መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
‹‹የማይመረመር ብርሃን!›› (ሥርዓተ ቅዳሴ)
የማይመረመረው ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳኑ ምሥጢር ከፍጥረት ረቂቅ (የማይመረመር) ነው፡፡ በመስቀል ላይ ሁኖ አምላክነቱን በገለጸ ጊዜ ጠላት ዲያብሎስ እንዲህ ብሏል፤ ‹‹… ያለኃጢአት የሞተ ይህ ማን ነው? በብርሃኑ ብዛት የጨለማውን አበጋዝ ዕውር ያደረገው ይህ ማን ነው?›› (ሃይማኖተ አበው ትምህርት ኅቡዓት ፬፥፲፮)
‹‹የወይን ግንድ ይቆረጣል›› (ተአምረ ማርያም)
እውነተኛው የወይን ግንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራውን ይፈጽም፣ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል መፀነሡን ያበስር ዘንድ ወደ እመቤታችን በተላከ ጊዜ የተነገረ ቃል ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ብሥራትን ይናገር ዘንድ ወደ እመቤታችን በተላከ ጊዜ በግንባሩ ተደፍቶ ልዑል እግዚአብሔርን ‹‹ጌታ ሆይ! የምትነግረኝ ይደረግ ዘንድ እንደምን ይሆናል?›› አለው፡፡ ጌታም ‹‹የጀመርኩትን ቸርነት ፈጸምኩ፣ የወይን ግንድ ይቆረጣል፤ ወይራም ከበለስ ጋር ይተከላል፤ ቅጽሮችም ይቀጸራሉ (ምግባር ከሃይማኖት ጋር ይሠራል)፤ ገብርኤል ሆይ! ሄደህ ለዳዊት ልጅ ‹‹እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ›› ብለህ አብሥራት›› አለው፡፡ ‹‹ለዘለዓለም ነግሦ የሚኖረውን እነሆ ትፀንሳለሽ በላት›› አለው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ሰምቶ ሰገደ፡፡ ጌታችን ‹‹እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ›› በማለት እንደተናገረው የወይን ግንድ የተባለ እርሱ ነው፡፡ (ዮሐ.፲፭÷፩)
“ሆሣዕና በአርያም” (ማቴ.፳፩፥፱)
ከደቀ መዛሙርቱም ሁለቱን ልኮ ቤተ ፋጌ ከምትባል ቦታ አህያ እና ውርንጫ አስመጥቶ በእነርሱም ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ገባ። በዚያን ሰዓት ከይሁዳ አውራጃዎች ሁሉ የፋሲካን በዓል ለማክበር የተሰበሰቡት ሁሉ የኢየሱስን ወደ ኢየሩሳሌም መምጣት ሰምተው በእልልታ እና በዝማሬ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።” (ማቴ.፳፩፥፱)
ወርኃ ሚያዝያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ስምንተኛው ወር “ወርኃ ሚያዝያ” በመባል ይታወቃል፡፡ ሚያዝያ ማለት “መሐዘ፣ ጎለመሰ” ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን “ጎለመሰ፣ ጎበዘ፣ አደገ፣ ሚስት ፈለገ፣ የሚዜዎችና የሙሽሮች ወር” የሚል ትርጒም ይይዛል። ይህን ስያሜም ያገኘው በሀገራችን በአብዛኛው ሰርግ የሚደረገው በዚህ ወር ስለሆነ ነው።
ይቅርታ
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? በፈቃደ እግዚአብሔር የጀመርነው የዐቢይ ጾም ሁዳዴ (ጾመ ክርስቶስ) ስድስተኛውን ጨርሰን ስምንተኛው ሳምንት ኒቆዲሞስ ላይ እንገኛለን፡፡ በአቅማችሁ በመጾም በጸሎት በርቱ!
ቤተ ክርስቲያንም ሄዳችሁ መንፈሳዊ ትምህርትን መማር አትዘንጉ! ዘመናዊ ትምህርታችሁንም ቢሆን በርትታችሁ ተማሩ! የሁለተኛው መንፈቀ ዓመት እየተገባደደ ነው! በርትታችሁ አጥኑ! ያልገባችሁን ጠይቁ! አብዛኛውን ጊዜያችሁን በትምህርታችሁ ላይ ትኩረት አደርጉ!፤ መልካም! በዛሬው ክፍለ ጊዜ “ይቅርታ” በሚል ርእስ እንማራለን፡፡
“እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ መጣ” (ዮሐ.፫፥፩)
የዓለምን ኃጢአት አስወግዶ፣ ኃጢአተኞችን በፍቅሩ መረብ አጥምዶ፣ በቃሉ ትምህርት ልቡናቸውን ማርኮ፣ በተአምራቱ ኅሊናቸውን ገዝቶ የፈጠራቸውን ሰዎች ወደ ሕይወት መንገድ ሊጠራ የመጣው መሲሕ በአይሁድ ቤት እንደ ባላጋራ ይታይ ነበር። ከዚያም አልፎ የአይሁድ አለቆች የሥልጣናቸውን በትር ተጠቅመው፣ ቀጥቅጠው፣ ከእግራቸው በታች አድርገው ሊገዙት ይሹ ነበር። ተግሣፁን እና የተአምራቱን ኃይል በአዩ ጊዜም በቅንዓት ተነሳሥተው ሊወግሩት ምክንያት ይፈልጉ ነበር። የባሕርይ አምላክነቱን ገንዘቡ እንደሆነ ሲነግራቸው፣ ራሱንም የእግዚአብሔር ልጅ እያለ ሲጠራ ሲሰሙ የቅን ተቆርቋሪ መሳይ ጠባያቸው እስከ መግደል ድረስ እንዲደርሱ አድርጓቸዋል።
አገልግሎቴን አከብራለሁ!
የመዝገበ አእምሮ ዝግጅት ከመጀመሩ በፊት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር አጥኚዎች የተወሰኑ የቤተ ክርስቲያንን የዕውቀት ሀብቶች ለመሰነድ ጥረቶች መደረጋቸውን የሚያስረዱ መረጃዎች አሉ። በአባቶች ብዙ ድካምና ጥረት ተሰንደው ከሚገኙት የቆዩ የቤተ ክርስቲያን የዕውቀት ሀብቶች መካከል ስንክሳር፣ ሃይማኖተ አበውና ገድላት የሚሉት መጻሕፍት ይጠቀሳሉ፡፡ ስንክሳር “የመላእክትን ማዕርግና ሹመት የሚያስረዳ፣ የነቢያትንና የሐዋርያትን፣ የጻድቃንንና የሰማዕታትን፣ የደናግልንና የመነኮሳትን ምግባር፣ መከራና ዕረፍት ከዕለት እስካመት የሚነግር፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ የእመቤታችንን ዜና፣ የልጇንም በጎ ሥራ ኹሉ በሰፊው” የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው፡፡ (ደስታ፣ ፲፱፻፷፪፤ ፲፩፻፺፬)
አገልግሎቴን አከብራለሁ!
በ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናትና ምርምር ማእከል›› በመክፈት ቅዱሳት መጻሕፍትን ማስተዋወቅ እና ከሚደርስባቸው ልዩ ልዩ ጉዳዮች አደጋዎች ተጠብቀው ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላላፉ ማድረግ ያቋቋመው የአገልግሎት ክፍል ለዛሬው የጥናትና ምርምር ማእከል መመሥረት ምክንያት ነው። ይህ ክፍል በተሻለ አደረጃጀትና የሰው ኃይል ተጠናክሮ ከኅዳር ወር ፳፻፩ ዓ.ም. ጀምሮ ‹‹የማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማእከል›› በሚል ስያሜ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
‹‹በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለው›› (ማቴ.፳፭፥፳፩)
በሰዎች ዘንድ መታመን መታደል ነው፤ እምነትን ጠብቆ መገኘት ደግሞ ታላቅነት ነው፡፡ መታመን የተሰጠን አደራ ጠብቆ መገኘት ለክብር ያበቃል፤ በሰውም ሆነ በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ መወደድንና መከበርን ያተርፋል፡፡ ለሰዎች ስንታመን እነርሱ ባያዩንም በሁሉ ቦታ ያለ፣ በቦታ የማይወሰን፣ በእርሱ ዘንድ ጨለማ የሌለበት እግዚአብሔር ያየናል፡፡ መታመናችን “ሰው አየን አላየን” ብለን ሳይሆን ለታመንንለት ነገር በፈቃዳችን መገዛት ስንችል፣ የታመነንን ስናከብር በምትኩ ለታላቅ ኃላፊነት እግዚአብሔር ይሾመናል (ይመርጠናል)፡፡
አገልግሎቴን አከብራለሁ!
አቡነ ጎርጎርዮስ ትምህር ቤት ከተመሠረተበት ከ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም. እስከ ፳፻፮ ዓ.ም. በባለቤትነት የአስተዳድረው የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን ነበር፡፡ ከአገልግሎቱ እና መዋቅራዊ አደረጃጀት ባሕርይው አንጻር ሁለት መሠረታዊ ተግዳሮቶች ሲፈትኑት ቆይተዋል፡፡ የመጀመሪያው ለትምህርት ቤት የሚሆን የራሱ የሆነ ሕንፃ አለመኖር ሲሆን ሁለተኛው የሚፈለገውን የትምህርት ጥራት ለማምጣት የሚያስችሉ ግብዓቶችን ለማሟላት የሚያስችል የገንዘብ አቅም ማነስ ነው፡፡ ይህንን ችግር በዘለቄታው ለመፍታት ይቻል ዘንድ ማኅበረ ቅዱሳን፣ አባላቱ፣ የተማሪዎች ወላጆች እና የዓላማው ደጋፊዎች የሆኑ ግለሰቦች በጋራ ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር (ኤስድሮስ በ፲፰ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአንድምታ ትርጓሜ መምህር የነበሩ ናቸው) በማቋቋም ከሐምሌ ወር ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ የባለቤትነት ዝውውር ተደረገ፡፡ (የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች መተዳደሪያ ደንብ)