ክፉና በጎ የሰው ልጆች ባሕርያት ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር ለመልካም ነበረ፡፡ (ዘፍ.፩፥፲፪) ምንም እንኳን የፍጥረት አክሊል የሆነው ሰው ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ከብርሃን ጨለማን፣ ከሕይወት ሞትን፣ ከመታዘዝ አለመታዘዝን ቢመርጥም እግዚአብሔር አምላክ የፈጠረው ስሙን እንዲቀድስ ክብሩን እንዲወርስ ነበረ፡፡ ለዚህም ክፉና ደጉን መለየት ይችል ዘንድ አስቀድሞ የሚያስተውል አእምሮ ሰጥቶት ነበር፡፡ በኅሊናው…
በዓላት ከማንኛውም ቀናት የበለጠ አምላካችን እግዚአብሔርን የምናመሰገንባቸውና የምናወድስባቸው፣ የተቀደሱትን ዕለታት በማሰብና በመዘከር በዝማሬ፣ በሽብሻቦና በእልልታ የምናከብርባቸው ናቸው፡፡ ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው የሚወጡባቸውና ሕዝበ ክርስቲያኑን የሚባርኩባቸው ስለሆኑም በክብርና በድምቀት ይከበራሉ፡፡
ምሥራቅ የቃሉ ፍቺ “የፀሐይ መውጫ” ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግሥ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ገጽ ፮፻፹) በሥርዓተ ቅዳሴ ላይ ዲያቆኑ “ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ” በማለት በዜማ ለምእመናኑ ያውጃል፤ በእርግጥ በቅዳሴ ጊዜ በመካከል የሚያነቃቁና የአለንበትን ቦታ እንድናስተውል የሚያደርጉ ሌሎች ዐዋጆች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል “እለ ትነብሩ ተንሥኡ፤ የተቀመጣችሁ ተነሡ” የሚለው ነው፡፡…
የካህን ልጅ ካህን፣ ምድራዊ የሆነ ሰማያዊ፣ ሰው ሲሆን መልአክ፣ ከሱራፌል ጋር የእግዚአብሔርን ዙፋን ያጠነ፣ ከመላእክት ጋር የተባበረ፣ ግዙፍ ሲሆን የረቀቀ፣ ባሕታዊ ሲሆን መምህር፣ ኢትዮጵያን በወንጌል ያበራ፣ የምድር ጨው፣ ስለአባታችን ተክለ ሃይማኖት ይህን እወቁ! የፀጋ ዘአብ ዘር ምን ያህል ቡርክት ነች፤ የእግዚእኃረያ ማህፀን ምን ያህል ለምለም ነች!? አንደበቱ ለምስጋና የተፈታ፣ መላእክት…
በሰማርያ ረኃብ በጸናበት ዘመን የሚቀመስም ጠፋ፤ ከረኃቡ ጽናት የተነሣ እናት ልጇን እስከ መብላት ደረሰች። በእዚያም ሀገር ኤልሳዕ የሚባል የእግዚአብሔር ሰው ነበረ። እንዲህም አለ፤ ነገ በዚህች ከተማ በአንድ ሰቅል አንድ መሥፈርያ መልካም ዱቄት በአንድ ሰቅል ሁለት መስፈርያ ገብስ ይሸመታል። ያኔ ንጉሡ በእግዚአብሔር ላይ ተገዳደረ፤ እንዴት ይቻላልም አለ። የእግዚአብሔር ሰው ኤልሳ እንዲህ…
በጸሎትና በስግደት እንዲሁም በምጽዋት የታገዘ ጾም በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ በመሆኑ ድኅነትን ማሰጠት ብቻም ሳይሆን በረከትን ያስገኛል፡፡ በዚህም የተነሣ ሥራችን፣ ትዳራችን እንዲሁም አገልግሎታችን ይባረክልናል፡፡
በሕይወታችን ለሚገጥመን ማንኛውም ችግር ከእግዚአብሔር ዘንድ መፍትሔ ይኖረዋል፡፡ በእርሱ አምነንና ታምነን እስከኖርን ድረስ ከመከራና ከሥቃይ ያወጣናል፡፡ ሰዎች በተለያዩ ጊዜያት በሕይወታቸው ውስጥ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ የሚረዳቸው ቤተሰብም ሆነ ዘመድ ከሌላቸው ደግሞ ችግራቸውን ስለሚያባብሰው ወደከፋ መከራ ውስጥ ሲገቡ ሰምተንም ሆነ ተመልክተን ይሆናል፡፡ ነገር ግን አምላካችን እግዚአብሔር ሰውን የሚፈትነው ለበጎ እንደሆነ በማወቅና በመረዳት…
‹‹የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትን ሥራቸውን ዕወቅ፤ ከሁሉ የሚደንቅ ክበባቸውን ከሁሉ የሚበልጥ ብርሃናቸውን ሁሉ ዕወቅ፤ በየወገናቸው የሚያበሩ የሚመላለሱ የእነዚህን የምሳሌያቸውን ሥራ ዕወቅ፤ ሁሉ ጊዜ እርስ በእርሳቸው እንደምንም እንደሚቀራረቡ ዳግመኛም እንደምንም እንደሚራራቁ ዕወቅ…›› (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ባስልዮስ ምዕራፍ ፴፭፥፲፯)