አብረን እንዘምር!

ታኅሣሥ ፳፰ ቀን ፳፻፲፬ .

ጌታ ተወለደ በትንሿ ግርግም፤

በከብቶቹ በረት ከድንግል ማርያም፡፡

እርሷም ታቀፈችው የተወደደ ልጇን፤

ሰማይና ምድር የማይወስነውን፡፡

በጨርቅም ጠቅልላ ግርግርም አስተኛችው፤

የተኛባት መሬት እንዴት ቻለችው?

መላእክቱ ታዩ ከእረኞቹ ጋራ፤

እየዘመሩለት ለእርሱ ድንቅ ሥራ፡፡

ሰብአ ሰገልም መጡ ከሩቅ ሀገር፤

ለአምላካቸው ሊሰግዱ በታላቅ ክብር፡፡

ወርቅና ከርቤ እጅ መንሻም አቅርበው፤

ለወጡ ኃላፊውን ክብር በሕያው፡፡

እኛም ከመላእክት ከእረኞች ክልል፤

እጅ መንሻን ካመጡት ከሰብአ ሰገል፤

ጌታን ስላየነው ከፍጥረት መሃል፤

አብረን እንዘምር እልልም እንበል!