ታቦተ ጽዮን
ታቦተ ጽዮን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትመሰላለች፤ ይህን ለመረዳት ስለ ታቦተ ጽዮን አሠራርና መንፈሳዊ ትርጉም አስቀድመን ልናውቅ ይገባናል፡፡
This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 1010 entries already.
ታቦተ ጽዮን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትመሰላለች፤ ይህን ለመረዳት ስለ ታቦተ ጽዮን አሠራርና መንፈሳዊ ትርጉም አስቀድመን ልናውቅ ይገባናል፡፡
በአለፉት ሳምንታት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ተማሪዎችን ከሚማሩበት ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች በማሳደድ እና የተወሰኑትን እንዳይወጡ በማገድ ሙሉ በሙሉ ከትምህርት ማፈናቀል የጀመሩት የጥፋት ኃይሎች በመቱና ቦንጋም ተመሳሳይ ድርጊት እየፈጸሙ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ኅዳር ፲፪ የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ከተከበረ በኋላ ኅዳር ፲፭ በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ ተሰቅለው የነበሩትን ሰንደቅ-ዓላማዎችን እያወረዱ ወደነበሩት የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮች…..
ጾመ ነቢያት ምንም እንኳን ዓላማው አንድ ቢሆንም የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡ በዋነኝነት ነቢያት ስለጌታ ሰው መሆንና ስለ ሰው መዳን የጸለዩትን ጸሎት የጾሙትን ጾም በማሰብ፤ የአምላክ ሰው መሆንን ምሥጢር በትንቢት ተመልክተው ለእኛ ለሰው ልጆች የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ አስበው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስንዱ እመቤት ስለሆነች ይህ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል በወቅቱ ለእስራኤል ዘሥጋ መሆኑን በኅዳር ዐሥራ ሁለት ቀን ትመሰክራለች፡፡ በዚህ ዕለት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን እየመራ ከግብፅ ምድር ከፈርዖን ግዛት ማውጣቱን ትዘክራለች፡፡
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን በየዘመናቱ በሚነሱ መናፍቃን ስትፈተን እንደኖረች በታሪክ የታወቀ ነው፡፡ ዛሬም የተለያዩ የጥፋት ኃይሎች ቤተ ክርስቲያንንና ክርስትናን ለማጥፋት ያቀዱትን ትልም ለማሳካት በተዘዋዋሪና በይፋ ግፍ እና በደል እየፈጸሙ ይገኛሉ፡፡
ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡
ስደት የተጀመረ በአባታችን በአዳምና፥ በእናታችን በሔዋን ነው፡፡ እነዚህ ወላጆቻችን ሕገ እግዚአብሔርን አፍርሰው በሞተ ሥጋ ላይ ሞተ ነፍስ፥ በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም ተፈርዶባቸው ለአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን ከነበሩበት ተድላ ደስታ ካለበት ገነት ተሰድደው ወደ ምድረ ፋይድ ወርደዋል፡፡
ለጊዜው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ስብከት የሰበከው አሕዛብ ለነበሩ የአቴና ሰዎች ቢሆንም፤ ለእኛም ጭምር ትልቅ መልእክትን የያዘ ቃል ነው፡፡ በተለይም ‹‹እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታቸው ንስሓ ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል፤››…..