መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
በቃጠሎ የወደመውን ቤተ ክርሰቲያን ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀመረ
በእንዳላ ደምስስ ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም በቃጠሎ የወደመውን የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ሊቀ ኅሩያን መ/ር ወጋየሁ ደምሴ የባሌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ዋና ጸሐፊ ገለጹ፡፡ “በቃጠሎው ቤተ ክርስቲያኑ ሙሉ ለሙሉ ወድሞ ነው የደረስነው፡፡ ሕዝቡም ከፍተኛ ሐዘን ነው የተሰማው፡፡ ሁላችንም ልባችን ተሰብሮ በዕንባ ስንራጭ ነበር፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ አልቅሶ ብቻ […]
በባሌ ሀገረ ስብከት የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለ
በባሌ ሀገረ ስብከት ሮቤ ከተማና አካባቢው ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘው የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ለጊዜው ባልታወቀ መንስኤ መቃጠሉን መ/ር ያሬድ ገ/ማርያም የወረዳው ቤተ ክህነት ጸሐፊ ገለጹ፡፡
በጥምቀት በዓል የሃይማኖት አባቶች የሰላም ጥሪያቸውን አስተላለፉ!
የጥምቀት በዓል አከባበር በጃንሜዳ እና በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በድምቀት በተከበረበት ቀን፤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ለቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ባስተላላፉት መልእክት ላይ ምእመናን በተለይም ወጣቶች በፍቅርና በመቻቻል መኖር እንዳለባቸው አሳሰቡ፡፡
የሊቃውንቱ ምንጭ እንዳይደርቅ ደቀ መዛሙርትን ማፍራት እንደሚገባ ተገለጸ
ዲ/ን ዘአማኑኤል አንተነህ የሊቃውንቱ ምንጭ እንዳይደርቅ ደቀ መዛሙርትን ማፍራት እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርሰቲያን የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገለጹ፡፡ ብፁዕነታቸው ይህንን ቃል የተናገሩት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በጎንደር ከተማ የደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የአቋቋም ትምህርት […]
ወርኃ ጥርና የወጣቶች ሕይወት
ዲ/ን ወልደ ቂርቆስ ደሳለኝ የወጣትነት ምንነትና ፈተናዎቹ በዚህ ጽሑፍ የወጣትነት ምንነት፣ መገለጫዎች እና ተግዳሮቶቹ ላይ ትኩረት አድርገን እንመለከታለን፡፡ ወጣትነት ፈጣን፣ አካላዊ፣ ስሜታዊና ማኅበራዊ ለውጦች የሚሰተናገዱበት ከልጅነት ወደ ጎልማሳነት፣ ከጥገኝነት ራስን ወደ መቻል መሸጋገሪያ ድልድይ የሆነ የዕድሜ ክልል ነው፡፡ እነዚህን ለውጦች ተክትሎ በወጣቶች ጠባይ (ባሕርይ) ላይ የሚከሠቱ ብዙ ጉዳዮች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል፡- ከፍተኛ የሆነ የአቻ ግፊት […]
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል፣ በሰላም አደረሰን/አደረሳችሁ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፡- ከሁሉ በማስቀደም፣ የዘመናት ባለቤት ልዑለ ባሕርይ እግዚአብሔር አምላክ፣ በረከት የምናገኝበትን ፆም በሰላም አስጀምሮ በሰላም […]
በአፋን ኦሮሞ የተዘጋጁ ሦስት የኮርስ መጻሕፍት ታትመው በሥርጭት ላይ የሚገኙት
– Barattootni Yaa’iiwwan Mooraa Afaan Oromoon barattan Baga Gammaddan! Kitaaboleen koorsii sadii Afaan Oromootiin, adeemsa barnoota isa haaraatiin qophaa’anii isiniif dhiyaataniiru! Kanneen kaanis dhiyootti isin harka gahu! በአፋን ኦሮሞ የምትማሩ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች፡- እንኳን ደስ አላችሁ! በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት በአፋን ኦሮሞ የተዘጋጁ ሦስት የኮርስ መጻሕፍት ታትመው ቀርበውላችኋል! ሌሎቹም መጻሕፍት በቅርቡ ታተመው በእጃችሁ ይገባሉ!!!
የተሰጠህን አደራ ጠብቅ (፩ጢሞ. ፮:፳) (በእንተ ላ ሊበላ)
ብዙአየሁ ጀምበሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሀገራችን ያበረከተችው አስተዋጽኦ በብዙ ዐውድ የሚገለጽ እና መጠነ ሰፊ ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል በቋንቋ፤ በባሕል፤ በአለባበስ፤በሥነ ጽሑፍ፤ በኪነ ጥበብ፤ በኪነ ሕንፃ እና በቅርጻ ቅርጽ ዘርፍ የተደረጉት አስተዋጽዖዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ይህች ስንዱ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ተፈጥሮአዊ የሆኑ የዕፀዋት ዝርያዎችን በአግባቡ በመጠበቅ እና በመንከባከብ የሀገር ሕልውናን በማስጠበቅ እና ተፈጥሮ ዑደቱ ሳይዛባ እንዲቀጥል […]
በትዳር ሕይወት የወላጆች ኃላፊነት
ዲ/ን ተመስገን ዘገየ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጠረው ይለናል (ዘፍ፪-፳፮) አዳም ብቻውን ይሆን ዘንድ ያልፈቀደውና ብቻውን ቢሆን መልካም እንዳልሆነ […]
አንቲ ውእቱ ጽጌ መዓዛ ሠናይ (ውዳሴ ማርያም ዘእሑድ)
መ/ር ዘለዓለም ሐዲስ ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭ ያለው ዘመን ወርኀ ጽጌ በመባል ይታወቃል፡፡ወርኀ ጽጌም […]