“አብዝቶ የመመገብ ጣጣው”
መግቢያ
መግቢያ
ከባሕር ዳር ማዕከል
ግንቦት23፣ 2003ዓ.ም
ብፁዕ አቡነ በርናባስ ግንቦት 20 ከምሽቱ 3.00 ማረፋቸው ይታወሳል፡፡
የብፁዕነታቸው የቀብር ሥነ ሥርዓት ግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም የተፈጸመ ሲሆን በሥርዓቱ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሣዕ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እንዲሁም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አያሌው ጎበዜና የክልሉ ባለ ሥልጣናት፣ ከአዲስ አበባ የመጡ የደብር አስተዳዳሪዎች፣ የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ የመጻሕፍት ትርጓሜ መምህር የሆኑት መምህር ደጉ ዓለም ካሣ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ ጸሐፊ አቶ ዘላለም አጥናፉ እንዲሁም ሌሎች በርካታ እንግዶችና ምዕመናን ተገኝተዋል፡፡
የብፁዕነታቸው የቀብር ሥነ ሥርዓት ከቀኑ 6.00 ላይ የሀገረ ስብኩቱ መንበር በሆነው በፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ተፈጽሟል፡፡
ርክበ ካህናትን ተከትሎ የሚደረገውን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ለመካፈል ወደ አዲስ አበባ መጥተው በነበሩበት ወቅት ታመው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህም ሳቢያ የምልዐተ ጉባኤውን የመጨረሻውን ቀን ማለትም የማክሰኞ ዕለት ስብስባ አልተካፈሉም፡፡ በዚህም ሁኔታ አርብ ግንቦት 19 ቀን 2003 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ተነስተው የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሆኑት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ጋር ደብረ ማርቆስ ገብተው ያደሩ ሲሆን ወደ ሀገረ ስብከታቸው መቀመጫ ባሕር ዳር ቅዳሜ 8፡00 ሰዓት ገብተው በመዋል ማታ 1፡30 ላይ እንዳረፉ ታውቋል፡፡
ግንቦት 13፣ 2003 ዓ.ም
ምንጩ ከየት ነው?
ጽሑፉ በራሱ ሥልጣን እየተጣጣረም ቢሆን ለመናገር የሚሞክረው "የማኅበረ ቅዱሳን ነኝ" እያለ ነው፡፡ ነገር ግን በመናገር እና በመሆን መካከል ያለውን ርቀት እንዳይፈራገጥ ባስገነዘው ጣእረ ሞት እንደያዘው የሚይዘውን የሚጨብጠውን ያጣ ወረቀት ነው፡፡ ለዚህም ጽሑፉ ሳያውቀው ምንጩን ሲናገር እናገኘዋለን፡፡ ይሁን እንጂ በመጀመሪያ ምንጩ ማኅበረ ቅዱሳን ሊሆን ይችላልን?
ስልታዊ እቅድ እንደመሆኑ መጠን በዘመናዊው አሠራር የራሱ ቅርጽ (format) አለው፡፡ ቢያንስ ቢያንስ መግቢያ፣ የማኅበሩን ማንነት፣ የማኅበሩ ዓላማ፣ ርእይ፣ ተልእኮ፣ እሴት፣ የባለድርሻ አካላት ትንተና፣ ውጫዊ አካባቢ ትንታኔ፣ እንዲሁም አስፈላጊነቱ ሌሎች ትንታኔዎች ምቹ እና ፈታኝ ሁኔታዎች፣ የምቹ እና ፈታኝ ሁኔታዎች ምዘና፣ ወሳኝ ጉዳዮች፣ ስልታዊ እቅድ ዓላማ፣ ግብና ስልት፣ ዝርዝር የአፈጻጸም መርሐ ግብር እንዲሁም የክትትልና የግምገማ ሥርአት ያለው ሊሆን ይገባል፡፡
በዚህ ቅርጽ መሠረት የማኅበረ ቅዱሳን ስልታዊ /ስትራቴጂክ/ እቅዱን አዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት በማቅረብ በእቅዱ መሠረት አገልግሎቱን በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ አሠራሩ ያልተመቻቸው አካላት የጐንዮሽ እቅድ በማቀድ የራሳቸውን የፈጠራ ሥራ አቅርበዋል፡፡ማኅበረ ቅዱሳንን ለመወንጀል ታስቦ የሐሰት ሰነድ (forged document) ተዘጋጅቶ የተበተነበትም ምክንያት ያንን እቅድ አባቶች እንደማያውቁት በማስመሰል ነው፡፡
የፖለቲካ አጠቃቀም
ማኅበሩ በመዋቅሩ ሥር ያሉትን አካላት በራሱ መጥራት የተሳነው አስመስለው ቀርጸውታል፡፡ ለማሳያ የሚሆነውም በዝርዝር እቅዱ ውስጥ በአንድ ላይ "በየንዑሳን ቅርንጫፍ በኩል" የሚል ሐረግ ይገኛል፡፡ ሲጀምር ማኅበሩ ቅርንጫፍ የሚባል ምንም ዓይነት መዋቅር የለውም፡፡
ከዋናው ማእከል ቀጥሎ ያሉት ማእከላት ይባላሉ እንጂ ንዑሳን አይባሉም፡፡ ይህም አጠቃቀሙ ሌላ አካል መሆኑን ያሳያል፡፡ በአስገራሚ ሁኔታ የተበተነው ወረቀት አንድ ተማሪ ክፍል ውስጥ ገብቶ ሲማር ከሚይዘው ማስታወሻ እንኳ ያነሰ፤ እቅድ መባል ካለበት እንኳ የጨነገፈ እቅድ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ሊያወጣው አይችልም፡፡ በዚህ መስፈርት እንኳን ቢታይ እቅዱ በምንም መለኪያ የማኅበረ ቅዱሳን አለመሆኑን ያረጋግጣል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ራሱን ሲጠራ ”ማህበረ ቅዱሳን” ብሎ አያውቅም። "እቅድ" የሚለውን ቃል አቅድ የሚለውን ተክቶ ለጥቅም እንዲውል አድርጐም አያውቅም፡፡ እነዚህን የተጠቀመው ጽሑፍ ራሱን እርቃኑን አቁሞ የማኅበረ ቅዱሳን አለመ ሆኑን የገለጠበት ዘርፍ ነው፡፡ ወረቀቱ ስለ እቅድ የሚናገር ከሆነ የተግባራዊነት ዘመኑ ከመቼ እስከ መቼ እንደሆነ እንኳ አለመገለጹ ድንገቴ እንደ ወራጅ ውኃ የፈሰሰ የጥቂቶች አሳብ እንጂ እቅድ አለመሆኑን ያሳብቅበታል፡፡ የስሕተት ሙሻዙር የጠመዘዛቸው አዘጋጆች እንደመሰላቸው እነርሱ ያስቀመጧቸውን በወንጀል ደረጃ የሚፈረጁ አደገኛ አሳቦች በማኅተም አትሞ በቲተር እና በፊርማ አስደግፎ ራሱን ለአደጋ አጋልጦ የሚያስቀምጥ ተቋም በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ይገኛል ብሎ ማሰብ ቂልነት ነው፡፡
በተሠራጨው እቅድ ላይ የተቀመጡት አሳቦች አሉታዊ እና አፍራሽ አስተሳሰቦች እንደመሆናቸው መጠን ማኅበሩ የቱንም ያክል ክፉ ነው ተብሎ ቢታሰብ እንኳ እንዲህ ያለ እቅድ በዚህ መልክ አዘጋጅቶ እና አንድ ቦታ አጠራቅሞ ይገኛል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ያንን ያክል ክፋት ማርገዝ የቻለ እኩይ ሕሊና ቢኖር እንኳ አካሔዱን እና አቀማመጡን አይጠበብበትም ነበር የሚለው ለአንባቢ የሚተው ውሳኔ ይሆናል፡፡ እነዚህን አካሔዶች ጠቅልለን ስንመለከታቸው ምንጩ ለጊዜው የማኅበረ ቅዱሳንን በመጨረሻም የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ጥፋት ሌት ተቀን ከሚለማመኑ አካላት የተቀዳ ለመሆኑ ከቶውኑ ማን ይመራመራል? መጽሐፍ “በክፋታቸው እየባሱ ይሔዳሉ” እንዳለው የማኅበረ ቅዱሳን መኖር የእግር እሳት ስለሆነባቸው በምን መንገገድ ስሙን ቢያጠፉ ተቀባይነት ሊያገኙ እንደሚችሉ ሁልጊዜ ወጥመድ ያጠምዳሉ፡፡ እስካሁን ድረስ የእግዚአብሔር ቸርነት ከልክሏቸው አልተሳካላቸውም እንጂ የወገባቸው የሐሰት ዝናር ሲያልቅባቸው በማኅበሩ ወንበር ተቀምጠው የሚናገሩ በማስመሰል ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ተልእኮ እንዳለው አድርገው ሊያቅዱለት ፈለጉ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ካባ ለብሰው ያቀዱለት እቅድ ግን ከተለመደው ክሳቸው የወጣ አለመሆኑ ነው፡፡
እስካሁን ድረስ ማኅበሩን ለምን ትቃወማላችሁ ሲባሉ ይሰጡት የነበረውን መልስ እቅድ ነው ብለው አቀረቡት እንጂ ምንም አዲስ ነገር አላመጡም፡፡ ስለሆነም በዚህ በጻፉት እቅዳቸው ምክንያት ማንም ሊደነግጥላቸው አይችልም፡፡ በተቻላቸው መጠን የመጨረሻዋን ጥይት ለመተኮስ ሲጥሩ መልሶ ራሳቸውን ወጋቸው፡፡ በተጉበትም መጠን በመጐዳታቸው አሟሟታቸውን ለማሳመር የሐሰት እና የጥፋት እቅድ ለማኅበሩ አወጡለት፡፡ የሚጠባበቁት ውጤት በእነዚያ ወንጀሎች ምክንያት ያቀዱለት አካል እለቱኑ ታንቆ እለቱኑ ሲሞት ለማየት በጉጉት ኮርቻ ላይ ተቀመጡ፤ የፈለጉት ማኅበሩ እነርሱ ጐን ቆሞ ቤተክርስቲያንን አንዲያጠፋላቸው ነበር፡፡
ግን ምን ያደርጋል? እነርሱም ታወቁ ሕልማቸውም መከነ፡፡ ራሱን በራሱ ሲቃረን አንድ ተቋም ራሱን ሲገልጽ ‘እኛ” በሚል ባለቤት ሊናገር እንደ ሚችል የተረዳ ነገር ነው፡፡ በጽሑፉ ላይ ግን አባቶችን አባላት በማድረግና ”ስብሰባቸው ላይ” የሚል አባባል ተጠቅመዋል፡፡ ስለራሱ እቅድ የሚናገር ሰው ”በስብሰባችን ላይ” ይላል እንጂ ”ስብሰባቸው ላይ” እንዴት ሊል ይችላል? በተጨማሪም ”በራሱ ጠቅላላ ጉባኤ መምራት” በማለት ማኅበሩ ራሱን ”እርሱ” እያለ እንዲጠራ አድርገው ጽፈዋል፡፡ እንዲሁም ”ካህናቱን ለድርጅቱ ሠራተኞች አድርጐ መቅጠር” በሚለው እቅዳቸው ላይ ”እርሱ” ብሎ ራሱን እንዲጠራ አድርገውታል፡፡
ከእነዚህ አገላለጾች የምንረዳው የሆነ አካል ራሱን አስገድዶ የማኅበሩ አካል አድርጐ በመቁጠር ስለማኅበሩ ሆኖ እንዲጽፍ እንደተጨነቀ ያሳያል፡፡ ታዲያ ምን ያደርጋል አልተቻለውም፡፡ ራሱን ጠፍሮ በማሠር ስለማኅበሩ እንዲናገር አሰቃየው እንጂ ስለሌላ ማኅበር እንደሚናገር ተገልጦበታል፡፡ ጸሐፊው ያለ እርሻው የበቀለ ከሌላ ዘር የመጣ ነውና የራሴ ነው ያለውን ማኅበር ”እነርሱ” ”እርሱ” እና ”እኛ” እያለ ጠራው፡፡ ያልሠለጠነ ውሸታም በመሆኑ እንዲጽፍላቸው የቀጠሩትን ሰዎች አጋለጣቸው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወዴት መሸሸግ ይቻላል? የጨለማው መጋረጃ ተቀደደባቸው፣ ከእነ ተንኮላቸው እጅ ከፈንጅ ተያዙ፡፡ ወዲህና ወዲያ እንዳይሉ በራሳቸው ገመድ ተጠፍንገው ታሠሩ፡፡ እግዚአብሔር ይፍታችሁ ከማለት ውጭ ምን እንላለን?
ማኅበሩ ማኅበሩን ሲቃወም በዕቅዳቸው ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን የሚያሳትማቸውን ኅትመቶች ያለ ኤዲቶሪያል ቦርድ ኅትመት አከናውኖ ማሠራጨት የሚል የተጠላለፈ አሳብ አስቀምጧል፡፡ በመሠረቱ ማኅበረ ቅዱሳን በመዋቅሩ እንዳመለከተው ማንኛውንም ኅትመት ኤዲቶሪያል ቦርዱ ዓይቶት ሲፈቅደው ይታተማል፡፡ ታዲያ እንዴት አንድ ማኅበር የራሱን መዋቅር የጣሰ ለመሥራት ያቅዳል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ቦርዱን ማፍረስ ሲችል እንዴት ስለመጣስ ያስባል። እንዲህ ያለ ዕቅድ ታይቶም ተሰምቶም አያውቅምና ዕቅድ አውጪዎቹ በጣም የተራቀቁ መሆን አለባቸው፡፡ ዕቅዳቸውን ለራሳቸው ጥብቅና ሲያቆሙት ቅድስቲቱን እምነት ለመበረዝ የተነሡ የተሐድሶ ኦርቶዶክስ ዓላማ አራማጆች ስውር ተልኮአቸው በአሁኑ ወቅት ስለተነቃባቸው ከገቡበት አዙሪት ለመውጣት ሲፍጨረጨሩ ይታያሉ፡፡
የጽንሰ ሐሳብ ችግር
ከዝርዝር ዕቅዳቸው አንዱ ባልተጠኑ ትምህርቶች የቤተርክስቲያኗን ምዕመናን ደጋፊ ማድረግ ይላል። አንድ ጤናማና የሚያስብ አእምሮ ያለው ሰው ይህንን አባባል እንዴት ይረዳዋል? ብሎ መገመት እጅግ ቀላል ይሆናል፡፡ ዕቅድ እያቀደ ያለ አንድ አካል እንዴት ባልተጠና ትምህርት ሌላውን ሊያሳምን ይችላል? ዕቅዱን ያቀዱት ሰዎች የሰለቻቸው ይመስላል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት /የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ተማሪዎችን/ የሚያስተምረው በተጠና ሥርዐተ ትምህርት መሆኑን ያወቁ እንዴት ይህን ሊሉ ቻሉ? በርግጥም ደክሟቸው መሆን አለበት፡፡
የጽሑፉ ዓላማ
ማኅበረ ቅዱሳን ከተለያዩ የቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ማኅበራትና ልጆች ጋር በመቀናጀት በአሁኑ ሰዓት ፀረ ተሐድሶ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት ማዕበሉ እያንጓለለ የለያቸው ያሉ የተደራጁ የሃይማኖት ጠላቶች ማምለጫ እስኪያጡ ድረስ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል፡፡ የተዋሕዶ ምዕመናንን እየሰለቿቸው መጥተዋል፡፡ በመሸማቀቅ በቁማቸው አልቀዋል፡፡ ከመጠን በላይ በመደንገጣቸው ምክንያት ሳያስቡት የመጣባቸውን እውነት ለመጋፈጥ የሚያስችል መንፈሳዊ ተክለ ሰውነት አጥተዋል፡፡ ስለሆነም አቋራጭ የመሰላቸው የጨነገፈ ስልት ነድፈዋል፡፡ በዋነኛነትም የሞት ሽረት ትግል ለማድረግ አስበዋል፡፡
ይህንን ከደረጃ ወጥቶ ጊዜ ወስዶ የተንኮታኮተ ጽሑፍ ዕቅድ ብለው ይዘው መዞራቸው በትክክል ማንነታቸውን ይገልጥባቸዋል፡፡ በየትኛውም መመዘኛ ማኅበረ ቅዱሳንን የማይመስል ወዘና የሌለው ወረቀት ብቅ ማድረግ ማንነታቸውን ገልጠዋል፡፡ በዝምታ ሊታለፉ አይገባቸውም፡፡
ማጠቃለያ
ይህንን ጽሑፍ ያሰራጩት አካለት እነማን ሊሆኑ እንደሚችሉ ማንም ሰው መገመት ይችላል፡፡ ከመገመትም አልፎ አገኘሁ ብሎ ማኅበሩን ለማጥላላት የሚጠቀምበት ሁሉ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ተቀባዮችም የሰጪዎችን ማንነት ያውቃሉ፡፡ እንዲያውም ከማብራሪያ ጋር እንደተቀበሉ ይታመናል ፡፡
1. ይህ የሐሰት ጽሑፍ የደረሳቸው አካላት ሰዎችን በማጋለጥ ሊተባበሩ ይገባል፤
2. ማኅበሩ እነዚህን አካላት በሕግ መጠየቅ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ቅዱስ ሲኖዶስ የእነዚህን ሰዎች ማንነት አጣርቶ ፍትሐዊ ውሳኔ እንዲሰጥን እንፈልጋለን፤3. ይህ ጽሑፍ የደረሳቸሁ ምዕመናን በሐሰት ሥራ እንዳትታለሉ እናሳስባለን። አስፈላጊ ሆኖ ካገኙትም ወደ ማኅበሩ ጽ/ቤት በመምጣት ተገቢውን ውይይት ማድረግ እንደሚችሉ እንጠቁማለን።
ግንቦት 10፣ 2003ዓ.ም
ከሓዋሳ የመጡ ምእመናን አስፈላጊውን የሕግ አግባብነት ተከትለው ቢመጡም ባልታወቀ ምክንያት ዱከም ላይ ታግተው የቀሩ ምእመናን እንዳሉ አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡
በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳንም የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በአጀንዳ ሊያያቸው ይገባል ያላቸውን ጉዳዮች በቀን 9/9/03 ዓ.ም በቁጥር ማ.ቅ.ሥ.እ.መ/17/02/ለ/03 በጻፈው ደብዳቤ አቅርቧል፡፡ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት እና በግለባጭ ለሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት በላከው ደብዳቤ በማኅበሩ ላለፉት 19 ዓመታት የተሠሩ ሥራዎች እንዳሉ ሆነው በአሁኑ ወቅት ግን ለቤተ ክርሰቲያን እድገትና መልካም አሠራር እንቅፋት የሆኑ ችግሮች መኖራቸውን በአጽንኦት ይገልጻል፡፡
ወቅታዊውን የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ በፊት ያሣለፋቸውን ውሳኔዎች ተፈጻሚነትን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ትውልድን የማፍራት ጉዳይ ይኸውም የሕፃናትና የወጣቶች ሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርትና የማደራጃ መምሪያ ኃላፊዎችን ችላ ባይነት፣ የማኅበሩን ስም ለማጥፋት እየተንቀሳቀሱ ስላሉ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ለቅዱስ ሲኖዶስ አባልነትና የሚቀርቡና የሚሾሙ ኤጲስ ቆጶሳትን ጉዳይ ይኸውም ወቅቱ የተሐድሶ መናፍቃን በቤተ ክርስቲያኗ መዋቅርና የሓላፊነት ቦታ ለመግባት ከፍተኛ ርብርብ የሚያደርጉበት ስለሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ለዚህ ጉዳይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የሚያመለክቱ አጀንዳዎች በአጀንዳነት ተይዘው ውሳኔ ሊሰጥባቸው ይገባል በማለት እንደልጅነታችን ሀሳባችንን እናቀርባለን ሲል ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተጻፈው ደብዳቤ ያሳስባል።
በተያያዘም እነዚህንና ከወቅቱ ሁኔታ ጋር የቀረቡ ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ በወቅታዊው የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ሠፋ ያሉ ዘገባዎች ቀርበዋል።
ቅዱስ ሲኖዶስንና መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ልዕልናውን፣ የወቅታዊውን የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ፣ እንዲሁም አጽራረ ቤተ ክርስቲያን፣ በማኅበረ ቅዱሳን የውሸት /forged/ ማኅተም «የማኅበረ ቅዱሳን የረጅም ጊዜ ዕቅድ» በሚል ያዘጋጁትን እና በክስ መልክ ለፓትርያኩ ያቀረቡትን የሐሰት ጦማርና ሌሎችንም ወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተ ሰፋ ያለ ዘገባ በመያዝ ወጥታለች፤ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም።
ቤተ ክርስቲያን የማትነጥፍ መንፈሳዊት ጥገት ሆና ከምታፈሰው መንፈሳዊ ሐሊብ /ወተት/ ምእመኖቿ እንዲጠቀሙ የቅዱስ ሲኖዶስ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ልዕልና መከበር ወሳኝ ነው።
ቤተ ክርስቲያንም የቅድስና ዘውዷንና የክብር አክሊሏን ከራሷ ሳታወርድ ልዕልናዋ እንዳለ ሁሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች መከበር አለባቸው ስትል ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ በልዩ እትሟ አስነብባለች።