በባዕድ ምድር እስከመቼ?
ሰኔ 14 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ዶ/ር መርሻ አለኸኝ
የስምዐ ጽድቅ ዝግጅት ክፍል በዝርወት ለሚኖሩት የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች የእናት ቤተ ክርስቲያናቸውን አስተምህሮ፣ ምክርና ተግሳጽ ይሰሙ ዘንድ ዓምድ በከፈተላቸው ጊዜ፤ መጀመሪያ ወዲያውም ዓምዱን ማስተዋወቂያ ቢሆን ብዬ የጻፍኩት ጽሑፍ ዐራት እትሞች ዘልቆ ተፈጸመ፡፡ ጽሑፉን አስመልክቶ ከተለያዩ ጓደኞቼ ካገኘሁአቸው አስተያየቶች በመነሣት እንደ አብርሃም ሁሉ የያዕቆብን የስደት ሕይወት በመመርመር ለዛሬዎቹ ስዱዳን አርኣያ በሚኾን መልኩ በአጭሩ ለማቅረብ መረጥኩ፡፡ ጽሑፉ ይኸውና፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ግን ኑሮአቸውን በስደት ያደረጉ ወንድሞችና እኅቶች ዕለት ከዕለት ከሚያጋጥማቸው ችግር በመነሣት ጽሑፎችን አዘጋጅተው ወደ ዝግጅት ክፍሉ በመላክ ቢማማሩ መልካም ነው፡፡