰረት ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በፊት ከታኅሣሥ ፯ ጀምሮ እስከ ፳፱ ያለው ወቅት ዘመነ ስብከት ይባላል፡፡ እያንዳንዱ ሳምንታትም ስብከት፣ ብርሃን እና ኖላዊ በሚል ስያሜ ይታወቃሉ፡፡ በዚህም ወቅት ስለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር መምጣት መወለድ ነቢያት የተናገሩት ትንቢት በስፋት ይነገርበታል፡፡

የነቢያት ጾም

በዘመነ ብሉይ ነቢያት እግዚአብሔር ወልድ ከንጽሕተ ንጹሐን፤ ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ለአዳም የገባለትን ቃል ይፈጽም ዘንድ ትንቢት በመናገር ለሕዝቡ የምሥራችን ቃል ያበሥሩ ነበር፡፡… ነቢያቱ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው ሆኖ ዓለምን የሚያድንበትን ዘመነ ሥጋዌ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ የነቢያት ትንቢትና ጸሎትም በእግዚአብሔር ሰው መሆን ተፈጽሟል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይህንን ታሳቢ በማድረግ በዘመነ ማቴዎስ፣ ማርቆስና ሉቃስ፤ ከኅዳር ፲፭ አስከ ታኅሣሥ ፳፱፤ በዘመነ ዮሐንስ ደግሞ እስከ ታኅሣሥ ፳፰ ጾም ታውጃለች፡፡

የጽጌ ጾም

የጌታችንና የእመቤታችን የስደት ወቅት በወርኃ ግንቦት ነው፤ ነገር ግን ዘመነ ጽጌ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችንን በአበባ፣ ጌታችንን ደግሞ በፍሬ እየመሰሉ ለማመስገንና ለማወደስ በሚያስችል ምሥጢር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የስደቱ ጊዜ በዘመነ ጽጌ እንዲዘከር አድርገዋል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለዘለዓለሙ የማይደርቀውን የሕይወት ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስን ያስገኘችልን ንጽሕት የማትጠወልግ አበባ ናትና፡፡ …

ጾመ ዮዲት

ዮዲት በናቡከደነጾር ዘመነ መንግሥት ትኖር የነበረች ባሏ የሞተባትና በንጽሕና ተጠብቃ፣ በጸሎትና በሕገ እግዚአብሔር የምትኖር ሴት ነበረች፡፡ በዚያን ጊዜ ንጉሡ ሥልጣኑን መከታ በማድረግ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በግድ እያስገደደ እጅ መንሻ ይቀበል ነበር፡፡ የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበለውንም እየገደለ፣ ጭፍሮቹ ኃያልነቱንና ገናናነቱን በዓዋጅ በጦር አዛዦች ጭምር እያሳወጀ፣ በርካታ የጦር ሠራዊቶችን አሰልፎ ከአይሁድ ከተማ ገባ፡፡ …

‹‹ፈለሰት ማርያም እምዘይበሊ ኀበኢይበሊ›› ቅዱስ ያሬድ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ዓለም ፷፬ ዓመታትን በሕይወተ ሥጋ ከቆየች በኋላ ሥጋዋ በምድር እንዲቆይ የአምላክ ፈቃድ አልበነረም፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእናቱን ተድላ ነፍሷን እንጂ ተድላ ሥጋዋን አይወድምና ከጌቴሴማኒ ሥጋዋ ተነጥቆ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር እስከ ነሐሴ ዐሥራ ስድስት ቀን ለሁለት መቶ አምስት ቀናት እንድትቆይ ፈቃዱ አደረገ፡፡ እርሱ ሞትን በሥልጣኑ እንዳሸነፈ ሁሉ በልጇ መለኮታዊ ኃይል ሞትን አሸንፋ ተነስታለች፡፡

ጾመ ሐዋርያት እና ጾመ ድኅነት

በዚህ ዓመት ጾመ ሐዋርያት ሰኔ ፩፤ ጾመ ድኅነት ደግሞ ሰኔ ፫ ቀን ይጀመራሉ፡፡ በመሆኑም የምንጠቀመው በራሳችን መልካም ተግባር፤ የምንወቀሰውም በራሳችን ኃጢአት መሆኑን ተረድተን ‹ይሄ የቄሶች፤ ይሄ የመነኰሳት ነው› የሚል ሰበብ ሳንፈጥር ሁላችንም በአንድነት ብንጾማቸው ከእግዚአብሔር ዘንድይቅርታ ጸጋና ምሕረትን እናገኛለንና ራሳችንን ለጾም እናዘጋጅ፡፡

ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን)

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡

ጸሎተ ሐሙስ

ጸሎተ ሐሙስ በብሉይ ኪዳን ለፋሲካ ዝግጅት ተደርጎበታል (ማቴ. ፳፮፥፯-፲፫)፡፡ ‹ፋሲካ› ማለት ማለፍ ማለት ነው፡፡ ይኸውም እስራኤላውያን በግብጽ ምድር ሳሉ መልአኩን ልኮ እያንዳንዱ እስራኤላዊ የበግ ጠቦት እንዲያርድና ደሙን በበሩ ወይም በመቃኑ እንዲቀባ ለሙሴ ነገረው፡፡ ሙሴም የታዘዘውን ለሕዝቡ ነገረ፤ ሁሉም እንደ ታዘዙት ፈጸሙ፡፡ በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ መቅሠፍት ታዞ መልአኩ የደም ምልክት የሌለበትን የግብጻውያንን ቤት በሞተ በኵር ሲመታ፤ የበጉ ደም ምልክት ያለበትን የእስራኤላውያንን ቤት ምልክቱን እያየ አልፏል፡፡ ፋሲካ መባሉም ይህን ምሥጢር ለማስታወስ ነው (ዘፀ. ፲፪፥፩-፳)፡፡

ሆሳዕና

ሆሼዕናህ ከሚል ከዕብራይስጥ ቃል የተገኘው ሆሳዕና ትርጓሜው እባክህ አሁን አድን ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል በዘመነ ብሉይ በቀደምት ነቢያት ዘንድ የተለመደ ቃል ነው፡፡ አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፡፡ (መዝ.፻፲፯፥፳፭-፳፮) የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሳዕና በአርያም በማለት ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡ በዓሉም ሆሳዕና የሚለውን ስያሜ ያገኘው በዕለቱ ከተዘመረው መዝሙር ነው፡፡