አሜሪካ አቀፍ የአቡነ ጎርጎርዎስ ተማሪዎች ዓመታዊ ውድድር መካሄዱ ተገለጸ

ፖርትላንድ የአጠቃላይ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ

ሚያዝያ ፳/፳፻፲፰ ዓ.ም

በአሜርካ በሀገር አቀፍ ደረጃ  ሁለተኛው የአቡነ ጎርጎርዮስ ተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር ቅዳሜ ሚያዝያ ፲፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም (April 25, 2026)  በችካጎ ከተማ  መደረጉን የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አስተዳደር ቦርድ ገልጿል::

ውድድሩ በመጀመሪያ በእያንዳንዱ ትምህርት ቤትና ቀጥሎም በማስተባበሪያ ማእከል ደረጃ በአራት የዕድሜ ክልል ተከፍሎ የተደረገ ሲሆን በአንድ የዕድሜ ክልል ሁለት ተማሪዎች ተመድበው ትምህርት ቤቶቻቸውንና የማስተባበሪያ ማእከላቸውን ወክለው በችካጎ ከተማ  ለ National AGA Tewahedo Bee Championship ሃያ አራት ተማሪዎች ተወዳድረዋል።

በዚህ ውድድር በትምህርት ቤቶችና በማስተበባሪያ ደረጃ  ከፍተኛ ውድድር የታየበት መሆኑም ታውቀዋል።

በውድድሩ የምእራብ ማስተባበርያን ወክለው ከተገኙት ት/ቤቶች መካከል አንዱ የሆነው የፖርትላንድ ግ/ጣቢያ አቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የአጠቃላይ ዋንጫው ተሸላሚ ሆኗል።

የዚህ ውድድር ዓላማ በትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን የትምህርት አሰጣጥ ወጥነትን ለማስጠበቅ፣ በትምህርት ቤቶችና ተማሪዎች መካከል ያለውን ግንኙኝነት ለማጠናከርና የትምህርት ጥራቱን ለማሻሻል እንደሚጠቅም ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ቃለ እግዚአብሔርን ለሌሎች ማስተላለፊያ መንገድ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ለዚህ ዝግጅት መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ለችካጎ የአቡነ ጎርጎርዮስ ተማሪዎች ቤተሰቦች፣ ምእመናን እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም  ለችካጎ ንኡስማእከል አባላት ቦርዱ ምስጋናውን አቅርቧል።

ውድድሩ  ቦርዱ ከማእከሉ ሚዲያ ክፍል ጋር በጋራ ያዘጋጀ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል::

ዘገባው የማእከሉ ሚዲያ ክፍል ነው።
👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://t.me/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905