ዳግመኛ መወለድ(ለሕፃናት)
ሚያዚያ 10 ቀን 2005 ዓ.ም.
በቤካ ፋንታ
እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች፡፡ ዛሬ የምንማረው የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚወለዱ ነው፡፡
አንድ መምህር በኢየሩሳሌም ነበረ፣ ስሙም ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ ቀን ቀን ተማሪዎቹን ሲያስተምር ይውልና ማታ ፀሐይዋ ስትጠልቅ በጨለማ ወደ አምላካችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይመጣል፡፡ ከዚያ እግሩ ሥር ቁጭ ብሎ ይማራል፡፡ ያልገባውን እየጠየቀ በደንብ ስለሚከታተል ጌታችንም እስኪገባው ድረስ ግልጽ አድርጎ ያስረዳውና የጠየቀውን ይመልስለታል፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ኒቆዲሞስ የእግዚአብሔርን ቃል ለመማር ከቤቱ ተነሥቶ በሌሊት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ መጣ፡፡ አምላካችንም በዚያ ሌሊት ለኒቆዲሞስ ያስተማረው ትምህርት እንዲህ የሚል ነበር፡፡ “ኒቆዲሞስ ሆይ፥ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ወደ መንግሥተ ሰማያት አይገባም፡፡”

በማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናት ልማት እና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ከየማዕከላቱ ለተውጣጡ 38 የክፍል ተጠሪዎች ከሚያዝያ 4 ቀን 2005 ዓ.ም. በዋናው ማእከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተካሄደ፡፡
ከንጋቱ 12፡30 ደምበጫ ከተማ ላይ ካረፍንበት የማኅበረ ቅዱሳን ከራድዮን ምግብ ቤት ተነስተን ከወረዳ ማእከሉ ወንድሞቻችን ጋር ሆነን ወደ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በማምራት ጸሎት አደረስን፡፡ በያዝነው እቅድ መሠረት ዲያቆን ቴዎድሮስ ኃይሉና ዲያቆን ዮሴፍ ይኩኖ አምላክ የጽርሐ አርያምን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንዲሰሩ እዚያው ትተናቸው የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጁ ቶማስ በየነ፤ የቪዲዮ ካሜራ ባለሙያው ሙሉጌታ፤ ዲያቆን ታደለ ሲሳይና እኔ ሆነን የደብረ ገነት ሸረት መድኀኔዓለም ገዳምን ለመዘገብ ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ሲሆን እግዚአብሔርን ተስፋ አድረገን በሾፌራችን ነብያት መንግስቴ እየተመራን የ47 ኪሎ ሜትሩን መንገድ ተያያዝነው፡፡