መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
‹‹ሰላም ለኒቆዲሞስ ለወልደ ማርያም ዘአምኖ››
በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው ሚያዚያ 5/2011 ዓ.ም. በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት፣ ከዐቢይ ጾም ሳምንታት መካከል ሰባተኛው ሳምንት በኒቆዲሞስ ተሰይሟል፡፡ ሳምንቱ በስሙ ከመጠራቱም ባሻገር በቤተ ክርስቲያን የሚቀርበው ትምህርትም ኒቆዲሞስ ከጌታ የተማረዉን ምሥጢረ ጥምቀት መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ይኸውም የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ ከውኃ እና ከመንፈስ ቅዱስ መወለድ እንደሚገባው ያትታትል፡፡ ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ ምዕራፍ ፲፮ ቍጥር ፲፮ ላይ […]
ገብር ኄር
መምህር ሶምሶን ወርቁ የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብር ኄር የተሰየመው በቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ በዚህ ሳምንት ለሰው ሁሉ የማገልገያ ጸጋ መሰጠቱን፣ ሰጪው እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን፣ ቅን አገልጋዮች ስለሚቀበሉት ዋጋ ፣ ሰነፍ አገልጋዮች ስለሚጠብቃቸው ፍርድ ይሰበካል፡፡ «ገብር ኄር ወገብር ምእመን ዘአሥመሮ ለእግዚኡ፤ ጌታውን ያስደሰተው አገልጋይ ታማኝና ቸር አገልጋይ ነው፤መኑ ውእቱ ገብር ኄር፤ ቸር አገልጋይ ማን ነው?» እያሉ […]
በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት የተሰረቁት የቅዱስ ገብርኤል፤የቅዱስ ዮሐንስና የገብረ ክርስቶስ ጽላቶች መገኘታቸውን ፖሊስ ገለጸ
በሕይወት ሳልለው ሰኞ መጋቢት ፲፮ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም.፤ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ከመቃጠሉ በፊት የቅዱስ ገብርኤልና የበዓለወልድ ጽላቶች በመሰረቃቸው በወቅቱ በአካባቢው ሰዎች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ለወረዳው ፖሊስ አስተዳደር በማመልከታቸውም በተደረገው ከፍተኛ ርብርብ፤ የቅዱስ ገብርኤል ጽላት ከሂደቡ አቦቴ ወረዳ እንድሪስ ወንዝ ውስጥ ሊገኝ እንደቻለ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡ ሆኖም ግን የበዓለወልድ ጽላት እስከአሁን እንዳልተገኘ አያይዞ […]
‹‹ወዕለቱሰ ለእግዚአብሔር ግብተ ትመጽእ ከመ ሰራቂ፤ የእግዚአብሔር ቀን እንደሌባ ድንገት ትመጣለች›› (፪ ጴጥ.፫፥፲)
መጋቤ ሐዲስ ምስጢረ ሥላሴ ማናየ ደብረ ዘይት ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ ምሥጢረ ምጽአቱን ያስተማረበት፤ የገለጠበት፤ ደቀ መዛሙርቱም የመምጣቱን ምሥጢር የተረዱበት፤ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኝ በወይራ ዛፍ የተሞላ፤የተከበበ ተራራ ነው፡፡ ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው አዘውትሮ ከተመላለሰባቸው ቦታዎችም አንዱ ነው፡፡ ቀን በምኩራብ ሲያስተምር ውሎ ሌሊት ሌሊት በደብረ ዘይት ያድር እንደነበር ቅዱስ ወንጌል ምስክር ነው፡፡ ‹‹መዓልተ ይሜህር በምኩራብ ወሌሊተ ይበይት ውስተ […]
በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረስብከት በኤጀሬ ወረዳ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለ
በሕይወት ሳልለው በትናትናው ዕለት በሰሜን ሸዋ በሰላሌ ሀገረስብከት በኤጀሬ ወረዳ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን የወረዳው ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች የቤተ ክርስቲያኑን ጣሪያና መጋረጃ በማቃጠል ግድግዳውን ሙሉ ለሙሉ አፍርሰዋል፡፡ቁጥራቸው ባልተረጋገጠ ግለሰቦች ላይ ከባድ ጉዳት ሲያደርሱ የቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያንንም እንደዘረፉ ፖሊስ አያይዞ አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም እንደተገለጸው፤ በቃጠሎው ሳቢያ በወቅቱ ረብሻ ተነስቶ ነበር፡፡ ሌሎች ሶስት […]
«ጌታችን ኢየሱስ መፃጒዕን ፈወሰው» (ዮሐ.፭፥፮-፱)
በሕይወት ሳልለው «መፃጒዕ» ለ፴፰ ዓመት የአልጋ ቁራኛ የነበረና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ሰንበት የፈወሰው ሰው ነው፡፡ ጌታችንም ያን ሰው በአልጋ ተኝቶ ባየው ጊዜ መዳን እንደሚፈልግ አውቆ ጠየቀው፤ «ልትድን ትወዳለህን?» መፃጒዕም «አዎን ጌታዬ ሆይ፤ነገር ግን ውኃው በተናወጠ ጊዜ ወደ መጠመቂያው የሚያወርደኝ ሰው የለኝም፤እኔ በምመጣበት ጊዜ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል፤ አለው»፤ ጌታም «ተነሥና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ» ባለው […]
ምኲራብ
[…]
የኀዘን መግለጫ
“ብንኖረም ብንሞትም ለእግዚአብሔር ነን”፤ሮሜ ፲፬፥፰ እሁድ መጋቢት ፩ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም. ከጠዋቱ ፪፡፵፰ ደቂቃ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተነስቶ ወደ ኬንያ ናይሮቢ በመጓዝ ላይ የነበረው ET ፫፻፪ የመንገዶኞች አውሮፕላን ከ፮ ደቂቃ በረራ በኋላ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ከምትገኘው ደብረዘይት ወድቆ መከስከሱ ይታወቃል፡፡በመሆኑም ፻፵፱ መንገደኞች ፰ የበረራ አስተናጋጆችን ጨምሮ በድምሩ ፻፶፯ ሰዎች በሙሉ […]
‹‹እንደሚንሿሿ ጸናጽል ሆኛለሁ›› (፩ኛቆሮ.፲፫፥፩)
ዲያቆን ዮሴፍ በቀለ ጸናጽል ድምፁ መልካም የሆነ የምስጋና መሳርያ በመሆኑ […]
‹‹እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ›› (ዘሌ.፲፱፥፪)
መምህር ኃይለሚካኤል ብርሀኑ የዐቢይ ጾም ሁለተኛው ሳምንት (ሰንበት) ቅድስት ይባላል፡፡ ስያሜው የቅዱስ ያሬድ ሲሆን የመዝሙሩ ርዕስ የጾመ ድጓው መክፈያ ሆኖ የሚጠራበት ስም ነው፡፡ ከቅድስት ሰኞ ጀምሮ ጾመ ኢየሱስ ይባላል፡፡ በዚህ ሳምንትም ስለ እግዚአብሔር ቅድስና የሚያነሱ መዝሙራት ይቀርባሉ፤ እኛም እግዚአብሔርን መቀደስ (ማመስገን) እንዳለብን የሚገልጹ ምንባባት ይነበባሉ፣ትምህርት ይሰጣል፡፡ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው፤ ቅድስናውም ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ […]