መስቀሉን ስከተል

በመዝሙርና ኪነ ጥበባት ክፍል

ጥቅምት ፳፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት

ሊሄድ በ’ኔ መንገድ

ሊከተለኝ ‘ሚወድ

ራሱን ለሚክድ

አይደንግጥ አይፍራ

አለሁ ከር’ሱ ጋራ

ብሎኝ

ትናንትና፡-

ቃሉንም ሰምቼው

አምኜ በነበር

ብከተለው ባልቀር

በሥራየ እንድከብር

ዛሬ፡-

ኀዘን እንጉርጉሮ…

ፍርሃት ሲዳስሰኝ

ሲለኝ እየሰማሁ

“እኔ ከአንተ ጋር ነኝ!”