ግሸን ማርያም

ወሎ፣ አምባሰል አውራጃ ውስጥ በደብር በሐይቅና በመቅደላ፣ በደላንታ፣ በየጁ መካከልና በበሸሎ ወንዝ አዋሳኝ የምትገኝ አንድ መግቢያ በር ብቻ ያላት ዙሪያውን በገደል የተከከበች አምባ ትገኛለች፡፡ በበርዋ ራስ ላይም የመስቀል ምልክት ሲኖር አጥርዋን አልፈን ከገባን በኋላ ግቢዋ ከላይ ሜዳና መስቀለኛ ቦታ ነው፡፡

ደብርዋም በመጀመሪያ ደብረ እግዚአብሔር በሚለው ስያሜ ትታወቅ ነበር፡፡ በንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ እጅ ከቋጥኝ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሠራ ቤተ መቅደስ በእግዚአብሔር አብ ስም ስለነበረ ደብረ እግዚአብሔር ተብሎ ተጠራ፡፡ ከዚያም የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ሲመሠረት ሐይቅ ደብረ ነጎድጓድ ተብሎ ሲሰየም ግሸን የሐይቅ ግዛት ስለሆነች ከደብረ እግዚአብሔር ደብረ ነጎድጓድ ተብላለች፡፡ ከዚያም በ፲፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ በዓፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት የክርስቶስ ግማደ መስቀሉ ግሸን ገብቶ ሲቀመጥ ከደብረ ነጎድጓድ ደብረ ከርቤ ተብላለች፡፡ የደብሩ አስተዳዳሪም መምህረ እሥራኤል ዘደብረ ከርቤ ትባል ነበር፤ ከደብረ ከርቤም ግሸን ማርያም ተብላለች፡፡

‹‹ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ›› (ፊልጵ. ፪፥፫)

ወገንተኝነትን አሉታዊ በሆነ መልኩ ስንገነዘበው ለወገን፣ ለዘመድ፣ ለጓደኛ፣ ወይም የራስ ለሚሉት አካል ማድላት ነው፡፡ አያሌ ተቋሟት ዓላማና ግቦቻቸውን በሚገልጡበት ጊዜ ከሚያስቀምጡዋቸው ዕሤቶቻቸው መካከል አንዱ አለማዳላት ነው፡፡ አለማድላት ደግሞ ወገንተኝነትን የሚኮንንና ፍጹም ተቃራኒው የሆነ ታላቅ ዕሤት ነው፡፡ ወገንተኝነት ወገኔ ለሚሉት አካል ጥፋት ሽፋን በመስጠት ይገለጣል፡፡ ቆሜለታለሁ ለሚሉትም አላግባብ ቅድሚያ መስጠት ሌላኛው መገለጫው ነው፡፡

‹‹መስቀል ኀይላችን፣ ጽናታችን፣ቤዛችን፣ የነፍሳችን መዳኛ ነው››

‹‹አይሁድ ይክዱታል፤ እኛ ግን እናምነዋለን፤ ያመነውም እኛ በመስቀሉ እንድናለን፤ ድነናልም››

ጼዴንያ ማርያም

የሁሉ አምላክን በማኅፀኗ የተሸከመችው ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምም በሥዕሏ ወዝ ብዙ ሕሙማንን ትፈውሳለች፡፡ ከቅዱሳን ልብስና ጥላ የእርሷ ሥዕል ይከብራልና በየዓመቱም መስከረም ፲ ቀን ቤተ ክርስቲያናችን ከእመቤታችን ፴፫ቱ በዓላት ውስጥ አንዱ አድርጋ በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡

‹‹ሁሉን መርምሩ፤ መልካሙን ያዙ›› (፩ኛተሰ.፭፥፳)

በምንኖርባት ዓለም መጥፊያውም ሆነ መዳኛውም ከፊት ለፊታችን ነው። ባለንበት ቦታ ሁነን እግዚአብሔር የወደደውን እናደርጋለን ወይም እኛ የወደድነውን እናደርጋለን። የምንሠራቸውን ነገሮች ልንመረምራቸው ይገባል፤ በእግዚአብሔር የተወደደ መሆኑን ማለት ነው። ካልሆነ መጥፊያችንን እያደረግን መሆኑን ማወቅ አለብን።
የስልኮቻችን አጠቃቀም፣ አዋዋላችን፣ አለባበሳችን፣ አመጋገባቸን፣ አነጋገራችን፣ ወዘተርፈ ሃይማኖት እንደሚፈቅድልን ወይስ እንደእኛ ደስታ የሚለውን ሊመረመር ይገባል። እግሮቻችን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ከሄዱ ስንት ጊዜ ሆናቸው? እጆቻችን ቅዱሳት መጻሕፍቱን የገለጡበት ጊዜስ? ዐይኖቻችን ከጉልላቱ ላይ መስቀሉን የተመለከትንበት ጊዜስ? አፋችን የእግዚአብሔርን ነገር የተናገርንበት ጊዜስ! ጆሯችን ቃለ እግዚአብሔር የሰማበት ጊዜስ? አንደባታችን (ጉሮሯችን) ቅዱስ ቁርባን የተቀበሉበት ጊዜስ? ሕዋሳቶቻችንን እንደተፈጠሩለት ዓላማ ያዋልንበት ጊዜ መቼ ነው?

‹‹ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ›› (ኤር.፲፰፥፲፩)

ሥነ ምግባር ሰዎች በዕለት ተዕለት ኑሮችን ውስጥ የምናሳየው ጠባይ ወይም ድርጊት፣ አንድን ነገር ለመሥራትና ላለመሥራት የሚወስኑበት ኅሊናዊ ሚዛን ነው፡፡ በጎ ሥነ ምግባር ክፉ የሆኑ ነገሮችን አስወግዶ ደግ የሆኑትን መምረጥ መሥራት ሲሆን በተቃራኒው ክፉ ሥነ ምግባር ከበጎ ይልቅ ክፉ ነገሮችን መርጦ መሥራት ማለት ነው፡፡ ክፉ የሚለው ቃል የመልካም ነገር ተቃራኒ፣ የበጎ ነገር መጥፋት፣ ሐሰት፣ ኃጢአት፣ በሰው ልጅ ላይ የሚደርስ የሥጋና የነፍስ መከራ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ልዑለ ባሕርይ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ክፉና በጎን መለየት እንዲችሉ አስቀድሞ በሕገ ልቡና ከዚያም በሕገ ኦሪት ከዚያም በሥጋ ተገልጦ የሰው ልጅ ሊኖር የሚገባውን ኑሮ ምሳሌ አርአያ ሆኖ አሳይቶናል፡፡

በዓለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ

…በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ እጆች ላይ ወደ አየር በረረች።….

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

ርእሰ ዐውደ ዓመት

በጊዜ ሥጦታ ቀናት ተፈጥራዊ ዑደትን ተከትለውና ወራትን ተክተው ዘመንን ይፈጥራሉ፤ የዘመናት ለውጥም አዲስ ዓመትን ይተካሉ፤ ይህ ሁሉ ግን በእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ሆነ፤ እኛም ለአዲሱ ዓመት ዘመነ ማርቆስ እንደ ቸርነቱ ደረስን፡፡…

መልእክት

ክርስቶስ በከበረ ደሙ የዋጃችሁ ሃይማኖታችሁ የቀና የተወደዳችሁ ምእመናን ሆይ ልዑል እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል። በይቅርታው ገናናነት በጎ የሆኑትን ሁሉ ስለሰጠን የልዕልናውን ምስጋና ጨምረን እጅግ ልናበዛ ይገባናል። እስከዚህች ዕለትና ሰዓት  አድርሶናልና።…