ቅድስት፡ የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት

የቅድስና ባለቤት የሆነው እርሱ እግዚአብሔር አምላክ ነው። እቀደስ አይል ቅዱስ፣ እባረክ አይል ቡሩክ ነው። በእርሱ የባሕርይ ቅድስና እኛን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ቡሩክ ሆኖ ባረከን፣ ቅዱስ ሆኖ ቀደሰን፣ሕያው ሆኖ ሕያዋን አደረገን። የጸጋ ቅድስናንም ከእርሱ አገኘን።

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት

በዚህ ሳምንት የቃል ርደት፣ የወልድ ልደት፣ የአዳም ድኅነት ቢነገርም እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ከሰማይ የወረደ ሰማያዊ፣ በክብር ያረገ በኩረ ትንሣኤ መሆኑ አይዘነጋም፡። ለዚህም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ነገር ግን ምስክርነታችንንም አትቀበሉትም። በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁኝ፥ በሰማይ ያለውን ብነግራችሁ እንዴት ታምኑኛላችሁ? ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው።

የሦስቱ ቀናት ጾም

በበደላቸው ምክንያት የነነዌ ሕዝብ ሊጠፉ በመሆናቸው ከሕፃናት ጀምሮ እስከ አረጋዊ ብቻም ሳይሆን እንስሳት ጭምር የጾሙት የሦስት ቀናት ጾም ‹‹ የነነዌ ጾም›› ተብሏል፡፡

‹‹የእግዚአብሔር ሰው›› (፩ኛሳሙ.፱፥፮)

መልእክተኛውም ሚክያስን ‹‹እነሆ ነቢያት ሁሉ በአንድ አፍ ሆነው ለንጉሡ መልካሙን ይናገራሉ፤ ቃልህም እንደ ቃላቸው እንዲሆን መልካም እንድትናገር እለምንሃለሁ›› ይለዋል፡፡ (፩ኛ ነገ.፳፪፥፲፫) ነቢዩ ግን ‹‹ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር የሚነግረኝን እርሱን እናገራለሁ›› አለው፡፡

‹‹የእግዚአብሔር ሰው›› (፩ኛ ሳሙ.፱፥፮)

የእግዚአብሔር ሰዎች ትክክለኛና እውነተኛ ሰዎች በመሆናቸው የተናገሩት ሁሉ የሚፈጸም ነው፡፡ በአንደኛ ሳሙኤል መጽሐፍ ላይ  እንዲህ የሚል ቃል አለ፤ ‹‹…እነሆ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በዚህች ከተማ አለ፤ እርሱም የተከበረ ሰው ነው፤ የሚናገረውም ሁሉ  በእውነት ይፈጸማል …፡፡›› (፩ኛሳሙ.፱፥፮)

‹‹የእግዚአብሔር ሰው›› (፩ኛሳሙ.፱፥፮)

ውድ የዚህ ጽሑፍ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ዘመነ ክረምቱን/ዘመነ ጽጌን እግዚአብሔር ረድቶን ብዙ ተምረንበት አልፏል፡፡ከፊታችን ኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ ፳፰/፳፱ ድረስ ደግሞ ዘመነ ነቢያትን የምንዘክርበት፣ ‹‹ጾመ ነቢያት›› ብለን ከጾም ጋር አገናኝተን ስለ ነቢያትና ነቢይነት፣ እንዲሁም ስለ ትንቢት ዓላማና ምክንያቱ  ቤተ ክርስቲያን ብዙ የምታስተምርበት  ወቅት ነው፡፡

‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ›› (መሓ.፯፥፩)

ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ከዚህ በፊት የእመቤታችንን የስደቷን ነገር አንሥተን ‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ›› በሚል ርእስ ከክፍል አንድ እስከ ሦስት አድርሰናችሁ ነበር፡፡ ጥሩ ትምህርት እንዳገኛችሁበት ተስፋ እናደርጋለን፡፡

የዛሬው ትኩረታችን ያን ሁሉ መከራ የተቀበለችበት የስደቷን ምክንያትና ዓላማ መዳሰስ ነው፡፡

‹‹ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ›› (መሓ.፯፥፩)

ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ፡፡ አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸውም ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ ወለደች፡፡……..ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሃ ሸሸች፡፡ (ራእ.፲፪፥፬-፮

‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሺ፥ ተመለሺ›› (መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን ፯፥፩)

 እሾህ በተባለ ጥንተ አብሶ አዳማዊና ሔዋናዊ ኃጢአት መካከል ያበበች የፍሬ ሕይወት ክርስቶስ መገኛ አማናዊት የሃይማኖት አበባ እመቤታችን በዚህ በአበባው ወቅት (በጽጌ ወራት) መራራው የጣፈጠበት፥ ፍሬ ሕይወት ልጇን እንዳይገሉባት መራራውን የስደት ሕይወት የተጋፈጠችበት መታሰቢያ ወቅት ነው፡፡

‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሺ፥ ተመለሺ›› (መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን ፯፥፩)

በብሥራተ መልአክ በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደችውን አንድያ ልጇን ሄሮድስ ሊገድልባት በፈለገው ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሀገር ወደ ሀገር መሰደዷን የሚያመለክተውን፣  ከስደትም እንድትመለስ ጠቢቡ በትንቢት ቀድሞ የተናገረው ይህን ቃል ነው፡፡ ወቅቱ አብዝተን ስለ ስደቷና ተያያዥ ታሪኮች የምንማርበት፣ የምንጸልይበት፣ የምናስተምርበትና የምንዘምርበት ወቅት በመሆኑ በዚህ ርእስ ተከታታይ ጽሑፎችን ለማቅረብ እንሞክራለን፤ ተከታተሉን!