ክብር ለኢትዮጵያውያን ሰማዕታት!

በዚህ ዓመት ታኅሣሥ ወር ፳፬ ቀን ጸጥታ አስከባሪዎች በሁለት ወጣት ኦርቶዶክሳውያን ላይ በግፍ የገደሉትን ስፍራ የ ‹‹፳፬ ቀበሌ›› ወደ ቀደመ ክብሩ ተመልሶ ሕንጻ ቤተክርስቲያን እንዲሠራበት በተላለፈው ውሳኔ መሠረት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት መጋቢት  ፮ ፳፻፲፪ ዓ.ም. የመሠረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡

“እነሆ÷ ድነሃል ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል ተጠንቀቅ” (ዮሐ.፭፤፲፬)

ቤተ ክርስቲያናችን ሁሉንም በሥርዓት የምታከናውን ስንዱ እመቤት ናትና በዐቢይ ጾም ከሚገኙት ሰንበታት ውስጥ ዐራተኛውን ሰንበት መጻጉዕ ብላ ሰይማዋለች፡፡ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብንወድቅ እንደሚያነሣን፣ ብንታመም እንደሚፈውሰን ለማስተማር፣ እንዲሁም ደግሞ ከመጻጉዕ ሕይወት እንማር ዘንድ መታሰቢያውን አደረገች፡፡ “ዳግመኛ እንዳትበድል ተጠንቀቅ” እንዳለ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ እንሸጋገር ዘንድ፣ የአምላካችንን ቃል መፈጸም እንደሚገባን፣ እሰከ ሞትም መታመን እንዳለብን ያስተምረናል፡፡

‹‹የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉ›› (ዮሐ.፪፥፲፮)

በዐቢይ ጾም ሦስተኛው ሳምንት በእለተ እሑድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ በቤተ መቅደስም በሬዎችንና በጎችን፥ ርግቦችንም የሚሸጡትን፥ ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፡፡ ይህን ባለመውደዱም የገመድ ጅራፍ ካበጀ በኋላ በጎችንና በሮዎችን እንዲሁም ሁሉንም ከቤተ መቅደስ አስወጣቸው፤ የሻጮቹንም ገንዘብ በተነባቸው፤ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፤ ርግብ ይሸጡ የነበሩትን ደግሞ ‹‹ይህን ከዚህ አውጡ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉ አላቸው፡፡›› (ዮሐ.፪፥፲፬-፲፮)

ቅድስት

ቅድስት ማለት የተለየች፣ የተመረጠች፣ የከበረች ማለት ነው። ቅዱስ የሚለው ቃል  እንደ  የአገባቡ  ለፈጣሪም  ለፍጡርም  ያገለግላል።  ለፈጣሪ ሲነገር  እንደ  ፈጣሪነቱ  ትርጉሙ  ይሰፋል  ይጠልቃል  ለፍጡር  ሲነገር ደግሞ  እንደ  ፍጡርነቱ  እና  እንደ  ቅድስናው  ደረጃ  ትርጉሙ ሊወሰን  ይችላል።

ቅድስት ማርያም (ባለሽቶዋ) እንተ ዕረፍት

ጌታችንም በስምዖን ቤት እንደ ግብፃውያን አቀማመጥ እግሩን ወደኋላ አድርጎ ነበር፤ አንድም ወንበሩ እንደ አፍርንጆች ወንበር እግር ወደኋላ የሚያደርግ ነው፤(ወንጌል ቅዱስ) እርሷም ከአጠገቡ ስትደርስ ከእግሩ በታች ከሰገደች በኋላ ‹‹በስተኋላውም በእግሩ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፤ በራስ ጠጉሯም ታብሰው፣ እግሩንም ትስመው፣ ሽቱም ትቀባው ነበረች፡፡›› (ሉቃ.፯፥፴፰-፴፱)

ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም

በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የረጅም ዘመን ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ በጎ ተፅዕኖ ካላቸው የአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አባቶች መካከል አንዱ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ነው፡፡ ይህ አባት ምንም እንኳን በቋንቋ ውሱንነትና በቦታ ርቀት በርካቶች ሥራዎቹና ጽሑፎቹ የታወቁለት ባይሆንም ሕይወቱን በብሕትውና የመራ የትርጓሜ መጻሕፍትን፣ የቅኔ፣ የግጥምና የወግ ጽሑፍ በማዘጋጀት የኖረ አባት ነው፡፡

ጸሎትና ክርስቲያናዊ ሕይወት

ጸሎት ክርስቲያኖች ከሚያከናውኗቸው መንፈሳዊ ተግባራት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ክርስቲያን በጸሎት የሚተጋ ሰው ነው፤ ያለ ምግብ ሰው መኖር እንደማይችል ሁሉ ክርስቲያንም ያለ ጸሎት መኖር አይችልም፡፡ ከውኃ ውስጥ የወጣ ዓሣ ሕይወት እንደማይኖረው ሁሉ ከጾም ከጸሎት እና ከንስሓ ሕይወትም የተለየ ክርስቲያን የሞተ ነው፤ ሕይወት የሌለው በነፋስ ብቻ የሚንቀሳቀስ በድንም ይሆናል፤ መጸለይ ሕይወት ነውና፤ አለመጸለይ ደግሞ የነፍስ ሞት ነው፡፡

ሰማዕታት ቅድስት ኢየሉጣ እና ሕፃን ቂርቆስ

ቅድስት ኢየሉጣ በሮም ግዛት በሚገኝ አንጌቤን በሚባል አገር በፈሪሃ እግዚአብሔር፣ በክርስትና ሃይማኖት እና በበጎ ምግባር ጸንታ ትኖር የነበረች ደግ ሴት ነበርች፡፡ በሥርዓት ያሳደገችው ቂርቆስ የሚባል ሕፃን ልጅም ነበራት፡፡

‹‹ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል፤ ድምጼንም ይሰማሉ፥ አንድ መንጋም ይሆናሉ እረኛውም አንድ ነው›› (ዮሐ. ፲፥ ፲፮)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአንቀጸ አባግዕ ሲያስተምር ‹‹ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል፤ ድምጼንም ይሰማሉ፥ አንድ መንጋም ይሆናሉ እረኛውም አንድ ነው›› ብሏል።(ዮሐ. ፲፥ ፲፮)

ጥምቀተ ክርስቶስ

በቅዱስ ዮሐንስ እጅ በማየ ዮርዳኖስ ተጠምቆ የባሕርይ ልጅነቱንና አምላክነቱን ከአብ እና ከመንፈሰ ቅዱስ አስመሰከረ፡፡