ቃና ዘገሊላ
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደ ሙሽራ አጊጣ፣ ለበጉ ሰርግ ያለ እድፍና ያለ ነውር ውብ ሆና ተዘጋጅታ በምትቀርብበት በዚያ ሰማያዊ ሰርግ ለመገኘትና ወደ በጉ ሰርግ ራት ገብተን፣ ካጌጡ ቅዱሳን ጋር ለመቀመጥና ለመብላት የበቃን ያድርገን፡፡
This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 1014 entries already.
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደ ሙሽራ አጊጣ፣ ለበጉ ሰርግ ያለ እድፍና ያለ ነውር ውብ ሆና ተዘጋጅታ በምትቀርብበት በዚያ ሰማያዊ ሰርግ ለመገኘትና ወደ በጉ ሰርግ ራት ገብተን፣ ካጌጡ ቅዱሳን ጋር ለመቀመጥና ለመብላት የበቃን ያድርገን፡፡
አሁን ግን ‹‹መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ›› እንዲል (፩ኛ ጴጥ.፪፥፭) ከኃጢአት ርቀን፣ በቅንነት፣ በእምነት፣ በበጎ ሕሊና እንድንመላለስ ከብርሃነ ከጥምቀት ጸጋና በረከት እንድናገኝ የአምላካችን ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን።
መጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ የተዘጋጀ ነው፡፡ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መጽሔቱን ያንብቡ!
በዘመነ ሥጋዌ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርተ ወንጌልን በቃሉ አስተምሮ እንዲሁም ለሐዋርያት ቃሉን በዓለም እንዲዘሩ ‹‹ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ለፍጥረትም ሁሉ ወንጌልን ስበኩ›› ብሎ ባዘዛቸው መሠረት ወንጌል በምንኖርባት ምድር ለዘመናት ስትሰበክ ኖራለች፡፡ (ማር.፲፮፥፲፭) ጻድቃን አባቶቻችንም ለእኛ ሐዲስ ኪዳን ሰዎች ቃሉን በአደራ እንዳስረከቡንም በተመሳሳይ መልኩ ለልጆቻችንና ለልጅ ልጆቻችን የእግዚአብሔርን ቃል አስተምረን በሃይማኖትና በክርስቲያናዊ ምግባር ኮትኩተን ማሳደግ ኃላፊነችን ነው፡፡
በደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ዳሰነች ወረዳ ፲፫፻፹፮ አዳዲስ አማንያን በማኅበረ ቅዱሳን የሐዋርያዊ ተልእኮ አስተባባሪነት የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን ማግኘታቸው የተገለጸ ሲሆን ተጠማቂያኑ ባለፉት ወራት መሠረታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት ሲማሩ ከነበሩ ወገኖች መካከል መሆናቸው ታውቋል፡፡ ሥርዓተ ጥምቀታቸውም በኦሞ ብሔረ ብፁዓን አቡነ ዜና ማርቆስ ወአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አንድነት ገዳም ጥር ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ተፈጽሟል።
በባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት ቀኑ ዐሥር ሰዓት ሲሆን ከዚህ በኋላ ሌሊቱ እየጨመረ ይሄዳል። ጥር የሚለው ስያሜ “ጠር፣ ጠይሮ፣ ጠየረ፣ ጠሪእ፣ (ጠርአ፣ ይጠርእ፣ ጸርሐ) ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጒሙም “መጥራት፣ መጮኽ፣ አቤት ማለት” ነው፡፡ (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፭፻፲) ጥር የወር ስም ሆኖ በታኅሣሥ ወር እና በየካቲት ወር መካከል የሚገኝ፣ ከዐሥራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ አምስተኛው ነው።
በዚህም ወር ዘመነ አስተርእዮ ይታሰባል፤ አስተርእዮ በጥሬ ትርጉሙ “መገለጥ” ነው፤ ይህም ወቅት በዋናነት ስውር የነበረ ምሥጢረ ሥላሴ የተገለጠበት፣ ሰማያዊ አምላክ በኩነተ ሥጋ ለድኅነተ ዓለም ሲል በዚህ ዓለም የተገለጠበት፣ ሰማያዊ ምሥጢርም የታየበት ድንቅና ልዩ ዘመን ነውና እንዲህ ተብሎ ተጠራ።
ውድ ክርስቲያኖች! ይህ የሰው ልጅ ታሪክ የተቀየረበትን ዕለት በደስታ፣ በፍቅር፣ የተጣላን ታርቀን፣ የበደልን ክሰን፣ በኃጢአት ያደፈ ሕይወታችን በንስሐ አንጽተን፣ በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ ሕይወታችንን አስቀድሰን እናክብረው!
መልካም በዓል!
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ! ነቢያት በብሉይ ኪዳን “አቤቱ ከሰማያት ወርደህ፣ ተወልደህ አድነን” ብለው የተነበዩት ትንቢት ተፈጽሞ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደበትን ቀን በድምቀት እናከብር ዘንድ ይገባል፡፡
ልጆች! ለዛሬ “የቱን ታስታውሳላችሁ?” በሚለው ላቀረብንላችሁ ጥያቄዎች ምላሾቹን ይዘን ቀርበናል፡፡ አንብባችሁ ምላሽ የሰጣችሁ በርቱ! ያልመለሳችሁ ደግሞ በቀጣይ በምናዘጋጀው ጥያቄና መልስ ተሳተፉ!
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤ በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው። ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል። የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና።”
ተወዳጆች ሆይ! ስሙ እንደ መዓር በሚጣፍጥ፣ መድኃኒትም በሚሆን፣ በቅዱስነቱ ዘለዓለም ያለ ረዓድ በአስጨናቂዎቻችን ፊት ክብር እና ሞገስ አግኝተን፣ ሕያውም ሆነን በምንኖርበት በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዴት ሰነበታችሁ? ፍቁራን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ፣ በባሕርይ አባቱ በአብ፣ በባሕርይ ሕይወቱ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ሳምንቱን አልፈን በቀጣይ ክፍል እነሆ ተገናኘን!
በባለፈው ሳምንት ስለ ማኅበራዊ ሕይወታችን፣ በእኛ ዘመን ምን እየሆነ፣ ምን እየሠራን እያለፍን እንደሆነ፣ ካለፈው ዘመን ጋር እያመሳሰልን ከራሳችን ጋር እየመዘንን በስሱም ቢሆን ገረፍ አድርገን ለማየት ሞክረናል። ዛሬም ያንኑ ርእሰ አንቀጽ ይዘን ማኅበራዊ ሕይወት በክርስትና አስተምህሮ እና በዘለዓለማዊ የሕይወት ሽግግራችን ያለውን ምልከታ፣ የማኅበራዊ ሕይወት መሳሳት መንሥኤዎችን እና መዳኛ የሚሆነንን ጠቅሰን እናልፋለን።
