ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም(ክፍል ሁለት)
ዲ/ን ዮሐንስ ልሳነወርቅ
በቅዱስ ኤፍሬም ሥራዎች ላይ በሚያጠነጥነውና የሚያበራ ዐይን በሚል ርእስ ሰባስቲያን ብሩክ ካዘጋጀው መጽሐፍ የተገኘው እንዲህ ተተርጉሞ ቀርቦአል። መልካም ንባብ
በዚህ ክፍል ውስጥ የምናየው ፈጣሪና ፍጡር፣/የተሰወረውና የተገለጠው/ሁለቱ ጊዜያትና ነጻ ፈቃድ በሚሉት ርእሶች ስር ቅዱስ ኤፍሬም በግጥም ያቀረበውን ትምህርት ነው።የቅዱስ ኤፍሬም መዝሙራት ከሚያጠነጥኑባቸው ርእሰ ጉዳዮች አንጻር ስያሜ ተሰጥቶአቸዋል። ለምሳሌ በእምነት ዙሪያ የጻፈውን -Faith ፣በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ የጻፈውን -Church የሚል ሲሆን ፤በዚህ ጽሑፍም እነዚህ በእያንዳንዱ መዝሙር ስር ተጠቅሰዋል።