የዓለሙ ፍጻሜ ምልክቱ ምንድን ነው? – ክፍል ሁለት
‹‹የጥፋት ርኵሰት በተቀደሰው ሥፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል›› ተብሎ እንደ ተጻፈው /ማቴ. ፳፬፥፲፭/፣ በየአጥቢያው የሚሰማውን ክፉ ወሬ ስናስተውል የዚህን ትንቢት ተፈጻሚነት እንረዳለን፡፡ የተሐድሶ ሤራ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚፈጠረው ጭቅጭቅ፣ ሐሜት፣ ሙሰኝነት፣ ዘረኝነት፣ ወዘተ. ምን ይነግሩናል? በአንዳንድ የውጭ አገር ክፍሎችም አብያተ ክርስቲያናት በሰበካ ጉባኤ ሳይኾን ለካህናት ክብር በማይጨነቁ የቦርድ አመራሮች መተዳደር ጀምረዋል፡፡ ይህ አሠራር ለዘመናት ቤተ ክርስቲያን ከኖረችበት አገልግሎት አንጻር ስናየው እጅግ የራቀና የከፋ ነው፡፡