ማኅበረ ቅዱሳን በገዳማትና በአብነት ትምህርት ቤቶች ዙሪያ እያከናወናቸው የሚገኙ ውጤታማ ተግባራት
መስከረም 8 ቀን 2007 ዓ.ም.
እንዳለ ደምስስ
በማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ገዳማት ከተረጅነት ወጥተው በራስ አገዝ የገቢ ምንጭ እንዲተዳደሩና አንድነታቸውና ገዳማዊ ሥርዓታቸው ተጠብቆ ለትውልድ እንዲሸጋገሩ፤ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኒቱ እምነት ሥርዓትና ትውፊት ሳይበረዝ፤ ተተኪ ሊቃውንትንና አገልጋዮችን ለማፍራት ትልቅ ድርሻ ያላቸው አብነት ትምህርት ቤቶችን በማጠናከር፤ ባልተቋቋመባቸውም አካባቢዎች የማቋቋም ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
ዋና ክፍሉ የገዳማትንና አብነት ትምህርት ቤቶችን ችግር ለመፍታት ከሰሜን አሜሪካና ከአውሮፓ ማእከላት፤ ከማኅበራት፤ በዋና ክፍሉና በማእከላት አስተባባሪነት በሀገር ውስጥ ከሚገኙ የማኅበሩን አገልግሎት ከሚያግዙ ምእመናን በተደረገ ድጋፍ የገዳማትንና አብነት ትምህርት ቤቶችን ችግር ለመቅረፍ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ ወደፊትም በቅዱሳት መካናት በየዘርፉ የሚታዩትን ችግሮች ለመፍታት ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከዋና ክፍሉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
በ2005 ዓ.ም. እና በ2006 ዓ.ም. በገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች ዙሪያ በልማትና በአቅም ማሳደግ ረገድ ራሳቸውን ችለው መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተከናወኑትን ተግባራት ዋና ክፍሉ ካደረሰን መረጃ ጥቂቶቹን እናቀርባለን፡፡
የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች፡-
በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የላይ ቤት የመጻሕፍት ትርጓሜ ሐተታ ስልት የሚሰጥበትና ማስመስከሪያ የሆነው የሞጣ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የመጻሕፍት ትርጓሜ ቤተ ጉባኤ 64 ተማሪዎችን እንዲሁም 2 መምህራንን ማስተናገድ የሚችል ባለ አንድ ፎቅ የመማሪያ፣ የማደሪያ፣ የቤተ መጻሕፍት ክፍሎች ያሉት ሕንፃ ከነ ሙሉ መገልገያው ተሠርቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
በምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት ለደብረ ካስዋ ጉንዳጉንዶ ቅድስት ማርያም ገዳም የገቢ ማስገኛ ይውል ዘንድ በዓዲግራት ከተማ ላይ ባለ ሁለት ፎቅ የሚከራይ ሕንፃ ፕሮጀክት አጥንቶ የምድር ወለሉን በማጠናቀቅ ቀጣይ የግንባታ ሥራ በመሠራት ላይ ይገኛል፡:
በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም አዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል፡፡
በሰሜን ምዕራብ ትግራይ /ሽሬ/ ሀገረ ስብከት በአስገደ ጽብላ የአቡነ ቶማስ ደብረ ማርያም ዘሃይዳ አንድነት ገዳም 150 ሺህ ሊትር ውኃ መያዝ የሚችል የውኃ ማጠራቀሚያ /ታንከር/ ተሠርቶ ለአገልግለሎት ተዘጋጅቷል፡፡
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም ዘመናዊ የወተት ላም እርባታ ፕሮጀክት ከገዳሙ ጋር በወጪ መጋራት ተጠናቆ ርክክብ ተደርጓል፡፡
በምሥራቃዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት የዲቦ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም የሽመና ቤት ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል፡: በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የደብረ ዘመዳ ቅድስት ማርያም ወአቡነ በርተሎሜዎስ አንድነት ገዳም የጎርፍ መቀልበሻ ግድብ ሥራ ተጠናቆ ገዳሙን ከጎርፍ ጥቃት ለመታደግ ተችሏል፡፡
በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት የበዴሳ መካነ ሰላም ቅድስት ማርያም የወተት ላም እርባታ፤ በአፋር ሀገረ ስብከት አዋሽ አርባ ቅዱስ ሚካኤል የመስኖ ልማት ፤ በሽሬ ሀገረ ስብከት ማይ ወይኒ ግዝግዝያ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የወፍጮ ተከላ፤ በከምባታ ሐዲያና ጠምባሮ ሀገረ ስብከት ዱራሜ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የበግ ማድለብ፤ ፤ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት አስፋ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የወፍጮ ተከላ፤ ፕሮጀክቶች በወጪ መጋራት መርሐ ግብር ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡
በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ደብረ ከርቤ ጥንታዊ ፍልፍል ቤተ ክርስቲያን የጊዜያዊ የጣሪያ ማልበስ ሥራ ተከናውኗል፡፡ በምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ደብረ ፀሐይ ዋንጣ ቅድስት ማርያም የንብ ልማት ፕሮጀክት ተጠናቆ ርክክብ ተደርጓል፡፡
በምእራብ ወለጋ ቂልጡ ካራ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እና በሆሣዕና ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ነባር አዳሪ ትምህርት ቤቶችን የመቀበል አቅም ለማሳደግ የማስፋፊያና የማጠናከሪያ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች፡-
በሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት የደብረ ኃይል ወደብረ ጥበባት በዓታ ለማርያም የአቋቋም ምስክር ጉባኤ ቤት ለ120 ተማሪዎች ማደሪያ፣ መማሪያና ቤተ መጽሐፍ ያለው ባለ ሁለት ፎቅ ሕንፃ እየተገነባ ሲሆን፤ ከ90 በመቶ በላይ ተጠናቋል፡፡
በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የደብረ ባሕርይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ወአባ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ባለ 3 ፎቅ ሁለገብ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡
በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ከምሥራቁ የሀገራችን ክፍሎች ተተኪ አገልጋዮችን ለማፍራት በሐረር ከተማ በደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ ገዳም ባለ አንድ ፎቅ የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት በአርባ ምንጭ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም ለተማሪዎች ልዩ ልዩ አገልግሎት መስጠት የሚችል አዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ እየተሠራ ይገኛል፤ ሥራውም በቀጣይ ጥቂት ወራት ይጠናቀቃል፡፡
የ100 ገዳማት የመረጃ ጥንቅር የምጣኔ ሀብት አመላካች መሠረታዊ መረጃ / Economical maping & profiling / የመሰብሰብ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
የአቅም ማጎልበቻ ሥራዎች፡-
ገዳማት በራሳቸው ተነሳሽነት በልማት ራሳቸውን እንዲያጠናክሩ ከ70 ገዳማት ለተውጣጡ የገዳማት አበምኔቶችና እመምኔቶች ስለ ሀብት ምንነትና አጠቃቀም፣ ስለ ፕሮጀክት አጠናን፤ እንዲሁም ስለ ሒሳብ መዝገብ አያያዝ የአንድ ሳምንት ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ በዚህም ጠንካራ ገዳማዊ ሥርዓት የሚመሠረትበትንና የገዳማት እርስ በእርስ ግንኙነት የሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
የአብነቱንና የዘመናዊዉን ትምህርት አቀናጅቶ መስጠት በሚያስችለው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነጻ የትምህርትና ሥልጠና እድል መርሐ ግብር የጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት 569 ተማሪዎችን በማሳተፍ በአራት አብነት ትምህርት ቤቶች ተጀምሯል፡፡
በ10 አብነት ትምህርት ቤቶች እና በ4 ገዳማት ለሚገኙ አባቶችና እናቶች ባለሙያዎችን በማስተባበር ሕክምና እንዲሁም የጤና፤ የግልና የአካባቢ ንጽሕና ትምህርት ተሰጥቷል፡፡
ለ120 የአብነት መምህራንና ተማሪዎች ልዩ ልዩ የአስተዳደርና የሥራ ፈጠራ ክህሎት ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
የተጠናቀቁ ጥናቶች፡-
በምዕራባዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት በሁመራ የአብነት ትምህርት ቤት እና የካህናት ማሠልጠኛ ለመሥራት የሚያስችል ጥናት ተጠናቋል፡፡
በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በጂንካ አንቀጸ ብፁዓን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም የአብነት ትምህርት ቤቱን የቅበላ አቅም ለማሳደግ ጥናቱ ተጠናቋል፡፡
በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ለዙር አባ ጽርሐ አርያም አቡነ አረጋዊ ገዳም የዝማሬ መዋስዕት ማስመስከሪያ ጉባኤ ቤት የትምህርት መስጫ ቁሳቁሶችን ለማሟላት ጥናት ተደርጎ የእቃ አቅርቦት በመደረግ ላይ ነው፡፡
በባሕርዳር ከተማ የግእዝና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሁለገብ የአብነት መምህራን፣ ተማሪዎችና መነኮሳት የሥልጠናና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ለመመሥረት የሚቻልበትን ሁኔታ ጥናት ተደርጓል፡፡ በጥናቱ መሠረትም አንድ ብሎክ ሕንፃ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦ ግንባታው ተጀምሯል፡፡
ልዩ ልዩ ድጋፎች፡-
በ162 የአብነት ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ለ182 መምህራንና ለ1,069 ተማሪዎች ወርሃዊ የገንዘብ ድጎማ ተደርጓል፡፡
ጤና ሀብት ነው በሚል መሪ ቃል 20 ሺሕ ለሚሆኑ የአብነት ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደረገ የግልና የአካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን፤ የግል ንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ተሰራጭተዋል፡፡
በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት በደብረ ሊባኖስ ገዳም፤ በምዕራፈ ቅዱሳን በልበሊት ኢየሱስ አንድነት ገዳምና በፍቼ ደብረ ሲና ዓራተ ማርያም ገዳም ለሚገኙ አብነት መምህራንና ተማሪዎች፤ እንዲሁም ለገዳማቱ ማኅበረሰብ ልዩ ልዩ የጤና ምርመራ የተደረገ ሲሆን፤ ለ80 የአብነት መምህራን የመነጽር እና የመድኃኒት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
ለ275 ቅዱሳት መካናት የእጣን፤ የጧፍ፤ የዘቢብ እና ሌሎች ንዋያተ ቅድሳት ድጋፍ ተደርጓል፡፡



በደቡብ ኦሞ ጂንካ ሀገረ ስብከት በማኅበረ ቅዱሳን የጂንካ ማእከል እየታየ ያለው ሐዋርያዊ አገልግሎት አበረታች መሆኑን የማእከሉ ሰብሳቢ አቶ ዘላለም ጌታቸው አስታወቁ፡፡
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰሜን አሜሪካ አኅጉረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ 14ኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤውን በአትላንታ መካነ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ እና በደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ወአቡነ አረጋዊ አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ት/ቤቶች አዘጋጅነት ከነሐሴ 23 – 25/2006 ዓ/ም (August 29 – 31/2014) አካሄደ።
አባላቱ የበለጠ ለአገልግሎት እንዲተጉ መነሳሳትን ፈጥሯል። በመቀጠልም ከሰባቱ የአንድነት ጉባኤው ክፍለ ግዛት መካከል በሰሜን ምዕራብ ክፍለ ግዛት ትምህርታዊ ጉባኤ ላይ ከቀረቡ ዝግጅቶች መካከል “የምንፈልገውን ወይስ የሚያስፈልገንን” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የምልከታ ጽሑፍ በዲ/ን ዳዊት ብርሃኑ አማካይነት ቀርቧል።
ከዓመታዊ የሀገረ ስብከት ስብሰባ ቆይታ በኋላ በዓመታዊ ጉባኤው ላይ ለመገኘት ቅዳሜ ምሽት አትላንታ የገቡት የዲሲ እና ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከአትላንታ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ የተክለ ሃይማኖት በዓለ ንግስ በኋላ አትላንታ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ጋር በመሆን እሁድ ከሰዓት በኋላ በጉባኤው ላይ ተገኝተዋል። ብፅዕነታቸው ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ለተመረጡት የሥራ አመራር አባላት ጸሎት ካደረጉ በኋላ ቃለ ቡራኬ አስተላልፈዋል። አንድነት ጉባኤው አገልግሎቱን አጠናከሮ መቀጠል እንደሚገባው፣ ወጣቱ ወደፊት ብዙ አገልግሎት እንደሚጠብቀው እና ሁል ጊዜ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ እንደሚገባው አባታዊ ምክርና ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል።
በዕለቱም በአብርሃም ሰሞሎን እና በቤዛ ኃይሉ የተዘጋጁ መንፈሳዊ ግጥሞች የዝግጅቱ አካላት ነበሩ። ዲ/ን ዳዊት ፋንታዬ፣ ጋሻው ታደሰ እና ሲሳይ ደንቦባ የሁለቱን ቀናት መርሐ ግብር በመምራት ዓመታዊ ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ አድርገዋል። በጉባኤው በተገኙ ዘማርያን እና አጠቃላይ አባላት በአንድነት በመሆን መዝሙር ከተዘመረ በኋላ የዓመታዊ ጉባኤው መርሐ ግብር በጸሎት ተፈጽሟል።



ለአንድ ቀን በተዘጋጀው ዐውደ ጥናት 6 በምርምር ማእከሉ የተመረጡ ጥናቶች ቀርበዋል፡፡ በዚህም መሠረት በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በመቄት ወረዳ የደብረ ገነት ናዙኝ ማርያምና የአቡነ አሮን መንክራዊ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ፤ ኪነ ሕንፃ፤ ተንቀሳቃሽ ቅርስና ያሉበት ሁኔታ በሚል ርዕስ በዲያቆን ፀጋዬ እባበይ በዲላ ዩኒቨርስቲ የአርኪዮሎጂ መምህር የመጀመሪያውን ጥናት አቅርበዋል፡፡
ሁለተኛው ጥናት ሥነ ምኅዳርን ያማከለ የአካባቢ ጥበቃ እቅድ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ደን የሥነ ምኅዳር አገልግሎት ለማሳደግ በሚል ርዕስ በመስፍን ሳህሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካባቢ ጥናት ተማሪ የቀረበ ሲሆን፤ የደብረ ሊባኖስን ገዳም ደን የሥነ ምኅዳር አገልግሎት ለማሳደግ በርካታ ሥራዎች መሠራት እንደሚገባቸው በጥናት አቅራቢው ተገልጿል፡፡ ቀድሞ የነበረው ተፈጥሯዊ ደን መመናመን፣ በተለያዩ ምክንያቶች መሬቱ እየተራቆተ መምጣቱ፤ የአፈሩ መሸርሸር፣ ለጐርፍ አደጋ ገዳሙ መጋለጡንና የአካባቢው የአየር ጸባይ መለዋወጥ ገዳሙን ለከፍተኛ አደጋ እንዳጋለጠው ጠቅሰዋል፡፡
ከፊደላት ጋር የሚከሰቱ ችግሮችን አስመልክቶም በአማርኛ ፊደል ገበታ ላይ ተመሳሳይ ድምጽ ያላቸው ስለሚገኙ፤ በአጻጻፍ ረገድ በርካታ ልዩነቶች መኖራቸው፤ ራብዕ ድምጸት ያላቸው ከግእዙ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ፊደላት መኖራቸው፤ ሳድስና ሳልስን እያቀያየሩ መጠቀም፣ ደቃልውና ፍንድቅ ፈደላትን በዝርዝር የመጠቀም ዝንባሌ፣ በመሠረታዊ ቃሉ ላይ የሌለውን ቃል መጨመር፣ የአናባቢዎች ቅጥል አለመለየት ችግሩን ይበልጥ እንዳሰፋው ጠቁመዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያን በዓላውያን ነገሥታት አሰቃቂ ስደት በደረሰባት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ምዕት ዓመታት ውስጥ ከተነሱት የቤተ ክርስቲያን አበው መካከል አንዱ የሆነውና ለዛሬው የተጋድሎውን ዜና በአጭሩ የምንመለከተው ሰማዕት ቅዱስ ሰራባሞን ዘኒቅዩስ ነው። አባቱ አብርሃም ይባላል፤ አያቱ የቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስ አጎት ሲሆን የተወለደው በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢየሩሳሌም ነው። ሲወለድ ወላጆቹ “ስምዖን” ብለው ስም አወጡለት፤ “ሰራባሞን” የጵጵስና ስሙ ነው። የዐረብኛ እና የግዕዝ መጻሕፍት “ሰራባሞን” ሲሉት፣ የቅብጥና እንግሊዝኛ ምንጮች ደግሞ “ሰራፓሞን” ብለው ይጠሩታል።
ማኅበረ ቅዱሳን በ2006 ዓ.ም. ከዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች ግቢ ጉባኤያት በርካታ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ በዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች ቆይታቸው ያስመዘገቡት ውጤት ከፍተኛ በመሆኑም በርካቶች የተሸለሙትን ዋንጫና ሜዳልያ በሥጦታ ለማኅበሩ በማበርከት ላይ ይገኛሉ፡፡
ደስታ ሲገልጹ “ይህ ውጤት በሀገራችን በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ታሪክ በጥቂቶች ብቻ ሊመዘገብ የሚችል ከፍተኛ ውጤት ነው፡፡ ካስመዘገበው ውጤት ይልቅ ደግሞ ታማኝ አገልጋይ ሆኖ በሕይወቱ አንድ ጊዜ ብቻ ሊገጥመው የሚችለውን እድል ውድ ሥጦታ ለማኅበሩ መሥጠቱ አስደንቆኛል፡፡ ብዙዎቻችንንም ያስተማረ ነው፡፡ ወደፊትም በሕይወቱ የተሳካ ጊዜ አሳልፎ ለሌሎች አርአያ እንዲሆን እመኛለሁ” ብለዋል፡፡
ማእከል የፈቃደ እግዚእ ኮሌጅ ተመራቂዎቹ ዘውዴ ደሴና ከፍያለው ስመኝ ለማኅበሩ ማእከላት ሜዳልያቸውን አስረክበዋል፡፡ እንዲሁም ከሐረር የሜንሽን አግሮ ቴክኒካል ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ ሰብሳቢ የሆነው ቃል ኪዳን ዓለሙ ሜዳልያውን በማእከሉ በኩል ለኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን እንዲሰጥለት አበርክቷል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ነሐሴ 24 እና 25 ቀን 2006 ዓ.ም. በማኅበሩ ሕንፃ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሀገር ውስጥና የውጭ ማእከላት፤ የወረዳ ማእከላትና ግንኙነት ጣቢያዎች፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት ተወካዮች፤ የማኅበሩ ሥራ አመራርና ሥራ አሥፈፃሚ አባላት፤ የማኅበሩ ልዩ ልዩ ክፍል ተጠሪዎች፤ ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት አካሄደ፡፡
የጠቅላላ ጉባኤው ተሳታፈዎች ከነሐሴ 23 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፤ የጸሎት፤ የመርሐ ግብር ትውውቅና ማስገንዘቢያ በጠቅላላ ጉባኤው አዘጋጅ አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ በዶክተር ዳኝነት ይመኑ ቀርቧል፡፡ የእጽበተ እግር መርሐ ግብርም ተከናውኗል፡፡
አገልግሎት ፤ የአብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማትን በማጠናከር ረገድ፤ የቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ አገልግሎት ለማጠናከር ከአህጉረ ስብከቶች ጋር እየተሠሩ ስለሚገኙ በርካታ ተግባራት ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያትን በማጠናከር ረገድ፤ የማኅበሩን ተቋማዊ አቅም ለማሳደግ እየተሠሩና በመሠራት ላይ የሚገኙ ሥራዎች፤ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሔዎችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
ጠቅላላ ጉባኤው በሁለተኛ ቀን ውሎው ብፁዕ አቡነ ሰላማ የምሥራቅ ሐረርጌ ሊቀ ጳጳስ የተገኙ ሲሆን፤ በሰጡት ቃለ ምእዳን “ያሰባሰባችሁ እግዚአብሔር ነው፤ በእናንተ ኃይል አልተሰባሰባችሁም፡፡ ፈቃደ እግዚአብሔር አስነስቷችኋልና በጉዟችሁ ፈተና ሊገጥማችሁ ይችላል፡፡ ፈተና ደግሞ ያለ ነው፤ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም፡፡ ከሚወድህ ይልቅ የሚጠላህ ይጠቅምሃል እንዲሉ አባቶቻችን ካልተፈተኑ ክብር አይገኝም፡፡ በአገልግሎታችሁ እንደጸናችሁ ሳትበሳጩ ልትጓዙ ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር ማኅበሩን ይባርክ” ብለዋል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን ስልታዊ እቅድ አጋማሽ ዘመን ግምገማ በማስመልከት ከጥር 2005 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 2006 ዓ.ም. የተከናወኑትን ሥራዎች ተገምግመው ሓላፊነት በወሰደው አጥኒ ቡድን ለጠቅላላ ጉባኤው ቀርበዋል፡፡ ጠቅላላ ጉባኤውም ውይይት በማድረግ አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሠረት ቀጣይ አፈጻጸማችን ምን መምሰል እንደሚገባው ለማሳየት ቢሞከር፤ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ከስትራቴጂክ እቅዱ አንጻር አስታርቆ ማስኬድ፤ የክብደት አሥራር ሥርዓቱን ግልጽ ማድረግ፤ ግምገማው ከስልታዊ እቅዱ ጋር በደንብ ቢታይ የሚሉና ሌሎችም ጠቃሚ ነጥቦች ከተካተቱት ውስጥ ይገኙበታል፡፡ የጥናት ቡድኑ ከጠቅላላ ጉባኤው በተሰጡት ሃሳቦች መሠረት የግምገማውን ውጤት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመደበኛ ሥራ አመራር ጉባኤ እንዲያቀርብ፤ ሥራ አመራር ጉባኤውም አጽድቆ በሚመለከታቸው አካላት ተግባራዊ እንዲደረግ እንዲያስተላልፍ ውሳኔ ላይ ተደርሷል፡፡