ማኅበረ ቅዱሳን ከ40,000 በላይ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን አስመረቀ
ሐምሌ 15 ቀን 2006 ዓ.ም.
እንዳለ ደምስስ
ማኅበረ ቅዱሳን በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ከ40,000 በላይ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን አስመረቀ ፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ካሉት 46 የሀገር ውስጥ ማእከላት መካከል በ38ቱ ማእከላት አስተባባሪነት በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አብዛኛዎቹ ዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛውን ውጤት በማስመዝገብ የዋንጫና የሜዳልያ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ከዩኒቨርስቲ ትምህርታቸው በተጓዳኝ መንፈሳዊ ዕውቀትን እንዲገበዩ በማድረግ ወደ ሥራ በሚሰማሩበትም ወቅት ራሳቸውን በመንፈሳዊውም በዓለማዊው ዕውቀት አዳብረው፤ በሥነ ምግባር ታንጸው ቤተ ክርስቲያንና ሀገራቸውን በታማኝነት እንዲያገለግሉ እንደሚረዳቸው በርካታ ተመራቂ ተማሪዎች ይገልጻሉ፡፡
የወልዲያ ዩኒቨርስቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ካስመረቃቸው 250 ተማሪዎች መካከል 50ዎቹ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም ውስጥ 17ቱ በማዕረግ የተመረቁ ናቸው፡፡ በአምቦ ዩኒቨርስቲ የወሊሶ ካምፓስ በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀው የሜዳልያ ተሸላሚ ከሆኑት 6ቱ ተመራቂዎች ውስጥ 4ቱ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች መሆናቸውን ከየማእከላቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በተጨማሪም የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሁለት ትምህርት ክፍሎችን ብቻ በዚህ ዓመት የሚያስመርቅ ሲሆን፤ ከሚመረቁት 70 ተማሪዎች መካከል 14ቱ ከፍተኛ ማዕረግ የሚመረቁ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ሲሆኑ ከ1-3 በመውጣትም የሜዳልያና የዋንጫ ተሸላሚዎች ናቸው፡፡ በተያያዘ ዜና ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ከተመረቁት ተማሪዎች መካከል ከ7 ዮኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች 3 የወርቅ ሜዳሊያ 2 ዋንጫ ያገኙት የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ናቸው፡፡



ከፍተኛ ድር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትርጉም ያለው የንባብ ባሕልን ለማሳደግ ከፍተኛውን ድርሻ መያዝ እንደሚገባት በማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ማእከል ባዘጋጀው የንባብ ባሕል አስመልክቶ በቀረበ የጥናት ጉባኤ ላይ ተገለጸ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በቀንና በማታ መርሐ ግብር ያስተማራቸውን ሦስት መቶ ደቀመዛሙርት አስመረቀ፡፡



በክብር እንግድነት ተገኝተው ዐውደ ርዕዩን በጸሎት የከፈቱት መልዐከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ሲራክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምስራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የፍራንክፈርት ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ናቸው፡፡ መልአከ ፀሐይ በመክፈቻ መርሐ ግብሩ ላይ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በፍራንክ ፈርት ከተማ ለአራተኛ ጊዜ እንደኾነ በማውሳት፤ ሁሉንም ዐውደ ርእዮች አዘጋጅቶ ለፍራንክፈርት ከተማና አካባቢው ሕዝብ ለዕይታ ያቀረበው በማኅበረ ቅዱሳን የጀርመን ቀጠና ማእከል ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡ ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን እየሰጠ ያለው አገልግሎት ሰፊና ጠቃሚ ነው ያሉት መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ሲራክ፤ ለዚሁ ደግሞ እኔ ራሴ ምስክር ነኝ በማለት በቅርብ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ሔደው ማኅበሩ በአቡነ ቶማስ ዘደብረ ሃይዳ ገዳም እያደረገ ያለውን የልማት እንቅስቃሴ በአብነት ጠቅሰዋል፡፡
ከሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ደብረ ብርሃን ከተማ በአሥር ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የአጤ ዋሻ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተዘርፎ ጅቡቲ ውስጥ ለ17 ዓመታት ተደብቆ የነበረው ታቦተ መድኃኔዓለም ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ሰኔ 21 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ መንበረ ክብሩ ገብቷል፡፡ /ሚያዚያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ታቦቱ ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ መግባቱን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል/
ሚያዚያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የቅርስ ጥበቃና ቤተ መዘክር ለጊዜው እንዲቀመጥ በማድረግ፤ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሰኔ 21 ቀን 2006 ዓ.ም. በከፍተኛ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ወደ አጤ ዋሻ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አሸኛኘት ተደርጎለታል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል የጀርመን ቀጠና ማእከል “ለሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን እድገት የድርሻችንን እንወጣ” በሚል መሪ ቃል ልዩ ዐውደ ርዕይ፤ ዐውደ ጥናትና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር በፍራንክፈርት ከተማ ኢኮነን ሙዚየም ከሰኔ 27- 29 ቀን 2006 ዓ.ም./July 4-6, 2014/ እንደሚካሔድ ቀጠና ማእከሉ አስታወቀ፡፡
ሠኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በተደረገው ጉባኤ ላይ የእንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ወኤልያስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ለካህናት ደመወዝ ለመክፈል በመቸገሩ በቤተ ክርስቲያኑ ተገቢውን መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት ችግር እያጋጠመው መሆኑን ገለጠ፡፡
የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ አባ ወልደ መድኅን ተክለ ብርሃን የእንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ወኤልያስ ቤተ ክርስቲያንና የርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከግቢያቸው አጥር ውጭ ምንም ይዞታ የሌላቸው በመሆኑ እና ቀደም ሲል የነበረው 270.9 ሄክታር ይዞታ በመነጠቁ ምክንያት አልምተን የገቢ ምንጭ የምንፈልግበት ሁኔታ የለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዓ.ም መጨረሻ ዐፄ ምኒልክ እንጦጦ ከተማ ከቆረቆሩ በኋላ፣ የልዑል እግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለማሳነጽ በነበራቸው ምኞት ከደብረ ሊባኖስ ገዳም አባቶችን አስመጥተውና ቦታውን አስባርከው የእንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ወኤልያስ ቤተ ክርስቲያን ሊታነጽ መቻሉን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ክርስቲያኑ ወደዚህ የተቀደሰ ቦታ በመምጣት፣ በመሳለምና የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማበርከት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡