ሰባቱ ኪዳናት
ኪዳን በሰውና በእግዚአብሔር እንዲሁም በሰውና በሰው መካከል የሚመሠረት ስምምነት ነው።ዋናው ጉዳያችን እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር የሚያደርገው ቃል ኪዳን ነው። በባሕርይ የማይታየው እግዚአብሔር ምሕረቱ የበዛ ስለሆነ ብዙ ጊዜ ከፍጥረቱ ጋር መሐላ ፈጽሟል። ከብዙ አበው ጋርም ቃል ኪዳን አድርጓል። የማይታይና ኃያል እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር የሚያደርገውን ውል ለተመለከተ ቸር አምላክ እንዳለው ያውቃል።