የማቴዎስ ወንጌል
ነሐሴ 9 ቀን 2006 ዓ.ም.
ምዕራፍ ስድስት
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የሚከተሉት አሳቦች ተጠቃልለው ይገኛሉ፡፡
-
የምጽዋት ሥርዓት
-
ጠቅላላ የጸሎት ሥርዓት
-
የአባታችን ሆይ ጸሎት
-
ስለ ይቅርታ
-
የጾም ሥርዓት
-
ስለ ሰማያዊ መዝገብ
-
የሰውነት መብራት
-
ስለ ሁለት ጌቶች
-
የዕለት ጉርስና የዓመት ልብስ
1. የምጽዋት ሥርዓት፡- ጌታችን በዚህ ትምህርቱ እንደ ግብዞች መመጽወት እንደማይገባ ተናግሯል፡፡ ግብዞች የሚመጸውቱት ሰው ሰብስበው፣ ቀን ቀጥረው በተመሳቀለ ጉዳና በአደባባይ ነው፡፡ የሚመጸዉቱትም ለመጽደቅ ሳይሆን ለውዳሴ ከንቱ ስለሆነ፤ ስለዚህም አንተ በምትመጸውትበት ጊዜ ቀኝ እጅህ የምትሠራውን ግራ እጅህ አትወቀው ብሏል፡፡ እንዲህም ያለበት ምክንያት፡-