‹‹ትነብር ውስተ ቤተ መቅደስ፤ በቤተ መቅደስ ውስጥ ትኖር ነበር›› ቅዱስ ያሬድ

ዓለም ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሷን ፀጉር የማያህል ደግ ፍጥረት፣ ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች፣ ንጽሕናዋንም ይሁን ቅድስናዋን ፍጥረት በአንደበቱ ተናግሮም ሆነ ጽፎ የማይጨርሰው፣ የአምላክ ማደሪያ፣ እመ አምላክ፣ እመ ብዙኃን፣ ሰዓሊተ ምሕረት፣ አቁራሪተ መዓት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት የከበረ በዓል ነው፡

ነቢዩ ኤልያስ

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች ! እንዴት አላችሁ? ባለፈው ትምህርታችን ስለ ቅዱሳን ነቢያት፣ እነርሱ ስለ ጾሙትና የነቢያት ጾም ተብሎ ስለሚጠራው ጾም በጥቂቱ ተመልክተናል፤ለዛሬ የምንነግራችሁ ደግሞ ስለ ከቅዱሳን ነቢያት አንዱ ስለሆነው ስለ ነቢዩ ኤልያስ ነው፡፡

ሃያ አራቱ አለቆች (መጽሐፈ ስንክሳር)

ምስጋና ለሥሉስ ቅዱስ ይድረስና ሁልጊዜ በየዓመቱ በኅዳር ፳፬ ቀን እኛ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን የካህናተ ሰማይ (ሱራፌ) በዓልን እንድናከብር አባቶች ሥርዓትን ሠርተውልናል፡፡

‹‹ጽዮንን ክበቧት›› (መዝ.፵፯፥፲፪)

፭፻ ዓመታት ገደማ በእስራኤል ብዙ ገቢረ ተአምራትን ስታደርግ የነበረችዋ በሙሴ የተቀረጸች ታቦት በቀዳማዊ ምኒልክ በኩል ለኢትዮጵያ ተሰጠች።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ኅዳር ፳፩ ቀን በታላቅ ክብር ታከብረዋለች፡፡ካህናቱም ከዋዜማው ጀምረው በከበሮና በጸናጽል ስብሐተ እግዚአብሔር ያደርሳሉ፡፡በጽዮን ፊት እንደ የመዓርጋቸው ቆመው ‹‹እግትዋ ለጽዮን ወህቀፍዋ፤ ጽዮንን ክበቧት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ›› እያሉ ይዘምራሉ፡፡

‹‹እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ›› (ኢያ.፭፥፲፫)

በቅድስና፣ በውዳሴ፣ በኅብረ ቀለም፣ በመላእክት ዝማሬ በደመቀው በዓለመ መላእክት ውስጥ ቅዱሳን መላእክት በነገድ ተከፍለው ይኖራሉ፡፡ እነርሱም የዘወትር ምግባራቸው እንዲያውም ምግባቸው ፈጣሪን ማመስገን ነው፡፡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው መላእክቱም በሦስቱ የመላእክት ከተሞች ኢዮር፣ ራማ እና ኤረር በአላቃቸው ስር ሆነው ዘወትር አምላክን ያገለግላሉ፡፡ በኢዮር ከተማ ደግሞ የኃይላት አለቃ አድርጎ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ሾሞታል፤

የእግዚአብሔር ሠረገላዎች (መጽሐፈ ስንክሳር)

እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን በዕለተ እሑድ ሲፈጥር በነገድ መቶ በአለቃ ዐሥር አድርጎ በሦስቱ ሰማያት አስፍሯቸዋል፡፡ከእነዚህ ቅዱሳን መላእክት መካከል ኪሩቤል ይገኙበታል፤ኪሩብ አራት አራት ገጽ ካላቸው ከአራቱ ጸወርተ መንበር አንዱ ሲሆን፣ ፍችው መሸከምን፣ መያዝን ይገልጣል፡፡

በዓለ ደብረ ቁስቋም

በከበረች በኅዳር ስድስት ቀን የምናስበው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ ከመድኃኒዓለም፣ ከአረጋዊው ዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር ከስደት መመለስ እንዲሁም በቁስቋም ተራራ መገኘት ታላቅ በዓል ነው፡፡

“ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሄዳለሁ” (መጽሐፈ ስንክሳር)

አምላካችን እግዚአብሔር ምስጋናይድረሰውና ለእኛ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ውስጥ ለምንኖር ምእመናን ብንቆጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ የሚበዙ ድንቅ ምስክሮችን ጻድቃንን በአማላጅነታቸው እንድንጠቀም አድለውናል፡፡ ከእነዚህ መካከል ጥቅምት ፲፬ ቀን በዓላቸውን የምናከብረው ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ እና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ይገኙበታል፡፡

‹‹ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ›› (መዝ.፹፰፥፫)

ነቢዩ ዳዊት ‹‹ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ፤ ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ›› ብሎ እንደነገረን እግዚአብሔር ባዘጋጀላቸው ማረፊያ ሊያኖራቸው ቃል ኪዳን የሰጣቸው ንዑዳን አሉ።(መዝ.፹፰፥፫) የአምላካችን ቃል ኪዳን ፍጻሜው በመንግሥቱ ማኖር ነው። እያንዳንዱ እንደተጠራበት ጊዜና ሁኔታ በተለያየ አኳኋን ጌታውን ቢያገኝም የአምላካችን ስጦታ ግን ለመረጣቸው ሁሉ አንዷ መንግሥተ ሰማያት ናት፡፡ (ማቴ.፳፥፱)

‹‹በደስታ በዓልን አድርጉ›› (መዝ.፻፲፯፥፳፯)

ቀናትን ሁሉ ባርኮ የሰጠን አምላካችን እግዚአብሔር ጊዜ የእርሱ ስጦታ በመሆኑ የከበረ ድንቅ ሥራውን ፈጽሞበታል፡፡ በእያንዳንዱ ዕለት ፍጥረታትን ከመፍጠሩ ባሻገር ለምስጋና፣ ለውዳሴ እና ለድኅነት ያከበራቸው በዓላትም አሉት፤ በእነዚህ ዕለታት ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡