[smartslider3 slider="3"]

የደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም የ፬ቱ ትርጓሜ መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ።

የደብረ ልዑላን መድኃኔ ዓለም የ፬ቱ ትርጓሜ መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት ላለፉት አምስት ዓመታት ያስተማራቸውን ፳፫ ደቀ መዛሙርት ግንቦት ፲፮/፪፳፲፰ ዓ/ም አስመርቋል። በማማያዝ ጉባኤ ቤቱ ዘመናዊ ባለ ሁለት ወለል የጉባኤ ቤቱን መንታ ሕንጻ ማስመረቁም ተነግሯል። የደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም የ፬ቱ ትርጓሜ መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት በአጼ ቴዎድሮስ መሠረት ጣይነት የተጀመረና ጥንታዊ ጉባኤ ቤት ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች ላለፉት […]

“ሕያው ዜማከ ወሕያው ድርሳንከ” በሚል መሪ ቃል የዝክረ ቅዱስ ያሬድ መርሐ ግብር እንደሚከናወን የዜማና ኪነ ጥበባት ማእከል አስታወቀ

ግንቦት ፲፪/፳፻፲፰ ዓ.ም በማኅበረ ቅዱሳን የዜማና ኪነ ጥበባት ማእከል “ሕያው ዜማከ ወሕያው ድርሳንከ” በሚል መሪ ቃል የዝክረ ቅዱስ ያሬድ መርሐ ግብር በዋናው ማእከል፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ማእከላት፣ በወረዳ ማእከላት እንዲሁም በግቢ ጉባኤያት  እንደሚከናወን አስታውቋል። ማኅበረ ቅዱሳን ከያዛቸው ዕቅዶች መካከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መዝሙራትን፣ የዜማ መሣሪያዎችንና ኪነ ጥበባትን በተመለከተ የተለያዩ መርሐ ግብራትን፣ ዐውደ ጥናቶችን […]

በማኅበረ ቅዱሳን ወሊሶ ማእከል ያስተማራቸውን ዲያቆናት ማዕረገ ቅስና እንዲቀበሉ በማድረግ አስመረቀ

በማኅበረ ቅዱሳን ወሊሶማእከልያስተማራቸውንዲያቆናትማዕረገቅስናእንዲቀበሉበማድረግአስመረቀ ግንቦት ፲፩/፳፻፲፰ ዓ.ም በማኅበረ ቅዱሳን ወሊሶ ማእከል ላለፉት ሦስት ወራት  በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥር ከሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች የተወጣጡ 17 ዲያቆናትን ሲያሠለጥን የቆየ ሲሆን ከሠልጣኞቹ መካከል 8 ደቀ መዛሙርት ማዕረገ ቅስና እንዲቀበሉ በማድረግ የተቀሩት ደግሞ ተጨማሪ የአቅም ማጎልበቻ ትምህርቶችን እንዲያገኙ መደረጉ ተገልጿል። ደቀ መዛሙርቱ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም በሸገር ሀገረ […]