የምን አለበት መዘዝ!

በዚህ ቃል ብዙዎች ሕይወታቸው ተጎድቷል፤ ሃይማኖታቸውም እንዲሁ፤ ለምሳሌ “ባንጾም ምን አለበት? እግዚአብሔር ምን ሠራችሁ እንጂ ምን በላችሁ አይለንም” የሚሉ አሉ፤ “መስቀል ባንሳለም ምን አለበት? ወደ ቤተ ክርስቲያን ባንሄድ ምን አለበት? እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ አለ” የሚሉ ሰዎችም አሉ፤ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ከሕዝባችን ባህል ውጪ “በምን አለበት” የሚጓዙ ሰዎች ጥቂቶች አይደሉም።፡

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት

በዚህ ሳምንት የቃል ርደት፣ የወልድ ልደት፣ የአዳም ድኅነት ቢነገርም እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ከሰማይ የወረደ ሰማያዊ፣ በክብር ያረገ በኩረ ትንሣኤ መሆኑ አይዘነጋም፡። ለዚህም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ነገር ግን ምስክርነታችንንም አትቀበሉትም። በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁኝ፥ በሰማይ ያለውን ብነግራችሁ እንዴት ታምኑኛላችሁ? ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው።

ሀልዎተ እግዚአብሔር

ዲያቆን ተስፋዬ ቻይ 

የካቲት ፳፮፤፳፻፲፮ ዓመተ ምሕረት

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች!  እንዴት አላችሁልን? ትምህርት እንዴት ነው? የግማሽ ዓመት ትምህርት ተጀምሯልና በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በነበረው የትምህርት ወቅት ደከም ያለ ውጤት ያስመዘገባችሁበትን ትምህርት በደንብ ትኩረት ሰጠታችሁ በመማር ማሻሻል ይገባል! ቤተ ክርስቲያን በመሄድም መንፈሳዊ ትምህርት መማርንም አትዘንጉ! ደግሞም ፳፻፲፮ ዓ.ም. (የሁለት ሺህ ዐሥራ ስድስት) ዐቢይ ጾም መጋቢት ሁለት ይጀምራልና ከምንጊዜውም በተለየ መልኩ በጸሎት መትጋት አለብን፡፡  ዕድሜያችን ከሰባት ዓመት በላይ የሆነን ደግሞ እንደ አቅማችን መጾም አለብን! መልካም!!!

ልጆች! አሁን ለዛሬ ወዳዘጋጀንላችሁ ትምህርት እናምራ! በባለፈው የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን “ሃይማኖት” በሚል ርእስ ተምረን ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ ስለ “ሀልዎተ እግዚአብሔር” ማለትም ዓለምን ሁሉ የፈጠረ የአምላካችን የእግዚአብሔር መኖር በምን እንደሚታወቅ እንማራለን፤ ተከታተሉን!

“ሀልዎት” ማለት “መኖር” ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ገጽ ፫፻፸) ሀልዎተ እግዚአብሔር ስንል ደግሞ የእግዚአብሔር መኖር ማለታችን ነው፤ ባለፈው ትምህርታችን ላይ ሁሉን ያስገኘና የፈጠረ እግዚአብሔር መሆኑን ያወቅነው በሃይማኖት እንደሆነ እንደተማራችሁት ዛሬ ደግሞ “የእግዚአብሔር መኖር በምን ይታወቃል የሚለውን በተወሰነ መልኩ እንማማራለን፡፡

የአምላካችን የእግዚአብሔር መኖር ከሚታወቅባቸው ነገሮች አንዱ ሥነ ፍጥረት ነው፤ ለዚህ ዓለም ፈጣሪ (አስገኚ) አለው፤ የሚታየውን እንደገናም እኛ የማናያቸውን ፍጥረታት ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ጻድቁ ኢዮብ እንዲህ ሲል መስክሯል፤ ‹‹አሁን ግን እንስሶችን ጠይቅ፤ ያስተምሩህማል፤ የሰማይንም ወፎች ጠይቅ፤ ይነግሩህማል፤ ወይንም ለምድር ተናገር፤ እርስዋም ታስተምርሃለች…፡፡›› (ኢዮብ ፲፪፥፯) አያችሁ ልጆች! እግዚአብሔር የሁሉ ፈጣሪ መሆኑን እንስሳትም እንኳን ምስክር ይሆነናሉ፡፡

ሌላው ደግሞ ልጆች! ነቢዩ ኢሳይያስ አምላካችን እግዚአብሔር ፍጥረታትን እንደፈጠረ እንዲህ ነግሮናል፤ ‹‹…ሠሪውም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ስለሚመጣው ነገር ጠይቁኝ፤  …እኔ ምድርን ሠርቻለው፤ ሰውንም በእርሷ ላይ ፈጥሬአለሁ፤ እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቻለው…፡፡››     (ኢሳ. ፵፭፥፲፩-፲፪)

ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስን ገና ስንገልጠው ባለው በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ፤ ‹‹በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ…፡፡›› (ዘፍ.፩፥፩) እንግዲህ ልጆች! እግዚአብሔር የዚህ ዓለም ፈጣሪ እንደ ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ማስረጃዎች አሉ፤ ለግንዛቤ ያህል ግን ይህን አቀረብን፡፡

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እግዚአብሔር ለመኖሩ ሌላው ምስክር ደግሞ ፍጥረታትን ስንመለከት ሁሉም ሥርዓታቸውን ጠብቀው መንቀሳቀሳቸውን ስንረዳ ነው፡፡ ለምሳሌ ፀሐይን ብንወስድ ጠዋት ከምሥራቅ ወጥታ ማታ በምዕራብ ትጠልቃለች፤ ጨለማና ብርሃን፣ ሌሊትና ቀንም፣ ክረምትና በጋም ይፈራረቃሉ፤ የእነዚህ ፍጥረታት እንቅስቃሴ እግዚአብሔር እንዳለ ያስረዳሉ፤ እኛም የሰው ልጆች እግዚአብሔር እንዳለ ምስክሮች ነን፡፡

ልጆች! ሃይማኖት ያለው ሰው እግዚአብሐር እንዳለ ያምናል፤ ይመሰክራልም፤ አንዴ ምን ሆነ መሰላችሁ? የእግዚአብሔር ወዳጅ አብርሃም አባታችን ቤተ ሰቦቹ ጣዖት የሚያመልኩ ነበሩ፡፡ ጣዖት ታውቃላችሁ አይደል ልጆች? ጣዖት ማለት ሰዎች ድንጋይ ጠርበው አልያም ደግሞ እንጨት አለዝበው የሚሠሩትና አምላክ ነው ብለው የሚያምኑት ማለት ነው፡፡ ታዲያ አብርሃም አባቱ ታራ የሠራውን ጣዖት እንዲሸጥ ወደ ገቢያ ላከው፡፡ አብርሃምም ዓይን እያለው የማያይ፣ ጆሮ እያለው የማይሰማ፣ እግር እያለው የማይሄድ ጣዖት የሚገዛ እያለ በገቢያ መሐል መዞር ጀመረ፡፡

ይገርማችኋል ልጆች! ሰው ሁሉ እርሱ ያላመነበትን እርሱ ያቃለለውን ማን ይገዛዋል እያሉ ሳይገዙት ቀሩ፤ አብርሃምም አባቱ እየሠራ የሚሸጠውን ጣዖት “አምላክ ከሆንክ አብላኝ፤ ርቦኛል፤ አጠጣኝ፤ ጠምቶኛል” አለው፤ ግን ምንም አልመለሰለትም፤ ግዑዝ ነገር (መናገር የማይችል) ነበርና፤ አብርሃምም ጣዖቱ አምላክ አለመሆኑን ተገነዘበ፡፡ ወዲያውኑ በደንጊያ ቀጠቀጠው፤ ከዚያም የሁሉን ፈጣሪ መፈለግ ጀመረ፤ነፋስን፣ እሳትን ፀሐይን፣ ጨረቃን ፣ ወንዙን፣ ተራራውን ሁሉ በየተራ እያፈራረቀ አምላክ መሆናቸውን ተመራመረ፡፡ አንዱ አንዱን ሲያሸንፈው፣ አንዱ በአንዱ ሲተከ ተመለከተ፡፡ የዚህን ጊዜ የእነዚህ ሁሉ ፈጣሪ እንዳለ ተገነዘበና “የፀሐይ አምላክ ተናገረኝ” ብሎ ለመነ ( ጸለየ)፡፡ እግዚአብሔርም ድምጹን አሰማው፤ ጣዖት ከሚመለክበትም ከተማ ተለይቶ እንዲወጣ ነገረው፡፡ አብርሃምም ከዚያ ከተማ እግዚአብሔር ወደ ነገረው ቦታ ሄደ፡፡ (ዘፍ.፲፩፥፳፰ አንድምታው)

ውድ እግዚአብሔር ልጆች! እግዚአብሔርን በዓይናችን ማየት ባይቻለንም በሥነ ፍጥረቱ በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት፣ በውስጣችን ባለው ኅሊናችን መኖሩን እናውቃለን፡፡ ቀን ፀሐይን ያወጣልናል፤ በክረምት ዝናም ይሰጠናል፤ የተዘራው ዘር እንዲያድግ ፍሬን እንዲይዝ ያደርግልናል፡፡ ክረምትና በጋን ያፈራርቃል፡፡ እኛንም ይመግበናል፤ ከጠላታችን ዲያብሎስ ይጠብቀናል፤ ሁሉን የፈጠረ፣ ሁሉን የሚያውቅ እግዚአብሔር መኖሩን ማመን መልካም ሥራን በመሥራት፣ ሕጉን ትእዛዙን በመጠበቅ ልንኖርና ልንመሠክር ያስፈልጋል፤ እግዚአብሔር መኖሩን ለሰዎች መልካም በማድረግ፣ አታድርጉ የተባልነውን ባለማድረግ፣ አድርጉ ተብለን የታዘዝነውን መልካም ነገር ደግሞ በማድረግ በእግዚአብሔር ማመናችንን መመስከር አለብን ፤ ቸር ይግጠመን!!!

ስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

“ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤ ድል ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው” (ምሳሌ ፳፩÷፴፩)

በማናቸውም ውጊያ እግዚአብሔርን ኃይል ያደረጉና ለእውነት የቆሙ ሁሉ የሚያሸንፋቸው ማንም አይኖርም፡፡ የእግዚአብሔር ወገን የተባሉ እስራኤል ዘሥጋ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከቤተ አሕዛብ ጋር እንደ ተዋጉና የእግዚአብሔርን ሕጉ ጠብቀው፣ ፈቃዱን በመፈጸምና እርሱን በመማጸን ሀገራቸውን፣ ርስታቸውንና እምነታቸውን ለመከላከል ለሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ ድል ያደርጉ እንደ ነበር መጽሐፍ ይነግረናል፡፡

ሀገሬ!

በአንቺ ነው መኖሬ

የምወድሽ ሀገሬ

ፊደላትን ቆጥሬ

ሃይማኖትን ተምሬ

ያፈራሁብሽ ፍሬ!

የሦስቱ ቀናት ጾም

በበደላቸው ምክንያት የነነዌ ሕዝብ ሊጠፉ በመሆናቸው ከሕፃናት ጀምሮ እስከ አረጋዊ ብቻም ሳይሆን እንስሳት ጭምር የጾሙት የሦስት ቀናት ጾም ‹‹ የነነዌ ጾም›› ተብሏል፡፡

ሰባቱ ኪዳናት፡- ኪዳነ ምሕረት

በድንቅ ጥበቡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ያደነው እጅጉን መሐሪ ስለሆነ ነው፡፡ የቀደሙት የብሉይ ኪዳን ኪዳናት ሕዝቡን ከሲኦል መታደግ አልቻሉም ነበር፡፡ ፍጹም የሆነው ኪዳን የተደረገው በሰባተኛው ኪዳን ይህም ለሰው ዘር ምሕረትን ባስገኝች በንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡

ሃይማኖት

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን! ብዙ ጊዜ እንደምንነግራችሁ አሁን ያላችሁበት ዕድሜ በምድራዊ ኑሮ ለነገ ማንንታችሁ መሠረት የምትጥሉበት ስለ ሆነ ጨዋታ እንኳን ቢያምራችሁ ቅድሚያ የምትሰጡት ለትምህርት መሆን አለበት! መልካም!
አሁን ሃይማኖት በሚል ርእስ ለዛሬ ወደ አዘጋጀንላችሁ ትምህርት እናምራ!

ነቢዩ ሶምሶን

ሶምሶንም “ከፍልስጥኤማውያን ጋር ልሙት” አለ፤ ተጎንብሶም ምሰሶቹን በሙሉ ኅይሉ ገፋ፤ ቤቱም በውስጡ በነበሩት በመኳንንቱም በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፤ በሞቱም የገደላቸው ሙታን በሕይወት ሳለ ከገደላቸው በዙ። ወንድሞቹም የአባቱ ቤተ ሰቦችም ሁሉ ወረዱ፤ ይዘውም አመጡት በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በአባቱ በማኑሄ መቃብር ቀበሩት፤ እርሱም በእስራኤል ላይ ሃያ ዓመት ፈረደ።

ቀለማትና ትርጉማቸው

ቀለማት በመንፈሳዊ እይታ ውክልና ትርጉም ሲኖራቸው በሌላ ስፍራ ደግሞ ሌላ ትርጉምና ውክልና አላቸው፤ በፍልስፍናው ዓለም ግን ሰዎች ሐሳባቸውን፣ ስሜታቸውንና አስተሳሰባቸውን ለመግለጽ ሲጠቀሙባቸው ይስተዋላል፡፡ ሰዎች ራሳቸው ተስማምተው ስያሜ ሰጧቸው እንጂ አሁን ያላቸውን ትርጓሜና ውክልና ይዘው አልተፈጠሩም፡፡ የሰው ልጆች በጋራ ስምምነት ለራሳቸው መግባቢያነትና ለነገሮች መግለጫነት የወከሏቸው መሆናቸውን ልብ ማለት ያሻል፡፡